TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION🚨

" አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከቫይረሱ በላይ #እርግዝናን_ይፈራሉ "

ስለኤች አይቪ/ኤድስ ስርጭት የሚሰጠው የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ከጊዜ ወደጊዜ እየተቀዛቀዘ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ገልጿል።

ችግሮች ከመባባሳቸው በፊት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ አሳስቧል።

ቫይረሱ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ በተሰራው እንቅስቃሴ ብዙ ለውጦች መመዝገባቸውን አስታውሷል።

ይሁን እንጂ የተመዘገቡት ለውጦች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መዘናጋት እንደፈጠሩ ፤ የሚዲያዎች ተሳትፎም መቀዛቀዙን ጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት ኤች አይ ቪ ቫይረስን በተመለከተ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ትኩረት የሚሹና በይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ ብቻ ትኩረት ያደረጉ ናቸው ብሏል።

እነዚህም ፦
- ሴተኛ አዳሪዎች፣
- አደንዛዥ እፅ የሚጠቀሙ ሰዎች፣
- የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣
- አፍላ ወጣቶች በተለይ (ከማኅበራዊ ሚዲያ ጋር በተያያዘ)፣
- የቀን ሠራተኞች፣
- ከማኅበራዊ ችግሮች ጋር ተያይዞ ተጋላጭ የሆኑት እንደሆኑ አመልክቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ ቢሆንም ከቦታ ቦታ በፆታ፣ በኅብረተሰብ ክፍል፣ በገጠርና በከተማ ከፍተኛ ልዩነት አለው ብሏል።

በከተሞች ያለው ስርጭት በገጠር ካለው በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥም ጠቁሟል።

ይህንን ልዩነት መሠረት ያደረገ አጠቃላይ ማኅበረሰቡን ተደራሽ የሚያደርግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተከናወነ አይደለም ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፦
° የመጠጥ ቤቶች ፣
° የጫት ቤቶች
° በሺሻ ቤቶች መስፋፋት ሌላ ተግዳሮቶች እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጿል።

" አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከቫይረሱ በላይ እርግዝናን ይፈራሉ። የወጣቶች አዲስ የመያዝ ምጣኔ ጨመረ ባይባልም እየቀነሰ አይደለም፤ ይህ በራሱ ችግር ለመኖሩ አመላካች ነው "ም ብሏል።

በተለይ በወጣቶች በኩል ሁሉን አቀፍ ሥራ ባለመሠራቱ እንደ ሀገር ዋጋ ሊያስከፍሉ የሚችሉ አጋላጭ ባሕሪያት እየተስተዋሉ መሆኑን አመልክቷል።

የኤች አይ ቪ ቫይረስን በተመለከተ ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እንደሀገር ማከናወን እንደሚጠበቅ አሳስቧል። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
#ATTENTION🔔

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ወላይታ ዞን ባሉ ወረዳዎች ያሉ መምህራን ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ስራ እንዳቆሙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ ፦

" ... ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ ነው። አሁን ላይ ' በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም ' በሚል መምህራኑ ስራ አቁመዋል።

በፐርሰንት እየተቆራረጠ የሚከፈላቸው ደመወዝ በዚህ ወር ለ16 ቀን ዘግይቷል።

ከደመወዝ በላይ የሌሎች ጥቅማጥቅሞች ፥ የወዝፍ ደሞዝ ፣ ከደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደሞዝ ጭማሪና የእርከን ጭማሪ መቅረት ፈተና ሆኖባቸዋል። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎችን ይልካል።

ከዚህ ቀደም ወላይታ ዞን ስለሚገኙ መምህራን ቅሬታ የቀረበ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/86484?single

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Attention ⚠️

" ራኒቲዲን #ካንሰርን ሊያመጣ የሚችል ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ምክንያት #ታግዷል " - የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን

ለጨጓራ ተያያዥ ህመሞች በመድኃኒትነት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው ' ራኒቲዲን ' የተባለው መድሃኒት በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል #ማገዱን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የባለስልጣኑ የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና የሕክምና ሙከራ መሪ ስራ አስፈጻሚ አስናቀች ዓለሙ ፤ " በመጀመሪያ ደረጃ በሌሎች ሀገር የወጡ ሪፖርቶችን አይተን ነበር። ስለዚህ በሀገራችንስ ይሄ መድሃኒት እንዴት ነው ? የሚለውን በማገናዘብ የላብራቶሪ ምርመራ አድርገናል " ብለዋል።

በዚህም መድሃኒቱ ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ' N-nitrosodimethylamine ወይም NDMA ' የተሰኘ ንጥረ ነገር እንደተገኘበት መሪ ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።

" በመሆኑም ይህንን መድሃኒት ከምዝገባ ፋይላችን አውጥተናል። የተሰራጩ መድሃኒቶችም #እንዲሰበሰቡ እና ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መልእክት አስተላልፈናል " ብለዋል።

" በዚህ በሰረትም ጥቅም እንዳይውል #ታግዷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

" የጤና ባለሙያዎችም፣ የጤና ተቋማትም ሌሎች አማራጭ መድሃኒቶችን እንዲያዙ እና እንዲጠቀሙ ይህንን መድሃኒት #እንዳይጠቀሙ " ሲሉም አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION🚨

“ የ2 አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” - ከእገታ ያመለጠ ተማሪ

“ ‘ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም ፤ ታግተናል ’ አለችኝና ከዛ ስልኳ አይሰራም ” - የአንዷ ታጋች ተማሪ እህት

“ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው ” - የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት

ሰኞ እለት ተሳፍረው ወደ ቤተሰብ እየተጓዙ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የዓይን እማኝ፣ የታጋች ቤተሰብና ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አንድ ከእገታው አመለጥኩ ያለ ተማሪ ፥ ሶስት (3) አውቶብሶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተጓዙባቸው የነበሩ ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ ገብረ ጉራቻ የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ከ3 አውቶብሶች 2ቱን ታጣቂዎች እንዳስቆሟቸው፣ ተሳፋሪዎቹን ካስወረዷቸው በኋላ አግተው ወደ ጫካ እንዳስገቧቸው፣ እርሱ ገለባ ውስጥ ተደብቆ እንዳመለጠ ገልጾ፣ “ የሁለቱ አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” ብሏል።

ከታጋቾቹ መካከል የሚያውቃቸው የIT ፣ የአኒሚል ሳይንስ ዲፓርትመንት ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ፣ ያገቷቸው “የሸኔ ታጣቂዎች” መሆናቸውን አስረድቷል።

አንዷ የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል፣ “ ረቡዕ 3 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ደወለችልኝ (እየሮጡ ነበር፣ የተኩስ ድምጽም ነበር) ‘በቃ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም። ላታገኝኝ ትችያለሽ በታጣቂዎች ታግተናል’ አለችኝ። መለሽ ስደውል ስልኳ አይሰራም ” ብላለች።

ቤተሰቡ ሁሉ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ታጋቾቹን በህይወት እንዲያተርፏቸው ተማጽናለች።

በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፤ የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በበኩሉ፣ እገታው እውነት መሆኑን እንዳረጋገጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ኀብረቱ በሰጠው ቃል “ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው። ‘ ገንዘቡን ካላመጣችሁ እንገድላችኋለን ’ እያሏቸው ይገኛል ” ሲል የሰማውን አስረድቷል።

የሞቱ ፣ የተጎዱ ስለመኖራቸው የደረሰው መረጃ እንደሌለ የገለጸው ማህበሩ ፣ የሚመለከታቸውን  አካላት ሁሉ ለማነጋገር ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

በጉዳዩ ላይ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሰጠንን ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#ATTENTION🔈

" ከሕጋዊው አካዉንት ውጭ በመጠቀም ድጋፍ የምታሰባስቡ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ !! " - የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት ናዳ ከተከሰተ ዛሬ 6ኛ ቀኑን ይዟል።

በዚህ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

የጠፉ ሰዎችን ፍለጋና አስከሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራ አሁንም የቀጠለ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

እስካሁንም ድረስ ያልተገኙ በርካታ የቤተሰብ አካላት በመኖራቸዉ የሟቾችን ቁጥር ቀድሞ ከተገለጸው ሊጨምር ይችላል።

ከጉዳቱ የተረፉ ሰዎችን ወደ አንድ አካባቢ አድርጎ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

ከአራቱም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚደረገው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ተብሏል።

ግን ከተፈቀደው የንግድ ባንክ አካውንት እና የአጭር መልዕክት ድጋፍ ማድረጊያ ቁጥር ውጭ " ድጋፍ እናሰባስባለን " በሚል አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ኢ/ር ዳግማዊ አየለ ፥ " ከተፈቀደዉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቁጥሮች ወጭ ጥቅም ላይ የዋሉ የንግድ ባንክ አካውንቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች እየተዘዋወሩ በመሆኑ በዚህ ድርጊት ላይ የምትሳተፉ አካላት ከድርጊታችሁ  እንድትቆጠቡ "  ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ፥ " አሁን ላይ ህጋዊ ሆኖ ገንዘብ የሚሰበሰብበት የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000511561276 እንዲሁም በአጭር መልእክት ድጋፍ ለማድረግ ደግሞ 8991 ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበረሰቡ ከዚህ ዉጭ በሚዘዋወሩ አካውንቶችን እንዳይጠቀም ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከመላው ኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ከጉዳት የተረፉ ወገኖችን ስነልቦና የማከሙ ስራ የቀጣይ ዋና ተግባር እንደሚሆንና ይህም የሁሉም ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #Silte ስልጤ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በመከሰቱ በርካታ ወገኖቻችን ለመፈናቀል መገደዳቸውን ነዋሪዎችና ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለይ በዞኑ የስልጢ ወረዳ ጎፍለላ ቀበሌ በጎርፍ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ወገኖቻችን ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ተፈናቅለዋል። አደጋው እንስሳትን ጨምሮ በንብረት ላይ ውድመት አስከትሏል…
#ATTENTION🚨

ከ6 ሽህ በላይ ወገኖቻችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

በስልጤ ዞን ባሉ 2 ወረዳዎችና 8 ቀበሌዎች ከአንድ ሺህ በላይ አባዉራ ቤትና ማሳዉ በውሀ መዋጡን ተከትሎ ከአካባቢዉ መነሳታቸው ተሰምቷል።

እስካሁን ባለዉ መረጃ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ድጋፍ እንደሚሹ የዞኑ የአደጋ ስጋት ኃላፊ ወሲላ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ጎርፉ የፈጠረዉን ሀይቅ በዚህ ወቅት ማፋሰስ አሰቸጋሪ መሆኑን ያነለከቱት ኃላፊዋ " የሁለቱን ወረዳ ነዋሪዎች በክልሉና በዞኑ ድጋፍና ትብብር አውጥተን በትምህርት ቤቶችና በአርሶ አደሩ የስልጠና መዕከላት አስፍረን ስላልበቃን ትርፍ ቤት ያለዉ ሁሉ ትርፍ ቤቱን በመስጠት በጊዜያዊነት ለማስጠለል ተሞክሯል " ብለዋል።

" የመሬቱ አቀማመጥና የጎርፉ ብዛት የፈጠረዉ የዉሀ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ዝናቡ እስኪቆም ዘላቂ መፍትሄ መስጠት አንችልም ፤ ይሁንና አንዳንድ ቦታ ላይ ቋሚ ሰብሎች እንዳይጎዱና ቤቶች እንዳይበሰብሱ አንዳንድ ስራዎች እየሰራን ነው " ሲሉ አክለዋል።

አሁን ላይ ለተጎጂዎች እየቀረበ ያለው የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የዞኑ አደጋ ስጋት ምክር ቤት ተቋቁሞ ድጋፍ የሚሰበሰብበት መንገድ መመቻቹትን አመልክተዋል።

የስልጤ ዞን የጎርድ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አካዉንት 1000647585535 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መሆኑ ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ? " እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ…
#Attention🚨

በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

" በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የተፈፀመ ነው። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል " ብሏል።

" በስምጥ ሸለቆች ውስጥ ንዝራቱ ከማሰማት  በሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈንታሌ ተራሮች ውጭ የደረሰ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም " ሲል አክሏል።

" በደሴ መስመር እስከ ኮምቦልቻ የተየውም ንዝራቱ ነው። ክስተቱ ከሰሞኑ ጀምሮ በፈንታሌ ተራራ እና አዋሽ አካባቢዎች የነበረ ስሜት ነው " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ? " እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ…
#ATTENTION🚨

ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ? መደረግ ያለበት ጥንቃቄስ ምንድነው ?

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ምን አሉ ?

" ድጋሚ ሊከሰት ይችላል ወይ ? የሚባለው ሰሞኑን በሙሉ ይሄን አይነት ንዝረቶች ነበሩ።

መሬት መንቀጥቀጥ መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን መተንበይ አይቻልም።

ስለዚህ ሊከሰት ይችላል ሊመጣ ይችላል። ይሄ ሁል ጊዜ በተለይ አዲስ አበባ የምንኖር ሰዎች ነቅተን የምንጠብቀው ነገር መሆን አለበት።

ስምጥ ሸለቆና የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ነቅተን የምንጠብቀው ነገር ነው መሆን ያለበት።

ለጊዜው መናገር የምችለው ከበድ ያለ ነገር ከመጣ አይመጣም ብለን ነው የምንገምተው ከመጣ ግን ምን መደረግ ስለለበት ጥንቃቄ ነው።

➡️ የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት ለምን መውረድ ሊከብድ ይችላል ቁልፍ ማክፈትም ሊከብድ ይችላል። ስለዚህ ኮለኖች አካባቢ መጠጋት።

➡️ ከተቻለ ጠረጴዛ ስር መግባት።

➡️ ሊፍት አትጠቀሙ። ማንም ሰው በሊፍት ለመውረድ እንዳይሞክር። ያን እንዳትጠቀሙ።

ይሄን ይሄን ጥንቃቄ ማደርግ ያስፈልጋል። ነገር ግን አሁን ባለው እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ከባድ ነገር አለ ብለን አንገምትም። "

#Ethiopia #AddisAbaba

@tikvahethiopia
#Attention🚨

“ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረው አንጻር ለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚዲያ፣ የተቋማት ትኩረት በመቀነስ ላይ ይገኛል። የሕሙማን ቁጥር ግን እየጨመረ ነው ” - ሆስፒታሉ

የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ መሆኑን መረጃዎች እየጠቆሙ ቢሆንም የሚዲያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ለቫይረሱ ያላቸው ትኩረት እየቀነሰ መሆኑን ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማህጸን ጫፍ፣ የቆዳ ካንሰሮች ኤች አይ ቪ ኤድስ ሲጨመር አብረው የመጨመር እድል ስላላቸው ከዓመታት በፊት እንደነበረው ሁሉ የሚዲያዎችና ሌሎች ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ በአዲስ አበባ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንዱዓለም ደነቀ አሳስበዋል።

ፕሮፌሰሩ በዝርዝር አሉ ?

“ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንደ ህመም አሁንም አለ። መረጃዎች እንደሚያሳዩት በተወሰኑ የአገራችን ክፍሎች አዲስ አበባን ጨምሮ የህሙማኑ ቁጥሩ እየጨመረ ነው። 

እኛ እንደ ተቋም የምንሰጠውን አገልግሎት አላቋረጥንም። እሱን እናካሂዳለን። ግን ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረው አንጻር ለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚዲያ፣ የሌሎች ተቋማት ትኩረት በመቀነስ ላይ ይገኛል። 

ይሄ ጉዳይ መታሰብና መሻሻል አለበት። ኤች አይ ቪ ኤድስ የተወሰነ ህክምና አለው። ግን አንዳንዴ ህክምና ማለት ራሱ ቀላል ነገር አይደለም። አለመታመምን አይተካምና።

የኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና በእድሜ ልክ የሚወሰድ ህክምና ነው ያለውና በትኩረተ ሊሰራበት ይገባል የሚል እምነት አለን።

አንዳንዴ ደግሞ መድኃኒቱም ሳይድ ኢፌክት (የጎንዮሽ ጉዳት) አለው። ከመድኃኒቱ በተጨማሪ ከህመሙ ጋር በተያያዣነት ሌሎች ህመሞች ይመጣሉና። 

አንዳንዴ ደግም ሰዎች ላያውቁት ይችላሉ፤ ሳያውቁት ሊቆዩ ይችላሉ እስኪመረመሩ ድረስ። ስለዚህ ምርመራውንም በተቻለ መጠን አጠናክሮ መስራት ያስፈልጋል። 

ድሮ እናቶች ለእርግዝና ክትትል፣ ሌሎች ሰዎችም ለአንዳንድ ህክምና ሲመጡ ይመረመራሉና ያም ነገር አሁንም በደንብ ተያይዞ መቀጠል አለበት።

አንዳንድ ህመሞች ከኤች አይ ቪ ኤድስ ጋር ቁጥራቸውም የመከሰት እድላቸውም ይጨምራል። ለምሳሌ የማኀጸን ጫፍ ካንሰር አንዱ ነው። የአንጀትና የቆዳ ካንሰሮች ሁሉ አሉ።

ሀገርም ደግሞ ምንም ህክምና ቢኖር ካላት ኢኮኖሚ ላይ ሸርፋ ነውና ለዚያ የምታውለውና ከዚህም አንጻር ሲታይ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው።

እኛ እንደተቋም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን ቢያንስ በማከም፣ በማስተማር። ግን አጠቃላይ እንደ አገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚዲያዎችን ጨምሮ አስፈላጊውን ሥራ ሁሉ እንዲሰሩ ይጠበቃል።

ኤች አይ ቪ ኤድስ የጤና ጉዳይ ብቻ አይደለም። የልማት ጉዳይ ነው ተብሎ ለብዙ ጊዜ የተኬደበት ጉዳይ ነውና አሁንም እንደዛው ታስቦ ነው መኬድ ያለበት ”
ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia