የትምህርትና ስልጠና የፍኖተ-ካርታው ረቂቅ ዝግጅት ትግበራ የአንድ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል።
********************
የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዝግጅት አማካሪ ካውንስል አባላት በተገኙበት የረቂቅ ትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዝግጅትና ትግበራ የአንድ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዴበታል፡፡
=================
የጥናቱን ውጤት መነሻ በማድረግ እስካሁን በተካዱ ህዝባዊ ውይይቶች ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ድረስ ወደ 3.5 ሚሊዮን ህዝብ በረቂቅ ፍኖተ-ካርታው ዝግጅት ዙሪያ እንዲወያዩ እና አስተያቶችን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ ተደርጎ በርካታ ግብአቶች የተሰባሰቡ መሆኑን ከሪፖርቱ ለማወቅ ተችሏል።
=================
እንደ ሪፖርቱ በጥናቱ ግኝት የተመላከቱና በህዝባዊ ውይይት ወቅት የተነሱ ምክረ ሃሳቦች ተብሎ ከቀረቡት፤
√ የቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት፣
√ የአንደኛ ክፍል የመግቢያ ዕድሜ፣
√ የትምህርትና ሥልጠና እርከን፣
√ የትምህርትና ሥልጠና ቋንቋ፣
√ የትምህርት ምዘናና ፈተና፣
√ የመምህራን ምልመላና ሥልጠና ፣
√ የመምህራን የትምህርት ባለሙያዎች የትምህርትና ሥልጠና ዩንቨርሲቲ፣
√ አሃዳዊ የክፍል አደረጃጀት፣
√ የግብረገብ ትምህርት፣
√ የትምህርት ሕግ፣
√ የተማሪዎች ብሔራዊና በጎ ፍቃድ አገልግሎት የመንግስትን ውሳኔ የሚጠይቁ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተነስተዋል።
****************************
በመድረኩ የ2012 ዓ.ም. ረቂቅ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታውን ተግባራዊ ለማድረግ የሽግግር ጊዜ መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ የሚቀርብበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በጉጂና ጌዴዖ ዞኖች ዜጎችን በማፈናቀል፣ ንብረት በማውደምና በመግደል የተጠረጠሩ ከ270 በላይ ተጠሪጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢፌዲሪ ሠላም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ የህግ የበላይነት ለማስከበሩ እየተደረገ ባለው ጥረት ወደ ቄያቸው የሚመለሱ ዜጎች ቁጥር ጨምሯል ብለዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጌዴዖ ዞን አስተዳደር ጋር በመሆን 15 የዓለምቀፍ ተቋማትና ረጅ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት ዜጎችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ሂደት ያለበትን ደረጃ ለዓለምቀፍ ማኅበረሰብ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
Via #VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የብሪታንያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ የፊታችን ግንቦት 30 ስልጣን እንደሚለቁ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ብሪታንያ ከህብረቱ ጋር በምትለያይበት ጉዳይ ላይ ከፓርላማ አባላት ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻላቸው ይታወሳል። የፍቺ ስምምነቱን ሦስት ጊዜ ፓርላማው አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ሰሞኑንም ስልጣን እንዲለቁ ወግ አጥባቂ የፓርላማው አባላትና ተቀናቃኛቸው ሌበር ፓርቲ ግፊት ሲያደርጉ ሰንብተዋል። ይህንንም ተከትሎ ቴሬዛ ሜይ ከደቂቃዎች በፊት ስልጣናቸውን የፊታችን ግንቦት 30 እንደሚያስረክቡ አስታውቀዋል።
Via #BBC/FBC/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #BBC/FBC/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሳምራዊት...
"የኢትዮጵያ ሴት ሚኒስትሮች ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጋር የእግር ኳስ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው፤ እሱ ብቻ አይደለም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ጋር የእግር ኳስ ጨዋታ ያደርጋሉ ተብላል።"

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከሰው ችሎት በቀረቡት ኮማንደር አለማየሁ ኃይሉ በሌሎች ተከሳሾች ድብደባ ተፈፀመባቸው‼️
.
.
በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከሰው ችሎት በቀረቡት በኮማንደር አለማየሁ ኃይሉ ላይ ሌሎች ተከሳሾች ድብደባ በመፈፀማው የዕለቱ ችሎት ለሐምሌ 1፣2011 ተዛወረ፡፡
በእነ ኮማንደር አለማየሁ ኃይሉ የክስ መዝገብ 10 የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ከ2005 እስከ 2010 በተለያዩ ጊዜያት ተጠርጣሪዎችን እነሱ በፈለጉበት መንገድ ቃላቸውን እንዲሰጡ በመደብደብ ከባድ የአካልና የሞራል ጉዳት አድርሰዋል በሚል ተከሰው ነበር በዛሬው ዕለት ችሎት ለመቅረብ ሲመጡ ሌሎች የቂሊንጦ የቀጠሮ እስረኞች ኮማንደር አለማየሁ ላይ ድብደባ የፈፀሙት፡፡
እነ ኮማንደር አለማየሁ ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረፊያ ቤት እያሉ በሌሎች የቀጠሮ እስረኞች ከዚህ በፊት በምርመራ ወቅት ተፈፅሞብናል ባሉት ድብደባ ይበቀሉናል በሚል ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተዛውረው ነበር፡፡
እናም በዛሬው ዕለት እነ ኮማንደር አለማየሁ እና የቂሊንጦ ማረሚያ የቀጠሮ እስረኞች ወደ ችሎት በመቅረብ ላይ እያሉ በመገናኘታቸው ኮማንደር አለማየሁ ላይ በካቴና ድብደባ ተፈፅሞብኛል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ጠቅላይ ዓቃቤ ህግም በተከሳሾች ላይ ዛሬ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 12ኛ የወንጀል ችሎት ምስክር ለማሰማት የነበረው ችሎት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ምስክር ሊሰማብን አይገባም በማለታቸው፣ችሎቱ ተከሳሾች ለሐምሌ 1 ዳግም እንዲቀርቡ አዟል፡፡
በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከሰው ችሎት ለመቅረብ እየመጡ ባለበት ወቅት በቂሊንጦ የቀጠሮ እስረኞች ተፈፀመ ስለተባለው ድብደባ አጣርቶ እንዲያቀርብም የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በችሎቱ አዟል፡፡
Via #etv

#update የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ቤተ መንግሥቱን ጎበኙ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በቤተ መንግሥት ግቢ ዉስጥ የሚሰሠሩ ሥራዎችን ጎብኝተዋል:: ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም በከተማዋ የሚተገበሩትን 'ሸገርን የማስዋብ' ፕሮጀክቶችና ለዜጎች የሚኖራቸዉን ሁለንተናዊ ፋይዳ አብራርተዉላቸዋል፡፡
ምንጭ፡- የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia