TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከወቅታዊው የመንገድ መዘጋት እና የሠላም መደፍረስ ችግር ጋር ተያይዞ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን እንደ አመጣጣቸው እንደሚቀበል የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል፡፡

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በያዝነው የትምርት ዘመን ለ3ኛ ዙር የተመደቡለትን አዲስ ተማሪዎች ለመቀበል ከጥቅምት 8 እስከ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መርሀ ግብር ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት ከተመደቡለት 2 ሺህ 769 ተማሪዎች መካከል እስካሁን የተቀበላቸውን 2 ሺህ 419 አዲስ ተማሪዎች በ48 መማሪያ ክፍሎች በመደልደል የእውቀትና ክህሎት ትምህርት የመስጠት ተግባሩን ጀምሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሮግራም ዲቨሎፕመንትና ሪቪው ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በየመማሪያ ክፍሎች በመዘዋወር የትምህርት አጀማመር ስነ-ሥርዓቱን ጎብኝተዋል፡፡

ሰሞኑን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ መንገድ ተዘግቶም ሆነ ከሠላም መደፍረስ ችግር ጋር ተያይዞ የዘገዩ ተማሪዎችን እንደመጡ የሚቀበል መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

Via ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያልተከተቡ ተማሪዎችም በፍርሃት ሲወድቁ ተስተውሏል ...

በአዲስ አባባ ከተማ የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል በየትምህርት ቤቱ በመሰጠት ላይ የሚገኘው የክትባት አገልግሎት በአዲስ አበባ የብርሃንና ሰላም ትምህርት ቤት እክል ገጥሞታል፤ ክትባቱ በሌሎች ቦታዎች በሰላም እየተከናወነ ቢሆንም የብርሃንና ሰላም ትምህርት ቤት ተማሪዎች የስነ ልቦና ምሁራን ሂስቴሪያ በሚሉት ስሜት መታወካቸው ተሰምቷል፤ ያልተከተቡ ተማሪዎችም በፍርሃት ሲወድቁ ተስተውሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ሀረር፣ ድሬዳዋ፣ባሌ ሮቤ፣ሞጆ እና አዳማ አካባቢ ተሰማርቷል። ሰራዊቱ “ከሀይማኖት አባቶች እና ከአባ ገዳዎች ጋር በመሆን የማረጋገት ስራን እየሰራ ይገኛል። የተዘጉ መንገዶችን እያስከፈተን ነው።

በተሰራው ስራ ተጨማሪ የሰው ህይወት እና ንብረት ከጥፋት ማትረፍ የተቻለ ቢሆንም መከላከያ ሰራዊት በፍጥነት ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ጉዳት ማጋጠሙ ተገልጿል።

“ሰላምን በታጠቀ ኃይል ብቻ ማረጋጋት አይቻልም” ያሉት የመከላከያ ሚኒስቴር የኢንዶክትሪኔሽን እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ሰላምን ለማስፈን የህብረተሰቡ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል ተናግረዋል።

Via DW
@tsegawolde @tikvahethiopia
#ADAMA

የቪኦኤ(VOA) ጋዜጠኛ ሙክታር ጀማል አዳማ ውስጥ በሥራ ላይ እንዳለ በወጣቶች ቡድን ጥቃት እንደደረሰበት የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጣቢያ አሳውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰሜን ሸዋ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፍተዋል!

በሰሜን ሸዋ አንዳንድ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር  ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፍተዋል። በተለይ ወደ ጎጃምና ጎንደር መተላለፊያ መንገድ ላይ በሚገኙ ገብረ ጉራቻ ፣ ደብረጽጌ እና ሙከጡሪን ጨምሮ በአዲስ አበባ ዙሪያ  ከተሞች ከትናንት በስቲያ ተዘግቶ የነበረው መንገድ ከትናንት ምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በመንገዱ መዘጋት በከተሞቹ ቆመው የነበሩ ብዛት ያላቸው የግልና የህዝብ ተሽከርካሪዎች   ስራ መጀመራቸው ተሰምቷል። መንገዱ ሊከፈት የቻለው የአካባቢው ወጣቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ባደረጉት ጥረት መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
10ሺህ ደም ልገሳና 100ሺህ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች ምዝገባ በአንድ ቀን።

15 ጥቅምት 2019 ፤ በመላው ኢትዮጲያ።

#ኢትዮጲያ #ህይወትለህይወት #ደምልገሳ

ቤተሰቦቻችን ተመዝገቡ👇
https://bloodbank.moh.gov.et/
ከአንድ ዓመት በፊት ተቋርጦ የቆየው ከኮምቦልቻ ባህር ዳር የቀጥታ በረራ ሊጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። በረራው ከጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀመር ተመልክቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 44 ደርሷል!

ረቡዕና ሐሙስ ዕለት ግጭት በተካሄደባቸው ኦሮሚያ ክልል፣ ድሬ-ደዋ እና ሐረር ከተሞች የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 44 ደርሷል። ከግማሽ በላይ ለሆነው የግድያ መንስዔ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት መሆኑን የየአከባቢዎቹ ባለስልጣናት፣ የሆስፒታል ምንጮች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዳማ

ዶ/ር ደሳለኝ ፍቃዱ በአዳማ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው። ከረቡዕ እስከ ዛሬ (ዓርብ ዕለት) ድረስ ወደ አዳማ ሆስፒታል ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው የመጣ ሰዎች እና የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይቶ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር በጠቅላላው 16 መሆኑን ያስረዳሉ።

ዶ/ር ደሳለኝ እንደሚሉት ረቡዕ ዕለት የ3 ሰዎች አስክሬን ወደ ሆስፒታል መጥቷል። ከእነዚህም መካከል ሁለቱ አፍሪካ ዱቄት ፋብሪካ ዘበኛ ጥይት ተኩሶ የገደላቸው ሰዎች ይገኙበታል።

የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ራውዳ ሁሴን የዱቄት ፋብሪካው ጥበቃ ጥይት ተኩሶ ሁለት ሰዎችን መግደሉን እና በዚህ የተበሳጩ ሰልፈኞ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ 15 መኪኖች ማቃጠላቸውን ረቡዕ ዕለት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ዶ/ር ደሳለኝ ትናንት ሐሙስ ሆስፒታሉ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ተጎጂዎችን ያስተናገደበት ቀን እንደሆነ ያስረዳሉ። "ትናንት ጉዳት ደርሶባቸው የመጡት ሰዎች ቁጥር ከ100 በላይ ይሆናል" ያሉ ሲሆን የጉዳቱ መጠን ከከባድ እስከ ቀላል የሚባል እንደሆነ ያሰረዳሉ።

"በዱላ የተደበደቡ፣ በስለት ጭንቅላታቸው ላይ የተመቱ፣ በጥይት የተመቱ ሰዎችም አሉበት" የሚሉት ዶ/ር ደሳለኝ፤ ትናንት ብቻ ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው የመጣ እና በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው የያለፈ ሰዎች ቁጥር 12 ነው ይላሉ።

ረቡዕ ዕለት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ከፍተኛ የህክምና ክትትል ክፍል (አይሲዩ) ውስጥ የነበረ ወጣት ዛሬ ጠዋት ህይወቱ አልፏል ብለዋል።

"አሁንም በሆስፒታሉ በአደጋኛ የጤና ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች አሉ። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። አይኑ የጠፋ፣ አጥንቱ የተሰበረ ብዙ ነው" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-25-2

@tikvahethiopia
#ADAMA

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ (ቪኦኤ) የአፋን ኦሮሞ ክፍል ሪፖርተር የሆነው ጋዜጠኛ ሙክታር ጀማል በአዳማ ከተማ 'ጀማል መጋዘን' ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በመንገድ ላይ ቃለ-መጠይቅ እያደረገ ሳለ ድብደባ እና ዘረፋ ተፈጽሞበታል። ጭንቅላቱ እና ወገቡ ላይ ጉዳት ያጋጠመው ጋዜጠኛ ሙክታር ሆስፒታል ተኝቶ የህክምና አገልግሎት እየተከታተለ ነው። ሙክታር ቃለ-መጠይቅ እያደረገ ሳለ የተደራጁ ወጣቶች መጥተው ድብደባ እንደፈጸሙበት ያስረዳ ሲሆን፤ "ቦርሳዬን ሲበረብሩ የኢቮኤ መታወቂያ ካርድ ካዩ በኋላ ትተውኝ ሄዱ" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።

Via ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮፈሌ

አብነት አክሊሉ በምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ከተማ ነዋሪ የነበሩ 2 ዘመዶቹ እና አንድ በዘመዶቹ ቤት ስላደገው ወጣት አሟሟት ለቢቢሲ ተናግሯል። አቶ ታምራት ጸጋዬ የአብነት አክሊሉ አጎት (የእናቱ ወንድም) ናቸው።

ረቡዕ ዕለት በተፈጠረው ግርግር አቶ ታምራት ጸጋዬ፣ ልጃቸው አቶ ሄኖክ ታምራት ጸጋዬ እና በአቶ ታምራት ቤት ሱቅ ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሌላ ወጣት ልጅ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መገደላቸውን አብነት አክሊሉ ይናገራል። "ተሰብስበው ወደ አጎቴ ቤት መጡ። ከዚያ በመጀመሪያ አጎቴን (አቶ ታምራት ጸጋዬ) ገደሉት። ከዚያ በተመሳሳይ ሁኔታ ልጁን ገደሉት። ከዚያ ቤት ውስጥ ያደገ ሱቅ ውስጥ ይሰራ የነበረ ልጅ ገደሉ" ይላል። አብነት የሟች አስክሬን ላይም አስነዋሪ ድርጊት መፈጸሙን ለቢቢሲ ተናግሯል።

የአቶ ታምራት ልጅ፤ ሄኖክ ታምራት ጸጋዬ በቅርቡ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ በምጣኔ ሃብት ዘረፍ እንደተመረቀ የሚናገረው አብነት፤ አቶ ታምራት በኮፈሌ ከተማ ወፍጮ ቤት፣ ሆቴል እና መኪኖች እንዳሏቸው ይናገራል። የቤተሰብ አባላቱን ከተገደሉ በኋላ የአቶ ታምራት መኖሪያ ቤት አና መኪና እንደተቃጠለም አብነት ጨምሮ ይናገራል።

የአቶ ታምራት እና የልጃቸው ትውልድ እና እድገት እዛው ኮፈሌ መሆኑን የሚናገረው አብነት "ተወልደው ባደጉበት ኮፈሌ እንኳ መቅበር አልቻልንም። በስንት መከራ ዛሬ በናዝሬት ከተማ 10 ሰዓት ላይ ቀብራቸው ተፈጽሟል" በማለት አብነት ያስረዳል።

Via BBC AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አምቦ | ረቡዕ እና ሐሙስ ዝግ ሆነው የነበሩት መንገዶች ከዛሬ ጠዋት (ዓርብ) ጀምሮ ክፍት ተደርገዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት በነበሩት ግጭቶ 5 ሰዎች ተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አንድ የፖሊስ አባል ይገኝበታል። ይህ የፖሊስ አባል የተገደለው ሐሙስ ዕለት ሲሆን ረቡዕ ዕለት በነበረው ግጭት 'ሰው ገድለሃል' ተብሎ በበቀል እርምጃ እንደተገለ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

(ቢቢሲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዶዶላ

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ረቡዕና ሐሙስ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል። ሐሙስ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ረቡዕ ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የቢቢሲ ዜናን ያዳምጡ!
#ETHIOPIA

ባለፉት ሁለት ቀናት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በታዩባቸው አንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም መመለሱ ኾኖም ነዋሪዎች ሥጋት ውስጥ መኾናቸውን ገለጡ።

ተቃውሞው ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት የመቀየር አዝማሚያ መያዙ በታየባቸው የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬም ውጥረት ሰፍኖ እንዳለ የዐይን እማኞች ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። ድሬዳዋ፣ አዳማ እና ባሌ ሮቤ ከተሞች ውስጥ ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለ ነው የዐይን እማኞቹ የተናገሩት።

በአዳማ ከተማ የነበረው ውጥረት ረገብ ብሎ በየቀበሌው ውይይት መጀመሩን የነገሩን አንድ የከተማው ነዋሪ እንዳሉት ከሆነ መንግሥት እና የሃይማኖት ተቋማት ከሕዝቡ ጋር ውይይት ማድረግ ጀምረዋል፤ ፍራቻው ግን አኹንም አለ።
«ሕዝቡ ውስጥ ፍራቻ አለ? አዎ አለ፤ ነገር ግር እርስ በራስ የሕዝቦች ለሕዝቦች ግንኙነትን መንግሥትም እየሠራ ይመስላል። የሃይማኖት ተቋማትም በጣም ተረባርበው [እየሠሩ ነው።] ጠዋት እኔ ዐይቼዋለሁ። ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በርካታ ሰዉ ይጸልያል። እና ደስ የሚል ነገር ነው ያየኹት፤ እና ያ ነው አሁን ያለው።»

በድሬዳዋ ከተማ የተቃውሞ ሰልፉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት ረገብ ማለቱ ተገልጧል። ኾኖም ዛሬ ከነጋ አንድ ባጃጅ መቃጠሉን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የከተማው ነዋሪ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የከተማይቱ ነዋሪዎች ከአንዱ ሰፈር ወደ ሌላኛው ሰፈር ለመሄድ እንደሚቸገሩም እኚሁ ነዋሪ አስረድተዋል። ስለኹኔታው ከአዳማ፣ ከድሬዳዋ እና ከባሌ ሮቤ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከፖሊስ አካላት ለማጣራት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ38 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት በበጎፈቃድ መሰብሰብ ተችሏል!

በትምህርት ሚኒስቴር አነሳሽነት የተጀመረው “የእኛ ለእኛ” የበጎ ፈቃደኞች መርኃግብር ላይ ላለፉት 3 ወራት ለተሳተፉ በጎፈቃደኛ ወጣቶች ዛሬ በትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በተገኙበት የሰርተፍኬት አሰጣጥ መርኃግር ተከናውኗል፡፡ በአጠቃላይ የበጎ ፈቃድ ዘመቻው ከ350 በላይ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ለሚገኙት በጎፈቃደኞች ይህ መርኃግብር ተዘጋጅቷል፡፡

በሦስት ወር የበጎ ፈቃድ ስራ በትምህርት ቁሳቁስ ከ3 ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ሺ በላይ የተሰበሰበ ሲሆን በአልባሳትና በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘውን ድጋፍ ጨምሮ 30 ሚሊየን የሚቆጠር ድጋፍ ማሰባሰብ ተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ግን በዚህ መርኃግብር 38 ሚሊየን ሀብት መሰብሰብ ተችሏል፡፡ በዚህም በበርካታ ቦታዎች የሚገኙ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ጉዳት ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉና ችግር ለደረሰባቸው አከባቢዎች ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ በቀጣይ የትምህርት ሚኒስቴር በእኛ ለእኛ የበጎፈቃድ አገልግሎት ስር “የተማረ ያስተምር” የተሰኘ መርኃግብር የሚጀመር ሲሆን በዚህም በርካታ በጎፈቃደኞች ይሳተፉበታል ተብሎ ይታመናል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ "የእንኳን ደስ አላችሁ!" መልዕክት ለማስተላለፍ የማይመች ቢሆንም ወድ ቤተሰቦቻችን ለሰራችሁት በጎ ስራ ከትምህርት ሚኒስቴር ሰርተፍኬት ተበርክቶላችኀል!

በኤ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ስር ለተደራጀው "እኛ ለእኛ" የኢትዮጵያ በጎፈቃደኞች መርኃግብር ላይ ተሳታፊ በመሆን በልዩ ልዩ ምክንያት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ላልተከታተሉ እና ላቋረጡ ተማሪዎቻችንን ትምህርት ማስቀጠያ የሚሆኑ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ከህብረተሰቡ በማሰባሰብ፣ በማምረት፣ በመለገስ ሂደት TIKVAH-ETH የቤተሰቡን አባላት በማስተባበርና መረጃዎችን በመስጠት ላደረገው አስተዋጽኦ ይህ የምስክር ወረቀት ተበርክቶልናል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘላቂ ሰላምን መገንባት!" በሚል ርዕስ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከኢንሼቲቭ አፍሪካ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው መርኃግብር ነገ በUNECA መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በኮንፍረንሱ ላይ የሁሉም የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችና የሰላም ፎረም አባላት ይገኙበታል፡፡ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦችም ባለፈው ዓመት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ባካሄዱት "የጥላቻ ንግግር እናቁም!" ዘመቻ ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ የሚገኙ ይሆናል፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
#EliasMeseret #TikvahFamily

የሀሰተኛ ዜናዎች መድሃኒት "ኤልያስ"!

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰባችን አባል የሆነው ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ነገ ከምሽቱ 12:00-1:00 ለናተ ለውድ ቤተሰቦቻችን የተመረጡ መረጃዎችን ያደርሳችኃል።

STOP FAKE NEWS!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር 67 ደርሷል!

#Reuters

ሮይተርስ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነገሩኝ ብሎ ባወጣው ዘገባ መሰረት ባለፉት ሁለት ቀናት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች በነበረው ተቃውሞ የ67 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ዘግቧል። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ የፖሊስ አባላት ናቸው። 13 ሰዎች ደግሞ በጥይት ተመተው የተገደሉ ሲሆን የተቀሩት በድንጋይ ተደብድበው እንደተገደሉ ነው የተገለፀው።

https://telegra.ph/ETH-10-25-3

https://www.dailystar.com.lb/News/World/2019/Oct-25/494338-67-people-killed-in-protests-in-ethiopias-oromiya-region-police.ashx#.XbNI_WnU9lV.facebook

Via #DailyStar
@tsegabwolde @tikvahethiopia