የመብራት ነገር....
"...እኔ የምኖርበት አካባቢ መብራት ካጣን ዛሬ 6ኛ ቀናችን ነው። በየቀኑ የጥገና ሰራተኞች እየመጡ ይህንንማ አንችለውም እያሉ ይመለሳሉ። በጣም ሰዉ ሲመረው ገንዘብ አዋጥቶ ሰጣቸውና ሰርተነዋል መብራት ሲለቀቅ ይመጣላችኋል ብለው ሄዱ እስካሁን ሰዓት ድረስ መብራት የለንም። የምንበላውን እንኳ ማብሰል አልቻልንም።"
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራን 28ኛ ዓመት የነፃነት በዓል አስመልክተው ለሀገሪቱ ህዝብና መንግስት የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ በመልዕክታቸውም ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በአሁኑ ወቅት የጋራ መተማመንና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ በጥሩ ሁኔታ በመቀጠሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
በቀጣይም የሁለቱ እህትማማች ሀገራት ህዝቦች ግንኙነት የጋራ ፍላጎትና ጥቅምን መሰረት በማድረግ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የሚከሰቱ ችግሮችን በጋራ ለመፍፍታት ቁርጠኛ አቋም ያላት መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ለኤርትራ ህዝቦች ሰላምና ብልፅግና መመኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Via #fbc

በጎሳ ግጭት ቢያንስ 11 ሰዎች ተገደሉ...
በኬንያ ውስጥ ኬሪዮ በተባለው አካባቢ ለሳምንታት ባጋጠመ የሽፍቶች ጥቃትና በጎሳ ግጭት ቢያንስ 11 ሰዎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ተፈናቀሉ።
በኬንያ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚገኘው ኬሪዮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የከብቶች ዘረፋ አጋጥሟል።
ረቡዕ እለት ምሽትም አንድ የጸጥታ ሰራተኛን ጨምሮ ሦስት የተገደሉ ሲሆን ባለፈው ሳምንትም ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ጥቃቱ በተፈጸመባቸው ሦስት አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቀያቸውን እየተወ ከብቶቻቸውን በመያዝ ከአካባቢው እየሸሹ መሆኑም ተነግሯል። በሚያጋጥሙት ግጭቶች የተነሳም አራት ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን በርካታ መምህራንም በጥቃት ከሚታመሰው አካባቢ ወደ ሌሎች ቦታዎች እንዲዘዋወሩ እየጠየቁ ነው።
በኬሪዮ አካባቢ ተደጋጋሚ የሽፍቶች ጥቃት አዲስ ነገር አይደለም። መንግሥትም ችግሩን በቁጥጥር ስር አውዬዋለሁ ቢልም በተደጋጋሚ እያገረሸ ነው። በአካባቢው በርካታ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እንዳሉም የመንግሥት ባለስልጣናት ይናገራሉ።
Via #BBC

#update የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ-ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) 21 የስራ አስፈጻሚ አባላትን መምረጡን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡ በመንግስት ትይዩ በተዋቀረው ስራ አስፈጻሚ ውስጥ የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ምክትል መሪው አንዷለም አራጌን ጨምሮ 7 ሰዎች በአባልነት ተካተዋል፡፡ የፓርቲውን የዕለት ተዕለት በሚከታተለው ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ደሞ የፓርቲው ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ፣ ምክትላቸው ጫኔ ከበደ፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ዋሲሁን ተስፋዬን ጨምሮ 14 የፓርቲው አባላት ተመርጠዋል፡፡
Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopi
Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopi
“ቪትዝ የተባለ መኪና ዋጋ በ70 ሺሕ ብር ገደማ፤ ኮሮላ በአንፃሩ 90 ሺሕ ብር ገደማ ሊጨምር ይችላል...”
.
.
የገቢዎች ሚኒስቴር ያገለገሉ ዕቃዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ከሚከፈልባቸው ቀረጥ በእርጅናቸው ምክንያት ይደረግ የነበረውን ቅናሽ አስቀርቷል። ውሳኔው በቀጥታ ከሚመለከታቸው መካከል ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች አስመጪዎች ውሳኔው በይፋ እጃቸው አልደረሰም። አውቶ ኢቲ የተባለው የተሽከርካሪ መገበያያ ድረ-ገጽ መሥራች እና ባለቤት አቶ እዮብ ከበደ የገቢዎች ሚኒስቴር ውሳኔ ለገበያው "ዱብ እዳ ሆኗል" ሲሉ ይናገራሉ። "አገር ውስጥ መኪና ያስገቡ ሰዎች በአዲሱ ቀረጥ እንዲቀርጡ እየተደረገ ነው። ዛሬ ጉምሩክ ብትሔድ [መኪና አስመጪዎች] በአዲሱ ነው የምትስተናገዱት ተብለው መኪና እንዳይወጣ ተይዟል" የሚሉት አቶ እዮብ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ጭምር አዲሱ ውሳኔ ተፅዕኖ ማሳደሩን ተናግረዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ውሳኔውን በይፋ ካላሳወቃቸው የተሽከርካሪ ነጋዴዎች መካከል አንዱ አቶ ኑረዲን ሬድዋን ናቸው። "በስሚ ስሚ ነው የሰማንው። ፎቶ የተነሳ ወረቀት ምናምን እንጂ ሙሉ መረጃው ወይም መመሪያው የለም" ሲሉ ይናገራሉ።
አቶ ሬድዋን የጠቀሱት እና በገቢዎች ሚኒስቴር ምኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ግንቦት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ተፈርሞ የወጣ የተባለ ደብዳቤ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ሲዘዋወር ታይቷል። "የጸደቁ መመሪያዎች ስለመላክ" የሚል ርዕስ የተሰጠው ይኸው ደብዳቤ ለጉምሩክ ኮሚሽን የተላከ እንደሆነ ይጠቁማል። በደብዳቤው "ማንኛውም ያገለገለ ዕቃ ተሽከርካሪን ጨምሮ ወደ አገር ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ቀረጥና ታክሱን ለመወሰን ምንም አይነት የእርጅና ቅናሽ አይደረግም።" የሚል ሐሳብ ተካቶበታል።
እስካሁን በነበረው በኢትዮጵያ መንግሥት አሰራር መሰረት የተሽከርካሪ ቀረጥ በመኪናው የሲሲ መጠን፣ በተመረተበት ጊዜ እና በተገዛበት ዋጋ ይተመናል። ከተመረተ አንድ አመት የሞላው ተሽከርካሪ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ከሚከፈለው ታክስ 10 በመቶ በእርጅና ሳቢያ ይቀነስለታል። ከተመረተ ሁለት አመት የሞላው ተሽከርካሪ የእርጅና ቅናሽ 20 በመቶ ነበር። ከሶስት አመት በላይ የሆናቸው ተሽከርካሪዎች ከሚከፈልባቸው ታክስ 30 በመቶ ቅናሽ ሲቀነስላቸው ቆይቷል።
ይኸ አሰራር በድንገተኛው ውሳኔ ሲቀየር በኢትዮጵያ ጎዳናዎች በብዛት የሚታየው ቪትዝ የተባለ መኪና ዋጋ በ70 ሺሕ ብር ገደማ፤ ኮሮላ በአንፃሩ 90 ሺሕ ብር ገደማ እንደሚጨምር አቶ እዮብ ተናግረዋል። አቶ እዮብ "ኢትዮጵያ ውስጥ ከድሮው በበለጠ ተሽከርካሪ የቅንጦት ነው የሚሆነው። አነስተኛ መኪና ከ500 ሺሕ ብር በታች አትገዛም። አንዲት ትንሽዬ መኪና 500 ሺሕ ብር ገዝቶ ሊጠቀም የሚችለው ምን ዓይነት ሰው ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ።አቶ ኑረዲን በበኩላቸው በዚህ ውሳኔ ምክንያት "አሁን ገበያ ላይ ያሉት መኪኖች ዋጋ ይጨምራል" ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ ከአምስት አመት በላይ ያገለገሉ መኪኖች ወደ ገበያው እንዳይገቡ ልታግድ ትችላለች። የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች "የሚያስከተሉትን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳትን ለመቀነስ" በተዘጋጀ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ይመለከታቸዋል ካላቸው ጋር በትናንትናው ዕለት ውይይት አካሒዷል። አቶ እዮብ በኢትዮጵያ ተሽከርካሪ በመገጣጠም እና ያገለገሉትን ከውጪ አገራት ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ መሳተፋቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቼ እንሚቀርብ የተረጋገጠ ነገር የለም። አቶ እዮብ ግን በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ሒደቱ ተጠናቆ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል የሚል ግምት አላቸው።
Via #DW

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሼር #Share የረመዳን ወርን በማስመልከት በአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት የተዘጋጀ አጭር ቪድዮ!
/ኢንጂነር ታከለ ኡማ/
"ይህ #በበረካ የተሞላ ወር ነው። ፍቅር፣ መተሳሰብ ፣አንድነት የረመዳን ባህሪያት ናቸው። እነዚህ ባህሪያት የሁል ጊዜ ተግባሮቻችን ይሁኑ! #ረመዳን_ከሪም" ኢንጂነር ታከለ ኡማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
/ኢንጂነር ታከለ ኡማ/
"ይህ #በበረካ የተሞላ ወር ነው። ፍቅር፣ መተሳሰብ ፣አንድነት የረመዳን ባህሪያት ናቸው። እነዚህ ባህሪያት የሁል ጊዜ ተግባሮቻችን ይሁኑ! #ረመዳን_ከሪም" ኢንጂነር ታከለ ኡማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) 21 የፓርቲውን የስራ አስፈፃሚ አባላት፦
በዚህም መሰረት፦
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፦ የፓርቲው መሪ
አቶ አንዱዓለም አራጌ፦ የፓርቲው ምክትል መሪ
አቶ ኑሪ ሙደሲር፦ የመንግስት/ትይዩ ካቢኔ እጩ ተወካይ
አቶ ተክሌ በቀለ፦ የመንግስት/ትይዩ ካቢኔ እጩ ተወካይ
አቶ ግርማ ሰይፉ፦ የፓርላማ አባላት እጩ ተወካይ
ኢ/ር ዳንኤል ሺበሺ፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት እጩ ተወካይ
አቶ የሺዋስ አሰፋ፦ የፓርቲው ሊቀመንበር
ዶክተር ጫኔ ከበደ፦ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር
አቶ አበበ አካሉ፦ የፓርቲው ዋና ፀሃፊ
አቶ ጁአልጋው ጀመረ፦ የፓርቲው በጀትና ፋይናንስ ሰብሳቢ
አቶ ዋስይሁን ተስፋዬ፦ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
አቶ ናትናኤል ፈለቀ፦ የፓርቲው የዝብ ግኑኝነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
አቶ አምሃ ዳኘው፦ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሰብሳቢ
ወ/ሪት ፅዮን እንግዳዬ፦ የወጣቶች ጉዳይ ተጠሪ
ወጣት ቴዎድሮስ አሰፋ፦ የወጣቶች ጉዳይ ተጠሪ
ወ/ሪት ናንሲ ውድነህ፦ የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ
ወ/ሪት ካውሰር እንድሪስ፦ የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ
ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ፦ የሙያ ማህበራት ግኑኝነት ተጠሪ
ወ/ሮ እሌኒ ነጋሽ፦ የሙያ ማህበራት ተጠሪ
አቶ ኢዮብ መሳፍንት፦ የዓለም አቀፍ አባላት ተጠሪ
አቶ ብርሃኑ ወ/ጊዮርጊስ፦ የፋይናንስና ክዋኔ ኦዲተር አባል
አቶ አበራ ገብሩ፦ የፋይናንስና ክዋኔ ኦዲተር አባል
አቶ ዳዊት መና፦ የፋይናንስና ክዋኔ ኦዲተር አባል
አቶ ማንአለኝ ፈረደ፦ የደንብ ተርጓሚና ዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል
አቶ እንድሪያስ አላምቦ፦ የደንብ ተርጓሚና ዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል
ወ/ሮ ሩሃማ ታፈሰ፦ የደንብ ተርጓሚና ዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል
ዶክተር ተስፋዬ ሞላ፦ የደንብ ተርጓሚና ዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል
አቶ ኡቻን ኡገቱ፦ የደንብ ተርጓሚና ዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል በመሆን መመረጣቸውን ነው ፓርቲው ይፋ ያደረገው።
ይህንንም ተከትሎ ተመራጮቹ ቃለመሃላ ፈፅመዋል።

#update የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ከባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋር❤️ኦሮሞ👆
የኦሮሞ እና አፋር ክልል ህዝቦች የወንድማማችነትና አንድነት መድረክ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
በመድረኩ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ አባገዳዎች፣ ወጣቶች እንዲሁም የሁለቱ ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ ሀላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
መድረኩ የሁለቱን ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ትስስር በቀጣይነት ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
በወንድማማችነትና አንድነት መድረኩ ላይ የሚሳተፉ በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የሚመራ ልዑክም በትናንትናው ዕለት አዳማ ከተማ ገብቷል።
ልኡካኑ አዳማ ከተማ ሲደርሱም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ፦
ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በክልላችን የተለያዩ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር መከሠቱና በሰው ህይበወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱና በርካቶች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀል የደረሰባቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ የክልሉ መንግሥት ከመከላከያ ሠራዊት ፣ ከፌዴራል ፖሊስና ከተጎራባች የኦሮሚያና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ጋር በመቀናጀት ግጭቶችን ለማስቆም ፣ ግጭት የተከሰተባቸውን አካባቢዎች ፀጥታ ለማረጋገት ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀድሞ ቀያቸው ለመመለስና በግጭቱ የተሳተፉ አካላትን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑም ይታወቃል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም አጠቃላይ ሀገራዊና ክልላዊ የፀታና የሠላም ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም በተለይም በመተከል ዞን በዳንጉር ፣ በማንዱራ፣ በፓዊና በድባጢ ወረዳዎች ተከስተው በነበሩ ግጭቶች መሠረታዊ መነሻ ምክንያቶች ፣ ግጭቶቹን ለማስቆም በተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ፣ እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
ውሳኔ 1፦
ግጭት በተከሰተባቸውም ሆነ በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ድምፅ አልባ መሣሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ውሳ 2፦
በልዩ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ የክልሉ ሚሊሻ ዓባላትም ሆኑ የቀበሌ ታጣቂዎች ህጋዊም ይሁን ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ውሳኔ 3፦
በተደራጀ መንገድም ሆነ በተናጠል ወደ አማራ ክልል አዋሳኞች ጥቃት ለመፈፀም የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት እንቅስቃሴዎች ፍፁም ህገ-ወጥ ፣ በየትኛውም አካላ ተቀባይነት የሌለውእና የተወገዘ ከመሆኑም ባለፈ በልዩ ሁኔታ በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው፡፡
ውሳኔ 4፦
ከመከላከያ ሠራዊትና ከፌዴራል ፖሊስ ውጭ በአስተዳደር ወሰን አካባቢዎች የክልሉ ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ በ5 ኪሎ ሜትር ራዲዬስ ውስጥ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፍፁም የተከለከለ ነው፡፡
የፀጥታ ምክር ቤቱ እነዚህን ውሳኔዎች ለጋራ ሠላምና ፀጥታ እጅግ በጣም ወሳኝና መሠራተዊ መሆናቸውን በጥልቀት በመገንዘብ የመተከል ዞንና ከፍ ሲል በተጠቀሱት አራት ወረዳዎች የተዋቀሩ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቶች በጥብቅ እንዲከታተሉና እንዲያስፈፅሙ ግልፅ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡
ምክር ቤቱ ከዚህም በተጨማሪ በግጭቶቹ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ አካላት ወደነበሩበት እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በቅርበት እንዲደግፍና የአካባቢው ሠላም ቀድሞ ወደነበረበት ሠላማዊ ይዞታው እንዲመለስ ከክልሉ መንግሥትና ከፀጥታ ሃይሉ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መስራት እንደሚጠበቅበት የአደራ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎን የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና በብጥብጡ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የተሳተፉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ የተጀመረውን ጥረት ስኬታማ ለማድረግ ያልተቆጠበ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪው አቅርቧል፡፡
የክልሉን ሠላምና መረጋጋት ይበልጥ በማስጠበቅ ረገድ ከማንም በላይና በፊት መላው የክልሉ ኗሪ ህዝብ ቀዳሚ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን በመገንዘብ በሁሉም የክልሉ አካባቢ የተፈጠረው አንፃራዊ ሠላምና መረጋጋት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል በየደረጃው ከሚገኙ ሠላም አስከባሪ የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የዜግነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአደራ ጭምር አሳስቧል፡፡
የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት
ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም
አሶሳ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያና አፋር ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ኮንፈረንስ ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-
• ኢትዮጵያ የሁላችንም እንድትሆን ሁላችንም በመተሳሰብ፤ በመቀራረብ መታገል አለብን፤ በጋራ ልንሰራም ይገባል፡፡
• ፈተናዎችን ማረም የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡
• አፋርና ኦሮሞ በአንድ ደም የተሳሰረ ህዝብ ነው፡፡ በአዋሽ ወንዝ ተጋምደዋል፡፡ ወደ ፊትም ግንኙነታቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠንክረን እንሰራለን፡፡
• ግጭቶችን በማስወገድ ሁሉም በነፃነት በፈለገበት ቦታ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ እንዲለወጥ በጋራ መስራት ወሳኝ ነው፡፡
• የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለዘላቂ የጋራ ተጠቃሚነት ችግሮችን ለመፍታት የጀመረውን ስራ ቀን ከሌት አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
• የአፋር ወንዶሞቻችን ወደ ቤታችሁ ወደ ቀያችሁ እንኳን በሰላም መጠያችሁ፤ ረመዳንን ከዚህ በኋላ ግማሹን በኦሮሚያ ግማሹን በአፋር እንፆማለን፡፡
• የረመዳን ወር የሰላም ወር፤ የእርቅ ወር፤ የፍቅር ወር፤ ከሁሉም በላይ ሰይጣን የሚታሰርበት ወር ሲሆን በዚህ በተቀደሰው ወር ግንኙነታችን እንዲጠናከር ቀን ከሌት እንሰራለን፡፡
• በሚቀጥሉት ጊዜያት አፋርኛና ኦሮሚኛ ተማምረን መድረኮቻችንን በአፋርኛ፣ በኦሮሚኛና በአማርኛ እናደርጋለን፡፡

ፌስቡክ የጥላቻ ንግግሮችን እያስወገደ ነው...
ፌስቡክ በስድስት ወራት ውስጥ 3 ቢሊዮን የሀሰት አካውንቶችን ማጥፋቱን አስታወቀ፡፡ ከሰባት ሚሊዮን በላይ #የጥላቻ_ንግግሮችን በማስወገድም በታሪኩ ከፍተኛ የተባለለትን እርምጃ ወስዷልም ተብሏል፡፡
ፌስቡክ ጥላቻ ንግግርና በሀሰተኛ መረጃዎች እየቀረበበት ያለውን ወቀሳ ተከትሎ ለጀመሪያ ጊዜ ምን ያህል ሀሰተኛ አካውንቶችንና ልጥፎችን ጭምር እንዳጠፋ በግምገማዊ ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
የፌስ ቡክ ዋና አስተዳዳሪው #ማርክ_ዙከርበርግ በትላንተናው ዕለት ፌስቡክን ለመቆጣጠር በተለያየ መልኩ ተከፋፍሎ እንዲደራጅ ለቀረቡለት ጥሪዎች ችግሩን ለመፍታት አሰራሮችን ማዘመን ብቸኛው መፍትሄ ነው ሲል መልሷል፡፡
እንዲወገዱ የተደረጉት የሀሰተኛ አካውንቶች ሁሉም በሚባል ደረጃ በማኅበራዊ አውታር "ንቁ" ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ዕድል ከማግኘታቸው በፊት ካለፈው ጥቅምት እስከ መጋቢት ድረስ እርምጃው እንደተወሰደባቸው ተመልክቷል፡፡
ፌስቡክ እንዳለው ሪፖርቱ የሚያሳየው የኩባንያውን ግልጽነትና ለተጠቃሚዎቻችን ተጠያቂነታችንን እና ምላሽ ሰጭነታችንን ለማሳየትና እምነት ለመገንባት የሚያስችለን ነው፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ

ይህ የገል ገፅ-- በዚህ ቻናል ላይ የማይዳሰሱና ልዩ ልዩ መረጃዎችን የሚዳሰሱበት ነው፦
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-WeEn84b8FUyA

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድምፅ👆
ቁጥራቸው 250 የሚሆኑ የጎንደር ዩንቨርስቲ የህክምና ሳይንስ ኢንተርን ተማሪዎች ግቢውን ለቀው አንዲወጡ ከተደረገ ቀናት አልፈዋል። የጎንደር ዩንቨርስቲ የህክምና ሳይንስ ኢንተርን ተማሪዎቹ እንደሚናገሩት ዩኒቨርስቲው በሆስፒታሉ ላይ ስላሉ ችግሮች ያነሳነውን ጥያቄ በ15 ቀን ውስጥ እመልሳለሁ ካለ በኃላ መልስ ስንጠብቅ ግቢውን ለቀን እንድንወጣ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ሰማን ግቢውን ለቀን ወጥተናል ይላሉ።
Via #VOA