TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የህወሓት አመራር አቶ ስብሃት ነጋ ይገኙበታል። በተጨማሪ ፦ - ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤት እና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበሩ፣ በኋላ በጡረታ የተገለሉ - ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዱ - ኮሎኔል የማነ…
#FDREDefenseForce

የወ/ሮ አልጋነሽ መለስ ገደል ውስጥ ገብተው ህይወታቸው ማለፉን እዛው የነበሩ ሰዎች ለመከላከያ ሰራዊት መረጃውን እንደሰጡ ብ/ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ተናገሩ።

ብ/ጄኔረሉ ይህን የተናገሩት በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በሰጡት አጭር ማብራሪያ ላይ ነው።

ሌሎች በህይወት እያሉ እንዴት እሳቸው ብቻ ህይወታቸው ሊያልፍ ቻለ ? ስለሚለው ጉዳይ በቦታው የነበሩ ሰዎች "ወደገደል ገብተው ሞቱ" የሚል መረጃ ብቻ እንደሰጧቸው አሳውቀዋል።

ወ/ሮ አልጋነሽ ህይወታቸው ካለፈ በኃላ አለመቀበራቸውን ገልፀዋል።

እንደ ብ/ጄነራል ተስፋዬ ገለፃ ፥ ወ/ሮ ኣልጋነሽ ህይወታቸው ያለፈው በጦርነቱ ምክንያት አይደለም።

ጦርነቱ ሲደረግ የነበረው አመራሮች ከነበሩበት ስፍራ ራቅ ባለ ተራራ ላይ ከህወሓት ቡድን አመራር ጠባቂዎች ጋር ነበር ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ850 በላይ ተማሪዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል።

ዛሬ መቐለ ዩኒቨርሲቲ የዓዲግራት ተማሪዎችን ሲቀበል ውሏል።

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መልዕክት መተላለፉ ይታወቃል።

ዛሬ እና ነገ ተማሪዎች የሚገቡ ሲሆን ጥር 2 ቀን 2013 ትምህርት ይጀመራል።

እስካሁን ድረስ ከ850 በላይ ተማሪ ግቢ ገብቷል።

ለተማሪዎች ትራንስፖርት / መኪና ለመመደብ እንቅስቃሴ እንደነበር ቢገለፅም ምንም የተመደበ መኪና የለም።

ወደ ግቢ የገቡ ተማሪዎች እንደገለፁት ከአዲስ አበባ በባስ 850 ብር ትኬት ቆርጠው ነው መቐለ የደረሱት።

ከአዲስ አበባ ውጭ ከመቐለ በቅርብ ርቀት ያሉ ከተሞች (ወልዲያ፣ ደሴ) የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ኮንትራት መኪና በራሳቸው ይዘው መቐለ እንደገቡ ተሰምቷል።

የትራንስፖርት ክፍያው ውድነት እንዲሁም ትራንስፖርት አጥተው የተቸገሩ የቲክቫህ አባላት ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ገንዘቡ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑና የትራንስፖርት እጥረት በመኖሩ ጉዟቸውን ፈታኝ እንዳደረገው አሳውቀዋል።

ምንም እንኴን እጥረት ቢኖርም ከአዲስ አበባ - መቐለ ትራንስፖርት አለ፤ መንገድ ላይም ምንም አይነት ችግር እንደሌለ ዛሬ መቐለ የገቡ ተማሪዎች ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ለፖለቲካ ችግሮቻችንም ሆነ ለነፃ፣ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋቱ ወሳኝ ነው"-ኦፌኮ

ኦፌኮ ትላንት ባወጣው መግለጫ ለሀገራችን የፖለቲካ ችግሮችም ሆነ ለነፃ ፣ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝቧል።

የፌዴራል ስርዓቱ ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲተገበር የክልሎች የራስን አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ ገብነት እና የሞግዚት አስተዳደር እንዲወገድ በኢህአዴግ በሚመራው መንግስት ላይ ለዓመታት የመረር ትግል በማድረጉ አያሌ አባላቱ ፣ ደጋፊዎቹ ላይ ግድያ ፣ ማሰር ፣ ማሰቃየት፣ ማፈናቀል፣ እና ማሳደድ ወንጀሎች እንደተፈፀመባቸው አስታውሷል።

ዛሬም በርካታ የኦፌኮ አባላትና ደጋፊዎች ከከፍተኛው አመራር እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ለህዝብ ነፃነትና መብት ፀንተው በመቆማቸው የውሸት እና የፈጠራ ወንጀል ተለጥፎባቸው በተለያዩ ማጎሪያ ካምፖች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ልዩ ኃል ካምፖች፣ በድርጅት ፅ/ቤቶች በመደበኛ እስር ቤቶች እና በመማሪያ ክፍሎች ሳይቀር ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብሏል።

ኦፌኮ መንግስት በኢፌዴሪ ህገ መንግስት እና በዓለም አቀፍ ህጎች የተደነገጉ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማክበር በተለያዩ አካባቢዎች በፖለቲካ አቋማቸው ያሰራቸውን አመራሮች እና አባላት፣ ደጋፊዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቋል።

በኃይል የተዘጉ ፅ/ቤቶች ተከፍተው ስራ እንዲጀምሩ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቋል።

ምርጫ የሚያስተባብሩ፣ የሚወዳደሩ እና የሚታዘቡ የፓርቲው አመራሮች፣አባላት እና ደጋፊዎች ታስረው ሌሎችም ከደረሰባቸው ማስፈራሪያ ተሰደው ፅ/ቤቶች በኃይል ተዘግተው ምርጫ ለመሳተፍ እንደሚቸገር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ፤ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም እንዲያውቁት እንፈልጋለን ብሏል።

#OFC
"አሜሪካ የሰሜን ኮሪያ ትልቋ ጠላት ናት" - ኪም ጆንግ ኡን

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ዩናይትድ ስቴትስ የአገራቸው 'ትልቋ ጠላት' መሆኗን በመግለጽ ማንም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢሆን ፒዮንግያንግን በተመለከተ ዋሽንግተን ፖሊሲዋን ትቀይራለች ብለው እንደማይጠብቁ ገልፀዋል።

ኪም በገዢው የሠራተኛ ፓርቲ ብዙም ያልተለመደ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ የሰ/ኮሪያን የኒውክሌር የጦር መሣሪያና የጦር አቅም እንደሚያሳድጉ ቃል ገብተዋል።

የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ ዕቅድ ለመጠናቀቅ ጫፍ ደርሷል ብለዋል።

ኪም ጆንግ ኡን ይህን የተናገሩት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት ነው።

ተንታኞች ኪም አስተያየት የሰጡት ባይደን በቅርቡ ቃለ መሃላ በመፈጸም በሚመሠርቱት በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ላይ ጫና ለማሳደር ነው ብለዋል።

በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ በተደረጉ ውይይቶች ብዙም ተጨባጭ ውጤት ባይመጣም ኪም ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር መልካም ወዳጅነት ነበራቸው።

ኪም ባደረጉት ንግግር ፒዮንግያንግ "የጠላት ኃይሎች" ቀድመው በአገራቸው ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ካላሰቡ ፒዮንግያንግ የኒውክሌር መሣሪያዎቿን ለመጠቀም አታስበም ብለዋል።

"አሜሪካ ለአገራቸን አብዮት ታላቋ ጠላታችን እና ትልቋ መሰናክል ነች ... ማንም ስልጣን ቢይዝ በሰሜን ኮሪያ ላይ ያለው የፖሊሲው አይቀየርም" ማለታቸውን የአገሪቱ መንግሥት ዜና ወኪል ዘግቧል። ~ BBC

@tikvahethiopiaBot
#Twitter

ትዊተር ላይ 88.7 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስከመጨረሻው ትዊተር እንዳይጠቀሙ አካውንታቸው ታገደ።

ትዊተር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ትራምፕ በአካውንታቸው ላይ 'በቅርቡ ያሰፈሯቸውን መልዕክቶች በደንብ ከመረመረ' በኋላ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProfessorBeyenePetros

ታዋቂው ፖለቲከኛ እና ምሁር ፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ በህይወት ዘመናቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ የምስጋና ስነ-ሰረዓት እየተካሄደላቸው ነው።

የምስጋና ስነስርዓቱ በአዲስ አበባ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የፕሮፈሰሩ 70ኛ አመት የልደት በአል እና የረጅም ጊዜ ፖለቲካዊ እና ምሁራዊ አገልግሎት ይዘከራል ተብሏል።

ፕሮፌስር በየነ ጴጥሮስ ለሰላማዊ የፖለቲካ ማጎልበት ያላቸው ሚና ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ ላይ በታዋቂ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፍ ይቀርባል።

ምንጭ፦ የደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች !

በትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ግጭት በርካታ ሰዎች በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለዋል።

66 ሺህ በላይ የሚሆኑትም ድንበር ተሻግረው ሱዳን ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል ምን ያህል ድጋፍ ፈላጊ ዜጎች አሉ ?

የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኣቶ ምትኩ ካሳ ለቢቢሲ የሰጡት መረጃ ፦

- ከኦፕሬሽኑ በፊት ከተለያዩ የክልሎች ተፈናቅለው ወደ ትግራይ የሄዱ 110 ሺህ ዜጎች አሉ። (እነዚህ በተለያዩ ጊዜት በተለያዩ ክልሎች በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለው ትግራይ ክልል የገቡ ናቸው)

- በአሁን ሰዓት የተፈናቀሉትን ለመለየት 3 ቡድን ተሰማርቷል። ቡድኑ ከኮሚሽኑ ፣ ከዓለም አቀፍ NGO የተውጣጣ ነው። ስራቸውን ሲጨርሱ በሚቀጥለው ሳምንት ቁጥሩ ይገለፃል።

- በመደበኛው ሰዓት (ከኦፕሬሽኑ በፊት) በትግራይ ክልል 1.8 ሚሊዮን ተረጂ ነው ያለው ፥ ከዚህ ውስጥ 1.1 ሚሊዮኑ ሴፍቲኔት ነው፣ 600 ሺህ የዕለት ደራሽ እርዳታ የሚቀርብላቸው ናቸው፣ 110 ሺህ ከላይ የተገለፁ ተፈናቃዮች ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅር በትግራይ ክልል 2.3 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደሚፈልጉ ገልጿል።

በሰሜናዊ ምዕራብ፣ ምስራቃዊ እና ማዕከላዊ ትግራይ በርካታ ቦታዎች እና የሽመልባ እንዲሁም ሒጻጽ ስደተኛ ጣቢያዎች አሁንም በጸጥታ ጉድለትና ቢሮክራሲ ሳቢያ ለዕርዳታ ተደራሽ አልሆኑም፡፡

በርካታ የጤና ማዕከሎች እና የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች እንደተዘረፉ እና ጉዳት እንደደረሰባቸው ሪፖርቱ ገልጿል።

https://www.unocha.org/story/daily-noon-briefing-highlights-ethiopia-9

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FreedomandEqualityParty

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምርጫ 2013 የሚያደርገውን ዝግጅት አካል የሆነው የቅድመ እጩ ምዝገባ በይፋ ጀምሯል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ሙሐመድ በአማራ ክልል የኦሮሞ ዞን ባቲ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር የቅድመ እጩነት ፎርም መሙላታቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EZEMA

ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)ን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎች ከዛሬ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ መታወቅ እንደሚጀምሩ ፓርቲው በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#GadaSystem የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የተመዘገበበትን አራተኛው ዓመት በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ይከበራል። ከ4 ዓመት ወዲህ የተከናወኑ ተግባራት የሚገመገሙበት መድረክ ጥር 1 እና 2 በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እንደሚካሄድ ተገልጿል። Via ENA @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የ "ገዳ ስርአት" ለአለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ አመት የመታሰቢያ በአል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የገዳ ፓናል ውይይት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች የፌዴራል መንግስት ኃላፊዎች ፣ የምእራብ ጉጂ ዞን ኃላፊዎች እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ የገዳ ስርአትን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል።

ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ይሆናል። ~ EPA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT