TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ፦

#ኢትዮጵያዊነትን የሚፈታተኑ #ችግሮችን ለመከላከል ህዝቡ ለአንድነቱ ፀንቶ መታገል እንዳለበት አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አሳሰበ፡፡

ከዘረኝነትና ከማንነት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ #ግጭቶችን በአገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የዜጎች #መፈናቀልና ሞት መፈጠሩ አሳስቦኛል ያለው ፓርቲው መንግስት ከሰብዓዊ መብትና ከፀጥታ ጋር ተያይዘው ያሉ ህጎች ባአስቸኳይ ሊያስፈፅም ይገባል ብሏል።

በሃገሪቱ እዚህም እዚያም ያሉ #ግጭቶችን የሚፈጥሩ ግለሰቦችንም ሆነ ፖለቲከኞች የመለየት ስራ የህዝቦችም ሃላፊነት ነው ያለው ፓርቲው በየትኛውም አካል ጥፋት ህዝቡ መጎዳት እንደሌለበት ገልጿል።

መንግስት #ህጎችን በማስከበር ዜጎች በፈለጉት ክልል በነፃነት የመኖርና የመንቀሳቀስ መብታቸውን የማስከበር ህገ መንግስታዊ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተገልጿል።

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን ዲላ🔝

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ነዋሪዎች በማስተባበር በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረግ የተንቀሳቀሱ መኪኖች ዲላ ገብተዋል፤ ነዋሪውም እንግዶቹን እየተቀበላቸው ይገኛል።

Via ፀጋዬ(ከዲላ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለOMN ጋዜጠኞች ከጃዋር መሀመድ የተፃፈ...

(ከEyasped Tesfaye)

ይህ ዛሬ #OMN ውስጥ ከሚሰራ ወዳጄ ያገኘሁት መረጃ ነው። ጃዋር መሀመድ በትናንትናው ዕለት ለ OMN staff የፃፈው ደብዳቤ ሲሆን ፤ ለ internal consumption ብቻ ይውል የነበረ ቢሆንም ለሌሎች ሚዲያዎችም ትምህርት እንዲሆን እና መንገዳቸውን መርምረው አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ ይረዳል ብዬ ስላመንኩ ለጥፌዋለሁ።
.
-ማንኛውንም ብሄር #በመጥፎ መልኩ የሚገልፁ ወይም የሚያቀርቡ ዜናዎችም ሆነ ፕሮግራሞች እንዳይኖሩ

-ግጭትን እና ፀብን የሚያነሳሳ ይዘት ያላቸው የሚመስሉ ማንኛውም ፕሮግራሞች #እንዳይቀርቡ

-እንዲሁም ሰላምን መቻቻልን እና መረዳዳትን ብቻ መሰረት ያደረጉ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ.....ወዘተ ይገልፃል ደብዳቤው።

(ሙሉ ደብዳቤው በምስል ከላይ ተያይዟል)

Via Eyasped Tesfaye
@tsegabwolde @tikvahethiopi
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አብራሪዎች ሥልጠናን በተመለከተ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዛሬ ያወጣውን ዘገባ «#ሐሰት» ሲል አስተባብሏል። የዩናይትድ ስቴትሱ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በድረ-ገጽ ዘገባው፦ «የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማክስ 8 ምስለ-በረራ (ሲሙሌተር) ነበረው፤ የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ ግን ስልጠናውን አላገኘም» በሚል ርእስ ዘለግ ያለ ጽሑፉን አስነብቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ቅር መሰኘቱን በማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ ዐሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎቹ ቦይንግ 737-8-ማክስን ማብረር ከመጀመራቸው በፊት፤ ቦይንግ-737 NG በሚባለው እና በቦይንግ-737 ማክስ መካከል ያለውን ልዩነት በቦይንግ ምክረ-ሐሳብ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትሱ የፌዴራል የበረራ አስተዳዳር (FAA) ልዩነታቸውን አስመልክቶ ባጸደቀው መሰረት ሥልጠና ማጠናቀቃቸውን ገልጧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፦ የቦይንግ-737-ማክስ ሙሉ ምስለ-በረራ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የMCAS ሥልት ችግርን ምስለ-በረራ ለማድረግ ተደርጎ የተቀናጀ አይደለም ብሏል። የMCAS ሥልት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአደገኛ መልኩ ወደላይ አስግገው መብረር ሲጀምሩ የአውሮፕላኖቹን አፍንጫ በራሱ ጊዜ ወደታች የሚጎትት ስልት ነው። በኢትዮጵያም ኢንዶኔዢያም የተከሰከሱት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የአደጋ መንስኤ አንዳንድ ግልጽ መመሳሰሎች እንደተገኘባቸው የኢትዮጵያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ #ዳግማዊት_ሞገስ በተለይ ለ«ጀርመን ራድዮ» ተናግረዋል። ደብረዘይት/ ቢሾፍቱ አጠገብ ወድቆ የተከሰከሰዉ አዉሮፕላን ሁለቱን ፓይለቶች ጨምሮ አሳፍሯቸዉ የነበሩ 157 ሰዎች በሙሉ አልቀዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያን🇪🇹ትወዳታለህ?

እንግዲያዉስ ከጎንህ ላለዉ አንድ ሰዉ አንድነትንና ፍቅርን አስተምር፣ ጥቅሙን ተናገር! በአሁኑ ሰዓት ለኢትዮጵያ የምታደርግላት #ትልቁ ዉለታ ይህ ነዉ!!

#የንጋትብርሃን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ጎንደር🕊

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #አደባባይ_ሙሉጌታ ከአብመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ዞኑ ወደ #ተረጋጋ ሕይወት መመለሱንና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የዞኑን ሕዝብ ዕድገት እና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ በማንነት ስም እየማሉና እየተገዘቱ ባሉ ጥቅመኞች የተሳሳተ አስተሳሰብ የተወለደ ግጭት ምክንያት የሰዎች ሕይወት ማለፉ፣ ንጹኃን ለጉዳት መዳረጋቸው፣ በርካታ ንብረቶች መውደማቸውና ሰዎች ቤት ንብረታቸውን አጥተው መፈናቀላቸው ትውልድ የማይዘነጋው የቅርብ ጊዜ ታሪክ መሆኑን ነው ዋና አስዳዳሪው ያስታወቁት።

በርካቶችም ለሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ መጋለጣቸውን ያብራሩት አቶ አደባባይ ‹‹ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ከእርሻ ማሳቸው ርቀው ጉልበታቸውን አቅፈው በባይተዋርነት ተቀምጠዋል›› ነው ያሉት። ችግሩን ለመፍታት መንግሥትና ሕዝብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እየሠሩ እንደሆነና በተሠራው የሰላም ማስከበር ተግባር በዞኑ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ መቻሉንም አብራርተዋል። በዞኑ ይስተዋላሉ የነበሩ ‹‹የግድያና እና ተደራጅቶ የመጠቃቃት፣ የመፈናቀል እና ሌሎች ወንጀሎችን ማስቆም ተችሏል›› ብለዋል።

ተዘግተው የነበሩ 12 ትምህርት ቤቶች፣ ሦስት የጤና እና ሁለት የሕግ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ገልጸዋል። ከፍተኛ የስጋት ምንጭ የነበሩ ዋና ዋና መንገዶችም ከስጋት ነጻ ሆነው ሰላማዊ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ተነግሯል።

በግጭቱ ወቅት ተዘርፎ የነበረ አምስት ሺህ የሚጠጋ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ከብቶች እና ሌሎች ንብረቶች ለባለቤቶቻቸው መመለሳቸውንም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። በዞኑ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ በግጭቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ማደኛ ወጥቶባቸው የነበሩ 46 ግለሰቦችና ሌሎች 68 እጅ ከፍንጅ የተያዙ ግለሰቦች በድምሩ 114 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው በሕግ አግባብ እየታዬ እንደሚገኝና ውሳኔም እንደ ጥፋታቸው ተሳትፎና እንደ ነፃነታቸው የሚወሰን እንደሆነ አስረድተዋል። የተፈናቀሉ ወገኖችን በቋሚነት በማቋቋም ሰላማዊ ኑሮ እንዲጀምሩ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ከመላው የዞኑ ሕዝብ ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ጋር ውይይት መደረጉንና በውይይቱም መሠረት ሕዝቡ የሰላምን አስፈላጊነት በመረዳት እርቀሰላም እንዲወርድ መጠየቁን ለአብመድ ተናግረዋል።

በተወሰኑ አካባቢዎች በአማራ ብሔርና እና ቅማንት ማኅበረሰብ መካከል እርቀ ሰላም መውረዱን ያስታወቀት አቶ አደባባይ ‹‹የተፈናቀሉትን በዘላቂነት ወደ ቀያቸው ለመመለስ በዞኑ የሚገኙ
ሁሉንም የአማራንና የቅማንት ማኅበረሰብ ለማስታረቅ እየተሠራ ነው። ይህንን እርቅ ተግባራዊ ለማድረግ ከሁለቱ ወገን የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ እናቶች እና ነዋሪዎች የተካተቱበት ኮሚቴ ተቋቁሟል›› ብለዋል።

ኅብረተሰቡን በቋሚነት ለማቋቋም ዞኑ 15 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ቀበሌ ድረስ እንቅስቃሴ እንደጀመረና ሕዝቡም ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኛነቱን እያሳየ መሆኑንም ዋና
አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በግንቢቹ ወረዳ ቱሉ ፈራ ቀበሌ ውስጥ  በተከሰከሰው ቦይነግ  737 ማክስ 8 ህይወታቸው ላለፈው 157 ሰዎች የወረዳው አባ ገዳ ዎች እና የጨፌ ዶንሳ ከተማ ነዋሪወች  ክተለያዩ የውጭ ሀገርልት ዜጎች ጋር በጋራ በመሆን በአከባቢው ላይ ችግኝ በመትከል ማስታወሻ አኑረዋል ያረፉትን ወንድሞቻችን እግዚአብሄር  ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን በማለት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ  በቦታውላይ ለሟቾች ምስታወሻ ይሚ ሆን ለመስራትም  እየተወያዩ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopi
#update ባለፈው አንድ ዓመት በሀገሪቱ ውስጥ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የተሰሩ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ያተኮረ መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ነው፡፡

Via FBC
Photo:Elias Mesrest & fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia