የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ !
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆን ዛሬ ይፋ ባደረገው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Metekel
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሳስ 13/2013 ዓ.ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መሆኑን የቡለን ወረዳው ኮሙኑኬሽን አሳውቋል።
በጥቃት ፈጻሚዎቹ በሰዓታት ውስጥ በተፈጸመው ጭፍጨፋ በቀበሌው ውስጥ ነዋሪ ከሆኑት ሰዎች መካከል 207ቱ በጥቃቱ መገደላቸውንና ሥርዓተ ቀብራቸው ትናንት፣ ሐሙስ መፈፀሙ ተገልጿል።
በተፈጸመው የጅምላ ጥቃት የተገደሉት የሦስት የተለያዩ እምነት ተከታዮች ቢሆኑም ለይቶ የተናጠል ቀብር ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ በጅምላ እንዲቀበሩ መወሰኑ ተሰምቷል። (BBC)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

በግልገል በለስ ከተማ የጦር መኮንኖች እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች እየተወያዩ ነው !
በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ያሉ መስሪያ ቤቶች በሙሉ ተዘግተው እንደሚገኙ አል ዐይን ኒውስ ዘግቧል። ከተማዋ በፀጥታ ውስጥ ነች ተብሏል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕብረት መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጄ አስራት ዴኔሮ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንና ከምክትላቸው ጌታሁን አብዲሳ ጋር በዝግ እየተወያዩ ናቸው።
በግልገል በለስ ከተማ ውስጥ ስታር ሆቴል እየተካሄደ ባለው ዝግ ስብሰባ የዞን አመራሮች እንዲወጡ መደረጉን ታውቋል።
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ውጭ እንዲሆኑ መደረጉን ተሰምቷል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ጠዋት ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከዞኑ አመራሮች ጋር ውይይት እንዳደረጉ አረጋግጠዋል።
አቶ አትንኩት እንዳሉት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕብረት መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መሪዎች በመተከል እየተወያዩ ነው፡፡
በመተከል ከሚፈጸመው የንጹኃን ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉ አመራሮች መኖራቸውን ተከትሎ ፣ ሌሎች አመራሮችስ እጃቸው የለበትም ወይ የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው አቶ አትንኩት የተጠረጠሩት አመራሮች ተይዘዋል እኛ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
አሁን ላይ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ከአቶ አሻድሊ እና አቶ ጌታሁን ጋር እየተወያዩ መሆኑንም አቶ አትንኩት አረጋግጠዋል፡፡
በግልገል በለስ ስታር ሆቴል ውስጥ የሚደረገውን ውይይት ተከትሎ የተለያየ እርምጃ የሚወሰድባቸው የከፍተኛ አመራሮች እንደሚኖሩ ይጠበቃልም ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopiaBOT

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጠ ማሳሰቢያ !
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን እሁድ ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጥዋቱ 12፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ፦
- በድሬዳዋ፣
- በሐረር፣
- በጭሮ፣
- በጅግጅጋ፣
- በፊቅ ፣
- በደገሃቡር፣
- በአዋሽ ሰባት ኪሎ፣
- በአዲጋላ፣
- በሁርሶ፣
- በአሰላ፣
- አዳማ፣
- አዳሚ ቱሉ እና ሻሸመኔ እንዲሁም በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን በኖሪያ፣ ቢሾፍቱ፣ በኢላላገዳ፣ በጆርጅ ጫማ ፋብሪካ፣ በሞጆ፣ በራም፣ በጎዴ፣ በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
ይህን በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደረጉ መልዕክት ተላልፏል።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የሙለር ሪል እስቴት ባለቤት አቶ ሙልጌታ ተስፋኪሮስ በ1 መቶ ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ፈቀደ ! አቶ ሙልጌታ ተስፋኪሮስ በተጠረጠሩበት የህወሓት ቡድንን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀል የ1 መቶ ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ ተፈቀደላቸው፡፡ በእሳቸው መዝገብ ያሉ 2 ተጠርጣሪዎች ፦ - ሓይላይ መዝገበ - ሳሙኤል አባዲ የ30,000 ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ…
* update
ዛሬ ዋስ ከእስር እንዲወጡ የተወሰነላቸው አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው አዲስ የምርመራ መዝገብ እንደተከፈተባቸው ተሰምቷል።
አቶ ሙልጌታ በመጪው ሰኞ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ይታያል ተብሎ ይጠበቃል።
በተመሳሳይ በሓይላይ መዝገበ እና ሳሙኤል አባዲ ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይግባኝ ጠይቋል።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,762
• በበሽታው የተያዙ - 481
• ህይወታቸው ያለፈ - 15
• ከበሽታው ያገገሙ - 754
አጠቃላይ 121,880 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,897 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 107,599 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
225 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#BulenWoreda
ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ታኅሣሥ 13 በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን ገልጿል።
የሟቾችን ማንነት የማጣራቱ ስራ በመታወቂያ እና ከጥቃቱ በተረፉ ሰዎች ምስክርነት አማካኝነት መጀመሩ ታውቋል።
በዚህም መሰረት፣ በጥቃቱ ሕይወታቸው ካለፉ አዋቂዎች መካከል 133ቱ ወንዶች ሲሆኑ 35ቱ ሴቶች ናቸው።
አንድ የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ በጥቃቱ አስራ ሰባት ሕጻናት ተገድለዋል። ቀሪ ሃያዎቹ አዛውንቶች መሆናቸው ተረጋግጧል።
ከሟቾች መካከል ሁለቱ በቡለን ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እያለ ታኅሣሥ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የሞቱ መሆናቸውን፣ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በቡለን ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች (ጭላንቆ ፣ በኩጂ ፣ ዲሽባኮ እና ባር) የተፈናቀሉና ቁጥራቸው ከ500 የሚበልጡ ሰዎች በጋሌሳ ቀበሌ በሚገኝ የአውቶቡስ መናኃሪያ እንዲሁም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀበሌውን ጥለው ከ40 ኪ.ሜ. በላይ በእግራቸው በመጓዝ ወደ ቡለን ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።
የቡለን ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተፈናቃዮችን እየመገቡ ነው።
ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እስከሚመለሱ ድረስ የሚቆይ አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ኢሰመኮ ያስታወቀ ሲሆን ተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች በሰብአዊ እርዳታ እጥረት ምክንያት ለተጨማሪ አደጋ እንዳይጋለጡ ለመከላከል የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስቧል።

የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ! ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆን ዛሬ ይፋ ባደረገው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው አሳውቋል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BONGA
ትላንት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ዉሳኔ መስጫ ቀን መግለጹን ተከትሎ ምሽቱን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች እንዲሁም የከተማይቱ ነዋሪዎች ደስታቸውን አደባባይ ወጥተው ሲገልፁ አምሽተዋል።
የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆነ የምርጫ ቦርድ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይጠቁማል።
Via Kafa Zone Communication
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ትላንት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ዉሳኔ መስጫ ቀን መግለጹን ተከትሎ ምሽቱን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች እንዲሁም የከተማይቱ ነዋሪዎች ደስታቸውን አደባባይ ወጥተው ሲገልፁ አምሽተዋል።
የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆነ የምርጫ ቦርድ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይጠቁማል።
Via Kafa Zone Communication
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
* የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ !
የትምህርት ቤቶችን ድጎማ በጀት (school grant) ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ የትምህርት ር/መምህራን፣ መምህራንና በጽ/ቤት ባለሙያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡
በባስኬቶ ልዩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በዳብፃ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ር/መምህር፣ ሁለት መምህራን፣ የወረዳው ት/ጽ/ቤት ልማት ዕቅድ አስተባበሪያ፣ የአንድ መምህር ባለቤትን ጨምሮ 5 አምስት ግለሰቦች ምናባዊ ትምህርት ቤት በመፍጠርና የሌለ ተማሪ በመመዝገብ ህገ-ወጥ የባንክ አካውንት በመክፈት 237,680.00 ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ከወረዳው ፀረ-ሙስና በደረሰን ጥቆማ መሰረት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ግለሰቦቹን ለህግ እንዲቀርቡ አድርጓል፡፡
በተደረገው የህግ ማጣራት ሥራ የባስከቶ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀለኛ ሆነው በተገኙ ግለሰቦች ላይ በ25/03/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በእያንዳንዳቸው ላይ ከአንድ ዓመት ተኩል እስከ አራት አመት ጽኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡና የወሰዱትን ገንዘብ ለመንግስት ተመላሽ እንዲያደርጉ መወሰኑን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በከፋ ችግር ውስጥ ያሉ የቡለን ወረዳ ተፈናቃዮች !
በቡለን ወረዳ "በኩጂ ቀበሌ" በተፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎቻችን የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ እየተናገሩ ነው።
የቡለን ወረዳ አስተዳደር ለዜጎቻችን አስቸኳይ የምግብ እና የመጠለያ ድጋፍ በማድረግ ወገንን እንታደግ ሲል ጥሪ አቅርቧል።
እስካሁን ለተፈናቃዮች ከመንግስትም ሆነ ከረጂ ድርጅቶች ምንም የተላከ የምግብ ድጋፍ የለም።
መንግስትም አስፈልጊውን ድጋፍ እንዲያድርግ ጥሪ ቀርቧል።
ችግሩ ግን በመንግስት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ለተፈናቀሉ ወገኖች እኔንም ይመለከተኛል የሚል ለወገኖቹ የሚቆረቆር ሁሉ ከሀገር ውስጥ ሆነ ከውጭ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

#Tigray
• የኮሪያ ሪፐብሊክ ምስራቅ ሱዳን ውስጥ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች የ300 ሺ ዶላር ድጋፍ ማድረጓን የሱዳን ዜና አገልግሎት በድረገፁ አስነብቧል።
የኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት የሱዳን ህዝብ እና የሱደን መንግስት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ተቀብሎ ስላስተናገደ ምስጋናውን አቅርቧል።
• የስዊድን መንግስት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።
ድጋፉ በIOM ፣ WFP፣ ICRC አማካኝነት ለተጎጂዎች እንደሚደርስ እንደሆነ የስዊድን ኤምባሲ ገልጿል።

#AddisAbabaUniversity
ዛሬ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን እና በማታ ያሰለጠናቸውን 4,087 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።
ከተመራቂዎቹ መሀከል ፦
• 48ቱ በ3ኛ ዲግሪ በቀን የሰለጠኑ
• 809 በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ ፕሮግራም
• 3,039 በቀን
• 18 በርቀት የሰለጠኑ ናቸው።
ዛሬ ከሚመሩቁ መካከል በህክምና ስፔሻሊቲ 26 ተማሪዎች ይገኙበታል።
የዛሬዎቹ ተመራቂዎች 2,635 ወንዶች ሲሆኑ 1452 ሴቶች ናቸው፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

#FDREDfeneseForce
መከላከያ በወሰደው እርምጃ የተደመሰሱ ከፍተኛ የሕወሓት አመራሮች መኖራቸውን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ፡፡
ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የሞቱ አመራሮች መኖራቸውን ተናግረው ይህም ወደፊት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
በመተከል ዞን ውስጥ በተደጋጋሚ እያጋጠመ ያለውን የዜጎች ጭፍጨፋ ለማስቆም የመከላከያ በሽፍታዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል፡፡
እንደ ጄኔራል ብርሃኑ ገለጻ ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮም ወደ መተከል የሄዱት ለዚሁ ተግባር ነው፡፡
እስካሁንም ሀገር መከላከየ በርካታ ጸረ ሰላም ኃይሎች ላይ እርምጃ እንደወሰደ ጄኔራሉ ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ይህ ሥራ በጸጥታ ኃይል ብቻ የሚሰራ እንዳልሆነና የፖለቲካ ስራ እንደሚጠይቅ ነው ያብራሩት፡፡
በአመራሮች መካከል ያለው የፖለቲካ ሽኩቻ፣መሬትህ ሊነጠቅ ነው በማለት ሽፍቶችን ማደራጀት እንዲሁም የውጭ ኃይሎች ተሳትፎ ለአካባቢው ቀውስ ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑም አንስተዋል፡፡
ይህም ነገሮችን እንዳወሳሰበ ነው ጄኔራሉ ያነሱት፡፡ ሽፍቶቹ እርምጃ ሲወሰድባቸው ጎረቤት ሀገር ጭምር እየሄዱ እንደሚሸሸጉም ጄኔራል ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡
ነባሩ (Indigenous) ማሕበረሰብ እንዲሁም ‘ደገኛው’ የየራሳቸው ችግር እንዳለባቸውም የተናገሩ ሲሆን ‘ደገኛው’ መተከል የኛ ነው የሚል ፖለቲካ የማራመድ ከነባር ብሔረሰቦች ደግሞ የጉሙዝ ሽፍቶች ንጹኃንን የመግደል ተግባሮች እንደሚፈጸሙ ገልጸዋል፡፡
ዋናው የፖለቲካው መበላሸት ስለሆነ ለዘላቂ መፍትሔ ፖለቲካዊ ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (አል ዓይን ኒውስ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,709
• በበሽታው የተያዙ - 533
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 670
አጠቃላይ 122,413 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,901 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 108,269 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
236 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።