TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከደቂቃዎች በፊት ከጠ/ሚሩ ፕረስ ሴክረታሪ ቢሮ ለጋዜጠኞች በተላለፈው መልእክት የሴክረታሪው ሀላፊዋን "ወይዘሮ" ወይም "ወይዘሪት" ማለት በመተው "ቢልለኔ ስዩም" ብቻ ብላችሁ ተጠቀሙ ተብሏል።

©ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikahethiopia
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ‼️

የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን መንግስት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል!
***

ሰሞኑን በአማራ «ክልል» በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት መውደም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ–አብን የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን እየገለፀ ለተጎጅ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን፡፡ አብን እስካሁን በደረሰው መረጃ መሰረት ከ50 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካቶች ቆስለዋል፡፡ እንዲሁም ውድ የሆነው የሰው ሕይወት አልፏል፡፡ ከሌላ አካል ተልዕኮ ተቀብለው በመጡና ራሳቸውን በቅማንት የማንነት ኮሚቴ ስም ባደራጁ እና ይሄን የጥፋት ተልዕኮ ተሸክመው በአማራ «ክልል» በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት በሚሰሩ ግለሰቦች በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት ከመሆኑም ባሻገር የቅማንት የማንነት ጉዳይ በክልሉ ምክር ቤት ተመልሶ ያደረና የመጨረሻ እልባት የተሰጠው በመሆኑ በሕዝባችን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ሊያስፈፅም የሚችል ነገር አለመኖሩን አብን ያምናል፡፡ የፌደራል መከላከያ ሰራዊትም ግጭቱ በተከሰተበት አቅራቢ ቢኖርም ለሕዝባችን ተገቢውን ከጥቃት የመከላከል እርምጃ እየወሰደ አይደለም፡፡

ስለሆነም የ«ክልሉ»ም ሆነ የፌደራል መንግስት በሕዝባችን ላይ በተደጋጋሚ የሚፈፀመውን ጥቃት የማስቆምና የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን በሚገባ ሊወጣ ይገባል፡፡
በድርጊቱ ፈፃሚዎችና ጠንሳሾች ላይም የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ አብን እየጠየቀ መላ ሕዝባችን ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን በማጠናከር መሰል በኅልውናው ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመመከት ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ አብን ያስገነዝባል፡፡

የፌደራልና የ«ክልሉ» መንግሥት የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ጥረት በሙሉ አብን ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ እየገለፅን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን በሕዝባችን ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት መንግሥት ማስቆም ካልቻለ አብን መላውን አማራ በማንቀሳቀስ ራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን እንዲጠቀም የሚያደርግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በድጋሚ ለተጎጅ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

ኅዳር 26/2011 ዓ/ም
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
አዲስ አበባ፥ሸዋ፣ ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን አምስት የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ግብረ ሀይል በዛሬው ዕለት ባካሄደው ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ዘመቻ ነው ተጠርጣሪዎቹ ቁጥጥር ስር የዋሉት።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊና የቀድሞ አሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንደሚገኙበት ግብረ ሀይሉ አስታውቋል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በሰኔ 17ቱ የአሶሳ ከተማ ግጭት እንዲሁም በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የችግሩ አባባሾች ሆነው የተጠረጠሩ ናቸው ብሏል ፌደራል ፖሊስ።

ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ግብረ ሀይሉ አስታውቋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ🔝

"ትላንትና ወለጋ ዩኒቭርሲቲ ውስጥ በፀጥታ ሀይል ከተመቱት ልጆች ዛሬ ጠዋት ላይ አንዱ ህይወቱ አልፏል እናም የወለጋ ተማሪዎች በዚህ አይነት መልኩ ሀዘናችንን ገልፀናል።"

@tsegabwolde @tikahethiopia
ጅማ JiT🔝በአሁን ሰዓት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሰሞኑን በኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ህይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሻማ መብራት ስነ ስርዓት እያደረጉ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvqahethiopia
#update በኢትዮጵያ የሀገረ ብሔር ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ የፖሊሲ ሃሳቦችንና የመፍትሔ አቅጣጫቸውን የሚያስቀምጥ 'የሀገረ-ብሔር ግንባታ ፕሮጀክት' ሰነድ ተዘጋጀ።

ሰነዱን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጅ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ የአለም አቀፍ የዴሞክራሲና የምርጫ ድጋፍ ኢንስቲትዩት እና መቀመጫውን በኖርዌይ ያደረገው አድላንድ ኮንሰልት ናቸው።

የፕሮጀክት ሰነዱ የታሪክ፣ የባህልና የጋራ እሴቶች ፣ የስብዕናና ስነምግባር ግንባታ፣ የፌዴራሊዝምና ያልተማዕከለ አስተዳደር ፣ ህገ መንግስታዊ ጉዳዮችን፣ የህግ የበላይነትና የዴሞክራሲያዊ ግንባታና ኢኮኖሚያዊ ነክ ጉዳዮችን ማካተቱ ተነግሯል፡፡

©ENA
@tsegabwolde @tikahethiopua
#Update የ13ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ምክንያት በማድረግ 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቡና ጠጡ ሥነ ሥርዓት ፕሮግራም ይታደማሉ፡፡ ፕሮግራሙ የሚካሄደው በዓሉን አስመልክቶ ”ኑ ለሰላም ቡና እንጠጣ” በሚል ነገ በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

@Tsegabwolde @tikahethiopia
ከASTU ተማሪዎች፦

ውድ የ TikvahEthiopia ቤተሰቦች በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን ፍፁም ኢትዮጽያዊነት በተመላ መንፈስ እያቀረብን እኛ የ ASTU ተማሪዎች እየደረሰብን ያለውን የ Academics እና ተማሪው ላይ የሚደርሰውን የመብት ጥሰትና የድምፅ አፈና ከ እኛ ጋር ሆናችሁ ትቃወሙ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡

ውድ ኢትዮጵያውያን እኛ ልጆቻችሁ እያቀረብን ያለነው ጥያቄ ከ politcal አጀንዳ ፈፅሞ የራቀ መሆኑን እንድትረዱ እንፈልጋለን፡፡ ከ ትምህርት ገበታችን ከ ራቅን የመማር ማስተማር ሂደቱ ከተቋረጠ እነሆ 8 ቀን ሞላን፡፡ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የጥያቄያችን አካል እና ሰሚ እንዲሆን የምናደርገውን ጥረት የግል እና የመንግሥት ሚድያዎች እንዲዘግቡልን የምናደርገውን ጥረት የ ጊቢው አስተዳደር የመግብያ በር በመዝጋት እና ሀይል በመጠቀም ለማፈን እየሞከረ ይገኛል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የሚመለከታቸሁ አካላት እንድተባበሩን እንጠይቃለን፡፡

እስካሁን ጥያቄያችን ሰላማዊ እንደሆነ 100% ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡ የግቢው አስተዳደር ግን ጥያቄያችን Political እንደሆነ በማስመሰል ጥፋተኛ ሊያደርገን እየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ውድ የ ኢትዮጵያውያን የ እኛ ልጆቻችሁ መውደቅያችን አያሳስባችሁም? እውነቱን እንድትረዱልን እንፈልጋለን፡፡ በዚሁ University የምንገኝ ከመላው ኢትዮጺያ የተሰባሰብን ተማሪዎች ለሀገርም ለወገንም የሚጠቅም አሌኝታም የሚሆን እውቀት, አስተሳሰብ እና ራዕይ እንዳለን እነኳ የትምህርት ተቋሙ አስተዳደር ከዚህ ቀድሞ ከተለያዮ የመንግስት አካላት ጋር በተደረጉ ውይይቶች መስክረዋል፡፡ አሁን ግን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፡፡ ለጥያቄያችን መልስ ለመስጠት እንኳ ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ስለ ጉዳዮ የማይመለከታችውን የመንግሰት አካላት እያመጡ ጥያቄያችን እንደተመለሰ አድርገው ለማለፍ ቢሞክሩም ተማሪው ግን ስብሰባ ረግጦ በመውጣት የሚመለከተው አካል እንዲመጣ እና አሰፈላጊውን ውሳኔ እንዲሰጠው አሁንም ነገም የሁልጊዜ ጥያቄው ነው፡፡
.
.
ጥያቄ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አቢይ!?

አብያችን ጥያቄያችን ካንተ ዘንድ እንዳይደርስ ከፍተኛ የሆነ ስራ እየተሰራ እንደሆነ እንረዳለን የኛ ጥያቄ ግን በ ቀጥታ አንተን ስለሚመለከት አስፈላጊውን ውሳኔ ከቻልክ ራስህ , የስራ ጫና እና ሀላፊነት ስለሚበዛብህ ቀድሞ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምንስትር የነበሩ ባልደረቦችህን በመላክ መልስ እንድትሰጠን እነፈልጋለን፡፡

ለማስታወስ፦

ዶር አብይ አሁን ጠቅላይ ሚንስትር ከመሆኑ አስቀድሞ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምንስትር የነበረ ሲሆን ለኛ የሚጠቅመንን የትምህርት አካሄድ የቀረፀ ነው፡፡

በወቅቱ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የ ላፕቶፕ እና Tab ሽልማት ሲሰጡ በወቅቱ ለተማሪው የገቡት ተስፋ የሚሰጥ ቃል ገብተው እንደነበረ የማይደበቅ ሀቅ ነው፡፡

ነገር ግን እሳቸው የገቡልን ቃል ወደ መሬት ሳይወርድ በ ሀሳብ ብቻ ስለ ቀረ እባኩዎትን ለነገ ሀገረ ተረካቢ ለሆንን ለእኛ መልስ ይሰጡን ዘንድ እንጠይቃለን፡፡
.
.
ቃል የተገቡልንን ደግሞ በቀጣይ እናቀርባለን

"ቃል ስትገቡ ለእናቶቻችንም ጭምር ነበረ"
"ASTU KEEP YOUR PROMISE "

ASTU STUDENTS
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በማእከላዊ ጎንደር #ቆላድባ ከተማ ዛሬ ቀትር ላይ በተነሳ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ሲጠፋ ሌሎች ሁለት ሰዎች #መቁሰላቸውን የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አስተዳደርና ጸጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ወንድዬ ወልደማርያም ለኢዜአ እንደገለጹት ግጭቱን ያስነሱት በከተማው የሚገኙ ወጣቶች በቁጣ ስሜት ተነሳስተው ነው፡፡

በግጭቱ ሁለት መኖሪያ ቤቶችም በቃጠሎ መውደማቸውን ሃላፈው ተናግረዋል፡፡

የወረዳው አስተዳደር የፖሊስ አባላትና የጸጥታ መዋቅሩ የተፈጠረውን ግጭት ለማስቆምና ከተማውን ወደ መረጋጋት ለመመለስ በጋራ እየተረባረቡ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በከተማው ታዋቂነት ያላቸው ወጣቶች የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎችም ወደ ግጭት የገቡ ወጣቶችን በማረጋጋት የማወያየት ስራ እያካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ጭልጋ አካባቢ ከትናት በስቲያ በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎች ስምንት ሰዎች መቁሰላቸውንና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የገቢዎች ሚኒስቴር ተጠሪነቱ ለፌደራል ፖሊስ የሆነ የጉምሩክ ፖሊስ ሊያዋቅር መሆኑን  ገለፀ። ከቀረጥ ነጻ በሚገቡ ዕቃዎች ምክንያት የግብር መጠኑ መቀነሱንም የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikahethiopia