CAR ውስጥ የUN ሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ።
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ 2 የቡሩብዲ ዜጎች የሆኑ የተመድ ሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
ሌሎች ሁለት ሰላም አስከባሪዎች ቆስለዋል።
ጥቃቱን ያደረሱት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ናቸው ተብሏል።
የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ የሆኑት ስቴፈን ዱጃሪች በሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት በጦር ወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል ነው ብለዋል።
የCAR ባለስልጣናት በአስቸኳይ ጉዳዩን መርምረው ተጠያቂዎችን ህግ ፊት እንዲያቀርቡ ጉተሬዝ ማሳሰባቸውን ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።
ዛሬ በሀገሪቱ ሀገር አቅፍ ምርጫ ይደረጋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#SNNPRS
በደቡብ ክልል እስካሁን ወደ ትምህርት ቤት ያልሄዱ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች አሉ።
እነዚህን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ የመመለስ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
ከ9 ወራት በኋላ የገፅ ለገፅ ትምህርት ቢጀመርም ተማሪዎች የሚጠበቀውን ያህል በትምህርት ገበታቸው ላይ አልተገኙም ብሏል ቢሮው።
አሁን እየተካሄደ ያለው ንቅናቄ ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ ተማሪዎች ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ ያለመ ነው።
* በደቡብ ክልል በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 4 ሚሊዮን 200 ሺህ ተማሪዎችን ለመቀበል ከታቀደው ውስጥ 77 ነጥብ 3 በመቶ ተፈፅሟል። ቀሪውን በንቅናቄው ለማሳካት እየተሰራ ነው ተብሏል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
በከፋ ችግር ውስጥ ያሉ የቡለን ወረዳ ተፈናቃዮች ! በቡለን ወረዳ "በኩጂ ቀበሌ" በተፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎቻችን የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ እየተናገሩ ነው። የቡለን ወረዳ አስተዳደር ለዜጎቻችን አስቸኳይ የምግብ እና የመጠለያ ድጋፍ በማድረግ ወገንን እንታደግ ሲል ጥሪ አቅርቧል። እስካሁን ለተፈናቃዮች ከመንግስትም ሆነ ከረጂ ድርጅቶች ምንም የተላከ የምግብ ድጋፍ የለም። መንግስትም…
#Metekel
በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው።
• ስንዴ 875 ኩንታል፣
• ዱቄት 1751 ኩንታል ፣
• ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
በዚህ መሰረት 7 የሚደርሱ መኪናዎች ድጋፉን ጭነው ወደ ቦታው አቅንተዋል።
ከሰሞኑ በቡለን ወረዳ በተፈፀመው የንፁሃን ጥቃት 35 ሺህ ዜጎቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለው በቡለን ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ።
በአጠቃላይ በመተከል ዞን 56ሺ የሚደርሱ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ።
[በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን]

#የእርቀ_ሰላም_ኮንፈረንስ
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳደር እንዲሁም ኧሌ ልዩ ወረዳ አስተዳደር በአንድ ላይ ተባብረው የተፈጠረውን ግጭት በእርቅ ለመፍታት የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ አዘጋጅተዋል።
ይኸው ኮንፈረንስ ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ትላንት ለዚሁ የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ዝግጅት የክልሉ ማርሽ ባንድ በካራት ከተማ ትዕይንት አቅርቧል።
በእርቀ ሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ከሁለቱም መዋቅሮች ከሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ ከአጎራባች ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የተጋበዙ እንግዶች፣ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ይሳተፉበታል ተብሏል።
መረጃው የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።

#የቅዱስ_ገብርኤል_ንግስ_በዓል_በሀዋሳ
በሲዳማ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ከተማ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንግዶችን መቀበል የሚያስችል ልዩ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተገልጿል።
ለበዓሉ ለሚመጡ እንግዶች በፆምና ፃም ባልሆኑ የምግብ አይነት ለማስተናገድ የሰራተኛ ቁጥር በመጨመር በቂ ዝግጅት እንዳደረጉ አሳውቀዋል።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ እንደማይደረግ የሀዋሳ ንግድና ገበያ ልማት አሳውቋል።
ድንገት ዋጋ የሚጨምር ነጋዴ ከተገኘ በህግ አግባብ ወዲያውኑ በማሸግም ሆነ በመቅጣት እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።
በሌላ በኩል የሀዋሳ ከተማ የትራፊክ አደጋ መከላከል እና ቁጥጥር ዋና ስራ ሂደት በበዓሉ የትራፊክ አደጋ አንዳይከሰት እና የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር የተሸከርካሪና የእግረኛ መንገዶች መለየታቸውን አሳውቋል።
የህዝብና የመንግስት ትራንስፖርት በተገቢው ሁኔታ መዘጋጀቱ የተነገረ ሲሆን ምንም አይነት የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ከወትሮው የተለየ ቁጥጥር ይደረጋል መባሉ ከሀዋሳ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሀዋሳ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ፦
ከፊደል ካፌ ወደ ቅዱስ ገብርኤል የሚያስወጣው መንገድ ፣ ከኬራውድ ሆቴል ወደ ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም ከዋርካ አደባባይ ወደ ቅዱስ ገብርኤል ያሉ መንገዶች ለተሸከርካሪ ዝግ ይሆናል።
ለእንግዶች መኪና ማቆሚያ የሚያገለግሉ የተለያዩ ቦታዎች ከበቂ ጥበቃ ጋር መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ለየትኛውም ጉዳይ ጥቆማ መስጠት ለሚፈልግ ሰው ካለ በ 0462201046 በመደወል 24 ሰዓት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ተገልጿል።

ተፈናቃይ እናቶች በቂ ድጋፍ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።
በቻግኒ ከተማ አስተዳደር "ራንች" በተባለ ስፍራ የተጠለሉ ተፈናቃይ እናቶች ናቸው በቂ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቁት።
ተፈናቃይ እናቶች ከባድ በደል እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልፀው ህጻን ለያዙ እናቶች በቂ ምግብ፣ መጠለያ እና አልባሳት ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
ተፈናቃዮችን በማስተናገድ ላይ የሚገኘው የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዋናው አይሸሹም ወደ ከተማው በርካታ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ እየገባ መሆኑን ለአብመድ ተናግረዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ለተፈናቃዮች የነበረውን ክፍት ቦታ በማዘጋጀት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ውሃ በታንከር የማቅረብ እና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።
ድጋፉ ለሁሉም እንዲዳረስ ደግሞ ከተፈናቃዮች የጤና ፣ የውሃ፣ የግብዓት አቅርቦት እና የጥበቃ አባላት ተቋቋሞ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።
ለህፃናት ፣ ለእናቶች ፣ ለአዛውንቶች እና ተከታታይ መድኃኒት ለሚወስዱ ተፈናቃዮች ቅድሚያ ድጋፍ እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡
(AMMA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የብሉ ናይል ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ሞቱ።
የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) በሱዳን የብሉ ናይል ግዛት ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አብዱረሃማን ኑረዳኢም ዛሬ ጥዋት በመኪና አደጋ መሞታቸውን ዘግቧል።
የግዛቱ አስተዳዳሪ ህይወታቸውን ያለፈው ዛሬ ወደ ካርቱም በመጓዝ ላይ እያሉ በገጠማቸው የመኪና አደጋ እንደሆነ የሱና ዘገባ ያሳያል።
አብዱረሃማን ኑረዳኢም በቅርቡ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር በሚል ወደ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መጥተው እንደነበር ይታወሳል። (SUNA)

በዌራ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ ዛሬ ከረፋዱ 5፡00 ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል፡፡
ለጊዜው የአደጋው ምክንያት አልታወቀም ተብሏል።
በአደጋው 11 መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጣሉ እና ንብረት መውደሙ ተገልጿል።
በአደጋው በሰው እና በእንስሳት ላይ እስካሁን ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰም።
አደጋውን ለመቆጣጠር የተቀናጀ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
የዌራ ወረዳ አስተዳደር ህብረተሰቡ የበጋ ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መሰለ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
(የሀላባ ዞን ኮሚኒኬሽን)

#የእርቀ_ሰላም_ኮንፈረንስ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳደር እንዲሁም ኧሌ ልዩ ወረዳ አስተዳደር በአንድ ላይ ተባብረው የተፈጠረውን ግጭት በእርቅ ለመፍታት የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ አዘጋጅተዋል። ይኸው ኮንፈረንስ ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ትላንት ለዚሁ የእርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ዝግጅት የክልሉ ማርሽ ባንድ በካራት ከተማ ትዕይንት አቅርቧል። በእርቀ ሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ከሁለቱም መዋቅሮች ከሁሉም…
#UPDATE
በኮንሶ ዞን እና በኧሌ ልዩ ወረዳ መካከል ተፈጠሮ የነበረው ግጭት በእርቅ መፈታቱ ተገልጿል።
የሰላም እና የእርቅ ስነ ስርአቱ የተካሄደው በሁለት ህዝቦች አጎራባች በሆነችው ዲመያ ቀበሌ ነው።
የ2ቱ አስተዳደር አካላት በጋራ ጉዳይ ላይ አብረው ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።
በእርቅ ስርነስርዓቱ ላይ አቶ ርስቱ ይርዳው (የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር።
ተመሳሳይ እርቀ ሰላም ኮንፈረንስ በኮንሶ እና ደራሼ ህዝቦች መካከል ሊደረግ እንደሚገባ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ አሳስበዋል።