TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Metekel

በድባጤ 'ዚጊ ቀበሌ' ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ንፁሃን ሲገደሉ አንድ ሰው ቆስሏል።

ጥቃቱ በትላንትናው ዕለት ማለዳ ላይ እንደተፈፀመ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ገልጿል።

የሟቾች የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት ተፈፅሟል።

በጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ አንደኛው ባለትዳር እና 5 ልጆች አባት እንደሆኑ ወንድማቸው ትላንት ምሽት በተሰራጨ መደበኛው የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ሲናግሩ ተደምጠዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ ታደለ ተረፈ ጥቃቱን አረጋግጠዋል ፥ እሳቸውም በድባጤ ወረዳ በዚጊ ቀበሌ ወደ ማሳቸው በሚሄዱ 3 ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ 2ቱ መገደላቸውን አንደኛው መቁሰሉን መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ትላንት የመተከል ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር በዞኑ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#SolianaShimeles

የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዝግጅት ፦

ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ (የምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ) ስድስተኛው (6) አገራዊ ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ቁሳቁሶች 90 በመቶ ተገዝተው መጠናቀቃቸውን ለኢፕድ ተናግረዋል።

ለምርጫው የተገዙት ቁሳቁሶቹ እንዲሁም ህትመቶች ከዚህ በፊት ምርጫ ከተደረገባቸው ቁሳቁሶች እና ህትመቶች የተለዩ እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው ብለዋል።

የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹ እና የመራጭ ካርዶቹ ደግመው መታተም የማይችሉ ፣ ከተነካኩ የሚያስታውቁ፣ የራሳቸው የሆነ ቀሪ ያላቸው ፣ ኮፒ ለመደረግ የሚያስቸግሩ እንዲሁም የድምጽ መስጫ ሳጥኖቹ አስተማማኝ እና መራጩ ድምጽ ሲሰጥ በነጻነት ለመስጠት የሚያስችል መከለያዎች ያሉት እንደሆነ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም በተካሄዱት ምርጫዎች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ የተለያዩ ማጭበርበሮችን የሚያስቀሩ የምርጫ ቁሳቁሶች መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል። ~ EPA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሎኮም የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ለደንበኞቹ እያቀረበ ይገኛል።

አገልግሎቱን ለማግኘት A ፣ C ወይም L ወደ 810 መላክ ወይም *810# ላይ መደወል እንደሆነ ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችሉ መስፈቶች ተከታዮቹ እንደሆኑ አሳውቋል ፦

• የቅድመ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ጊዜ ያላለፈባቸው።

• የሞባይል አገልግሎታቸው በማንኛውም ምክንያት ያልተቋረጠ።

• ከአሁን በፊት የወሰዱትን ክሬዲት በሙሉ አጠናቀው የከፈሉ።

• ከ3 ወራት ያላነሰ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ የቆዩ እንዲሁም በየወሩ የ30 ብር የሞባይል አየር ሰዓት በመሙላት ሲጠቀሙ የነበሩ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።

ለክሬዲት አገልግሎት የተዘጋጁ የሞባይል ድምፅ እና ኢንተርኔት ጥቅሎች ዝርዝር ከላይ ባሉት 2 ምስሎች ተያይዟል።

* ኢትዮ ቴሌኮም 10% የአገልግሎት ክፍያ ቀጣይ ከሚሞሉት የአየር ሰዓት እንደሚቀንስ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ቅየራ ድጋሚ ተጀምሯል፡፡

የብር ቅየራው ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AgituGudeta #EthiopiaEmbassyRome

በጣሊያን ውስጥ ከፍየል ወተት በምታዘጋጀው አይብና ለስደተኞች መብት ተቆርቋሪነቷ የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ አጊቱ ጉደታ ቤቷ ውስጥ ተገድላ መገኘቷን ፖሊስ ማሳወቁን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለቢቢሲ አረጋገጠ።

የኤምባሲው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሠራተኛ የሆኑት አቶ ደሳላኝ መኮንን እንደተናገሩት ትናንት ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ማጣራትና ምርመራ በአጊቱ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ተጠርጣሪ ስደተኛ ወንጀሉን መፈጸሙን እንዳመነ ገልጸዋል።

በሮም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም የአጊቱ ጉደታን ሞት በተመለከተ በፌስቡክ ገጹ ላይ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፤ ግድያውን በተመለከተም ኤምባሲው ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በቶሎ ተጣርቶ ይፋ እንዲደረግና ወንጀለኛው ለፍርድ እንዲቀርብ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አመልክቷል።

የአጊቱ ግድያ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቻ ሳይሆን በጣሊያኖችም ላይ ትልቅ ድንጋጤና ሐዘን የፈጠረ መሆኑን የገለጹት አቶ ደሳለኝ በተለይ በስደት ወደ ጣሊያን የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያንን በመርዳት ስለምትታወቅ ወንጀሉ በስደተኞች ዘንድ ታላቅ ሐዘንን አስከትሏል ብለዋል።

ፖሊስ እንዳለው አጊቱ ጉደታ ትሬንቲኖ ውስጥ በሚገኘው ፍራሲሎንጎ በተባለው ስፍራ ባለው መኖሪያ ቤቷ ውስጥ ጭንቅላቷ ላይ ጉዳት ደርሶባት አስከሬኗ አግኝቷል።

ምርመራ እያደረገ እንደሆነ የገለጸው ፖሊስ የአጊቱ ጉደታ ሞት ጭንቅላቷ ላይ በመዶሻ በመምታት የተፈጸመ የግድያ ወንጀል ሳይሆን እንዳልቀረ ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopia
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ድጋፍ አደረገ።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ግምታቸው ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ከ350 ሺህ በላይ ደብተሮች እና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች አበረከተ።

ደብተሮቹ ላይ የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ፎቶግራፍ እና የክለቡ አርማ ያረፈባቸው ሲሆኑ መታሰቢያነቱም ለእሳቸው እንደሆነ ተገልጿል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ማህበር ያሰባሰበው ቁሳቁስ ከፍተኛ መጠን ያለው በመሆኑ በአዲስ አበባ፣ በማይካድራ፣ በመቐለ ፣ በመከተል እና በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ለተቸገሩ ተማሪዎች ተደራሽ ይሆናል ብሏል።

እንዲሁም ለተመረጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የተለያዩ ተቋማት ልገሳ አድርጓል ፦

- ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
- ለተስፋአዲስ የህጻናት ካንሰር መርጃ ድርጅት (TAPCCO)
- ለመከላከያ ሰራዊት
- ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
- ለትኩረት በጎአድራጎት ማህበር
- ለህይወት የተቀናጀ የልማት ማህበር
- ለትምህርት ሚኒስቴር

መልዕክቱን የላከልን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Yemen

አዲስ የተመሰረተውን የየመን መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ ጭኖ የነበረ አውሮፕላን ካረፋ ከጥቂት ቆይታ በኋላ በኤደን አየር መንግድ ተኩስና ፍንዳታ መከሰቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ማአን አብዱልማሊክን ጨምሮ የካቢኔ አባላት ወደ ቤተመንግስት በሰላም መድረሳቸው ተዘግቧል፡፡

በፍንዳታው የደረሰው ጉዳት እስካሁን አለመታወቁን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

የመን ውስጥ የእርስ በእርስ ግጭት ከተከሰተ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ የመናውያን ለስደት እንዲሁም ለሞት ተዳርገዋል፡፡

Via #AlAIN / Reuters / Hesmat Alavi
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በአ/አ አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ እና ምዝገባ አገልግሎት ተጀምሯል !

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም አዲስ የነዋሪነት ምዝገባ እና የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎቶች ላልተወሰነ ግዜ የታገደ መሆኑን ማሳወቁ ይታወቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ እገዳዉ ተነስቶ አገልግሎቱ መጀመሩን የኤጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮናስ አለማየሁ አሳዉቀዋል፡፡

ታህሳስ 21/2013 ዓ.ም
ወ/ኩ/ም/መ/ኤጀንሲ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,402
• በበሽታው የተያዙ - 468
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,131

አጠቃላይ 123,856 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,918 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 111,870 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

243 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Yemen አዲስ የተመሰረተውን የየመን መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ ጭኖ የነበረ አውሮፕላን ካረፋ ከጥቂት ቆይታ በኋላ በኤደን አየር መንግድ ተኩስና ፍንዳታ መከሰቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ማአን አብዱልማሊክን ጨምሮ የካቢኔ አባላት ወደ ቤተመንግስት በሰላም መድረሳቸው ተዘግቧል፡፡ በፍንዳታው የደረሰው ጉዳት እስካሁን አለመታወቁን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ የመን ውስጥ የእርስ በእርስ ግጭት ከተከሰተ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AdenAirport

በየመን ኤደን ኤርፖርት በነበረው ጥቃት እስካሁን 26 ሰዎች መሞታቸውን ኤ ኤፍ ፒ አስነብቧል።

በፍንዳታው ከ50 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።

አዲሱ ጠ/ሚ ማዒን አብዱልማሊክ ሰዒድ ጥቃቱን “በፈሪ ሽርተኞች የተቃጣ ነው” ያሉ ሲሆን ድርጊቱን “የግልበጣ ሙከራ” ብለውታል።

እሳቸው ከነ ካቢኔያቸው ደህና መሆናቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል፡፡

የመረጃ ሚኒስትሩ ሞሃማር አል ኤርያኒም ጥቃቱ "በሃውቲ አማፅያን" ነው የተፈጸመው ብለዋል።

እስካሁን ድረስ ግን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን በይፋ የወሰደ አካል የለም፡፡

ምንጭ፦ አል ዓረቢያ ኒውስ፣ አል ዓይን ኒውስ፣አልጀዚራ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጋዜጠኛ አዲብ አልጃኒ ህልፈት !

ዛሬ የመን በኤደን ኤርፖርት በነበረው ጥቃት ለBelqees TV የሚሰራው ጋዜጠኛ አልጃኒ ህይወቱ አልፏል።

ጋዜጠኛው ከህልፈቱ በፊት በቀጥታ ስርጭት ላይ በኤርፖርቱ ስለነበረው ሁኔታ ለሚሰራበት የቴሌቪዥን ጣቢያ ማብራሪያ ሲሰጥ ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፦

MoSHE የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እንዲማሩ መልዕክት አስተላልፏል።

በ2012 ዓ/ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በጥገና ላይ ስለሆነ ትምህርታቸውን መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተምረው እንደሚመረቁ MoSHE አሳውቋል።

ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 1 የምዝገባ ጊዜ መሆኑም ተገልጿል።

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ኩሃ ግቢ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ጥር 2 ትምህርት ይጀምራል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ግብጽ የኢትዮጵያን አምባሳደር ለማብራሪያ መጥራቷን ገለጸች !

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡት መጥራቱን አህራም ዘግቧል።

አምባሳደሩ የተጠሩት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ግብፅን በተመለከተ አስተያየት በመስጠታቸው ነው ተብሏል።

አህራም አምባሳደር ዲና የግብጽን ውስጣዊ ጉዳይ በመጥቀስ ሰሞኑን ማብራሪያ ሰጥተዋል ብሏል።

ይሁንና ቃል አቀባይ ዲና ከሰሞኑ በሰጧቸው መግለጫቸው ግብጽ የሚልን ቃል ከመጥቀስ ተቆጥበው ነበረ።

ቃል አቀባዪ በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንደነበሩ ይታወቃል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
መልዕክት ፦

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ :

የገና ስጦታ የልገሳ ጊዜ ከታህሳስ መጀመሪያ ጀምሮ እየተካሄደ ነው። ሜሪ ጆይ አረጋውያና ህፃናት በዓሉን በደስታ ያሳልፉት ዘንድ እርሶም ድጋፍ ያደረጉ ዘንድ መልዕክት አስተላልፏል።

ድጋፉን ፦
- በአልባሳት
- በቁሳቁስ
- በገንዘብ ማድረግ ይቻላል።

ሚሪ ጆይን በ 0987626262 or 0983636363 or 0911208518 ላይ ብትደውሉ ልታገኟቸው ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia