ኮቪድ-19 ባለፉት 24 ሰዓታት በሀገራችን ኢትዮጵያ ፦
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ዘጠኝ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲሞቱ ከተደረገው 7,566 የላብራቶሪ ምርመራ 1,202 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 893 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 168,335 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,451 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 139,532 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 427 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ሰሞኑ በሀገራችን በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል ፦
"...ልክ ፀሎት ይደረግ ተብሎ ፤ በፀሎት ሲጀመር የታጠቁ ኃይሎች መጥተው ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ አደረጉ" - በአማሮ ልዩ ወረዳ ዳኖ ቀበለ የተፈፀመው ጥቃት ዓይን እማኝ
ከሰሞኑ ጥቃት ካስተናገዱ አካባቢዎች አንዱ የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ ዳኖ ቀበሌ በእርቅ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ተፈፀመው ነው።
በጥቃቱ በርከቶች ሞተዋል፤ ብዙዎችም ቁስለኛ ሆነዋል።
የአይን እማኞች ድርጊቱን /የተፈፀመውን ጥቃት ኢሰብዓዊ የሆነ ጭፍጨፋ የተፈፀመበት ብለውታል።
በሌላ በኩል ፦
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ከ እሁድ ጀምሮ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መግደላቸው ፣ መቁሰላቸው እና ማገታቸውን ነዋሪዎችን በማሳወቅ ላይ ይገኛሉ።
አበደንጎሮ በተባለ ወረዳ 29 ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው ነዋሪዎች አሳወቀዋል።
ነዋሪዎች እንደሚገልፁት "ደቢስ" በተባለው ቦታ ከተገደሉት ሰዎች መካከል ህፃናት፣ አዛውንቶች እና የሃይማኖት አባቶች ይገኙበታል።
መንግስት ተፈፅሟል ስለተባለው ጥቃት በሚዲያዎች ማብራሪያ እና መረጃ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ያለው ነገር የለም።
https://telegra.ph/Ethiopia-03-10-2

Telegraph
Ethiopia
የሰሞኑ የዜጎች ግድያ ፦ "...ልክ ፀሎት ይደረግ ተብሎ ፤ በፀሎት ሲጀመር የታጠቁ ኃይሎች መጥተው ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ አደረጉ" - በአማሮ ልዩ ወረዳ ዳኖ ቀበለ የተፈፀመው ጥቃት ዓይን እማኝ ከቀናት በፊት በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ፣ ዳኖ ቀበሌ ውስጥ ታጣቂዎች ከፈፀሙት ጥቃት የተረፈ አንድ ሰው ስለነበረው ሁኔታ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ቃሉን ሰጥቷል። ጥቃቱ የተፈፀመው ለእርቅ በተሰበሰቡ የሃይማኖት…
#IOM
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ባደረገው ቅኝት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከ131 ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዳሉ አመለከተ።
ድርጅቱ እንዳለው ተፈናቃዮቹ በትግራይና ተጎራባች በሆኑት የአፋር እንዲሁም የአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 39 በሚሆኑ ተደራሽ ስፍራዎች ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።
ይህ የተፈናቃዮች መረጃ የተሰበሰበው አዲስ በሆነው "ዲስፕሌስመንት ትራኪን ማትሪከስ" በተባለ ዘዴ ሲሆን በዚህም የሕዝብ ቁጥርን በተመለከተ መረጃ በመሰብሰብና የሰዎችን ተጋላጭነት እንዲሁም የተፈናቃዮችን ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ መረጃን በመሰብሰብ የሚተነትን ነው።
አይኦኤም እንዳለው በዚህ የቅኝት ተግባሩ 30,383 ተፈናቀሉ ቤተሰቦችን መለየት ችሏል።
ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያ ፣ ምግብና ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቶችን እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት "ይህ መረጃ በተከሰተው ቀውስ ምክንያት የተፈናቀሉትን አጠቃላይ ሰዎች የሚያመለክት አይደለም። ከዚያ ይልቅ መረጃውን ለማሰባሰብ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች በአገር ውስጥ የተፈናቀሉትን ሰዎች ብቻ የሚወክል ነው" ማለቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኮቪድ-19 ክትባት ወደ ክልሎች እየተጓጓዘ ነው።
ኢትዮጵያ ያለፈው እሁድ 2.2 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት መረከቧ የሚታወስ ነው።
የኮቪድ-19 ክትባቱ ወደ ተለያዩ ክልሎች የማሰራጨት ስራ እየተሰራ መሆኑ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ሙሉቀን ዮሐንስ ገልፀዋል።
ከቅዳሜ ጀምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ክትባቱን የመስጠት መርሃ ግብር ይጀመራል ብለዋል።
አሁንላይ ክትባቱን የሚያገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች ውስን ስለሆኑ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል የኮቪድ-19 መከላከያ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ገልፀዋል።
የኮቪድ-19 ክትባት በአንድ ጊዜ የሚመጣ ባለመሆኑ /ተቆራርጦ የሚመጣ ስለሆነ አብዛኛው ማህበረሰብ በሚቀጥለው አንድ ዓመት ክትባት ላያገኝ ይችላል ተብሏል።

አምባሳደር ጊታ ፓሲ ዛሬ ወደ ትግራይ ይጓዛሉ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ከኤምባሲው ባለደርቦች ጋር በመሆን የመጀመርያ ይፋዊ ጉብኝታቸው በትግራይ ያደርጋሉ።
አምባሳደሯ በትግራይ ክልል ያለውን አሁናዊ ሁኔታ ይመለከታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአምባሳደሯ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት አጋርነት የሚያሳይ እንደሆነ ኤምባሲው በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት መግለፁን አል አይን አስነብቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት... "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 በረራ ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ተነሥቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር በነበረው አውሮፕላን በደረሰው የመከስከስ አደጋ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ልባዊ ኀዘኑን ይገልጻል።" @tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET-302 አደጋ ዛሬ ሁለተኛ ዓመቱ ነው።
ET-302 ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ (ናይሮቢ) ሲበር "ቢሾፍቱ" አቅራቢያ ተከስክሶ ሁሉም ተሳፋሪዎች እና የበረራ ሰራተኞች ህይወታቸውን እንዳለፈ አይዘነጋም።
አየር መንገዱ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ መንገደኞችን እና ሰራተኞቹን ዛሬ እያሰበ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ET-302 ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ (ናይሮቢ) ሲበር "ቢሾፍቱ" አቅራቢያ ተከስክሶ ሁሉም ተሳፋሪዎች እና የበረራ ሰራተኞች ህይወታቸውን እንዳለፈ አይዘነጋም።
አየር መንገዱ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ መንገደኞችን እና ሰራተኞቹን ዛሬ እያሰበ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእጩዎች ምዘገባ በይፋ ተጠናቀቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን ከየካቲት 08/2013 ዓ.ም ጀምሮ በ2 ዙሮች ሲያከናውን እንደነበር እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ተጨማሪ ቀናት በመጨመርና የፓርቲዎችን አቤቱታዎች በመፍታት ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሷል።
በዚህም መሰረት የእጩዎች ምዝገባ ትላንትና የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ/ም በይፋ መጠናቀቁን አሳውቋል።
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢሮዎች ችግር የተነሳ በልዩ ሁኔታ የሚታይ ካልሆነ በስተቀር ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባ መዘጋቱን ቦርዱ ገልጿል።
አጠቃላይ የጸደቁ የእጩዎች ዝርዝርን በቅርቡ ይፋ የሚያደረገ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

3ኛው ቀን የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመላው ሀገሪቱ እየተሰጠ ይገኛል።
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም የጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።
ፈተናው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።
PHOTO : Addis Ababa Education Bureau & Somali Region Education Bureau
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም የጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።
ፈተናው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።
PHOTO : Addis Ababa Education Bureau & Somali Region Education Bureau
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰሞኑ በሀገራችን በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል ፦ "...ልክ ፀሎት ይደረግ ተብሎ ፤ በፀሎት ሲጀመር የታጠቁ ኃይሎች መጥተው ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ አደረጉ" - በአማሮ ልዩ ወረዳ ዳኖ ቀበለ የተፈፀመው ጥቃት ዓይን እማኝ ከሰሞኑ ጥቃት ካስተናገዱ አካባቢዎች አንዱ የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ ዳኖ ቀበሌ በእርቅ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ተፈፀመው ነው። በጥቃቱ በርከቶች ሞተዋል፤ ብዙዎችም ቁስለኛ ሆነዋል። …
"...ታጣቂዎቹ በፈጸሙት ጥቃት 22 ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል" - አቶ በቀለ ደቻሳ
የኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ደቻሳ በዞኑ አቤ ደንጉር ወረዳ ዳቢስ በሚባል ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውን ገልፀዋል።
ጥቃቱ ያነጣጠረው በአካባቢው በሚኖሩ የአንድ ብሔር አባላት ላይ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ አረጋግጠዋል።
ከጥቃት የተረፉ ወገኖች በአሰቃቂ ሁኔታ ህፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋዊያን ሳይቀሩ በግፍ በታጣቂዎች መገደላቸውን ገልፀዋል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ከሰሞኑ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ እና በአማሮ ልዩ ወረዳ በተፈፀሙት አሰቃቂ ግድያዎች አዝነናል ፤ አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል።
የቅዳሜው የሆሮ ጉድሩ ግድያ በስለት መፈፀሙንና ህፃናትም መገደላቸውን የገለፁት ኮሚሽነር አራርሳ "ኦነግ ሸኔ" ማህበረሰቡን ማፈኑን የሚገልፅ መረጃ ሲደርሰን ወደ አከባቢው ተንቀሳቀስን ነገር ግን ስንደርስ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለው አግኝተናል ብለዋል።
ኦሮሚያ ፖሊስ "አርሶ አደሩን ትጥቅ አስፈትቷል" በሚመል ለሚነሳው ጥያቄ አንድም ትጥቅ ያስፈታነው አርሶ አደር የለም ፤ ይልቅ በርካቶችን በማስታጠቅ እራሳቸውን እንዲጠብቁ እያደረግን ነው ብለዋል ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ።
ከጥቃት የተረፉ የዓይን እማኞች ፣ ከሚዲያዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት መልስ የተሰጠበት ዝርዝር መረጃ በ Instant View በመግባት ማንበብ ትችላላችሁ።
https://telegra.ph/Horo-Guduru-Welega-Zone-03-10

Horo Guduru Welega Zone
የዜጎች ጥቃት በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ፦ የኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ደቻሳ በዞኑ አቤ ደንጉር ወረዳ ዳቢስ በሚባል ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውን አረጋገጡ። ጥቃቱ ያነጣጠረው በአካባቢው በሚኖሩ የአንድ ብሔር አባላት ላይ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ አረጋግጠዋል። አቶ በቀለ ስለተፈጸመው ግድያ ሲያብራሩ "የካቲት 27 በዞናችን ውስጥ በምትገኘው አቤ ደንጎሮ…
ኢሰመኮ ስለ ኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ ምን ይላል ?
"ኬላ" ከተሰኘው የአሐዱ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተቋማቸው በትግራይ ጦርነት የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ እንዳደረገ ያምናል ወይ ? ተብለው ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ዳንኤል ተቋማቸው አሁን ላይ የምርመራው ስራ ሳይጠናቀቅ ሙሉ መደምደሚያ ላይ ላለመድረስ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
እስካሁን በተደረገው ምርመራ በምዕራብ ትግራይ የተወሰኑ የኤርትራ ወታደሮች/የኤርትራ ወታደር ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎች/በአካባቢው የተመለከቷቸው ሰዎች የኤርትራ ወታደሮች ናቸው ብለው የገለጿቸው ሰዎች መኖራቸውን እንዳረጋገጡላቸው አሳውቀዋል።
አምንነስቲ ባቀረበው የአክሱም ሪፖርት ጉዳይም ፤ ኢሰመኮ እስካሁን ባደረገው ክትትል በአክሱም በተፈፀመው ክስተት የኤርትራ ወታደሮች ተሳታፊ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ማስረጃዎች መሰብሰባቸውን ዶ/ር ዳንኤል ገልፀዋል።
ነገር ግን የስፋቱን መጠን፣ የተሳተፉት ሰዎች ብዛትና መጠን፣ የደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት መጠን፣ የሰብዓዊ ጥሰቱ ምንነት እና አይነት ፣ የኤርትራ ወታደሮች የተሳትፎ መጠን፣ ቁጥራቸው ስንት ነው የሚለውን ኢሰመኮ ምርመራውን ስላላጠናቀቀ ዝርዝር ውስጥ መግባት እንደማይፈልግ ዶ/ር ዳንኤል ተናግረዋል።
ኢሰመኮ እያደረገ ባለው የምርመራና የክትትል ስራ ቦታው ላይ ተገኝቶ ሳያጣራና ሳያረጋግጥ መደምደሚያ ላይ መድረስ ስለሌለበት አሁንም በምርመራ ስራው መቀጠሉን ገልጾ ፤ ኮሚሽኑ የሚደርስበትን ግኝት ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 170 ሺህ እየተጠጋ ነው።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,819 የላብራቶሪ ምርመራ 1,543 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል።
ትላንት 503 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 169,879 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,466 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 140,035 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 438 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,819 የላብራቶሪ ምርመራ 1,543 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል።
ትላንት 503 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 169,879 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,466 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 140,035 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 438 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አሁን ላይ በትግራይ 72 % አስተዳደራዊ መዋቅሩን መዘርጋቱን ማሳወቁ።
- የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር የአስተዳደር እና የወሰን ጥያቄዎች ጉዳይ የትግራይ ህዝብ ችግር ላይ በወደቀበት በአሁን ሰዓት መነሳታቸው ተገቢነት እንደሌለው መግለፁ።
- ለአምባሳደሮች ስለትግራይ ሁኔታ ማብራሪያ መሰጠቱ።
- በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ቪድዮዎች መነጋገሪያ መሆናቸው።
- የUNDP ኃላፊ በትግራይ ለተፈጠረው ችግር ህወሓት ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት ስለማለታቸው።
- በመቐለ ዛሬ እንቅስቃሴ ተቋርጦ መዋሉ/የቤት መቀመጥ አድማ
- ኮማንድ ፖስት በመቐለ የሰዓት ገደብ ወደ 1 ሰዓት ማሻሻሉ።
[ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የቀረበ]
መጋቢት 1 ቀን 2013 ዓ/ም
https://telegra.ph/Tigray-Report-Tikvah-Ethiopia-03-10-2

Tigray Report [Tikvah-Ethiopia]
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ቆይታ ከቪኦኤ ጋር ፦ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ከሰሞኑ ከቪኦኤ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅሩን መዘርጋት የቻለው 72 በመቶ ብቻ እንደሆነ ገልፀዋል። ትግራይ ኮማንድ ፖስት ስር ነው የምትገኘው ፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የመደራጀት ስራ እየሰራ ቢሆንም በደቡብ እና ምዕራብ ትግራይ ችግር አለ ብለዋል።…
በትግራይ አዲስ የተደራጀው ኮማንድ ፖስት ዛሬ ስራ ጀመረ።
አዲሱ የትግራይ ኮማንድ ፖስት በዛሬው ዕለት በይፋ ስራውን ጀምሯል።
ኮማንድ ፖስቱ የትግራይ ህዝብን ለማዳን አጥብቆ እንደሚሰራ መግባባቱን ከህዝብ ሰላም በላይ የሚታይ አካል የሌለ በመሆኑ ለህዝብ ደህንነት እና ሰላም መረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን በየደረጃው እንደሚሰራ ዛሬ ምሽት ባሰራጨው መግለጫ አሳውቋል።
ሁሉም አካላት በተለይ የክልሉ ህዝብ የክልሉን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎችን በመደገፍ ትብብር እንዲያደርግ ኮማንድ ፖስቱ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።

"...በሩን ክፈቱ ሲሉ የነበሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የት ሄዱ ብላችሁ ጠይቁ" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ፥ ስለሰብዓዊ ቀውስ ሲኮንኑ ለቆዩ ምዕራባዊያንና ግብረ ሰናይ ተቋማት በሩ ክፍት የተደረገላቸው ቢሆንም በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረጉ አይደለም ብለዋል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፥ ተርዓዶ የሚሰጡት ተቋማት እንደከዚህ በፊቱ ፍቃድ ሳያስፈልጋቸው ለሰላም ሚኒስቴር አሳውቀው ዝም ብለው እርዳታ ይዘው ወደትግራይ መሄድ ይችላሉ የሚል ውሳኔ ከዚህ በፊት መተላለፉን አስታውሰዋል።
በሩን ክፈቱ ፣ ህዝቡ ተጎድቷል ፣ ተርቧል ፣ እያለ ለሰብዓዊ መብት ሲጮህ የነበረው ኃይል እና ተቋማት በሩ ከተከፈተ በኃላ የሉም ፤ ስለዚህ የት ሄዱ ? ብላችሁ ጠይቁ ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል።
እንደነበረው ጥያቄ በእርዳታ ማቅረብ ከፍተኛ መጥለቅለቅ የሚፈጠር ይመስል ነበር ነገር ግን በሩ ሲከፈት እርዳታ የለም ፤ አንዳንዱ ባዶ ኪሱን መድሃኒትም ፣ ገንዘብም ምንም ሳይዝ ይመጣል ብለዋል።
ምንም እንኳን በትግራይ ለሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ለሚሰሩ ድርጅቶች ያልተገደበ ይለፍ የተመቻቸ ቢሆንም አሁንም ድረስ 70% ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ያለው በመንግስት መሆኑን አሳውቀዋል።

የወር ደሞዛቸው የታገደባቸው ዜጎች ችግር ላይ ናቸው።
ከውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ ብሔራዊ ባንክ ዕግድ ከጣለባቸው ግለሰቦች ጋር በስም መመሳሰል፣የወር ደመወዛቸው የታገደባቸው ግለሰቦች፣ በችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ደመወዛቸውን ከባንክ ለመቀበል (ለማውጣት) የሄዱ በርካታ ግለሰቦች፣ በባንኩ ሠራተኞች በልዩ ትኩረት እየታዩ፣ ‹‹መንግሥት ሒሳባችሁ እንዲታገድ ትዕዛዝ ደርሶናል›› በማለት እየመለሷቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለምን እንደታገደ ሲጠይቁ እንኳን ተገቢ ምላሽ እንደማያገኙ ወደ ኃላፊዎች ቢሄዱ ምላሽ ስለተነፈጋቸው ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል፡፡
‹‹ጥፋተኛን በሠራው ነገር መጠየቅ ወይም አጣርቶ ምላሽ መስጠት ሲገባ፣ እኛ ለምን ያለሥራችን ከእነ ቤተሰቦቻችን እንድንቸገር ያደርጋል?›› በማለት የሚጠይቁት ግለሰቦቹ፣ የሚመለከተው አካል ወይም መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ፥ ችግሩ መኖሩን አረጋግጠው፣ ነገር ግን ስማቸው ተመሳሳይ የሆኑ ግለሰቦችን ማንነታቸውን በፊርማ ናሙና የመለየት ሥራ መከናወኑን እና በ2 ሳምንታት ውስጥ መፍትሔ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-03-11-2

Reporter Newspaper
በስም መመሳሰል የባንክ ሒሳባቸው የታገደባቸው ግለሰቦች፦ ከውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕግድ ከጣለባቸው ግለሰቦች ጋር በስም መመሳሰል፣ የወር ደመወዛቸው የታገደባቸው ግለሰቦች፣ በችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ 65 ግለሰቦችና ተቋማት፣ ከሁሉም ንግድ ባንኮች ጋር ያላቸው የቢዝነስ ግንኙነት እንዲቋረጥ፣ የባንክ…