TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#updateየቡራዩ ከተማ ፖሊስ⬆️

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ በተለያዩ ቀበሌዎች የጸጥታ አካላት ደንብ ልብስ፣ የጦር መሳሪያ፣ ገንዘብ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን #በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

በግለሰቦች መኖሪያ ቤትና በተሸከርካሪዎች ላይ በተደረገ ፍተሻ የአዲስ አበባ ፖሊስና የአገር መከላከያ ሰራዊት ደንብ ልብስ፣ 3 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 5 ሽጉጥ፣ የተለያዩ ህገወጥ ማህተሞች፣ 45 ሺህ ብርና ሌሎች ድምጽ አልባ መሳሪያዎች ተይዘዋል።

እንዲሁም #ግጭቱን ለማስተባበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ቪትስ መኪናዎች ከነአሽከርካሪያቸው ጋር መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ጠቁሟል።

የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ደረጀ ባይሳ እንደተናገሩት፤ በቡራዩና አካባቢዋ በደረሰውን ጥቃት የተጠረጠሩ ሰዎች ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

“ከዚህ #ወንጀል በስተጀርባ ያሉ የተለያዩ ዕቃዎችም ተይዘዋል።ሽጉጦች፣ ክላሾች፣ በዚህ በወንጀል ድርጊቱ በሰው ግድያ ላይ በተለይ የተጠረጠሩ ሰዎች ተይዘዋል። እነዚህ ሰዎች #እንዲጨፋጨፉ፣ ለወንጀል ድርጊት እና #ለሞት መንስዔ የሆኑ ናቸው ተብሎ ህብረተሰቡ በሰጠን ጥቆማ፣ በሁለት ቪትስ መኪና እየተንቀሳቀሱ የተያዙ ሰዎች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ውጤቱ ለህዝብ ይፋ ይሆናል።

በዚህ ሂደት የተለያዩ ዩኒፎርሞች፣ የተለያዩ ዕቃዎች፣ የቢሮ ማህተሞች ተይዘዋል። ከዚህ ከግድያ ጋር ላይያያዝ ይችላል። የተለያዩ የሚሊተሪ፣ የፖሊስ ልብስ ተይዘዋል። ፖሊስ አስመስሎ፣ ፖሊስ እንደዚህ አደረገ በማለት ይህን በመልበስ የክልሉን ፖሊስ ስም በማጥፋት የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ይሆናሉ ብለን የያዝነው አለ በምርመራ፣ በቁጥጥር ስር ውሎ-#እያጣራን ነው። የአገር መከላከያ ደንብ ልብስ እራሱ ሬንጀር ለብሶ ከቤቱ የተገኘ ስላለ እሱንም የአገር መከላከያ ሰራዊት ስም ለማበላሸት እነሱ ናቸው እንደዚህ የሚያደርጉ የሚል ግምት ስላለ እሱንም አሁን በቁጥጥር ስር አውለን ከዚህ ጋር በተያያዘ ወደ 8 ሽጉጥ፣ 3 ክላሽ ተይዞ በዚህ ይዞ ሲንቀሳቀሱ ያየነው አሁን በቁጥጥር ስር አውለን እያጣራን ነው።

ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ላይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ በጥቃቱ የደረሰውን ጉዳት የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ፖሊስ የከፋ ጉዳት እንዳይከሰት ከወጣቶች፣ ከአድማ በታኝ ፖሊስና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ችግሩን ለመቆጣጠር የተለያዩ ስራዎች ሰርቷል።

እስከ ትናንት ድረስ በወንጀሉ ተጠርጥረው የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

በደረሰው ጥቃት የተፈናቀሉ ወገኖች ቢኖሩም ድርጊቱ #የኦሮሞ ተግባር #ሳይሆን የተጀመረው አገራዊ ለውጥ እንዳይቀጥል የሚፈልጉ ሃይሎች ተግባር እንደሆነ በመግለጽ ሳይፈናቀሉ የቀሩ ሰዎች እንዳሉ ገልጸዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመመለስ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት ያለው ኮሚቴ ተቋቋሞ እየተሰራ እንደሆነ የጠቆሙት ምክትል ኮማንደር ደረጀ ህብረተሰቡ የተፈናቀሉትን ዜጎች ለመቀበል ዝግጁ እንደሆነ ተናግረዋል።

የፖሊስ አዛዡ ከዚህ በኋላ በዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሚሆን ጠቁመዋል።

©OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአጋሮ⬇️

"ሀይ ፀግሽ ከደቂቃዎች በፊት ዶ/ር አብይ አህመድ የትውልድ ከተማቸው አጋሮን አይተው ተመልሰዋል አብረዋቸው ኦቦ ለማ እና ዶ/ር ወርቅነህ ነበሩ። አዩብ ነኝ ከአጋሮ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሊሰረዝ ነው⬇️

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊያደርገው የታቀደው ኮንሰርት #ሊሰረዝ መሆኑን ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹልኝ ብሏል።

እንደ ዘ-ሀበሻ ምንጮች ዘገባ #ቴዲ ለአዘጋጆቹ "በዚህ የሃዘን ወቅት መድረክ ላይ ወጥቼ የመዝፈን አቅም የለኝም - አልችልምም" ብሏቸዋል ተብሏል።

ድምጻዊው ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ሊያደርገው የነበረው ኮንሰርት በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሊደረግ የነበረ ሲሆን ባለው አለመረጋጋት የተነሳ ወደ ፊታችን #ቅዳሜ ተዘዋውሮ ነበር።

ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይኸው ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ የማይካሄድ ሲሆን መቼ እንደሚደረግ እንደማይታወቅ ታውቋል።

ሰው እየሞተ መዝፈን አልችልም ያለው ቴዲ አፍሮ በነገው ዕለት ጠዋት በመድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት በቡራዩና በአካባቢው የተፈናቀሉ ወገኖችን እንደሚጎበኝ በተጨማሪም የገንዘብ እርዳታ እንደሚያደርግ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ነግረውኛል ብሏል።

@tsegabwklde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ⬇️

በአዲስ አበባ ነገ እውቅና የተሰጠው #ሰልፍ አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በከተማው ሕገ ወጥ ሰልፍ የሚደረግ ከሆነ በሕግ አግባብ #እርምጃ እንደሚወሰድም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

አንዳንድ ግለሰቦች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ #መሟለት ያለባቸውን መስፈርቶች ማለትም የሰልፉ አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ፣ እንዲሁም ሰልፉ ላይ የሚገኝ የሰው ብዛት ሳያሳውቁ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰልፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ለህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት ሲባል አብዛኛው የጸጥታ ኃይል በሌላ የጸጥታ ስራ ላይ በተሰማረበት በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ አለመኖሩን ኮሚሽኑ አስታውቆ፣ #ነገ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መሟለት ያለባቸውን
መስፈርቶች ሳያሟሉ ሰልፍ ለማድረግ የተዘጋጁ አካላት ከሕገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባና ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፈው በሚወጡ አካላት ላይ ኮሚሽኑ በሕግ አግባብ #እርምጃ ለመውሰድ እንሚገደድ አስታውቋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቡራዩና አካባቢ ተከስቶ በነበረው ችግር ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የጸጥታ አካላትና የስራ ኃላፊዎች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር #ነገሪ_ሌንጮ ገለጹ፡፡

እንዲሁም ችግሩን ለማረጋጋት በተሰራው ስራ አማካኝነትም ወደ ሰላም መመለሱን ዶክተር ነገሪ ሌንጮ አንስተዋል፡፡

በግጭቱ #ተጎድተው ከነበሩ ሰዎች መካከል በዛሬው ዕለት የሦስት ሰው ህይወት ማለፉን ገልጸው በአጠቃላይ እስከአሁን የሟቾቹ ቁጥር 26 መድረሱን በፌስቡክ ገጻቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፍትህ ለእህቶቻችን⬆️

ከሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ #ቡልጋሪያ አካባቢ ስለደረሰ የመኪና አደጋ መረጃ ሰጥቻችሁ ነበር። አደጋው በሁለት ሴቶች ላይ የደረሰና አደጋውን ያደረሰው የፖሊስ መኪና እንደነበር አይዘነጋም። በነገራችን ላይ አደጋው የደረሰባቸው እህትማማቾች ነበሩ። በዚህ አደጋ የወጣት #ሳራ_ተወልደ ህይወት ወዲያው ሲያልፍ እህቷ #እየሩስ በወቅቱ ለህክምና እርዳታ ሆስፒታል ብትገባም ህይወቷን ማትረፍ አልተቻለም። እንግዴ ከአንድ ቤት ሁለት ሰው ማጣት ቤተሰቡን ምንኛ በሀዘን እንደሚጎዳ መገመት ቀላል ነው።

ዛሬ ደግሞ የሰማሁት እጅግ በጣም አሳዛኝ መረጃ ነው። የመኪና አደጋውን ያደረሰው ግለሰብ እስከዛሬ ለፍርድ አልቀረበም፤ በህግም አልተጠየቀም። ቤተሰቦች #ፍትህ እየጠየቁ ናቸው። አደጋውን ያደረሰው ግለሰብ ለፍርድ እንዲቀርብ እና እንዲጠየቅም ቤተሰቦች ጠይቀዋል።

የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ ተከታትሎ አጥፊውን ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል‼️

የህግ የበላይነት ይረጋገጥ!
ፍትህ ለእህቶቻችን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ📌

መስከረም 9/2011 ዓ.ም

ማስታወቂያ፦

በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲዩት በ 2010 ዓ.ም የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት ለነበራችሁና የማጠቃለያ ፈተና ሳትወስዱ ለቀራችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-

ከመስከረም 11/ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ሪፖርት እንድታደርጉ ጥሪ ማስተላለፋችን የሚታዎቅ ሲሆን ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን እየገለጽን የመግቢያ ጊዜውን ወደፊት የምናሳውቅ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት,ባሕር ዳር

©የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ⬆️ይህ ከ56,000 በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡን ገፅ የዩኒቨርሲቲው ትክክለኛ ገፅ ነው። ይህንንም ከተማሪዎች ህብረት ተወካይ ማረጋገጥ ችያለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የትውልድ ከተማቸውን አጋሮን ጎብኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ‼️ በአዲስ አበባ ከተማ ነገ የሚደረግ እውቅና የተሰጠው ሰልፍ የለም። በከተማዋ ውስጥ ህገ ወጥ ሰልፍ በሚያደርግ ማንኛውም አካል ላይ ፖሊስ #እርምጃ እንደሚወስድ #አስጠንቅቋል። በመሆኑም ውድ የTIKVAH-ETH ተከታዮች እና የተከታዮቻችን ወዳጆች በሙሉ በየትኛውም አይነት ህገ ወጥ ሰልፍ ላይ እንዳትሳተፉ #አጥብቀን እንመክራለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

50 ሽጉጦች በህገ ወጥ መንገድ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲል በእንጦጦ ኬላ #በቁጥጥር ስር መዋለቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል አባላት ናቸው በሰሜን አደስ አበባ በኩል ወደ መዲናዋ ሊገቡ የነበሩ ሽጉጦቹን በቁጥጥር ስር ያዋሉት።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችም 50 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ መሆናቸውንም የፌደራል ፖሊስ ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል።

አንደ ፖሊስ ገለጻ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩት ሽጉጦች የተያዙት ኬላ ላይ በነበረው ፍተሸ ነው።

ምንጭ ፦የፌደራል ፖሊስ ኮሙዩኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኮምቦልቻ መጠነኛ አለመረጋጋት እንዳለ እየተሰማ ይገኛል። ያለውን ሁኔታ ተከታትዬ አደርሳችኋለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ⬆️የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ በዛሬው እለትም ቀጥሎ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ይገኛል።

©fbc
@tikvahethiopia @tsegabwolde