TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SafaricomEthiopia

ይጋብዙ ፣ ይሸለሙ ! የመጀመሪያ ተሸላሚዎቻችን ሽልማታቸውን ተረክበዋል 🎁 👉🏽@sosi0076, @habt0713, @Seifegebriell

ከእናንተ የሚጠበቀው የሳፋሪኮም መስመራችሁን በመጠቀም ከላይ የተጠቀሱትን ቅደም ተከተሎች መተግበር ነው🫰🏽 ያስተውሉ 👉🏽 በእርስዎ ጋባዥነት የሚቀላቀለው ሰው ቁጥር ሲጨምር የሽልማቱም መጠን እየጨመረ ይሄዳል 😱 እንዲሁም ተጋባዦቻችሁ ገፁን ከተቀላቀሉ በኃላ “back” የሚለውን ተጭነው “check subscription” እንዲያደርጉ ያሳስቡ 💥

የቴሌግራም ቻናላችን 👉🏽 https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://t.iss.one/official_safaricomet_bot

መልካም እድል 🎁

#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#ሴጅ_ማሰልጠኛ

የጋዜጠኝነት ስልጠና በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር ምዝገባ ላይ ነን።   
በስልጠናው፦
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሖች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና ዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube journalism አካቷል፡፡
👉 በተጨማሪም የስራ ላይ ስልጠና (Internship) አካቷል፡፡ ስልጠናው ለ6 ወር የሚቆይ ሲሆን በቅዳሜና እሑድ መርሐግብር ይሰጣል።

ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
" ህፃናት አደጋ ደርሶባቸው በቀርቀሃ ተጠፍረው ታስረው ፤ እየጮኹ እግር እና እጅ ያጡ አሉ ፤ ...ህዝቡን አደራ የምለው የአጥንት ህክምና አለ፤ ሂዱና ታከሙ " - ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ

የኢትዮጵያ አጥንት እና መገጣጠሚያ ሃኪሞች ማህበር (ESOT) ያደራጀው " BOne Setting Associated Disability (BOSAD) " አገር አቀፍ የጥናት እና ምርምር ቡድን ከሰሞኑን አመታዊ የምርምር ግምገማ መድረክ አካሂዶ ነበር።

በዚህ መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ስፔሻሊስት የሆኑት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ ተገኝተው ነበር።

ፕሮፌሰር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ በሃገራችን ከአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳቶች ጋር በተያያዘ በማህበረሰቡ እንደ አንድ የህክምና አማራጭ የሚወሰደው የባህል ህክምና (ወጌሻዎች የሚሰጡት) ዘርፈ ብዙ የጤና ችግሮችን እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ጤና ተቋም ከመሄድ ይልቅ ወደ ወጌሻዎች እንደሚሄዱ የገለጹት ፕሮፌሰር " በዚህም አካል መቆረጥን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳቶችን ያስተናግዳሉ። ህፃናት ደግሞ ተጋላጭ ናቸው " ብለዋል።

" ባለፉት 10 አመታት በየጊዜው እጅ እና እግር በየቦታው የሚቆረጡትን (በተለይ ህፃናት) መደበኛ ዳታ ቤዝ ላይ እንሰበስባለን። ቁጥራቸው አራት ሺ፤ አምስት ሺ አልፏል። ይሄ ከባድ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" አንዳንዶቹ ምንም ያልተሰበሩ ምንም ያልሆኑ ናቸው ። ህፃናት በቀርቀሃ ተጠፍረው ታስረው፤ እየጮኹ 'ዝም በሉ' እየተባሉ በዚህ ምክንያት ብዙዎች እግር እና እጅ አጥተው ቤት ቁጭ ብለዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የአጥንት ህክምና ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ እንዳለ ፕ/ር ብሩክ የተናገሩ ሲሆን " ህዝቡን አደራ የምለው አጠገባችሁ የአጥንት  ህክምና አለ። ሂዱና ታከሙ " ነው ያሉት።

በአገሪቱ ከባድ ስብራት የሚታከምበት 55 ሆስፒታል እንዳለም ፕ/ር ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የአጥንትና መገጣጠሚያ ጉዳት ደርሶባቸው ' በባህል ህክምና ታክመዋል ' ከተባሉት ታማሚዎች ዉስጥ 77 በመቶዎቹ የጎንዮሽ ጉዳት እንደሚገጥማቸው የቦሳድ ጥናት ማሳየቱን የጠቀሱት ፕሬፌሰር " ይህንን ወደ ተወካዮች ምክር ቤት ወስደን፣ አጀንዳ እናስይዛለን " ብለዋል።

በጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢሉባቦር ቡኖ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በጉዳዩ ላይ የተሰሩት ጥናቶች ለፓርላማ ይቀርባሉ ብለዋል።

" ደምብም መውጣት ካለበት መመሪያም እስከማውጣት እንሄዳለን ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ገልጸዋን።

" ደምብ እና መመሪያ መውጣቱ ብቻ ችግሩን አይቀርፍም ፤ ማህበረሰቡ የአጥንት ህክምናን ለማግኘት ወደ ጤና ተቋም እንዲሄድ ትልቅ ግንዛቤ መፈጠር አለበት " ብለዋል።

የባህል ህክምና የሚሰጡትን (ወጌሻዎችን) ማሰልጠን፣ ጉዳት የሚያደርሱትንም እንዲያቆሙ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው በጉዳዩ ላይ ውይይት ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
በሶማሊያ ያለው ከፍተኛ ውጥረት ወዴት ያመራ ይሆን ?

የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ መንግሥት አሕመድ ማዴቦ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። የጁባላንድ መንግሥት ደግሞ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አውጥቷል።

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ ራስገዝ አስተዳደር መሪዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ሰንበትበት ብሏል።

ምክንያት ?

በአገሪቱ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየውን ክልላዊ የውክልና ምርጫ በማስቀረት አገራዊ ምርጫ እንኪካሄድ የፌደራል መንግሥቱ መወሰኑን ተከትሎ ነው።

የጁባላንድ መሪዎች ይህ ውሳኔ የአገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚጥስ ነው በማለት በቅርቡ በተናጠል ክልላዊ ምርጫ አድርገዋል።

በዚህ ምርጫ አሕመድ ሞሐመድ ኢስላም (አሕመድ ማዶቤ) በመሪነት ተመርጠዋል። ለ3ኛው ጊዜም ነው ያሸነፉት።

ከዛስ ምን ተፈጠረ ?

በፌዴራሉ መንግሥት እና በጁባላንድ መንግሥት መካከል ውጥረቱ እያየለ መጥቷል።

የፌዴራሉ መንግሥት ወታደሮቹን " ራስ ካምቦኒ " ወደተባለችው ኬንያ ድንበር ላይ በምትዋስን ከተማ ላይ አስፍሯል።

ፌደራል መንግሥት ጦሩን ማደራጀቱን የተመለከቱት የጁባላንድ ወታደሮችም ለሚፈጸም የፌደራል መንግሥቱን ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በተጠንቀቅ ቆመዋል።

አሁን ደግሞ ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ የሚመሩት ማዕከላዊ መንግሥት የጁባላንድ መሪው አሕመድ ማዶቤ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።

በምላሹ የጁባላንድ መንግሥት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ የእስር ማዘዣ አጥቷል።

ኦብነግ ምን እያለ ነው ?

እዚህ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) በጁባላንድ ያለው ውጥረት " አሳሰበኝ " ብሏል።

" እየተቀሰቀሰ ያለው ቀውስ የጁባላንድን እና አጠቃላዩን የሶማሊያ ቀጣናን መረጋጋት ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚጥል ነው " ብሏል።

" እየተባባሰ የመጣው መቃቃር የንጹሃንን ሕይወት አደጋ ላይ መጣል ብቻ ሳይሆን አፍራሽ ኃይሎች ሁኔታውን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመውሰድ በቀጣናው ደኅንነት እና ልማት ላይ ተጽዕኖ ሊያደርሱ ይችላሉ " ሲልም ገልጿል።

በሶማሊያ ወገኖች መካከል ያለው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ይፈታል የሚል እምነት እንዳለውም ገልጿል።

የመረጃ ምንጭ ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#ጽዮንማርያም

የ2017 ዓ/ም የአክሱም ህዳር ፅዮን ሃይማኖታዊ በዓል ከነገ በስቲያ ህዳር 21 ይከበራል።

የትግራይ ባህልና ቱሪዝምና ቢሮ ፤ " በቅድስት የአክሱም ከተማ እና በሌሎችም የክልሉ አከባቢዎች የህዳር ፅዮን በዓል የሚያከበሩ ገዳማት ቱሪዝምን በማነቃቃት የበኩላቸው አስተዋፅኦ አላቸው " ብሏል።

ቢሮው ፤ ህዳር 21 የአክሱም ፅዮን በዓልን ለሚያከብሩ ሁሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል።

ህዝቡ በዓሉ ለአገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች ያለው አስተዋፅኦ በመገንዘብ በየአከባቢው የሚገኙ ቅርሶች በመንከባከብና ትውፊታዊ መልኩ በጠበቀ መልኩ በዓሉ እንዲያከብር ጥሪ አስተለልፏል።

በርካታ ምእመናን ቅዳሜ ለሚከበረው በዓል ወደ አክሱም እየተጓዙ ይገኛሉ።

ለበዓሉ ሁሉም አይነት ዝግጅቶች መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ወደ ስፍራው እየተጓዘ ሲሆን በከተማው ከደረሰ በኃላ ያለውን የበዓል መረጃዎችን ያካፍላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሶማሊያ ያለው ከፍተኛ ውጥረት ወዴት ያመራ ይሆን ? የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ መንግሥት አሕመድ ማዴቦ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። የጁባላንድ መንግሥት ደግሞ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አውጥቷል። በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ ራስገዝ አስተዳደር መሪዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ሰንበትበት ብሏል። ምክንያት ? በአገሪቱ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየውን ክልላዊ…
#Update

የጁባላንድ መንግሥት ከሶማሊያ ፌዴራሉ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ይፋ አደረገ።

የጁባላንድ ካቢኔ ስብሰባ ካደረገ በኃላ ይፋ እንዳደረገው  " ሙሉ በሙሉና በይፋ ከሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን የስራም ሆነ ማንኛውንም ግንኙነት " አቋርጧል።

የጁባላድ መንግሥት ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድን ፦
- ኃይላቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም
- የእርስ በእርስ ጦርነት በማነሳሳት
- ሰራዊትን በማውደም
- በሙስና ... ከሷል።

ሕገመንግስቱን በማጣስ ወንጅሎም " በፌዴራል መንግሥት የተደረጉ የሕገመንግስት ማሻሻያዎችን አንቀበልም " ሲል አሳውቋል።

ቀደም ሲል የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ መንግሥት በጁባላንድ ፕሬዝዳንት አሕመድ ማዴቦ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።

የጁባላንድ መንግሥት በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ የእስር ትዕዛዝ በማውጣት አፀፋውን መልሷል።

በፌዴራል መንግሥቱ እና በጁባላንድ መንግሥት መካከል ውጥረቱ መባባሱ ተሰምቷል።

NB. ባለፈው አመት የፑንትላንድ መንግሥት ከማዕከላዊው የሶማሊያ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

ዲኤስቲቪ ሁሉንም የእግር ኳስ ውድድሮችን ባንድ ላይ ማግኘት የሚያስችል አዲስ የሜዳ ስፖርት ፓኬጅ አቀረበ

ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ለተመልካቾች በማቅረብ የሚታወቀው ዲኤስቲቭ አዲስ የስፖርት ፓኬጅ አቅርቧል።

አዲሱ የዲኤስቲቪ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅ በሜዳ እና በሜዳ ፕላስ ፓኬጆች መካከል አንዱ ተጨማሪ ፓኬጅ በመሆን ይፋ ሆኗል።

የእግር-ኳስ አፍቃሪያን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ የጣሊያን ሴሪ ኤ እና ላ ሊጋን ጨምሮ ሌሎች የእግርኳስ ይዘቶችን እንዲሁም አለም አቅፍ ተከታታይ ፊልሞችን እና ሃገርኛ ድራማዎችን እና መዝናኛዎችን በአቦል ቲቪ እና በማዲ አቦል ቻናሎች- ሁሉንም በአንድ ላይ በሜዳ ስፖርት ፓኬጅ መቅረቡ ተገልጿል።

ሁሉንም የእግር ኳስ ውድድሮችን ባንድ ላይ እንዲያገኙ ተደርጎ የተዘጋጀው ይህ የሜዳ ፓኬጅ በወር በ1 ሺህ 699 ብር ያስከፍላል ተብሏል።

አዲሱ የዲኤስቲቪ ፓኬጅ - ሜዳ ስፖርት ከሕዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለደንበኞች ቀርቧል።
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ወንጀል ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ ገፁ በሰጠው ማብራርያ ፤ " ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 :00 ሰዓት አካባቢ ከአክሱም ወደ መቐለ ከተማ በመኪና በመጓዝ ላይ የነበሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ የሚያጣራ ቡድን ተቋቁመዋል…
#Tigray

በቅርቡ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው የተናገሩት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ በአዲስ አስተዳዳሪ ተተኩ።

ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ፤ ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ በተባሉ አዲስ አስተዳዳሪ ነው የተተኩት።

አዲሱ የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ህዳር 18 / 2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ መተካታቸው ለማወቅ ተችላል።

በአቶ ሰለሞን መዓሾ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ የትግራይ ክልል ፓሊስ እያጣራሁት ነው ማለቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#ጥቆማ

እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኘውን የ " The Earthshot Prize 2025 " ኢትዮጵያውያን እንዲወዳደሩ ጥሪ ቀረበ።

በእንግሊዝ ልዑል ዊሊያምና ሮያል ፋውንዴሽን በፈረንጆቹ 2020 የተቋቋመውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአካባቢና አየር ብክለት የፀዳ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያበረክትና ለተፈጥሮ ተስማሚ የሆነ ስራ እየሰሩ ያሉ ተቋማትን ፣ የቢዝነስ ፈጠራ ባለሙያዎችን (ኢንተርፕረነሮችን) ወይም ግለሰቦችን የሚሸልመው " The Earthshot Prize 2025 " የዘንድሮ እጩ ተወዳዳሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

በአፍሪካ የውድድሩ ዋና አጋር መልቲቾይስ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

በ5 የተለያዩ ምድቦች የሚካሄደው ይህ ዓመታዊ ሽልማት ላይ በተለይ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑና ተፈጥሮን የማይበክሉ ቢዝነሶችን የሚያንቀሳቅሱ ኢትዮጵያውያን  መሳተፍ ይችላኩ።

ውድድሩ እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኝ ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቶቻቸውን ለማስፋፋትና እየተባባሰ ለመጣው የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ እንዲያበረክቱም ያግዛል።

መልቲቾይስ አፍሪካ ፤ በደቡብ አፍሪካ በተከናወነው የ2024 ውድድር ከጋና " ግሪን አፍሪካ ዩዝ ኦርጋናዜሽን " እንዲሁም ከኬንያ " ኪፕ ኢት ኩል" የተሰኙ የአረንጓዴ ጉዳይ አቀንቃኞችና የሥራ ፈጣሪዎች አሸናፊ እንደሆኑ አስታውሷል።

ለዚህ ዓመቱ ሽልማት ማመልከት የሚቻለው እስከ ፈረንጆቹ ዲሴምበር 04 / 2024  ሲሆን ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እና ተቋማት  በ https://www.multichoice.com/earthshot-nomination.php#prId=324466  እንዲያመለክቱ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopia

Via @TikvahethMagazine
" ምን ያልተጎዳ አለ፣ አገሩ በሙሉ ነው የተጎዳው " - ሰብላቸው የተጎዳባቸው አርሶ አደር

ሰሞኑን በአማራ ክልል ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አቅራቢያ የጣለው ከባድ ዝናብ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን አርሶ አደሮች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ 700 የሚጠጉ አርሶ አደሮች ሰብላቸው ወድሟል።

ዝናቡ በደረሱ የስንዴ ፣ የቦቆሎ ፣ የገብስና ሌሎች አዝርዕቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

ለእንሳቱ የሚሆን ቀለብ እንኳ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ወድሟል።

እንስሳቱም ለርሀብ መጋለጣቸውን አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።

ከ600 በላይ አባዎራዎችም ለችግር ተዳርገዋል።

ቃላቸውን የሰጡ አርሶ አደሮች ሕዳር 14 ቀን 8 ሰዓት ጀምሮ ከ30 ደቂቃ በረዶ ቀላቅሎ በዘነበው ከባድ ዝናብ " በገብስ፣ ባቄላና ጤፍ ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል " ብለዋል።

ከዛሬ ነገ የደረሰውን ሰብል በደቦ ለመሰብሰብ እየተዘጋጁ በነበረበት ወቅት ነው ድንገት የዘነበው ዝናብ ውድመት ያደረሰው።

በዝናቡ ሰብላቸው ከተጎዳባቸው አርሶአደሮች መካከል አቶ ቢራራ ሁነኛው "... የደረሰ ባቄላና ገብስ ነበረኝ፣ በጣም ጉዳት ደርሶበታል፣ ምን ያልተጎዳ አለ፣ አገሩ በሙሉ ነው የተጎዳው " ብለዋል።

በጉዳቱ 10 ኩንታል ምርት የወደመባቸው ሌላው አርሶአደር ዝናቡ ባልተጠበቀ መንገድ ጉዳት አድርሷል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

ፎቶ ፦ ኤኤምሲ

@tikvahethiopia