TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ

ባለፈው ሳምንት በትግራይ 2 ወረዳዎች የነበረውን ሃይለኛ ዝናብን ተከትሎ በተፈጠረው ከባድ ጎርፍ የ3 ሰው ህይወት ጠፍቷል።

በክልሉ ምስራቃዊ  ዞን ጉሎመኸዳ ወረዳ አዲስ ተስፋ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ደንጎሎ መንደር ነሃሴ 16/2016 ዓ.ም ሌሊት የዘነበው ከባድ ዝናብ ቤት አፈርሶ የአንድ ሰው ህወይት አሳጥቷል።

እሁድ ነሃሴ 19/2016 ዓ.ም በደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሕንጣሎ ወጀራት ወረዳ ዓዲ ቐይሕ ከተማ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ሃይለኛ ጎርፍ የ2 ህፃናትን ህይወት ቀጥፏል።

በደቡባዊ ዞን የሰለዋ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር  ያጋጠመው የመሬት መደርመስ አደጋ በርካቶች አፈናቅሏል።

ተፈናቃዮቹ የመጠለያ ፣ የምግብና ሌሎች መሰረታዊ ነገሮች እገዛ ባለማገኝታቸው ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፥ የተከዘ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ሙላትን ለመቀነስ አልሞ የተለቀቀ ውሃ ከተፋሰሱ በታች በሚገኙ አከባቢዎች ጉዳት አድርሷል።

በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የታሕታይ አድያቦ ወረዳ እንዳስታወቀው ውሃው በሰፋፊ የአርሶ አደሮች መሬት የበቀለውን እህል በማጥለቅለቅ ከጥቅም ውጭ አድርጓል።

#ትግራይ #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#ትግራይ

በአንድ ሳምንት ብቻ የክረምቱ ከባድ ዝናብና ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የሰው ህይወት ጠፍቷል። አዝርእት ወድሟል። በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተወስደዋል። 26 አባወራዎች አፈናቅሏል።

በያዝነው ሳምንት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በከባድ ዝናብና ጎርፍ ከፍተኛ የተባለ አደጋ ደርሷል።

በአጠቃላይ 25 ሰዎች እንደሞቱም ተነግሯል።

በአፅቢ ወረዳ ያጋጠመው አደጋ ግን የከፋ ነው ተብሏል።

በአፅቢ ወረዳ " ስዩም ቀበሌ ገበሬ ማህበር " ሃይለኛ ዝናብ ቤት አፍርሶ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው አልፏል።

ቤቱ በውድቅት ሌሊት መፍረሱ አደጋውን የከፋ አደርጎታል።

ቤተሰባቸው ያጡ እማወራ እንዳሉት ፥ ባለቤታቸውና ሁለት ልጆቻቸው በአደጋው ምክንያት በማጣታቸው የመኖር ተስፋቸው ጨልሞ ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

የአደጋው ሰለባ የመኖር ተስፋቸው ዳግም እንዲያንሰራራ መንግስትና አቅም ያለው ሁሉ እንዲያግዛቸው ጥሪ አማቅረባቸውን ከዞኑ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተያያዘ በቀጠለው ሃይለኛ ዝናብና ከባድ ክረምት በተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መንሸራተት እየተስተዋለ ነው።

በአምባላጀ ፣ በእንትጮ ከተማ ዙሪያ ሃይለኛ ዝናብ ያስከተለው የመሬት መንሸራተት 31 ቤቶች አፍርሶ 31 ሄክታር መሬት ላይ የነበረውን አዝርእት ከጥቅም ውጭ በማድረግ ዘጠኝ አባወራዎች አፈናቅሏል።

እንስሳትም በጎርፍ ተወስደዋል። 

በመቐለ ዙሪያ የሚገኘው የገረብ ግባ ግድብ ከልክ በላይ ሞልቶ በመፍሰሱ ምክንያት በ 138 ሄክታር መሬት የተዘራ እህል ላይ ጉዳት አድርሷል።

በአደጋው የተጎዱ 270 የእንደርታ ወረዳ አርሶ አደሮች ጊዚያዊ  አስተዳደሩ ግብረ ሃይል አቋቁሞ እንዲያግዛቸው ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray🚨 በሓውዜን ወረዳ በተጣለ ተተኳሽ #የ4_ሰዎች ህይወት ጠፋ።   በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል። ሰኔ 1/2016 ዓ.ም በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ፤ ሓውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በፈነዳ ተተኳሽ የ4 ወገኖች ህይወት #ተቀጥፏል። ከአራቱ የአደጋው ሰለባዎች ሶስቱ የአንድ…
#ትግራይ

" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች ከ51 በላይ ወገኖች ሲቀጠፉ ፤ ከ286 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ሰለባ ሆኗል " - በትግራይ ማእከላይ ዞን የየጭላ አበርገለ ወረዳ የፀጥታ ፅ/ቤት

በትግራይ በነበረው አውዳሚ እና አሰቃቂ ጦርነት ወቅት ተቀብረው እና ተጥለው ያልመከኑ ተተኳሾች የንፁሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፍና አካል ማጉደል ቀጥለዋል።

በየጭላ አሸርገለ ወረዳ የእምባ ሩፋኤል ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ አርሶ አደር ባልመከነ ተተኳሽ 2 ልጆቻቸው ሲያጡ አንዱ ቆስሎ ተርፎላቸዋል።

ሌላዋ እናት ቁርስ አብልተው ለእንጨት ለቀማ የላኩዋቸው ልጆቻቸው አንዱ በተጣለ ተተኳሽ ሲሞት ሌላኛው የአካል ጉዳተኛ ሆኗል።

በጦርነቱ ወቅት በአከባቢው በነበረው የጦር መሳሪያ ዲፓ የቀሩ የተጣሉና የተቀበሩ በርካታ ያልመከኑ ተተካሾች መኖራቸው የጦቆሙት የጥቃቱ ሰለባዎች ፤ በሰው እና በእንስሳ ከፍተኛ አደጋ በማድረስ የሚገኘው ተተኳሽ እንዲወገድላቸው ጠይቀዋል።

የክልሉ እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት የአደጋው አስከፊነት በመረዳት አከባቢያቸው ከተተካሾች እንዲታደጉላቸውም ተማፅነዋል።

የወረዳው የፀጥታ ፅ/ቤት የአርሶ አደሮቹ አስተያየት በመጋራት ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ከ51 በላይ ወገኖች ባልመከኑ ተተኳሾች ህይወታቸው ሲቀጠፍ ፤ ከ286 በላይ ደግሞ ለአካል ጉዳት እንደተጋለጡ ገልጸዋል።

" ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ነው " ያለው ፅ/ቤቱ ህዝቡ ከስጋት ድኖ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ መንግስትና ለጋሽ ደርጅቶች አከባቢውን ከተተኳሾች ለማፅዳት የበኩላቸው እንዲተባበሩ ጠይቋል።

" ዘላቂው መፍትሄ በአከባቢው ላይ ያለውን ተተኳሽ ማፅዳት ነው ፤ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት የወዳደቁና የተቀበሩ ተተኳሾችን በማስወገዱ በኩል አከባቢያችን ትኩረት ያሻዋል " ሲል ፅ/ቤቱ አስገንዝቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከድምፂ ወያነ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች ከ51 በላይ ወገኖች ሲቀጠፉ ፤ ከ286 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ሰለባ ሆኗል " - በትግራይ ማእከላይ ዞን የየጭላ አበርገለ ወረዳ የፀጥታ ፅ/ቤት በትግራይ በነበረው አውዳሚ እና አሰቃቂ ጦርነት ወቅት ተቀብረው እና ተጥለው ያልመከኑ ተተኳሾች የንፁሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፍና አካል ማጉደል ቀጥለዋል። በየጭላ አሸርገለ ወረዳ የእምባ…
#ትግራይ

ያልመከነ ተተኳሽ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ቀጠፈ።

ጥቅምት 21 /2017 ዓ.ም በትግራይ ማእከላይ ዞን አበረገለ ጭላ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዘገልዋ መንደር ውስጥ ባልመከነ ተተኳሽ  ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው ጠፍቷል።

ህይወታቸው የጠፋው ባል እና ሚስት ከ5 ዓመት ልጃቸው ጋር ነው።

የወረዳው ፓሊስ አከባቢው በትግራዩ ጦርነት ከባድ ውግያ የተካሄደበት ከመሆኑ  ጋር ተያይዞ ያልመከኑ ተተኳሾች አደጋ ሲያደርሱ ቆይቷል እያደረሱም ይገኛሉ ብሏል።

ፓሊስ እንዳለው ህይወቱ የተቀጠፈው ህፃን ወድቆ ያገኘውን ተተኳሽ ወደ ቤቱ ወስዶ ከእሳት በማነካካቱ ፈንድቶ ሦስቱ የቤተሰቡ አባላት ወድያውኑ ሞተዋል።

በወረዳው ከፕሪቶሪያ ስምምነት ወዲህ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች የአሁኑን ጨምሮ ከ53 ሰዎች በላይ መሞታቸው ያስታወቀው የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት በበኩሉ አሁንም የሚመለከተው አካል አከባቢው ካልመከኑ ተተኳሾች በማፅዳት ህዝቡ እንዲታደግ ተማጽኗል። 

መረጃው  ከወረዳው የህዝብ ግንኙነት ፅህፈት ቤት ነው የተገኘው። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Tigray " የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ ነው " - ሀጂ አወል አርባ የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከፍተኛ አመራርን ላካተተዉ ሉዑካን ቡድን ምን አሉ ? " የአፋርና ትግራይ ህዝቦች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው። በሁለቱ ክልሎች…
#አፋር #ትግራይ

የትግራይ እና የዓፋር አጎራባች ዞኖች አመራሮች ዛሬ ጥቅምት ለሁለተኛ ጊዜ በዓፋርዋ የአብዓላ ከተማ ተገናኝተዋል።

ለግማሽ ቀን በተካሄደው የሁለቱ ክልል አጎራባች ዞኖች አመራሮች ግንኙነት ፦
- የሁለቱም ክልል ህዝቦች የፊት ለፊት ግንኙነት እንዲጀመር፤
- የተከለከሉ መንገዶች ተከፈትው ነፃ የህዝቦች ግንኙነት እንዲቀጥል፤
- ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ ክልል ህዝቦች የሰላም  እና የልማት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፡
- ሁለቱም ክልሎች ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ፤
- ሁለቱም ክልሎች የሰላምና የፀጥታ እቅድ በማውጣት  በየወሩ እየገመገሙ እንዲጓዙ፤

ተወያይተው መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ግንኙነቱ በማስመልከት አስተያየት የሰጡት የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ሰላምና ልማት መሰረት እንዲይዝ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የላቀ ዝግጁነት አለው " ብሏል።  

በያዝነው ጥቅምት ወር መጀመሪያ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ዓፋር ሰመራ ድረስ በመጓዝ ከርእሰ መስተዳደር ሃጂ ኣወል ኣርባ ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት ማካሄዳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo Credit - Tigrai Television

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተደደር ዛሬ ህዳር 1/2017 ዓ.ም የፅሁፍ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም " በአንደኛው ገፅ ልዩነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረሩ ሄደዋል በሌላኛው ገፅ ደግሞ የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች የማደናቀፍ እና የማዳከም የተቀናጀ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቷል አሁንም ቀጥሏል " ሲል ገልጿል።

በተለይም ከነሀሴ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና በግልፅ የታየው ልዪነት መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄያዎች በተቀናጀ መልኩ እንዳይፈቱ ከባድ እንቅፋት ፈጥረዋል ብሏል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች በተቀናጀ መልኩ የሚያደናቅፈው ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ከፍተኛ አመራር ነው ያለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ " ደርጊቱ ህዝቡ ተስፋ እንዲቆርጥ ሆነ ተብሎ የሚደረግ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ሲል አውግዞታል። 

" የቡድኑ ተግባር የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች ከማደናቀፍ በዘለለ ይፋዊ ወደ ሆነ የመንግስት ግልበጣ እና ስርዓት አልበኝነት ማስስፋፋት ከፍ ብሏል " ሲል ከሷል።

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በመቐለ ከተማ  ፣ በሰሜናዊ እና ማእከላዊ ዞኖች የታዩት የመንግስት ግልበጣና ስርዓት አልበኝነት ምልክቶች የቡድኑ ህግ አልበኝነት ማሳያ ናቸው ሲል አስረድቷል።

" ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የመንግስት የአመራር እርከን ከላይ እስከ ታች ለመቆጣጠር ጨርሰናል " የሚል የማደናገሪያ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

" የቡድኑ ማደናገሪያ በአጉል ተስፋ ራስን ከማታለል የዘለለ ቅንጣት ሀቅ እንደሌለው መታወቅ አለበት " ያለው አስተዳደሩ " ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ መጥቷል " ሲል ገልጿል።

" ' ከሰራዊት አመራሮች ተግባብተናል ' በሚል እየነዛው ያለው ማደናገሪያ ለጠባብ የስልጣን ፍላጎቱ ማሟያ ነው " ብሏል።

" በትግራይ ህልውና የቆመው ሃይል ከመጠቀም እንደማይመለስም ማሳያ ነው " ሲል አክሏል።

" ቡድን " ሲል የገለፀው አካል በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው ነገሮች በውይይት የመፍታት ሂደት እንደማይቀበል በአደባባይ ገልፀዋልም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮቼ አሁንም ነገሮች በሰከነ አኳሃን በሰላም እና በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ናቸው ብሏል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች የጀመሩት የሰላምና የውይይት ጥረት እንዲሳካ ሁሉም ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።

በቅርቡ የትግራይ ሃይማኖት አባቶች የህወሓት አመራሮች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በንግግር እንዲፈቱ ለማድረግ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ ጌታቸው ረዳ እና አመራሮቻቸውን በአካል አገናኝተው ነበር።

ከዚህ መድረክ በኃላ በወጡ የተለያዩ ፎቶዎች በርካቶች " ችግሩ በንግግር ሊፈታ ነው " በሚል ብዙ ተስፋ አድርገው ነበር።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትናንት በትግራይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ያደረጉት የፊት ለፊት ግንኙነት ከብፁአን የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅና ምክር የዘለለ ውጤት እንደሌለው ተናገረ።

የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ዛሬ ምሽት አጭር መግለጫ አውጥቷል።

አንዳንድ ሚዲያዎች ደግሞ " ለእርቅና ሽምግልና ተስማምተዋል " የሚል መረጃ እስከማሰራጨትም ደርሰው ነበር።

በኃላ በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ፥ " በብፁአን አበው የተዘጋጀው ፊት ለፊት የማገናኘት መርሃ ግብር ልዩነቶች በህግ ፣ ተቋማዊ ስርዓት ማእከል በማድረግ ህዝብን ከአደጋ መታደግ በሚችል የሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችን እንድንፈታ ያለመ የምክርና የተግሳፅ መድረክ ነበር " ሲል አሳውዋል።

" ብፁአን አበው ላቀረቡልን ምክርና ተግሳፅ ያለንን ክብርና ድጋፍ ገልፀናል ፤ ከዚህ በዘለለ የተለያዩ አካላትና ሚዲያዎች ' ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል ' በማለት የሚያሰራጩት መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " ሲል ነበር የገለጸው።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ።

#TikvahEthiopiaFamilyAA #Tigray #Mekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ጊዚያዊ አስተደደር ዛሬ ህዳር 1/2017 ዓ.ም የፅሁፍ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም " በአንደኛው ገፅ ልዩነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረሩ ሄደዋል በሌላኛው ገፅ ደግሞ የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች የማደናቀፍ እና የማዳከም የተቀናጀ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቷል…
#ትግራይ

" ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው።

" ህጋዊ ያልሆነው ቡድን "  ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል ሲል በድጋሜ ከሷል።

" ህጋዊ ያልሆነው ቡድን " በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች " ህጋዊ ያልሆነ " የስራ ምድባ በማካሄደ የመንግስት ግለበጣ በማካሄድ የቀን ተቀን ስራ የማደናቀፍ ኢ-ህጋዊ ተግባሩ ቀጥሎበታል ሲል ጠቅሰዋል።

" ህጋዊ ያልሆነ ቡድን " ህጋዊ ያልሆኑ የስራ ምደባዎች በማካሄድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ከማደናቀፍ አልፎ ስራውን በሚመሩት ላይ አላስፈላጊ ጫና በመፍጠር የመንግስት ስራ እንዲቆም እያደረገ ነው ሲልም ገልጿል።

በየደረጃው የሚገኙ የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅሮች ፣ በትግራይ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አካላት እና ተቋማት ፣ የፌደራል መንግስት እንዲሁም የዓለም ማህበረሰብ " ህጋዊ ባልሆነው መንገድ " የሚመድቡ እና የሚመደቡ በማንኛውም መንግስታዊ ሃላፊነት ስም እንዲንቀሳቀሱ ምንም እውቅና የሌላቸው እንደሆኑ እንዲገነዘቡ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመልክቷል።

" ህጋዊ ባልሆነው ቡድን " የሚመደቡት አካላት የሚያስተዳድሩት ማንኛውም ሃብት የለም ያለ ሲሆን የፀጥታ አካላት ፣ የፍትህ መዋቅር እና ባንኮች ይህንኑ በመገንዘብ ህግ እንዲያስፈፅሙ ሲል አስገንዝበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከታማኝ ምንጮች ባገኘው መረጃ ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ህጋዊ ያልሆነ ቡድን " ሲል በፈረጀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተመደቡ የአስተዳደር አካላት ስም ጠቅሶ ማንኛውም የመንግስት ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ የሚያግድ ደብዳቤ ወደ ባንኮች ፅፏል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው። " ህጋዊ ያልሆነው ቡድን "  ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል…
#ትግራይ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደተር በ4 ከተሞች የጠራቸው የህዝብ ስብሰባዎች በአንዱ ሲካሄድ በሦስቱ  ተስተጓጉሏል።

ለስብሰባዎች መሰተጓጎል የፀጥታ ስጋት እንደ ምክንያት መቀመጡ አንዳንድ የከተሞቹ ነዋሪዎች ይገልፃሉ።

ባለፈው እሮብ ህዳር 4/2017 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ  ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተሾሙት ሰለሙን ትኩእ በዓዲግራት ከተማ ከዛላኣንበሳ ከተማ ተፈናቃዮች ለመወያየት እና በህዝብ የተመረጠ አዲስ አስተዳዳሪ ለመሾም የጠሩት ስብሰባ ፈተና የበዛበት ነበር።

ስብሰባ ከተከናወነበት አዳራሽ የወጡ የቪድዮ እና ድምፅ ፋይሎች እንደሚያሳዩት የማይናቅ ቁጥር ያላቸው እናቶች በስድብ ፣ ጩኸት እና ዋይታ ሰብሰባው እንዳይካይሄድ ሲከላከሉ ታይተዋል።

ቢሆንም የእናቶቹ ረብሻ በፀጥታ አካላት እንዲረገብ ሆኖ ወይይቱ ተካሂዶ የዛላምበሳ ከተማ አስተዳዳሪ በህዝብ ድምፅ እንዲመረጥ ሆኗል።

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የጉሎመኸዳ ወረዳ ሦስተኛ ከተማ የሆነችው የዛላኣንበሳ ከተማ እስካሁን በኤርትራ ስራዊት ቁጥጥር ስር እንደምትገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የወረዳው አስተዳዳሪዎችን ዋቢ በማድረግ በተደጋጋሚ  መዘገቡ ይታወሳል።

እሁድ ህዳር 8 /2017 ዓ/ም በትግራይ ምስራቃዊ  እና ማእከላዊ ዞኖች በሚገኙ ውቕሮ ፣ ዓብዩ ዓዲ እና አክሱም ከተሞች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተጠሩ ህዝባዊ ስብሰባዎች መሰረዛቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል።

ስብሰዎቹ ከፀጥታ ስጋት ጋር በተገናኘ የተሰረዙ እንደሆነ የገለጹ አሉ።

ከዚህ ተቃራኒ አስተያያት የሰጡ ደግሞ " በተለይ በዓብዩ ዓዲ እና አክሱም ከተሞች ሊካሄዱ ታቅተደው የተሰተጓጎሉት ህዝባዊ ስብሰባዎች በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በዞኑ ያካሄደው የአስተዳደር  የስልጣን ግልበጣ አካል ናቸው " ብለዋል።

ዛሬ ሊካሄድ የታሰበው ስብሰባ የተሰተጓጎለባቸው የውቕሮ ፣ የተምቤን ዓብዩ ዓዲ እና የአክሱም ከተሞች በአሁኑ ሰዓት ከወትሮ የተለየ የፀጥታ ስጋትና መደፍረስ እንደሌለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ወደ ከተሞቹ ስልክ በመደወል አረጋግጧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" ' ተቀምተናል ' የሚሉትን ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው "  - ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ 

ዛሬ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የፀጥታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝብ ጥቅም ማእከል አድርጎ በሚንቀሳቀስ የፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ ለግሉ ጥቅም ብቻ የሚያስብ አመራር ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ሆኗል " ብለዋል።

" ' ስልጣን ለኛ ነው የሚገባው ' የሚሉ የህዝብ አጀንዳ በማፈን ፍላጎታቸው ለማሳካት የግጭትና የግርግር መልእክቶች በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ " ሲሉም ገልጸዋል።

እነዚህን አካላት በስም አልጠቀሷቸውም።

ፕሬዜዳንቱ በስም ያልገለፁዋቸው አካላት " ተቀምተናል " የሚሉት ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እያካሄዱ እንደሆነ አመላክተዋል። 

" ትኩረታችን የትግራይ ህዝብ መሆን ይገባ ነበር " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ለወንበር ሲባል የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች የማደናቅፍ ስራዎች ተባብሰው ቀጥለዋል " ሲሉ ገልፀዋል። 

" ' ሰራዊት ከኛ ጎን ነው ' በማለት የግለሰቦችን ስልጣን ለማርካት ታስቦ የፀጥታ ሃይል ለመከፋፈል አልሞ እየተሰራ ነው " ሲሉም አክለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፥ " በትግራይ ሁሉንም ነገር በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የቆየ ሃይል አሁንም የፀጥታ ሃይል ፤ ሚድያ ተቆጣጥሮ በለመደው መንገድ በመሄድ የግል ጥቅሙን ለማረጋገጥ ጠላት ከሚለው እየተደራደረ ይገኛል " ብለዋብ።

" ጠላት " ያሉትን ሃይል በስም አልገለፁም። 

የም/ ቤት አባላት በማንሳት የአስተዳዳሪዎች ስልጣን እንዲለወጥ መስራት መፈንቅለ መንግስት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው " መንግስትን ለማፍረስ የሚደረጉ መድረኮች በመንግስት በጀት ነው የሚካሄዱት " ሲሉ ተግባሩን ኮንነዋል።

" ' የፀጥታ ሃይል ከኛ ነው ' የሚለው አነጋገር የፀጥታ ሃይሉን በመጠቀም ' ከስልጣን እናስወግዳችኋለን ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ የሚሰራ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ፎቶ፦ DW

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችን በውይይት መፍታት ካልቻልን ትግራይን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው በግልፅ ነግሮናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ  ወደ ሁለት በተከፈሉ የህወሓት አመራሮች እየታመሰ የሚገኘው የክልሉ የፓለቲካ ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ ተባብሶ መቀጠሉ ተናግረዋል።

" በምንገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ የፓለቲካ የአሰላለፍ ለውጥ እየተፈጠረ ነው ፤ የትግራይ ሁኔታም ከሚታየው ለውጥ ተያይዞ ያሉት ዕድሎች እና ፈተናዎች መተንተን ያስፈልጋል "  ብለዋል።

" የትግራይ ፓለቲካ ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ መገንዘብ ትቶ በአመራሮቹ እየታመሰ ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

" የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችንን እንድንፈታ እየገለፀ ነው ካልተቻለ ግን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው ግልፅ አድርጓል " ሲሉም አክለዋል።

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት ለሚካሄደው በፕሪቶሪያ የሰላም አፈፃፀም የሚመለከት የግምገማ መድረክ ከወዲሁ " እኔ ነው መሳተፍ ያለብኝ " ወደ ሚል መሳሳብ ተገብቷል ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

" የህወሓት አመራር ሉአላዊ የትግራይ ግዛት ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ታጣቂዎች ነጻ ሆኖ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ዋና አጀንዳ ዘንግቶ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የእለት ተእለት ስራዎች በማድናቀፍ ተጠምዷል " ሲሉም ከሰዋል።

" ከፕሬዜዳንት ስልጣን ወርደዋል ፤ ወደ ውጭ አገር ሊወጡ እያመቻቹ ነው ፤ ውጭ ሀገር ወጥተው እንዲቀሩ መንግሥት እያመቻቸላቸው ነው "  ተብሎ ሲወራባቸው ስለ መሰንበቱ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ " ለስራ በምወጣበት ጊዜ ከሁለቱ ምክትሎች አንዱ መወከል የተለመደ አሰራር ነው መወከሌም እቀጥላሎህ ፤ ' ከሀገር ሊወጣ ነው ' ተብሎ የተነዛው ወሬም ከሃቅ የራቀ መሰረተ ቢስ የውሸት ወሬ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

' ለስልጣን መቆራቆስ ትተን በጦርነት እና ጦርነት ወለድ ችግሮች የተጎሳቆለው ህዝባችን መካስ ማስቀደም አለብን " ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ በእሳቸው የሚመሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው የህወሓት ከፍተኛ አመራር ጋር የሃይማኖት አባቶች በጀመሩት የእርቅ ጥረት ችግሮቻቸው ለመፍታት ቁርጠኛ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia