2 ተማሪዎች ወረቀት ሲለጥፉ በዩኒቨርሲቲው የጥበቃ ሥራተኞች እና በክልሉ ልዮ ኃይሎች እጅ ከፍንጅ ተያዙ!
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዳር 24/2012ዓ.ም ምሽት 1:30 ላይ ጠዳ ግቢ አንድን ብሄር ከሌላ ብሄር የሚያጋጭ ጽሑፍ ተበትኖና ተለጥፎ ወዲያው በጸጥታ ኃይሎች እንደተያዘ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። በተመሳሳይ ቀን ከምሽቱ 4:05 አካባቢ ሁለት ተማሪዎች ወረቀቱን ሲለጥፉ በዩኒቨርሲቲው የጥበቃ ሥራተኞች እና በክልሉ ልዮ ኃይሎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
ተማሪዎች በሁሉም ግቢዎች ያለውን ሰላማዊ መማር ማስተማር የሚያውኩ ማንኛውም እንቅስቃሴ ከጸጥታና ደህንነት እይታ ውጭ አለመሆኑ እንዲያውቁት ያለው ተቋሙ እየተለየ ተልዕኮ ያላቸውን አካላት ከጥፋት ድርጊታቸው እንድትቆጠቡ አሳስቧል።
በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተጠርጣሪ ተማሪዎች ጉዳያቸው ተጣርቶ ሲጠናቀቅ። ውጤቱን ለሚመለከተው ሁሉ እደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደቱ እንደተለመደው ይቀጥላልም ብሏል።
(ጎንደር ዩኒቨርሲቲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ለዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች የሰላም ጥሪ ቀረበ!
የአማራና የኦሮሞ የሃይማኖት አባቶች፣የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ለዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ። የሃይማኖት አባቶች ፣የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ባደረጉት የሰላም ጥሪ አሁንም በከፍተኛ የትምህረት ተቋማት ትምህርታቸውን ያልጀመሩ ተማሪዎች እንዳሉ ገልጸዋል።
እነዚህ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ገብተው ሰላማዊ የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲቀጥሉ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎቹ ጥሪ አስተላልፈዋል። በተለይ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ዩኒቨርስቲዎች ወደትምህርት ገበታቸው የተመለሱ መሆኑን የጠቀሱት የሃገር ሽማግሌዎቹ ሌሎቹም ይህንን ጥሪ ተከትለው ወደሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
አንዳንድ ግለሰቦችም ተማሪዎችን ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረጓቸው እንደሆነም ታውቋል፤እነዚህም ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሃይማኖት አባቶች አሳስበዋል። በትምህርት ገበታቸው ያልተገኙ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ወደትክክለኛ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲገቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
መምህራንም የነገ የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆኑ ተማሪዎችን በአግባቡ በማረቅ ኃላፊነታቸውን ይወጡ ዘንድም አሳስበዋል። የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች የተውጣው አብይ ኮሚቴዎች ወደ መማር ማስተማሩ ያልገቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መምህራን፣ ተማሪ እና የአካባቢ ነዋሪዎችን ያወያያሉ።
(ENA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

'THE GUARDIAN' ኢትዮጵያዊውን ጋዜጠኛ መርጧል!
የ እንግሊዙ ተነባቢው ድህረ-ገፅ THE GUARDIAN የአመቱ መቶ ምርጥ ሴት ተጫዋቾች ይፋ ሲያደርግ በዳኝነት 93 የቀድሞ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና ጋዜጠኞችን ከተለያዩ የአለም ሃገራት አካቷል ::
ስምንት አፍራካዊያንን THE GUARDIAN ለዳኝነት ሲመርጥ ኢትዮጵያዊው የስፖርት ፀሃፊ እና የቲኪቫህ ስፖርት ቤተሰብ እንዲሁም የተለያዩ ጠቃሚ ትንታኔዎችን ወደ እናንተ የሚያደርሰው ፍሬው አስራት ከሌሎች ሰባት አፍራካዊያን ጋር በመሆን የድምፅ ሰጪው ፓናል አባል ነበረ።
Join👇
@tikvahethsport
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

ዮዌሪ ሙሴቬኒ የመሩት የጸረ ሙስና ሰልፍ!
የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በትናንትናው ዕለት በመሩት ጸረ ሙስና ሰልፍ ላይ ሙሰኞች የህዝብን ሃብት የሚመጠምጡቱ ተውሳኮች ናቸው ሲሉ ተናገሩ።
የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ነቃፊዎች ግን ፈጥነው ይሄ ለታይታ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም ብለዋል፡፡ ዩጋንዳ በዓለም ላይ በከፋ ደረጃ በሙስኛ ከዘቀጡ ሃገሮች መካከል የምትጠራ ስትሆን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ፡፡
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል በአምና ሪፖርቱ ዩጋንዳን ሙስና በከፋ ሁኔታ ከተንሰራፋባቸው የአፍሪካ ሃገሮች አንዱዋ አድርጎ አስቀምጧታል።
አክሺን ኤይድ የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅትም በአብዛኛው ተጠያቂው መንግሥታቸው ሆኖ ሳለ የእርሳቸው ጸረ ሙስና ሰልፍ መምራት የሚገርም ነው ብሎታል፡፡
(VOA)

መንግስት ሳያውቅ ቀርቶ ነው?
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
ለመሆኑ የት የት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ትምህርት እንዳልተጀመረ፣ የተወሰኑ ተማሪዎች እየተለዩ እንዳይማሩ ማስፈራሪያና መስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው፣ የትኞቹ ግቢዎች ውስጥ የማስፈራሪያ ወረቀቶች እንደሚለጠፉ፤ እንደሚበተኑ፣ የት የት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተማሪዎች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳሉ፣ ከየት የት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱ፣ያልቻሉ ደግሞ በየሰው ቤት እና በየእምነት ተቋማት እንዳሉ፣ በየትኛው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ዛሬም በሚሰራጩ የማስፈራሪያ ፅሁፎች ተማሪዎች ሰግተው ከማደሪያቸው ወጥተው ውጭ እንዳሉ...የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች፣ ከፍተኛ አመራሮች አያውቁም? ሀገሪቷን እያስተዳደረው የሚገኘው መንግስት አያውቅም?
ዩኒቨርሲቲዎችን የሚያሰተዳድረው አካል አያውቅም? መንግስት ይህ ሁሉ ሲደረግ፣ የማስፈራሪያ ፅሁፍ እንደልብ ሲሰራጭ፣ እከሌ ተማር እከሌ ውጣ ሲባል ቁጭ ብሎ ነው የሚመለከተው? የክልል መንግስታት የተማሪዎችን ሁኔታ ሳያውቁ ቀርተው ነው? ተማሪዎችን የሚያስፈራሩ ከህግ በላይ የሆኑ ሰዎች እንዲህ ሲፈነጩ ምን እስኪሆን እየጠበቀ ነው? መፍትሄ መስጠት ስለማይቻል ነው? ካልተቻለ ተማሪ በዚህ ሁኔታ እንዲማር ማስገደድ ምን የሚሉት አሰራር ነው? ተማሪው እና ወላጆች የዚህ አይነት ሁኔታ ሲገጥማቸው፣ችግሮች ቶሎ ካልተፈቱላቸው በሀገራቸው ተስፋ እንዲቆርጡ እንደሚያደርግ፤በመንግስት ላይም እምነት እንዲያጡ እንደሚያደርግ ሳይታወቅ ቀርቶ ነው?
ባለፉትን ሳምንታት የት የት ችግር እንደነበረ በየዕለቱ እየገለፅን ስንጮህ ነበር። ከቀን ወደ ቀን ሁሉም ነገር ወደ መደበኛ ሁኔታ ይመለሳል ብለን ስንከታተል ችግሩ በዘላቂነት ሳይፈታ ዛሬ ላይም የስጋት መልዕክቶች መቀበላችን ቀጥለናል!
@tikvahethiopiaBot

ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአራት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ተፈረመ!
ከ6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 299 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍኑ የአራት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ተፈረመ፡፡ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች፣ የፓርላማ አባላት፣ ከአራቱም የመንገድ የፕሮጀክት የመጡ የህዝብ ተወካዮች በተገኙበት 299 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍኑ የአራት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ከ6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከአሽናፊ የስራ ተቋራጮች ጋር በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈርሟል። የተፈረሙት አራት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የሃሙሲት - እስቴ፣ ጩለሴ - ሶያማ፣ የአደሌ - ግራዋ እና የጎዴ - ቀላፎ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
(ERA)

#LemmaMegersa
አሜሪካ - ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እያበረከተች ያለውን በጎ ሚና አደነቀች!
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በዋሽንግተን ዲሲ የተወያዩ ሲሆን፣ በውይይቱ ላይ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም የሚታበረክተው በጎ ሚና እና በመከላከያ ዘርፍ የምታካሄደውን ማሻሻያ አድንቀዋል፡፡ የሁለቱ አገራት 9ኛው የሁለትዮሽ የመከላከያ ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ በዋሽንግተን ከተማ ተካሂዷል።
በስብሰባው ሁለቱ አገራት በቀጣናው የጸጥታና ደህንነት፣ የመረጃ፣ ሰላም ማስከበር እና መከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ ገምቢ ምክክር ያደረጉ ሲሆን፣ ይህም የአገራቱን በጸጥታና ደህንነት ዙሪያ ያላቸውን ትብብር የበለጠ እንደሚያጎለብት ተገልጿል፡፡
አገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የበለጠ እንዲጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለጹ ሲሆን፣ ባለፉት 18 ወራት በጸጥታው ዘርፍ እያደገ የመጣው ትብብርም ለዚህ ማሳያ እንደሆነ ነው የተገለጸው። የሁለትዮሽ የመከላከያ ኮሚቴ ስብሰባው ኢትዮጵያና አሜሪካ ያላቸውን ጠንካራ ግንኙነት በማበልጸግ በጸረ ሽብር፣ በደህንነት መረጃ እና ሌሎች የትብብር ዘርፎችን በመለየት በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ እንደሚያስችላቸው ከአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
(ኢቢሲ)

#INSA
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለቀይ መስቀል የቢሮ መገልገያዎችን ድጋፍ አደረገ። ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2012 ዓ.ም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለቀይ መስቀል ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ 50 ኮምፒውተሮች፣ 28 የሀላፊ ወንብሮች ፣ ጠረጴዛ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጋል። ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን ወደ 400,000 /አራት መቶ ሺህ ብር/ የሚገመት ነው። ይህ ድጋፍ ቀይ መስቀል ለሚሰጠው አገልግሎት መጠናከር አይነተኛ አስተዋፅዖ ያለው በመሆኑ ለተቋሙ በአገልግሎታችን ተጠቃሚዎች ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን የሚል መልዕክት በቲክቫ ኢትዮጵያ በኩል እንዲደርሳቸው መልእክቱን ያስተላልፈዋል።
ህዝብ የቀይ መስቀል መስረት ነው!
የቀይ መስቀል አባል በመሆን ይመዝገቡ!
ለሰብአዊነት እንኖራለን!
(ማንደፍሮ ነጋሽ)

#Day3 #አርባምንጭ #ዊዝደምአካዳሚ
"የነገ ተስፋችሁ እኛነንና ፍቅርን አስተምሩን"
ዛሬ ከሰዓት በኃላ በነበረን መርኃግብር "በዊዝደም አካዳሚ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት" ተማሪዎች ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። ተማሪዎቹ ልዩ ልዩ የባህል ፕሮግራሞችን አዘጋጅተው የጠበቁን ሲሆን በህጻናት ግጥሞች ቀርበዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ አባቶች ተገኝተው ልጆቹን የመረቁ ሲሆን የአርባ ምንጭ የህክምና ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን

ተስፋችሁ እኛ ነን፤ ፍቅር አስተምሩን!
አርባ ምንጭ❤️ዊዝደም አካዳሚ❤️
እነዚህ ትንንሽ የነገ ሀገር ተረካቢዎች ስናይ ተስፋችን ተሟጦ እንዳላለቀ በደንብ እንገነዘባለን። ለተተኪው ትውልዱ ከቂም፣ ከክፋት፣ ከተንኮል፣ከመገፋፋት፣ ከጥላቻነፃ የሆነች ሀገር የማስረከብ ግዴታ አለብን። ለነዚህ ሀገር ተረካቢ ልጆች ፍቅር፣ መዋደድን፣ መተባበርን፣ መደጋገፍን የማስተማር ግዴታ አለበን።
#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ኡቡንቱ #Day3
ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛው አይነት ሃሳብ፣ አስተያየት እና መልዕክት ካላችሁ በ @tsegabwolde ወይም በ @tikvahethiopiaBot ላይ ማድረስ ትችላላችሁ!
@tikvahethiopia

የኢትዮጵያና የአሜሪካ የጦር አዛዦች ተገናኙ!
የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታ ማዦር ሹም ጄነራል አደም መሐመድ ማህሙዴና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ጆን ሃይተን ትላንት ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ ተገናኝተዋል፡፡
የኢታ ማዦር ሹም ፅህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ ሻለቃ ትሪሻ ጉይቦ ዛሬ ባወጡት ፅሁፍ ነው የሁለቱን የጦሮች አዛዦች ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ ተገናኝቶ መወያየት ያሳወቁት፡፡
ለአካባቢያዊ መረጋጋት ኢትዮጵያ ስላላት አስተዋፅዖና ቁርጠኛነት፣ በመላ አፍሪካ ላለው የተባበሩት መንግሥታት ሰላም የማስከበር ተልዕኮዎች ስላላቸው ድጋፍም ጄነራል ሃይተን ለጄነራል አደም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ አዛዦቹ ወታደራዊ ትብብሮቻቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው መንገዶች ላይም ተወያይተዋል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ መካከል ያለው አጋርነት ለምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋር እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን የቃል አቀባይዋ የሻለቃ ጊዮቦ የፅሁፍ መግለጫ አመልክቷል፡፡
(ቪኦኤ)

አሜሪካ ጉብኝት እያደረጉ ላሉት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ የአሜሪካ ጦር የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ፕሮግራም አዘጋጅቷል!
ፕሮግራሙ የተከናወነው ቪርጂንያ፣ አርሊንግተን በሚገኘው "ያልታወቀው ወታደር መቃብር" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ሲሆን የአሜሪካ ጦር ብርጋዲየር ጀነራል ኦማር ጆንስ አዘጋጁ ነበሩ።
Photo: U.S. Army Photography
(Elias Meseret)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሮግራሙ የተከናወነው ቪርጂንያ፣ አርሊንግተን በሚገኘው "ያልታወቀው ወታደር መቃብር" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ሲሆን የአሜሪካ ጦር ብርጋዲየር ጀነራል ኦማር ጆንስ አዘጋጁ ነበሩ።
Photo: U.S. Army Photography
(Elias Meseret)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመከላከያ ሚ/ር አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ቲቦር ናጅ ጋር ተወያዩ!
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ቲቦር ናጅ ጋር በአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በዋሽንግተን ዲሲ ተወያይተዋል።
በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በሶማልያ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለቀጣናው ገንቢ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሆነ በውይይቱ ወቅት መገለፁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል ።
በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራው የልዑካን ቡድን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በአሜሪካ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

የትግራይ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን 87 ሚሊዮን ብር የመንግስት ገንዘብ እንዲመለስ አደረገ!
የትግራይ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በተያዘው ሩብ ዓመት ብቻ በተለያየ ምክንያት ተጭበርብሮ የቆየ ከ87 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ማድረጉን አስታወቀ። የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በዓል በክልል ደረጃ ለ14ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ እንደሚከበር ተገልፇል።
የክልሉ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርሃነ ተክሉ እንደገለጹት ከመንግስት ካዝና ያለ አግባብ ለግለሰቦች ተከፍሎ የነበረ የመንግስት ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆን ተደርገዋል። የክልሉ ውሀ ስራዎች ኮንስራክሽን ኢንተርፕራይዝ ያለ አግባብ ከአንድ ግለሰብ ጋር በተጋነነ ዋጋ ያደረገውን የስራ ስምምነት እንዲሰረዝ በማድረግ 83 ሚሊዮን ብር ለመንግስት እንዲመለስ መደረጉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
ቀሪው ደግሞ በመቀሌና ዓድዋ ከተሞች ለሁለት አመታት ያህል ለመንግስት መከፈል የነበረበት የከተማ መሬት የሊዝ ውዝፍ ክፍያ መሆኑን አስረድተዋል። ከማጭበርበር ስራው ጋር ግንኝነት የነበራቸው የመንግስት ተቋማትና ግለሰቦችም በህግ እንዲጠየቁ ይደረጋል ብለዋል።
(ኢዜአ)