This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Jack Ma ማነው?? ብላችሁ ለምትጠይቁ ይህን አጭር ቪድዮ ተመልከቱ፤ ከልጅነት ጀምሮ አሁን እስካለበት ድረስ ያስቃኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የJack Ma የስኬት ሚስጥር ምን ይሆን?
"We won't be #successful until we make 10,000 mistakes" - Jack Ma
(4 MB)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"We won't be #successful until we make 10,000 mistakes" - Jack Ma
(4 MB)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Jack Ma ለወጣቶች ምን ይመክራል?
“Today is hard, tomorrow will be worse, but the day after tomorrow will be sunshine.” - Jack Ma
(4 MB)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“Today is hard, tomorrow will be worse, but the day after tomorrow will be sunshine.” - Jack Ma
(4 MB)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
10 ቢሊዮን ብሩ የት ደረሰ?
- በተለይ "ለወጣቶች ስራ ፈጠራ" በሚል ከዓመታት በፊት እንዲተላለፍ የተወሰነው10 ቢሊዮን ብር ለማን ተሰጠ? ምን ያህሉስ ተመላሽ ሆነ?
(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- በተለይ "ለወጣቶች ስራ ፈጠራ" በሚል ከዓመታት በፊት እንዲተላለፍ የተወሰነው10 ቢሊዮን ብር ለማን ተሰጠ? ምን ያህሉስ ተመላሽ ሆነ?
(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Twitter #Ethiopia
ጃክ ፓትሪክ ዶርሴይ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው!
የትዊተር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጃክ ፓትሪክ ዶርሴይ በኢትዮጵያን ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ ዋና ስራ አስፈፃሚው ለአንድ ወር በቆየው የአፍሪካ ጉብኝታቸው ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ እና ጋናን የጎበኙ ሲሆን የመጨረሻ መዳረሻቸን ኢትዮጵያ አድርገዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጠሪ የሆነው ማህበራዊ ሚዲያ ዋና ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያን ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጃክ ፓትሪክ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከቴክኖሎጂ ንግስቷ ቤተልሄም ደሴ እና የአፍሪካ ቴክ ኔክስት አንዱ መስራች ከሆነው ኖኤል ዳንኤል ጋር ውይይቱ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም ዋና ስራ አስፈፃሚው ከሌሎቸ በርካታ ስራ ፈጣሪዎች ጋር ሰፊ ጊዜን እንደሚያሳልፉ ነው የተነገረው፡፡ የትዊተር ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ጃክ ፓትሪክ ዶርሴይ በአሜሪካ የኮሙፒውተር ፕሮግራመር እና ኢንተርኔት ስራ ፈጣሪ እንዲሁም ስኩዌር የተባለው የሞባይል የክፍያ ኩባንያ ስራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
(ኤፍ ቢ ሲ)

#ቤጉህዴፓ - የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) ዛሬ በአሶሳ ከተማ ባካሄደው አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባዔ የኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶች ውህድ የሆነውን የብልጽግና ፓርቲን እንደሚዋሃድ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የቀድሞ የፀረ ሽብር ህግ ሠለባዎች መንግስትን ሊከሱ ነው!
የቀድሞ የፀረ ሽብር ህግ ሠለባዎች ለደረሰባቸው የስነልቦና አካላዊና ማህበራዊ ጉዳት መንግስትን በፍ/ቤት ለመክሰስ ማቀዳቸውን አስታወቁ፡፡ በቁጥር 3 መቶ ያህል የሚሆኑት የቀድሞ የፀረ ሽብር ህግ ሠለባ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ እና ሌሎች ግለሰቦች ከ14 ወራት በፊት በማህበር መልክ ተሰባስበው መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀው ጥያቄያቸውም ተቀባይነት አግኝቶ የነበረ ቢሆንም እስከዛሬ ተግባራዊ ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ የኮሚቴው ህዝብ ግንኙነት አቶ ዳንኤል ሽበሽ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡
ባለፈው አመት ጥር 2011 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል ከፀረ ሽብር ህጉ ሠለባዎች ጋር ውይይት ተደርጐ እንደነበር እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይም ጥያቄው ለጽሑፍ ቀርቦላቸው እንደነበር ለአዲስ አድማስ ያስረዱት አቶ ዳንኤል በወቅቱ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣችኋል ቢባልም ጉዳያችን የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል ብለዋል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-25

ሰበር ዜና!
የህወሃት ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ የኢህአዴግን ውህድት በተመለከተ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ወሰነ፡፡ የህወሃት ሊቀመንበር ዶ ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል በሰጡት መግለጫ ስለ ውህደቱ ለመወያየት ህወሓት በቅርቡ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ደብረጽዮን ኢህአዴግ እየተዋሃደ ሳይሆን እየፈረሰ ነው፤ ብልጽግና ፓርቲም ውህድ ፓርቲ ሳይሆን አዲስ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴም ሆነ ማዕካለዊ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ መወሰን ስላማይችል አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ እና እንዲወያዩበት ውሳኔ አሳልፏል።
(አውሎ ሚዲያ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የህወሃት ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ የኢህአዴግን ውህድት በተመለከተ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ወሰነ፡፡ የህወሃት ሊቀመንበር ዶ ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል በሰጡት መግለጫ ስለ ውህደቱ ለመወያየት ህወሓት በቅርቡ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ደብረጽዮን ኢህአዴግ እየተዋሃደ ሳይሆን እየፈረሰ ነው፤ ብልጽግና ፓርቲም ውህድ ፓርቲ ሳይሆን አዲስ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴም ሆነ ማዕካለዊ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ መወሰን ስላማይችል አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ እና እንዲወያዩበት ውሳኔ አሳልፏል።
(አውሎ ሚዲያ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BHU - የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳደርና አባገዳዎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር የበኩላችን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አሃዱ ቲቪ ሎጎዬን ተጠቅሞ ሀሰተኛ መረጃ አቅርቧል፤ ድርጊቱ ተገቢ ስላልሆነ ሊቆም ይገባል ብሏል!
"የአሃዱ ቲቪ መማርና ማስተማር ያልጀመሩ ብሎ በዜና ላይ ከጠቀሳቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን ሎጎ በመለጠፍ የሃሰት ዜና በቀን 10/03/2012 ዓ.ም በምሽት 2፡00 ሰዓት ዜና ላይ አሰራጭቷል። ይህ ደርጊት ተገቢ ስላልሆነ ሊቆም ይገባል።" - ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
መረጃውን የተከታተሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቡሌ ሆራ ቤተሰቦችም የተሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ ነው፤ ይህን መሰል ድርጊቶች ወላጆችን ስለሚረብሽ ሊታረም ይገባዋል፤ ጣቢያው ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል ብለዋል። እስካሁን በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ችግር አልገጠመንም የመማር ማስተማር ስራውም አልተቋረጠም በሰላም እና በፍቅር እየተማርን እንገኛለን ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ቀን 4 ተማሪዎቹን በትራፊክ አደጋ አጣ!
ትላንት በሆለታ በደረሰው የመኪና አደጋ ከሞቱ 18 ሰዎች መካከል ሶስቱ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ (አዋሮ ካምፓስ) ተማሪዎች ናቸው። ሁለቱ የ5ኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎች ነበሩ(ሴቷ የአርክቴክቸር እና ከተማ ፕላን ትምህርት ዘርፍ እንዲሁም ወንዱ የመካኒከል ምህንድስና ተማሪ)፤ ሶስተኛዋ ተማሪ ደግሞ የ5ኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተማሪ ነበረች፡፡
ሌላኛዋ በትላንትናው ዕለት በመኪና አደጋ ህይወቷ ያለፈው የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ ተማሪ ናት። ተማሪዋ የ3ኛ ዓመት የፐፕሊክ አድምንስትሬሽንና ዴቨሎፕመንት ማነጅመት ተማሪ ነበረች። ትላንት ከቀኑ 7:30 ወሊሶ ከተማ በተፈጠረ የመኪና አደጋ ነው ህይወቷ ያለፈው።
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የቤተሰባችን አባላት ወንድምና እህቶቻቸው በማጣታቸው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትላንትናው ዕለት በተለያዩ ቦታዎች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ሃዘን ይገልፃል፤ እንዲሁም ለተማሪ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል።

#MoSHE
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በድጋሚ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አሳሰበ!
- "በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች አከባቢ በመገኘት ወደሌላ ዩኒቨርስቲ እንደትዘዋወሩ እናመቻቻለን እያሉ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ የሚያነሳሱና ምዝገባ የሚያካሂዱ አካላት መኖራቸው ተደርሶበታል፡፡ ሆኖም ተማሪዎችም ሆኑ የተማሪዎች ቤተሰቦች ይህ ነገር ፈፅሞ የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝበው ተማሪዎች ባሉበት ዩኒቨርስቲ ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እናሳስባለን፡፡"
(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ተጀመረ!
ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ዛሬ መጀመሩን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል። ሰላም በማውረዱ ሥራ ውስጥ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የከተማዪቱ ነዋሪዎች፣ የፀጥታ መዋቅሩና የባህር ዳር ወጣቶች ጉልህ ተሣትፎ ማድረጋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ዛሬ መጀመሩን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል። ሰላም በማውረዱ ሥራ ውስጥ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የከተማዪቱ ነዋሪዎች፣ የፀጥታ መዋቅሩና የባህር ዳር ወጣቶች ጉልህ ተሣትፎ ማድረጋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ማስታወሻ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም ያካሒዳል፡፡
የመወያያ አጀንዳዎቹም የሚከተሉት ናቸው፦
1. የም/ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣
2. የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣
3. የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፤

#ኡቡንቱ #Ubuntu
“Umuntu Ngumuntu Ngabantu" የባንቱዎች ቋንቋ ነው:: ሰው ሰው የሚሆነው በሌሎች ሰዎች ውስጥ ነው እንደማለት ነው። በእኛ በሰዎች መካከል አንድ ጥብቅ ቁርኝት አለ:: በዚያ ሰው የመሆን ሚስጥር ውስጥ የኛነታችን ምክንያት እናገኘዋለን። በኡቡንቱ አመለካከት የተሞላ ሰው ህይወት በክፍልፋይ የምትገነባ ሳትሆን በአብሮነት ስሜት የምትሰራ መሆኗን ይረዳል።
አንድ ትልቅ የፈጣሪ ቤተሰቦች በአንዱ ማደግ ሌሎችም እንደሚያድጉ በአንዱ መውደቅ ሌሎችም እንደሚወድቁ ማመን ሲጀምር ከኡቡንቱ ጋር ተዋውቋል ማለት ነው።
አንድ ከምዕራብ የመጣ የማህበረሰብ ጥናት ባለሙያ ብዙ ጊዜውን ከአፍሪካ ህፃናት ጋር ያሳልፍ ነበር:: አንድ ቀን ከህፃናቱ ጋር መጫወት ፈለገና ዛፍ ላይ ከረሜላ አስቀምጦ ህፃናቱን እንዲህ አላቸው " ከእናንተ ውስጥ ሮጦ አንደኛ የወጣ ቅርጫት ውስጥ ያለውን ከረሜላ በሙሉ ይወስዳል..."
ህፃናቶቹ መሮጥ ጀመሩ ግን አንደኛ ለመውጣት ሳይሆን እጅለእጅ ተያይዘው ነበር የሚሮጡት። ሁሉም እኩል ደረሱ ሁሉም ከረሜላውን እኩል ተካፍለው በሉት። ይህ ሰውዬ ገረመው 'አንዳቹ ቀድማቹ ሁሉንም መብላት ስትችሉ እንዴት አንድ ላይ ትሮጣላቹ?" ብሎ ጠየቃቸው። ህፃናቶቹ በአንድ ላይ "ኡቡንቱ!" አሉት። ሌሎች ተከፍተው እንዴት ደስተኛ መሆን ይቻለናል? እንደማለት ነው።
(Abrar Amdela)

40/60...
"በ2011 ዓ.ም የካቲት ወር አጋማሽ ላይ በ2ኛ ዙር የ 40/60 የቁጠባ ቤቶች ላይ ዕጣ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ እኛ የዚህ ዕጣ ተሳታፊ ዕድለኞች አስፈላጊውን የምዝገባ፤ የመረጃ ማሟላትና የውል ስምምነት ሂደቶችን ደንቡ በሚያዘው መሰረት ከፈፀምን በኀላ የቤቶቹ ግንባታ ሳያልቅ እና ቤቶቹን ሳንረከብ አግባብነት በሌለው አካሄድ ከመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ግንባታቸው ባላለቀና ባልተረከብናቸው ቤቶች ላይ የሚታሰብ ከፍተኛ ወርሃዊ ወለድ ለባንክ እየከፈልን የቤቶቹንም ቁልፍ ርክክብ በትዕግስት በመጠበቅ ላይ እንገኛለን፡፡ ስለዚህ የሚመለከተው የመንግስት አካል ቤቶቹ ግንባታቸው ተጠናቆ ለርክክብ የሚበቁበትን መፍትሄ እንዲሰጥበት እና ግንባታው ተጠናቆ የቁልፍ ርክክብ እስከሚፈፀም ድረስም ጫና እየፈጠረብን ላለው ተገቢ ያልሆነ የወለድ ክፍያ የእፎይታ ግዜ እንዲሰጠን እንጠይቃለን!"

#ሶዴፓ
የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶዴፓ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ተጀምሯል። የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው እያካሄደ ባለው ስብሰባ በኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ ህግና ደንብ ዙሪያ እየመከረ ይገኛል። እንዲሁም በፓርቲው የፖለቲካ ፕሮግራም አሰራርና አደረጃጀት ዙሪያ ምክክር እያካሄደ መሆኑ ተመላክቷል። ኮሚቴው በተጠቀሱት አጀንዳዎች በጥልቀት ከተወያየ በኋላም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ!
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ካነሱ በኋላ ነው ምክር ቤቱ ረቂቁን ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ የመራው።
በሃሰተኛ መረጃዎች የተነሳ በሃገሪቱ የሰው ህይወት ሲጠፋ እና ንብረትም ሲወድም የሚስተዋል ነው። በመሆኑም ይህ ረቂቅ አዋጅ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን በህግ መከልከል አስፈላጊ በመሆኑ ነው የወጣው ተብሏል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-26
(EBC)

በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ እንደሚገኝ ተገለፀ!
በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንዲገኝ እንዳደረገው የክልሉ ጤና ቢሮና አጋር ተቋማት ገለጹ። በትግራይ ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ የስራ ሂደት ባለቤት አስተባባሪ አቶ ፍስሃ ብርሃነ እንዳሉት በሽታውን ለመከላከል በክልሉ ውስጥ ቀደም ሲል የነበሩ እንቅስቃሴዎች እየተቀዛቀዙ መጥተዋል። በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቀደም ሲል በየደረጃው ባሉ መንግስታዊና አጋር ተቋማት የነበረውን ቅንጅታዊ አሰራር እየተዳከመ መምጣቱን አስተባባሪው ተናግረዋል። እንዲሁም የበጀት ውስንነት፣የባለድርሻ አካላትና የመላው ህብረተሰብ ሚና መላላት ለበሽታው ስርጭት እየተበራከተ መምጣት ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል።
(ENA)

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሃዘን ላይ ነው!
እሁድ ሆለታ ከተማ በደረሰው ዘግናኝ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ካለፈው 18 ሰዎች መካከል ስድስቱ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና አንድ በዩኒቨርሲቲው የቅጥር ሂደት በመፈፀም ላይ የነበረ መምህር እንደነበር ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ባወጣው የሃዘን መግለጫ ገልጿል። በተመሳሳይ ቀን በወሊሶ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የሌላ አንድ ተማሪ ህይወት አልፏል።
ህይወታቸው ካለፈው 7 ተማሪዎች መካከል አራቱ በዘንድሮው ዓመት የሚመረቁ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች ነበሩ። ዩኒቨርሲቲው በተማሪዎቹ ሞት የተሰማውን መሪር ሃዘን የገለፀ ሲሆን በአደጋው 5 ተማሪዎችን ባጣው የቴክኖሎጂ ተቋም ዛሬ ከቀኑ 11:15 የሻማ ማብራት እና የሀዘን መግለጫ ስነ ስርዓት እንደሚኖር አሳውቋል። ተማሪዎችም በስፍራው እንዲገኙ እንዲሁም በሁሉም ካምፓሶች በተመሳሳይ ሰዓት ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ባለበት ሆኖ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።