TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በዛሬው ዕለት 'የወረቀት አልባ ጉምሩክ አገልግሎት' ምረቃ ስነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተከናውኗል።

አገልግሎቱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት የንግድ ትስስር እንዲጠናከር ፣ የጋራ የድንበር አስተዳደር ስርዓት በውጤታማነት እንዲከናወን፣ እንዲሁም በጉምሩክ እና በንግዱ ማህበረሰብ መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲፈጠር ያስችላል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ አስተደር እና ልውውጥ ስርዓትን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማዘመን እንዲሁም በጉምሩክ ስርዓት ሂደት ተጠያቂነት እና ግልጸኝነትን በመፍጠር፣ የሰነድ መጭበርበርን በማስቀረት ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓት እንዲሰፍን አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 2/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች፦

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 114 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው አልተገኘም።

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 51 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 682 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 80 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,408 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 17 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከመኮድ ህክምና ማዕከል)

በቫይረሱ የተያዙት፦
- 6 ከባህር ዳር ከተማ
- 3 ከአዊ ብ/ሰብ ዞን
- 2 ከምዕ/ጎጃም ዞን
- 4 ከጎንደር ከተማ
- 2 ከሰ/ወሎ ዞን

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 148 የላብራቶሪ 15 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1,178 የላብራቶሪ ምርመራ 47 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት፦
- ከቤንች ሸኮ ዞን 16 (8 ከሚዛን አማን፣ 6 ከሸኮ እና 2 ከደቡብ ቤንች)
- ከወላይታ ዞን 12 (11 ከቦሎሶ ቦምቤ እና 1 ከሶዶ ከተማ)
- ከጌዴኦ ዞን 8 (4 ከኮቾሬ እና 4 ከይርጋጨፌ)
- ከደቡብ ኦሞ ዞን 6 (5 ከጂንካ ከተማ እና 1 ከሳላማጎ)
- ከጉራጌ ዞን 3 (3ቱም ከቸሀ)፣
- ከጋሞ ዞን 2 (2ቱም ከአርባምንጭ ከተማ) ናቸው

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 123 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 6 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

መስከረም 2/2013 ዓ/ም

የተደረገ ላብራቶሪ ምርመራ - 8,191
በቫይረሱ የተያዙ - 521
ህይወታቸው ያለፈ - 10
ያገገሙ - 469

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወላጆች ስጋት!

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ)

አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ባስቀመጡት ቀነ ገደብ ወላጆች ምዝገባ ካላደረጉ በቀጣይ እንደማይቀበሏቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እያላኩ ይገኛሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ የግል ትምህርት ቤት ሁለት ልጆቹን የሚያስተምረው ወላጅ ልጆቹ ካለባቸው የመተንፈሻ አካል ችግር በቀጣይ እንዴት ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ለከፍተኛ ጭንቀት እና ስጋት እንደዳረገው ይናገራል።

ስለሆነም መንግስት መቼ እና እንዴት ትምህርታቸውን መከታተል እንደለባቸው ግልጽ ባልሆነ መልኩ ባለ ማስቀመጡ የተነሳ ወላጆች ለተጨማሪ ችግር እየተዳረጉ ይገኛሉ።

በተለይም የግል ትምህርት ቤት ክፍያዎች እጅጉን ውድ በመሆናቸው በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ሲዘጋ ከክፍያው አንጻር የተመጣጠነ እውቀት ሳያገኙ ክፍያ ብቻ መክፈላቸው ሳያንስ ዛሬም ዳግም መንግስት መቼ እና እንዴት እንደሚማሩ ሳይገልጽ ምዝገባ ብቻ እንዲያካሂዱ መደረጉ ፍጹም ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ።

ይህንን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ከምዝገባው ተጨማሪ የኳርተር (የሩብ አመት) ክፍያን እንድንከፍል የተለያዩ ዛቻ የሚመስሉ የማስጠንቂያ ደብዳቤዎች በመላክ ስጋት ውስጥ እንደከተቷቸው ይናገራሉ።

ስለዚህም የትምህርት ሚኒስቴር እና የሚመለከታቸው ሁሉ በቀጣይ የመተንፈሻ አካላት እና ተዛማጅ በሽታ ባለባቸው ህጻናት ዙሪያ እንዲሁም ክፍያን በተመለከተ ተገቢውን ግልጽ የሆነ መግለጫ መስጠት እና መፍትሄ መፈልግ ይኖርባቸዋል በማለት ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ።

እኛም ትምህርት ቤቱ የላከውን የማስጠንቀቂያ መልዕክት በማያይዘን ትኩረት ለህጻናት እንዲሰጥ በማለት መልዕክታችንን እናደርሳለን።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር አስታወቁ!

በዛሬው እለት ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት ፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ በሁሉም የሶማሌ ክልል አከባቢዎች ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር እና ከአሁን በኋላ ለአንድም የሲቪል ማህበረሰብ ትጥቅ እንደማይፈቀድላቸው አስታወቀዋል።

በተጨማሪ ከመንግሥት ጦር መሳሪያ ውጭ ፣ ለሲቪል ግለሰቦች ታጥቆ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑንም ዋና አዛዥ መሀመድ አህመድ ገልፀዋል ።

አክለውም ይህ የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ውሳኔው ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ተብሎ የታወጀ ውሳኔ እንደሆነ ኃላፊው አብራርተዋል።

የክልሉ ፀጥታ አካላት በክልሉ ውስጥ ያለው የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ዘመቻ በቂ አቅምና ዝግጅትም አላቸው ያሉት ዋና አዛዥ መሀመድ አህመድ ሁሉም የክልሉ ፀጥታ አካላት በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ህዘቦች ላይ ከማንኛውም የፀጥታ ችግር የመከላከል ግዴታቸውን እንዲወጡና በአንድም የሲቪል ግለሰብ እጅ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ እንዳይታይ አሳስበዋል።

በክልሉ ውስጥ በተለይ በማህበረሰቡ ይዞታ ያለውን ጦር መሳሪያዎች በአርብቶና አርሶ አደሩ ማህበረተሰብ መካከል ግጭት በመፍጠር ለዜጎች ኪሳራና የህይወት ማጥፋት አደጋ እንደሚያስከትልም ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ ለሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ የመመርመርያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካ በይፋ መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማምረቻ ፋብሪካውን መርቀው የከፈቱት ቦሌ ለሚ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ነው። (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ የተመረቀው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መመርመሪያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ስራ ለሰሩት ዶ/ር አርከበ እቁባይ ምስጋና አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዓለም ተስፋ የጣለበት የኦክስፎርድ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ክትባት ምርምር እንዲቆም ተደረገ። የመጨረሻ የክሊኒካል ሙከራ ላይ የነበረው እና ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የቆየው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከመድሃኒት አምራቹ አስትራዜኔካ ኩባንያ ጋር እያበለጸጉት የነበረው የኮሮና ክትባት ነበር። ምርምሩ ለጊዜው ባለበት ይቁም ተብሏል። ምክንያቱ ደግሞ የክትባት ቅንጣቱን የወሰዱ በጎ ፍቃደኛ…
#UPDATE

ከጥቂት ቀናት በፊት ተቋርጦ የነበረው አስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እየሰሩት ያለው ዓለም ተስፋ የጣለበት የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ዳግም ሊጀመር መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

የክትባት ሙከራው እንዲቆም የተደረገው በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ አንድ የሙከራው ተሳታፊ ላይ የጎንዮሽ ችግር በመታየቱ ነበር።

ባሳለፍነው ማክሰኞ አስትራዜኔካ፤ ምርምሩ እንዲቆም የተደረገው በሙከራው ተሳታፊ ላይ የታየው የጤና ችግር ከክትባቱ ጋር ይያያዝ ፤ አይያያዝ እንደሆነ ለመፈተሽ እንደሆነ ተናግሯል።

ይሁን እንጅ ትላንት ቅዳሜ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የክትባቱን ሙከራ መቀጠል እንደሚቻል አስታውቋል።

ምርምሩ ተሳታፊ ያጋጠማቸው ጤና እክል በተመለከተ ሚስጢር ለመጠበቅ ሲባል እንደማይገልፅ የተነገረ ቢሆንም ኒው ዮርክ ታይምስ በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የሚገኙት የሙከራው በጎፈቃደኛው በአንድ በኩል ያለው የአከርካሬ አጥንታቸው ላይ ያሉ ነርቮች መቆጣት እንዳጋጠማቸው ዘግቧል።

Via BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የአዲስ አበባ ኮቪድ-19 የፊልድ ሆስፒታል በዛሬው እለት በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል፡፡ ሆስፒታሉ ከባድ የኮቪድ ምልክቶች ለሚያሳዩ ህመምተኞች ህክምና የሚሰጥ ሲሆን አቅማችንን የሚያሻሽሉ በቂ የህክምና መሳሪያዎችም እንዲሟሉም አድርገናል። ሆስፒታሉ በቀጣይ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ለአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ሰጪ የህክምና ቡድኖች ስልጠናን ይሰጣል፡፡" - ዶክተር ሊያ ታደሰ (የጤና ሚኒስትር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቤት ለቤት እየዞረች ትምህርት የምታስተምረው ቱርካዊቷ መምህርት!

(BBC)

በምስራቃዊ ቱርክ በምትገኘው ቫን ግዛት የምትገኝ ጋምዜ አርስላን የተባለች መምህርት በበይነ መረብ ትምህርታቸውን መከታተል ለማይችሉ ተማሪዎች ቤት ለቤት እየዞረች ትምህርት ትሰጣለች።

"በትምህርት ቤታችን ውስጥ ኢንተርኔት አለ ነገር ግን በዚያ ማስተማር እልቻልንም። ምክንያቱም በርካታ ወላጆች በቤት ውስጥ ኢንተርኔት የላቸውም" በማለት ሃበርቱርክ ለተባለው የዜና ወኪል ተናግራለች።

"ነጭ ሰሌዳዬን ይዤ ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት እየሄድኩ አስተምራለሁ" በማለት የምትናገረው ጋምዜ በቫን ቱስባ ግዛት ውስጥ ያሉ መንደሮችንም ማካለል አለባት።

በየቀኑም ማስተማር ፣ የቤት ስራቸውን በአግባቡ ሰርተው እንደሆነ መቆጣጠርና መከታተል ከዚያም በተጨማሪ አካላዊ ርቀታቸውንና ንፅህናቸውን በጠበቀ መልኩ የመማር የማስተማር ሂደቱ እንዲከናወንም ዋናው ኃላፊነት የሷ ነው።

የጋምዜ አርስላን መልካም ተግባር ከተሰማ በኋላ በርካቶች እያሞገሷትና እያወደሷት ይገኛሉ። የተለያዩ ሚዲያ ቀልብንም መሳብ ችላለች። 'ኢንተርኔት ላይኖር ይችላል ግን መምህርት ጋምዜ አለች' በሚልም በአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ፕሮግራም ተሰርቶላት ነበር ፤ የአካባቢው ባለስልጣናትም አመስግነዋታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር ከ1,000 አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,162 የላብራቶሪ ምርመራ 413 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 490 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 64,301 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,013 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 24,983 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SHARE #ሼር

አፋር የመንግስትን እና የህዝብን አስቸኳይ ድጋፍ እና እርዳታ ይሻሉ!

ይህን ከባድ የተፈጥሮ አደጋ በቸልታ የሚታለፍ አይደለም።

አፋር የሃገራችን ዳርድንበር ለዘመናት እየጠብቁ የቆዩ ፣ የሰው ልጆችን ሁሉ በእኩልነት እና በክብር ተቀብለው የሚያስተናግዱ እንግዳ ተቀባይ እና ከሌሎች ጋር ተካፍለው መብላት ህይወታቸው የሆነ የኢትዮጵያ ውድ ህዝቦች ናቸው።

እነዚህ ወገኖቻችን ባጋጠማቸው ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ ከ200 ሺህ ህዝብ በላይ ተፈናቅሎ የመንግስትን እና የህዝብን ድጋፍ እየጠበቁ ነው።

ሰብዓዊነት ሁሉም ሊሰማው ይገባል። አንድ አካላችን ሲታመም ሁሉም አካላችን እንደሚታመም ሁሉ የአፋር ወገኖቻችን ጉዳት እና ህመም እኛንም ሊያመን ይገባል።

በሌላ በኩል ፦

ጣና ሐይቅ በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩ የተነሳ ውሃው ተመልሶ በሐይቁ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችን እያጥለቀለቀ ይገኛል።

በዚሁ ምክንያት እስካሁን ድረስ በደንቢያ ወረዳ ከ600 በላይ ሰው እንደተፈናቀለ መረጃ የደረሰኝ ሲሆን ፎገራ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች፤ ሊቦ ከምከም ወረዳ ደግሞ አራት ቀበሌዎች በውሃ ተጥለቅልቀዋል።

የውሃው መጠን አሁን ካለው በላይ ጨምሮ ጉዳት እንዳይደርስ ሕዝቡ ከአካባቢው እንዲነሳና ወደ ደረቅ ቦታ እንዲሰፍር ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ክትትል ሊያደርጉ ይገባል።

(ኢስታዝ አቡበክር አህመድ፣ መልካሙ ሹምዬ ኮከብ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia