TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Day3 #አርባምንጭ #ኡቡንቱ

ዛሬ በአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"


ለሁሉም አካላት ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን!

#TIKVAH_FAMILY

#ፒስሞዴል #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ጋሞዞን #አርባምንጭፖሊቴክኒክኮሌጅ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Day3 በደም ልገሳ❤️

ዛሬ በአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር ላይ የኡቡንቱ አስተባባሪዎች፣ ሃሳብ አመንጪዎች፣ አዘጋጆች የሆኑ የምናከብራቸው በጎፈቃደኛ የሀገራችን ወጣቶች በደም ልገሳ መርኃግብር ላይ በመሳተፍ ደም ለግሰዋል፡፡

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

ዛሬ ማለዳ የላዳ ታክሲ በመንገድ ፅዳት ላይ የነበረች የ40 ዓመት ሴት ገጭቶ መግደሉ ተሰማ። አደጋው የደረሰው በቦሌ ክፍለ ከተማ ደሳለኝ ሆቴል አካባቢ ማለዳ 12 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተሰምቷል፡፡ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የሚዲያ ዘርፍ ሀላፊው ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እንደተናገሩት በመንገድ ፅዳት ላይ እያለች በላዳ ታክሲ ተገጭታ ሕይወቷ ያለፈው ሴት የሁለት ልጆች እናት ናት ብለዋል፡፡ የላዳ ታክሲው አሽከርካሪ የመኪናው የኋላ መስታወት ተሰብሮ እንደወጣና በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“ሁሉም ሰው ለሰላም ዘብ መቆም አለበት” በሚል መሪ ቃል የሀገር ሽማግሌዎች ውይይት እያካሄዱ ነው!

የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች ማህበር “ሁሉም ሰው ለሰላም ዘብ መቆም አለበት” በሚል መሪ ቃል ከሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በሰላም ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

የዚህ መድረክ ዋነኛ ዓላማ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም ሁሉም ዜጋ ሰላሙ የእኔ ነው የሚል ስሜት እንዲያድረበት ማድረግ እንደሆነ የሀገር ሽማግሌዎች ማህበር ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩም ላይ የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን ያከናወኗቸውን ተግባራት የሚቀርቡበትና ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል። ከዚህም ባሻገር መድረኩ በማህበሩ የወደፊት ዕቅድ ላይም ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡

(EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EthioTelecom #EliasMeseret

ዛሬ ለበርካታ ደቂቃዎች ኢንተርኔት የተቋረጠበትን ምክንያት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ለAssociated Press ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል፦

"በመጀመርያ ለኢንተርኔት መቋረጡ ይቅርታ እንጠይቃለን። እኛ ሁል ግዜ የኔትወርክ ለውጥ የምናደርገው ብዙ ሰው ኢንተርኔት በማይጠቀምበት ሰአት ለሊት ላይ ነው። ዛሬ ላይ የተከሰተው የኢንተርኔት መቋረጥ ግን በእኛ ቁጥጥር ስር የነበረ አይደለም፣ አቅደነውም የነበረ አይደለም። በፋይናንስ ተቋሞቻችን ላይ ሊደርስ የነበረ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል INSA ኔትወርኩን ለማቋረጥ ተገድዶ ነበር። እኛም መቋረጡን ለደንበኞቻችን ለመንገር ግዜ አልነበረንም፣ ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጥ አልነበረም። ለጥቂት ደቂቃ በማቋረጥ ጥቃቱን ለመከላከል ይቻላል ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነው። ከ INSA ጋር እየተነጋገርን ነው የምንሰራው። ዛሬ ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ችግር አጋጥሟቸው የነበረ ይመስለኛል። አሁን ጉዳዩ ላይ እየተነጋገርን ነው።"

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
የአፋር ከልል የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ!

የአፋር ከልል የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን እንዲያሳውቁና እንዲያስመዘግቡ  የፌዴራል ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን አሳሰበ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አያሌው ሙሉአለም የመንግስት ባለስልጣናት የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነትን የማረጋግጥ ግዴታ እንዳለባቸው በአዋጅ መደንገጉን ገልጸው፤ አትዮጵያ ከራሷ አዋጅ ባሻገር ዘርፉን የሚመለከቱ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችን ጭምር መፈረሟን ተናግረዋል። በመሆኑም በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናት ለሚመሩት ህዝብ ያላቸውን ታማኝነትና የአሰራር ግልጸኝነት ለማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰራበት ያለውን የሃብት ማሳወቂያ ምዝገባ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መንግሥት ምን እያደረገ ነው?

ብዙኃኑ ተማሪዎች በጥቂት ሥርዓተ አልበኞች ሲሰቃዩ፣ የመማር ማስተማሩ ሒደት ሲቃወስና ሕግ የማስከበር ተግባር ሲንቀረፈፍ ምንድነው የሚባለው? በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች በአገር ሽማግሌዎች ጥረት ትምህርት ለማስጀመር ጥረት የተደረገ መሆኑ ሲሰማ፣ መንግሥት ምን እያደረገ ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

ተማሪዎች ከዕኩለ ሌሊት በኋላ በመኝታ ቤቶች አካባቢ ለምን ይዘዋወራሉ? የሌሎችን የፖለቲካ አጀንዳ የተሸከሙ በግላጭ ወጥተው ትምህርት ለምን ያስቆማሉ? ከዩኒቨርሲቲዎች ጥበቃ በላይ የሆኑ አደገኛ ድርጊቶች ከመከሰታቸው በፊት፣ የፀጥታ ኃይሎች በፍጥነት እንዲደርሱ ለምን አይደረግም? ሥጋት የገባቸው ተማሪዎች የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ ለምን ዝም ይባላል? በአንዳንድ አካባቢዎች የተደራጁ ኃይሎች ከውጭ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ሲታገሉ በግላጭ እየታየ ሕጉ የታለ? ሕግ አስከባሪውስ? ዩኒቨርሲቲዎችን በጊዜያዊ ሽምግልናና በማለባበስ ዕርቅ ወደ መደበኛ ተግባራቸው መመለስ አይቻልም፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተልዕኮ ተቀብለው የመሸጉ ኃይሎች ዋና ፍላጎት የብሔርና የእምነት ግጭት በመቀስቀስ አገሪቱን ትርምስ ውስጥ መክተት ነው፡፡ ይህንን እኩይ ዓላማ በመረዳት አስፈላጊውን ዕርምጃ መውሰድ ካልተቻለ፣ ለፀፀት የሚዳርግ አደገኛ ሁኔታ እንደሚፈጠር መጠራጠረ አይገባም፡፡ መሬት ላይ ያለው ዕውነት ይህንን ነው የሚያሳየው፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#AddisAbeba #Lyon

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከፈረንሳይዋ ሊዩን ከተማ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ኬሚልፊልድ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በሊዬን ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን በተለያዩ መስኮችም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#INSA

የዛሬው የኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት...

በሀገሪቱ የፋይናስ ተቋሞች ላይ ሊደርስ የነበረ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል በዛሬው ዕለት INSA ኔትዎርክ ለማቋረጥ ተገድዶ እንደነበረ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃኒ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገለፁ። ዛሬ የተከሰተው የኢንተርኔት መቋረጥ በኢትዮ ቴሌኮም ቁጥጥር ስር የነበረ እንዳልሆነና፤ ታቅዶም እንዳልነበር አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጥ አልነበረም፤እኛም መቋረጡን ለደንበኞቻችን ለመንገር ግዜ አልነበረንም፣ ለጥቂት ደቂቃ በማቋረጥ ጥቃቱን ለመከላከል ይቻላል ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነበር ብለዋል።

ከINSA ጋር እየተነጋገርን ነው የምንሰራው ያሉት ወ/ሪት ፍሬህይወት በዛሬው ዕለት ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ችግር አጋጥሟቸው የነበር ይመስለኛል፤ አሁን በጉዳዩ ላይ እየተነጋገርን ነው ብለዋል። ለኢንተርኔት መቋረጡ ይቅርታ ጠይቀዋል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#INSA

በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፍ ተቻለ!

ዛሬ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የሳይበር ጥቃት ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የፋይናንስ ተቋሞችን የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኔትወርኩን ከ15 እስከ 20 ደቂቃዎች ለማቋረጥ ተገድዶ እንደነበር የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ተናግረዋል፡፡

ተመሳሳይ ችግሮችን ለማክሸፍ ኤጀንሲው ከኢትዮ ቴልኮም ጋር በመሆን እየሰራ መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በኤጀንሲ ውስጥ ኢትዮ ሰርት የሚባል የፋይናንስ ተቋማትን ለ24 ሰዓት የሚከታተል እና አዲስ ጥቃቶች ሲቃጡ የመከላከል ተግባር ያለው ክፍል መኖሩን ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ክፍል ጥቃቱ ሳይደርስ መከላከል መቻሉን ኢንጅነር ወርቁ ተናግረዋል፡፡

ስራው ብዙ ጊዜ የተለመደውና የኔትወርክ ለውጥ የሚደረገው ብዙ ሰው ኢንተርኔት በማይጠቀምበት ሰአት ምሽት እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ዛሬ ላይ የተፈጠረው አስቸኳይ ስለነበር ቀን ላይ እርምጃው መወሰዱን ተጠቁሟል፡፡ ጥቃቱ ከየት እንደተሰነዘረ ዝርዝር ጉዳዮችን እየተመለከቱ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የተሰማሩ ሁለት ፖሊሶች ተገደሉ!

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ አዱላላ ቦኩ በሚባል ቀበሌ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪን ለመያዝ የተሰማሩ ሁለት የዞኑ የፖሊስ አባላት መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ሽፈራው ጉቱ "ፖሊሶች ወደ ቀበሌው ሄደው ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲሉ 'ለምን ይያዛሉ?' በሚል ረብሻ ተነስቶ የአከባቢው ሰዎች በፖሊስ አባሎቻችን ላይ ጉዳት አደረሱ" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአካባቢው ነዋሪዎች የተቃጣው ጥቃት የሁለት የፖሊስ አባላቶችን ህይወት ከመቅጠፉም በላይ አንድ ሲቪል ህይወቱ ያለፈ ሲሆን በሁለት የፖሊስ አባላት ላይ ደግሞ ጉዳት ማድረሱን ኮማንደር ሽፈራው ተናግረዋል።

ረቡዕ ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ ላይ በተፈጠረው ክስተት ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ የፖሊስ አባላት ሆስፒታል ተኝተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል።

የተፈጠረው ምን ነበር?

ረቡዕ ጠዋት የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ አባላት ሃሰተኛ መስክርነት በመስጠት የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦችን በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት በቁጥጥር ሥር ለማዋል ወደ አዱላላ ቦኩ ቀበሌ ያመራሉ።

"ከዚህ በፊት ሶስቱ ግለሰቦቹ 'ሰው ገድሏል' በማለት በሃሰት መሰከሩ። የክስ መዝገቡ ምረመራ ከተጠናቀቀ በኋላ በድጋሚ ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ። የሰጡት ምስክርነት የሃሰት መሆኑ ሲታወቅ ፍርድ ቤት ተይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጠ። የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለመፈጸም ፖሊሶች ወደ ስፍራው ከተሰማሩ በኋላ ነው ይህ የሆነው" በማለት የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ያስረዳሉ።

More👇
https://telegra.ph/BBC-12-05

(BBC አማርኛው አገልግሎት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #DrAbiyAhemed

"ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር"--- የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር

"የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት"--- የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም

የኖርዌይ የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኦላቭ ጆልስታድ ጠ/ሚር አብይ ከአምስት ቀን በሁዋላ ሽልማታቸውን በሚቀበሉበት ወቅት ጥያቄዎች የሚጠየቁበት ፕሮግራም ላይ እንደማይገኙ ገልፀው "ይህ በጣም ችግር ነው። ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር" ብለው ለአሶሼትድ ፕረስ ተናግረዋል።

ዛሬ የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም ለAssociated Press ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት በሰጡት መረጃ - "የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት። ስለዚህ ጠ/ሚሩ በተመረጡ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ላይ ከኖቤል ኢንስቲትዩት ጋር በመነጋገር ይካፈላሉ" ብለዋል።

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ባሰራጨው መረጃ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በ2009 የኖቤል የሰላም ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት የሚድያ ፕሮግራሙ ላይ ሳይሳተፉ ቀርተው እንደነበር አስውሷል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot