TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተሸለመ🔝

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ እና #አመልድ የሀገሪቱን #ጥራት ሽልማት አሸነፉ፡፡ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት በጥራት መስፈርት ካወዳደራቸው 52 ተቋማት መካከል 40ዎቹን በተለያየ ደረጃ እንዲሸለሙ አድርጓል፡፡ ውድድሩ አገልግሎት ሰጪዎችን፣ የግንባታ ድርጅቶችን፣ አምራችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ያካተተ ነው፡፡

በውድድሩ መሰረት የአንደኛ ደረጃ ዋንጫ አሸናፊ የሆኑት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ አማራ መልሶ ማቋቋም ድርጅት እና ሀረር ቢራ አክሲዮን ማህበር ናቸው፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ውድድር ለሦስት ተከታታይ ጊዜ አሸናፊ በመሆኑ የልዩ ዋንጫም ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ምርቶች እና አገልግሎቶች በዓለም ገበያ ተቀባይነትን አግኝተው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በጥራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን ክብርት ፕሬዝደንት ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ያቀረባቸውን የጥራት ውድድር አሸናፊዎች ሸልመዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀላባ ከተማ ይቅርታ ጠየቀ🔝

ባሳለፍነው እሁድ በ6ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሀላባ ከተማ በሜዳው ኢትዮጵያ መድንን ያስተናገደበት ጨዋታ በ76ኛው ደቂቃ ላይ ከተመልካች በተወረወረ #ድንጋይ የመሐል ዳኛው #ኤፍሬም_ደበሌ ላይ ጉዳት በመድረሱ ምክንያት መቋረጡ የሚታወስ ነው። ይህንን አስመልክቶም የሀላባ ከተማ ክለብ ለፌዴሬሽኑ የይቅርታ ደብዳቤ አስገብቷል።

የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አንዋር ሲራጅ ስለ ጉዳዩ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በተፈጠረው ስርዓት አልበኝነት በጣም እንዳዘኑ ገልፀው የሀላባ ከተማ በእግርኳስ ውድድሮች ባለፉት 10 ዓመታት ሲሳተፍ እንዲህ አይነት ድርጊት ታይቶ እንደማይታወቅ በማውሳት ከጨዋታው መቋረጥ በኋላ አመራሩ እንዲሁም የከተማው አስተዳደር ማምሻውን ስብስባ አድርጎ ወደ እርምጃ በመግባት ሁለት ተጠርጣሪዎችን ወዲያው በመያዝ በቀጣዩ ቀንም 9 ወጣቶችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ ለማቅረብ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል። 

ፕሬዝዳንቱ የሀላባ እግር ኳስ ክለብ እና የከተማው አስተዳደር የተፈጠረውን ሁሉ አጥብቆ እንደሚቃወምና እንዲህ አይነት ድርጊት ዳግም እንዳይፈፀም አጥብቀው እንደሚሰሩ በመግለፅ የሚመለከታቸው አካላትን በክለቡ እና በሀላባ ህዝብና አስተዳደር ስም ይቅርታ መጠየቀቸውን ለሶከር ኢትዮጽያ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#Update በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር በአማራና በቅማንት መካከል ትናንትና ዛሬ ተባብሷል የተባለውን ግጭት ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት መተማ መግባቱን የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ቢሮና መከላከያ አስታወቀ።

በሁለት ቀናት ግጭትና የእርስ በእርስ ጥቃት ሰዎች መገደላቸውንና ቤቶች መቃጠላቸውን ሁለቱም አካላት አስታውቀዋል። የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ እስካሁን በቁጥር የተጣራ መረጃ የለም ብለዋል።

በሌላ በኩል፤ ማክሰኞ ዕለት በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃና ኮኪት መከላከያ በወሰደው ከመጠን ያለፈ እርምጃ አንድ ታዳጊን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸውንና 18 ሰዎች መቁሰላቸውን የአማራ ክልል ፀጥታ ቢሮ አታውቋል። መከላከያ ደግሞ ፤ አድፍጦ የታጠቀ ኃይል ወደ ሠራዊቱ በመተኮሱ ምክኒያት ሠራዊቱ እራሱን ሲከላከል እንደነበር ገልፆ “የማን ጥይት ማንን እንደመታ ገና አልተረጋገጠም” ብሏል።

ምንጭ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢው የጥበቃና ደህንነት አሠራር ላይ ያላቸው ከፍተኛ #ተቃውሞ ከምሽቱ 4:30 አንስቶ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

በተለይም የተቋሙ ሴት ተማሪዎች፦ መብታቸው እንዲከበር፤ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፤ በግቢ ውስጥ የሚፈፀሙ ዝርፊያዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

🔹በሌላ በኩል የተቋሙ ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ከሚፈፀሙ ዝርፊያዎች በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው አካባቢ ያለው ዝርፊያ መንግስት በአስቸኳይ እንዲያስቆም እና ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

▫️በአሁን ሰዓት #የሀገር_መከላከያ_ሰራዊት እና #ፌደራል_ፖሊስ ወደ ዩኒቨርሲቲው በመግባት ተማሪዎችን ለማረጋጋት እና ለማነጋገር እየጣሩ ይገኛሉ። ከተማሪዎች እንደሰማነውም በነገው ዕለት ተማሪው የሚካፈልበት ስብሰባ ተጠርቷል።

ምንጭ፦በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tukvahethiopia
አገር መከላከያ ሰራዊት‼️

#በዳውድ_ኢብሳ የሚመራው #ሸኔ የተሰኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ክንፍ በምእራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች እየፈጸመ ያለው ፀረ-ህዝብና ፀረ ሰላም ተግባር ህዝቡ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን #ማስወገዱን የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ አስታወቁ።

ቡድኑን #ትጥቅ_የማስፈታት ስራም አጠናክሮ እያከናወነ መሆኑንም ጀነራሉ ተናገረዋል። ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማካሄድ ከመንግስት ጋር #ተስማምቶ ወደ አገር የተመለሰው የዳውድ ኢብሳው ኦነግ የገባውን ቃል ኪዳን #በማፍረስ ህዝብና አገርን በሚጎዳ ተግባር በመሰማራቱ እርምጃው እየተወሰደበት መሆኑን ነው ጀነራሉ በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት።

በአሁኑ ወቅት ቡድኑ አፈግፍጎ ወደ ጫካ #እየሸሸ ቢሆንም ሰራዊቱ ህግ የማስከበር ስራውን ከአካባቢው ህዝብና የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አክለው ገልጸዋል።

እርምጃው የሚወሰደው በኦነግ ታጣቂዎች የተለያየ ህገ ወጥ አርምጃና ግፍ የተማረረው ህዝብ #ባቀረበው_ጥያቄ መሰረት መሆኑንም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ🔝አክቲቪስት #ጃዋር_መሃመድ በአሁን ሰዓት ከጅማ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ ናቶሊ ሀሰን(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በሴራሊዮን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ በሴራሊዮን መዲና ፍሪታውን በደረሰበት ወቅት በሃገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia