TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ደረሰኝ

🔴 " ከዛ ቤት የሚወጣ እቃ ደረሰኝ አያውቅም ይሄንን ሳታውቁ ቀርታችሁ አይደለም። ቻይኖቹን ፈርታችሁ ይሁን ምን ይሁን እኛ አይገባንም " - የውይይት ተሳታፊ

🟠 " የ1 ሚሊዮን ብር እቃ ገዝታችሁ የ300 ሺህ ብር ደረሰኝ ነው የሚፅፉት (ይህ ምሳሌ ነው) " - የውይይት ተሳታፊ

🔵 " ከቻይኖች (ከፋብሪካዎች) ጋር የተነሳው ጉዳይ ከፌዴራልም ጋር በነበረን መድረክ ተነስቷልግብረኃይልም ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል " - የአ/አ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

👉 " ያለ ደረሰኝ ግብይት ፈጽማችሁ የምትገኙ ከሆነ በ100 ሺህ ብር ቅጣት ብቻ አናልፍም ! "

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም የተነሳ ከአሰራር ጋር ተያይዞ ከነጋዴዎች በኩል አንዳንድ ቅሬታዎች መደመጣቸው አይዘነጋም።

በተለይ ታች ያለው ነጋዴ " ጉዳዩ ስር የሰደደ ነው ከላይ ጀምሮ መጥራት አለበት። መቼ ፋብሪካዎች፣ አስመጪዎች ፣ አምራቾች አከፋፋዮች ደረሰኝ ይሰጡናል ፤ ዝም ብለው አይደል የሚያወጡት መጀመሪያ እነሱን መቆጣጠር አለባችሁ " የሚሉ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር።

ከቀናት በፊት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢንያም ምክሩን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ከአስመጪዎች እና አከፋፋዮች ጋር ውይይት ተካሂዶ ነበር።

አንድ የውይይቱ ተሳታፊ " እኛ ፎሬይን ዳይሬክት ኢንቨስትመንት አይተግበር እያልን አይደለም ነገር ግን ዱከም ኢንዱስትሪ ዞንን ዞር ብላችሁ ያያችሁትም አይመስለኝም ፤ እኔ አሁን አሁንማ የሌላ ሀገር እየመሰለኝ መጥቷል። እሱ ቦታ ከዛ ቤት የሚወጣ እቃ ደረሰኝ አያውቅም ይሄንን ሳታውቁ ቀርታችሁ አይደለም። ቻይኖቹን ፈርታችሁ ይሁን ምን ይሁን እኛ አይገባንም " ብለዋል።

" ግራ እየገባን ነው እኛ ሀገራችን ነው ብንሰርቅም እዚሁ ነው የምንጥለው የሆነ ሰዓት መገኘታችን አይቀርም እነሱ ግን ሀገራቸው አይደለም ሰርቀው ይዘውት ነው የሚሄዱት " ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላ ተሳታፊው " በኢስት ኢንዱስትሪ ዞን ያለው ነገር ግልጽ ነው ይሄ ለናተ ተደግሞ መነሳትም ያለበት ነገር አይደለም ፤ የ1 ሚሊዮን ብር እቃ ገዝታችሁ የ300 ሺህ ብር ደረሰኝ ነው የሚፅፉት (ይህ ምሳሌ ነው)" ብለዋል።

" በአንድ ደረሰኝ ከ20 እና 30 በላይ መኪና ይመላለሳል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ኢንቨስትመንቱ ሁሉም ነገር እንዳለ ሆኖ ግን ሀገራችን ላይ እናተ በአቅማችሁ ደረጃ ማኔጅ ማድረግ የማትችሉትን ነገር ነው መሰለኝ እየፈቀዳችሁ ያላችሁት ለፎሬይን ኢንቨስትመንት ምክንያቱም ከውጭ ፌሬይን ኢንቨስትመንት ይግባ ሲባል ያንን ማኔጅ ማድረግ እንችላለን ወይ ? የሚለው ጥያቄ አብሮ መመለስ አለበት ካልሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል እንደ ሀገር ። እዛ ላይ የሚመለከተው አካል ይስራበት " ሲሉ አክለዋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ የከተማው ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ቢንያም ምክሩ ሃሳባቸውን ሰጥተው ነበር።

" የተነሳው ትክክል ነው እኛም እናውቀዋለን " ብለዋል።

" ከቻይኖች ጋር የተነሳው ጉዳይ ከፌዴራልም ጋር በነበረን መድረክ ተነስቷል። ከዚህ ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሚፈታ በክብርት ሚኒስትሯ የሚመራ የፌዴራል ገቢዎች ፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ኦሮሚያ ክልል መንግሥትን ያቀፈ አንድ የጋራ ቅንጅት የሚመራበት ማንዋል ፀድቆ ወደ ስራ ተገብቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ የኢስት ኢንዲስትሪ ዞንና ሌሎች ጋር የተገናኙ ወደ ከተማው የሚገባ ምርት በሸገር ከተማ ዙሪያ የሚመረቱ ነገር ግን ያለደረሰኝ ከፋብሪካ የሚወጡትን እዛ ያለው አዲስ የተቋቋመው ግብረኃይል ይከታተለዋል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊው በመርካቶም ሆነ በሌላ የከተማው አካባቢ የሚካሄደው የደረሰኝ ቁጥጥሩ ወቅታዊ ሳይሆን በዘላቂነት የሚሰራበት ነው ብለዋል።

ከአሰራር ጋር በተያያዘ ያሉት ችግሮች እንደሚፈቱ ቃል ገብተው ለአስመጪና አስከፋፋዮች ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ኃላፊው ፤ " ከዚህ በኃላ በግልጽ ልንነግራችሁ የምንፈልገው አስመጪ እና አከፋፋይ የሆናችሁ ያለ ደረሰኝ ግብይት ፈጽማችሁ የምትገኙ ከሆነ በ100 ሺህ ብር ቅጣት ብቻ አይደለም የምናልፈው " ብለዋል

" በቀጥታ የኦዲት ምርመራ (Investigation Audit) ውስጥ ነው የምንገባው ይህ ደግሞ በጣን ክፉኛ ይጎዳችኋል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" መርካቶ ውስጥ ያለ ድረሰኝ ግብይት ሙሉ ለሙሉ መቆም አለበት " ያሉም ሲሆን ከጊዜ ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ጥያቄ " ለዝግጅት የሚሰጥ ጊዜ የለም ቁጥጥራችን ይጠናከራል "  ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

ጊዜ እና ገንዘባችን ሳይባክን በM-PESA ያለምንም ክፍያ ብር በመላክ ነጻ አገልግሎታችንን እናጣጥም!

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
 
#FurtherAheadTogether
🇪🇹 ማጀስቲክ ትሬዲንግ 🇪🇹

ለቢሮ፤ ለሆቴል፤ ካፌዎች ለተለያዩ የንግድ ሱቆች እና ለመኖሪያ ቤቶች የሚሆኑ ፡-
-Design-Built - Interior Design -Woodworking - Finishing works
-Furniture (Office Furniture's , Sofas ,Beds) - IT and System - Consulting

በማንኛውም ጊዜና ቦታ ካሉበት ሆነው ምን ማሰራት እንደሚፈልጉ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ባለሙያዎቻችንን ያማክሩ፡፡ ቁልፍ ሰተው ቁልፍ የሚረከቡበት አገልግሎት።
Contact :-
+251901288882 - +251901919991
+251901911111 - +251911253679/89

TikTok:- Majestic Trading Website:- https://www.majestictradingplc.com
አድራሻችን፡-
📍Dembel New building, 2nd floor
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጽዮንማርያም የ2017 ዓ/ም የአክሱም ህዳር ፅዮን ሃይማኖታዊ በዓል ከነገ በስቲያ ህዳር 21 ይከበራል። የትግራይ ባህልና ቱሪዝምና ቢሮ ፤ " በቅድስት የአክሱም ከተማ እና በሌሎችም የክልሉ አከባቢዎች የህዳር ፅዮን በዓል የሚያከበሩ ገዳማት ቱሪዝምን በማነቃቃት የበኩላቸው አስተዋፅኦ አላቸው " ብሏል። ቢሮው ፤ ህዳር 21 የአክሱም ፅዮን በዓልን ለሚያከብሩ ሁሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል። ህዝቡ በዓሉ…
የአክሱም ፅዮን በዓል !

" አክሱም ፍፁም ሰላም ናት ፤ ለአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የሚያውክ የፀጥታ ስጋት የለም " - የአክሱም ከተማ ከንቲባ አበበ ብርሃነ

ዓመታዊው የአክሱም ህዳር ፅዮን 2017 ዓ.ም በዓል በልዩ ድምቀት መከበሩን አክሱም የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።

በዓሉ ለመታደም ከቅርብ እና ከሩቅ የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ምእመናትና ጉብኚዎች ተገኝተው ነበር።

በዓሉ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁም ታውቋል።

አክሱም ከተማ እጅግ ደምቃለች።

ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ግን ወደ አክሱም የሚደረግ የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ልክ በዓሉ ሲቃረብ መጨመሩ በርካቶችን እንዳስከፋ ከበዓሉ ታዳሚዎች ለመረዳት ችለናል።

የዋጋ ጭማሪው ከተጓዦች ባለፈ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔዎች መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን በጉዳዩ ላይ እንደሚነጋገሩበት ለመረዳት ተችሏል።

በሌላ በኩል ፤ ካለፉት የአከባበራ ዓመታት በተለየ መልኩ ዘንድሮ በበዓሉ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ የተገኘ ከፍተኛ የመንግስትም ሆነ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር  የለም።

በአክሱም የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከበዓሉ አዘጋጆች ጠይቆ ባገኘው መረጃ ፤ ለሁለት የተከፈሉት የህወሓት አመራሮች በበዓሉ መልእክት እንዳያስተላልፉ መከልከላቸውን አረጋግጠዋል።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በ X ገፃቸው ፤ የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በፌስኩክ ገፃቸው " የእንኳን አደረሳችሁ !! " መልእክት አስተላልፈዋል።  

ዛሬ በተከናወነው ደማው የበዓል ስነስርዓት የአክሱም ከተማ ከንቲባ አበበ ብርሃነ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

" ስጋት ያንዣበበባቸው የአክሱም ሀውልቶች የመጠገን ስራ ተጀምረዋል " ያሉ ሲሆን ጅምሩ ከጫፍ እንዲደርስ የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ የቅርሶች ተቆርቋሪ ተቋማት ድጋፋቸው እንዲቸሩ ጠይቋል።

" አክሱም ፍፁም ሰላም ናት፣ ለአገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች የሚያውክ የፀጥታ ስጋት የለም " ያሉት ከንቲባው " በትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ላይ የሚደረገው ስም የማጥፋት ዘመቻ በመከላከል ህዝቡ የበኩሉ እንዲወጣ " ሲሉ አደራ ብለዋል።

በዋዜማ እና በዋናው የበዓሉ ዕለት በ14 ቤተ መቅደሶች በአበው ጳጳሳት የተመሩ የቅዳሴ ፣ የስብከት እና የመዝሙር ስነ-ሰርዓቶች ተከናውነዋል።

ከታሪካዊቷ ዓድዋ በ25 ኪ/ሜ ፣ ከእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ በ60 ኪ/ሜ ርቀት የምትገኘው ቅድስት እና ታሪካዊትዋ የአክሱም ከተማ በውስጥዋ እና በዙሪያዋ በቱሪስት መስህቦች የበለፀገች ናት።
- የታቦተ ፅዮን ማድሪያ
- የበርካታ ሀውልቶች መገኛ 
- የማህሌታይ ያሬድ የሙዚቃ ኖታ እና የፈላስፋ ዘርዓያዕቆብ ማህደር
- የኢትዮጵያ ፊደላት ፣ ቁጥር ፣ የግእዝ ቋንቋና  የዘመን አቆጣጠር ያበቀለች
- የኢትዮጵያ የኪነ-ህንፃና ስነ-ፅሁፍ መፍለቂያ
- የነገስታት መቃብር
- የተለያዩ የእጅ ጥበብ ውጤቶች
- ጥንታዊ ሙዝየሞችና ሌሎች መገኛ ናት አክሱም። 

እንዲሁም በአርኪሎጂስቶች ግኝት መሰረት ከአክሱም ከተማ ቀድሞ መመስረቱ የሚነገርለት በእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ አጠገብ የማይ አድራሻ ጥንታዊ ከተማ ፤ ነጮች የተሸነፉበት የዓድዋ እና የተምቤን ወርቃኣምባ ታሪካዊ ተራራዎች ከአክሱም ከተማ በቅርብ ርቀት ይገኛሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyAxum

ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" በተፈጸመባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታለች፤ የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " - የቤተሰብ አባል በኦሮሚያ ክልል ፣ በምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ' የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም ' በሚል ከዛፍ ጋር ታስራ በባለቤቷ ክፉኛ የተደበደበችና የተገረፈች የ3 ልጆች እናት በአስጊ ጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የቤተሰብ አባሏ ተናገሩ። በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ የምትገኘው…
" ባለቤቷን ጨምሮ ታስራ እንድትደበደብ ውሳኔ ያሳለፉ ሽማግሌዎች የፍርድ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል " - የወረዳው አቃቤ ሕግ

በምስራቅ ቦራና በውጫሌ ወረዳ የ3 ልጆች እናት የሆነችውን ገበያ መሀል አስረው ግርፋት የፈጸሙ ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸው ተገልጿል።

ወ/ሮ ኩሹ ቦናያ በገበያ ቦታ ላይ ከዛፍ ጋር ታስራ በባለቤቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮ ከታየ በኋላ በርካቶችን ማስቆጣቱ ይታወሳል።

ይህ ግርፋት የተፈጸመው ደግሞ በአካባቢ ሽማግሌዎች ትዕዛዝ ሲሆን፣ የታሰረችውም በርካታ ሰዎች ቆመው በሚያዩበት የገበያ ስፍራ ነበር።

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የዋጪሌ ወረዳ ፍርድ ቤት ድርጊቱን በመፈፀም እና በመተባበር የተከሰሱ አራት ግለሰቦች ላይ ሕዳር 19 /2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ከ7 እስከ 4 ዓመት የሚደርስ እስራት ወስኗል።

የወረዳው አቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ ጉያ አሬሮ ምን አሉ ?

" ጥቃቱን በመፈጸም የመጀመሪያ ተከሳሽ ሆኖ የቀረበው ድብደባውን የፈጸመው ባለቤቷ ጋልጋሎ ዋሪዮ ነው።

ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሳሾች ታስራ እንድትደበደብ ውሳኔ ያሳለፉ ሽማግሌዎች ናቸው።

በዚህም መሰረት አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሽ በ6 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።

ሦስተኛው ተከሳሽ የሆኑት የአካባቢ ሽማግሌ ከዛፍ ጋር ታስራ እንድትገረፍ ብቻ ሳይሆን፣ ከግርፋቱ በኋላም ታስራ እንድትቆይ በመወሰናቸው 7 ዓመት ከ2 ወር እስራት ተፈርዶባቸዋል።

አራተኛው ተከሳሽ የቃቃሎ መንደር የሰላም እና ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ናቸው።

ሽማግሌዎቹ በግርፋት እንድትቀጣ ሲወስኑ ሚስትየው ወደዚህ ግለሰብ ሄዳ ጣልቃ እንዲገባ እና እንዲያስቆም ብትጠይቅም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ተበዳይ በወቅቱ ኃላፊውን ' አንተ የሕግ ሰው ነህና አስቁምልኝ ' ስትል ብትጠይቃቸውም ' በፍርዳቸው ጣልቃ መግባት አልችልም ' በማለት መልሷል።

ድብደባ ከተፈጸመባት በኋለ ' ሚሊሻዎቹ ሴትዮዋን ይዘው ወደ ማቆያ ጣቢያ እንዲወስዷት አዟል ' በሚል በሁለት ወንጀል ተከሷል።

በግለሰቡ ላይ ፍርድ ቤት የ4 አመት እስራት እና 5ሺህ 500 ብር እንዲከፍል የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል " ብለዋል።

ተበዳይ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች ?

ስለ ወቅታዊ ሁኔታ የተጠየቀው የወረዳው አቃቤ ሕግ በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላት መሆኑ አሳውቀዋል።

" አሁን በሕክምና ሕይወቷን ማትረፍ ተችሏል " ብለው  በጥሩ ጤንነት ላይ መሆኗን እና ብይኑ ሲሰጥም በችሎቱ ላይ መገኘቷን ተናግረዋል።

የ3 ልጆች እናት የሆነችውን ሴት የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም በሚል ዋጪሌ ገበያ ላይ አስሮ የመግረፉ ድርጊት የተፈጸመው መስከረም 9/ 2017 ዓ.ም. ነበር።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል ነው።

ፎቶ / ቪድዮ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል።

አቶ ግርማ ሰይፉ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ተነስተው የከተማ ውበትና አረንጏዴ  ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል

ወ/ሮ ቆንጂት ደበለ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዋል።

ከዚህ ባለፈ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ⁠ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዋል።

ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ከከተማ ውበትና አረንጏዴ  ልማት ቢሮ ኃላፊነት ተነስተው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል።

አቶ ሙባረክ ከማል የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ፤ አቶ ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

አቶ ታረቀኝ ገመቹ ደግሞ የንግድ ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ⁠ ሆነዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" አየር መንገዱ ላደረገው ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ  ማብራርያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በክልሉ ትራንስፓርት እና መገናኛ ቢሮ በኩል ባወጣው መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም ህዳር ፅዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመሳተፍ በተጓዙ ወገኖች ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል አለ።

ይኸው የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ " ኢ-ፍትሃዊ እና አስደማሚ ነው " ብሎታል።

ቢሮ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ለፌደራል የትራንስፓርት ሚንስቴር በፃፈው ድብዳቤ እንደጠቆመው፤ " ተቋሙ የፈፀመው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ታማኝነቱ ጥያቄ ውስጥ ከማስገባት ባለፈ ሌላ ፓለቲካዊ መልክ የሚያስይዝ ነው " ሲል አብራርተዋል።  

ስለሆነም የበደላቸው ተጓዥ ደንበኞቹ እንዲክስ ፣ እንዲደግፍና ተግባሩ እንዲፈፅም ምክንያት የሆነውን በቂ ማብራርያ ለህዝብ እንዲሰጥ ቢሮው ጠይቋል።

ከአክሱም ህዳር ፅዮን በዓል ተጓዥ ተሳታፊዎች ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያደረገው የትኬት ጭማሪ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ካቢኔ መወያያ አጀንዳ እንዳደረገው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia