TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ10 ሚሊዮን አለፉ!

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ቁጥር ከ10 ሚሊዮን መብለጡን የworldometers ድረገፅ መረጃ ያሳያል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሟቾች ቁጥር 498,952 የደረሰ ሲሆን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 5,414,648 ደርሰዋል።

ከፍተኛ የሰው ቁጥር በቫይረሱ ከተያዘባቸው የዓለም ሀገራት መካከል አሜሪካ (2.5 ሚሊዮን ሰዎች) ፣ ብራዚል (1.2 ሚሊዮን ሰዎች) እና ሩሲያ (627,627 ሰዎች) በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የህዳሴ ግድቡ ደህንነት እንዴት እየተጠበቀ ነው ?

ጀነራል ብርሃኑ ጁላ (የጦር ኃይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት ፦

...ከደህንነት አንፃር በኃይል የሚሆን ነገር የለም ፤ ጦርነት ጥፋት ነው እንጂ ውሃም አያስገኝም ፣ ልማትም አያስገኝም ቀጠናውን በሙሉ ነው የሚጎዳው የበለጠ ደግሞ የምትጎዳው ግብፅ ልትሆን ትችላለች።

እኛ ባለመልማታችን ችግር ላይ ነው ያለነው ለመልማት ነው እየሞከርን ያለነው፣ ለመልማት የሚሞክርን ሀገር መደገፍ ነው እንጂ ማደናቀፍ ተገቢ አይደለም።

በዚህ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም ኢትዮጵያን እየደገፈ ነው ፤ ከኢትዮጵያ ጎን ነው። ያ የመጀመሪያው ሞቅታ ልክ አይደለም!

ግድቡ እየተሰራ ነው ፤ ስራውም ይቀጥላል። ግድቡን የሚያጠቃ ነገር ይመጣል ብለን አንጠብቅም ፤ ከመጣም እንመክታለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተማሪዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ ምንድነው ?

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምከንያት በተቋረጠው ትምህርት ዙሪያ የተማሪዎች ቀጣይ እጣ ፋንታ አገር አቀፉ ኮማንድ ፖስት በሚያስተላልፈውና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሚወሰን መሆኑን ኢ.ፕ.ድ. (EPA) ዘግቧል : https://telegra.ph/EPA-06-28

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በ2 ሳምንት ስምምነት ላይ ባይደረስስ ?

የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች ቡድን አባል ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው በትላንትናው ዕለት ከአልጀዚራ የአረብኛው ክፍል ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። ይህን ቆይታቸውን ኡስታዝ ጀማል በሽር አህመድ ተርጉሞ ለህዝብ አሰራጭቷል።

በአልጀዚራ አረብኛው ክፍል ከተነሳላቸው ወሳኝ ጥያቄዎች አንዱና የብዙ ሰዎች ጥያቄ የሆነው እንደው አይበለውና በሁለት ሳምንት ውስጥ በሀገራቱ መካከል ስምምነት ላይ ባይደረስ ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት ትችጀምራለች ? የሚለው ነበር።

የአልጀዚራ ጋዜጠኛ : በሁለት ሳምንት ውስጥ ስምምነት ላይ ባይደረስ ኢትዮጵያ ውሃውን መሙላት ትጀምራለች ? በአጭሩ ይመልሱልኝ።

ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው : አዎን/نعم/na'am/yes

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3895 የላብራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5689 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 87 (52 ከጤና ተቋም እና 35 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 4 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ህይወታቸው ያለፈ 4 ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ20 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በሕክምና ላይ የነበረ።

2. የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በሕክምና ላይ የነበሩ።

3. የ80 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

4. የ21 ዓመት ወንድ የሐረሪ ክልል ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረ።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 98 ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 117 ሰዎች (78 ከአዲስ አበባ፣ 35 ከትግራይ ክልል እና 4 ከድሬደዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2132 ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
#COVID19Harari

ከአዲስ አበባ ከተማ ቀጥሎ ከፍተኛው የ24 ሰዓት ኬዝ የተመዘገበው በሐረሪ ነው። 100 የላብራቶሪ ምርመራ 7 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

6 ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ ሁለቱ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ፤ አምስቱ ለህክምና ወደ ሐረር መጥተው ናሙና የተወሰደላቸውና ነዋሪነታቸው 1 ሰው ሱማሌ ክልልና 6 ሰዎች ምስራቅ ሐረርጌ ዞን የሆኑ ናቸው።

#COVID19Tigray

በትግራይ ክልል ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ያገገሙ ሰዎች 96 ደርሰዋል። ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 19 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል (የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ላይ አልተገለፀም)።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 195 የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል (2 ሰዎች የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸውና 1 ሰው ንክኪ ያለው ነው)፤ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 209 ደርሰዋል።

#COVID19Oromia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 215 የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ከተገኝቶባቸዋል። የ24 ዓመት እድሜ ያለው የምሥራቅ ሐረርጌ ነዋሪ ከማህበረሰቡ የተገኘ ፣ የ55 ዓመት እድሜ ያላቸው የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ነዋሪ ከማህበረሰቡ የተገኙ እንዲሁም 20 ዓመት ሴት ከምዕራብ ሐረርጌ ናት።

#COVID19Amhara

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 451 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሰው ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ቫይረሱ የተገኘበት የ23 ዓመት ወጣት ሲሆን በወረይሉ አውቶብስ መናኸሪያ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ነው ቫይረሱ ሊገኝበት የቻለው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ሶስት 3,735 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 99 ሰዎች ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው አንድ (1) ፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሁለት (2) ሲሆን የቀሩት ዘጠና ስድስት (96) ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሬዝዳንት ዩዋን ኦርላዶን ሄርናንዴዝ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!

(በአል አይን - AlAin)

የሁንዱራሱ ፕሬዝዳንት ዩዋን ኦርላንዶን ሄርናንዴዝ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተይዘው ሆስፒታል እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ቅዳሜ ዕለት ዶክዩመቶችን እያነበቡ የሚያሳዩ ሁለት ፎቶዎችን በትዊተር ገጻቸው “አሁንም ድረስ ሆስፒታል ውስጥ ነኝ ፤ ነገር ግን ሕዝቤን ለማገልገል ሁልጊዜም እሰራለሁ” ከሚል ጽሁፍ ጋር አስፍረዋል፡፡

በሆስፒታል ሆነው የተለያዩ ህግና ደንቦችን መፈረማቸውንም ፕሬዝዳንት ሄርናንዴዝ ገልጸዋል፡፡

አንድ የመንግስት ቃል አቀባይ ፕሬዝዳንቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና መሻሻል እያሳዩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሲኤንኤን እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው እ.ኤ.አ. ሰኔ 16 ሲሆን ባለቤታቸው እና ሁለት ረዳቶቻቸውም ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ህዝቡን የሚያውኩ ከሆነ ከሰራዊቱ ጋር ይጣላሉ" - ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

የጦር ኃይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ከOBN HORN AFRICA ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ምርጫ እንዴት ነው የሚካሄደው ፣ ምርጫ እንዴት ነው የሚራዘመው ፣ በምን ምክንያት ነው የሚራዘመው ፣ ህገመንግስታዊ ትርጉሙ ምንድነው ? የሚሉ ስራዎች የእኛ ስራ አይደሉም ብለዋል።

ጀነራሉ ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ሁሉም ፓርቲዎች ሀሳባቸውን የመስጠት ፣ የመከራከር ፣ የተለያየ አማራጭ የማምጣት መብት አላቸው ፣ ፓርቲዎች ህገ መንግስት ይሻሻል፣ ፓርላማ ይበተን ፣ ህገ መንግስት ይተርጎም ፣ የሽግግር መንግስት ይመስረት፣ ባላደራ መንግስት ይቋቋም ሊሉ ይችላሉ ይህ ሁሉ ስራ ግን የፖለቲከኞች እንጂ የሰራዊቱ ስራ አይደለም ሲሉ ገልፀዋል።

አንዳንዶች ሐምሌ ወር ምርጫ ማድረግ አለብን የሚሉም አሉ ይህን ማለትና መከራከር ይችላሉ እኛ እዛ ውስጥ አንገባም ስራችንም አይደለም ብለዋል።

ጀነራል ብርሃኑ የሰራዊቱ ስራ የህዝቡን ደህንነት በህገ መንግስት መሰረት መጠበቅ ነው ፤ በሰላም ወጥቶ እዳይገባ፣ ሰርቶ እንዳይበላ፣ የሚያስጨንቀውና የሚያንገላታው፣ የህይወቱን ዋስትና የሚያሳጣው ነገር እንዲፈጠር በፍፁም አንፈቅድም ሲሉ ተናግረዋል።

'በፖለቲከኛው እርግጫ ህዝቡ መረገጥ የለበትም' ያሉት ጀነራል ብርሃኑ ፖለቲከኞች መደራደር ፣ መፎካከር ፣ መወያየት ፣ በሃሳብ መፋጨት ፣ ጎዳና ወጥተው ሰልፍ ማድረግ ፣ ተደራድረው ስልጣን መካፈል ፣ በሰላማዊ መንገድ ተወዳድሮ በማሸነፍ ስልጣን መውሰድ ይችላሉ ነገር ግን ህዝቡን የሚያውክ ነገር ካደረጉ ከሰራዊቱ ጋር ይጣላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አጫጭር መረጃዎች ኮቪድ-19፦

- በብራዚል ትላንት 30,476 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,344,143 ደርሷል።

- በአሜሪካ ትላንት 40,540 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ የ285 ሰዎች ህይወት አልፏል።

- ትላንት በኒው ዮርክ 5 ሰዎች ብቻ በቫይረሱ ሞተዋል፤ ከመጋቢት ወር ወዲህ የተመዘገበ ዝቅተኛ የሞት ቁጥር መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

- በUAE የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ከሰኔ 28/2012 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ስራቸው እንደሚመለሱ ተገልጿል።

- በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 504,779 ደርሷል።

- በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ385,000 በላይ ሆኗል፤ የሟቾች ቁጥርም ወደ 10,000 እየተጠጋ ነው።

- ጋና ለጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ጥቅማ ጥቅም በ3 ወር ማራዘሟን ቢቢሲ ዘግቧል ፤ በዚህም የጤና ባለሙያዎቹ ደመወዛቸው ላይ የ50% ጭማሪ የሚያገኙ ሲሆን ለሐምሌ ነሐሴና መስከረም ወራት የገቢ ግብርም አይከፍሉም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ዛሬም ገዳይ ነው!

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ)

- ዛሬም በቻይና ሄቤይ ግዛት 400 ሺህ ሰዎች በአስገዳጅ እንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ ይገኛሉ።

- ዛሬም በአሜሪካ በ30 ግዛቶች ኮቪድ-19 እንደ አዲስ በማገርሸት ላይ የሚገኝ ሲሆን የሟቾችም ቁጥር ከ128 ሺህ በላይ ሆኗል።

- በብራዚል 57 ሺህ 658 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

- በዓለማችን እስከዛሬ ድረስ ከ500 ሺህ ሰዎች በላይ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ህይወታቸው አልፏል።

- በዓለማችን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ10 ሚሊየን በላይ ሆኖ ተመዝገቧል።

ስለዚህ ዛሬም በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ይገኛል። የሟቾችም ቁጥር በመጨመር ላይ ሲሆን ሚዲያውም ሆነ የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ህዝባችንም ዘውትር ጥንቃቄ ሊኖረው ይገባል ምክንያቱም በሽታው ዛሬም ገዳይ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሃሳባችሁን አጋሩ!

በኢትዮጵያ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ እንዴት እያያችሁት ነው ? በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ይታወቃል።

ምን ታዘባችሁ ? ምን የተሻሻሉ ነገሮች አሉ ? የሚታየው ቸልተኝነት ፣ የሀገሪቱ ሚዲያዎች እንደ መጀመሪያው ሰሞን ትኩረት አለመስጠታቸው ፣ መሰላቸቱ ፣ ብዙ ሰዎች ስለጉዳዩ እንደበፊቱ መስማት አለመፈለጋቸው... ያሳደረባችሁን ስጋት እንዴት ትገልፁታላችሁ ?

በተጨማሪ በኮቪድ-19 ላይ እየሰራችሁ የምትገኙ የጤና ባለሞያዎች ምን ገጠማችሁ ? ስታነሱት የነበረው ጥያቄ በአግባቡ እየተፈታላችሁ ነው ?

አስተያየት መቀበያ 👉 @tikvahethiopiaBot

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር!

የትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ ላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እና አጠቃላይ ስለ ትምህርት ጉዳይ በተመለከተ በቅርቡ ከጤና ሚኒስቴር በሚሰጥ አቅጣጫ መሰረት ጋዜጣዊ መገለጫ እንደሚሰጥ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አስታውቀዋል - @tikvahethmagazine

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ ባይደረስም የውሃ ሙሌቱን ታከናውናለች!

(የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል)

ኢትዮጵያ በጋራ የመጠቀምና አብሮ የማደግ መርህን የምትከተል ሀገር ናት፡፡ ይሁንና በራሷ የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም የሌሎችን ፈቃድ ወይም ይሁንታ የማግኘት ግዴታ የለባትም፡፡

በዘንድሮው የክረምት ወቅት ለታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ለመያዝ የምትሰራው ስራ 60 በመቶ የሚሆነው የሃገራችን ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኝ የተጀመረውን ጥረት ያግዛል፡፡

በአንፃሩ በጋራ ተጠቃሚነት ለማታምነው ግብፅ ‹‹ከእኔ ብቻ ልኑር›› የዘመናት ግትር አስተሳሰቧ እንድትወጣና በፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት ምህዋር ላይ እንድትሽከረከር ያደርጋታል፡፡

ግብፅ በቀጠናውም ሆነ በአህጉሪቱ ላይ ሁለንተናዊ ብልጫን መያዝ ስለምትፈልግ ግድቡ ውሃ እንዳይያዝ ዓለም አቀፍ ተቋማትን በመጠቀም ተፅዕኖ ለማሳደር ስትሞክር ትታያለች፡፡

ይህም ድርጊቷ የሃገራችንን ውሳኔ የሚቀለብስ ባይሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ በሃገራቱ መካከል ፍጥጫ እየተካረረ እንዲመጣ አድርጓል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኃላፊነቱን ወስዶ የኢትዮጵያ ፣ የሱዳንና የግብፅ መሪዎችን በመጋበዝ ዓርብ ምሽት ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ውይይት ማድረጋቸው በዚህ መነሻነት ነው https://telegra.ph/GERD-06-29

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia