TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የጤናባለሞያዎች

" የ5 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ አልተከፈለንም !  አፋጣኝ ምላሽ እንፈልጋለን " - በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የንግስት እሌኒ መሐመድ ሆስፒታል ሰራተኞች

" በጀቱ ስለተለቀቀልን ክፍያዉን በሁለት ቀን ውስጥ እናጠናቅቃለን ተረጋጉ " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሀመድ ሆስፒታል ውስት የሚሰሩ ሰራተኞች 5 ወር ሙሉ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ለወራት የትርፍ ሰአት ክፍያ ስንጠይቅ ነበር " ያሉት ሰራተኞቹ ከሰሞኑ ድምጻቸዉን ለማሰማት ሰልፍ ለመውጣት መገደዳቸውን አመልክተዋል።

" የዘገየዉ ገንዘባችን ይሰጠን  !! " ሲሉም ለሚመለከተዉ አካል መልእክታቸዉን አሰምተዋል።

" የኑሮ ዉድነት ምን ያክል ፈተና እንደሆነብን እየታወቀ የትርፍ ሰአት ክፍያችን በጠየቅን ቁጥር ቀጠሮ መስጠት የማይሰለቸዉ የሆስፒታሉ አስተዳደር ትእግስታችን ተፈታትኖታል " የሚሉት ሰራተኞቹ " ከዚህ በላይ መታገስ የምንችልበት ሁኔታ ላይ ባለመሆናችን ጥያቄያችን በቶሎ ይመለስ " ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞቹን ጥያቄ ይዞ የሆስፒታሉን ስራ አስኪያጅ ዶክተር አያኖ ሻንቆን አነጋግሯል።

" ምንም እንኳን ችግሩ የታወቀ ቢሆንም የ5 ወር መዘግየት ሰልፍ የሚያስወጣ አልነበረም " ብለዋል።

አሁን ላይ ክፍያዉን ለማጠናቀቅ ቢበዛ 2 ቀናት ብቻ እንደሚበቃቸዉ ገልጸዋል።

የገንዘብ እጥረቱ የተከሰተዉ የነበረውን የበጀት እጥረት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲው ቅድሚያ ለተማሪ በማለቱ እንደሆነ አስረድተዋል።

" አሁን ላይ በጀቱ ተለቋል " ብለዋል።

ለክፍያው የተፈቀደው ገንዘብ በጽሁፍ እንጅ በካሽ አለመለቀቁን ተከትሎ ክፍያዉ በቶሎ አለመጀመሩን የገለጹት ስራ አስኪያጁ ፥ " አሁን ገንዘቡ በመድረሱ በ2 ቀን ውስጥ ክፍያዉ ይጠናቀቃል " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#የጤናባለሞያዎች

➡️ " የ6 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ ካለመከፈሉ በላይ ደመወዝም በአግባቡ ስለማይከፈል ሰራተኛው ስራ እየለቀቀ ነው " - የሀላባ ዞን አቶቴ ኡሎ ወረዳ የጤና ባለሞያዎች

➡️ " የ4 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ ነው ያልተከፈላቸው እንከፍላለን ፤ የሰራተኛ መልቀቅ ግን በስራችን ላይ ችግር አልፈጠረብንም " - የወረዳው ጤና ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን አቶቴ ኡሎ ወረዳ ያሉ የጤና ባለሙያዎች የ6 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ አለመከፈሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ክፍያው ወደ 2017 ከተሸጋገረ እንደሚቃጠልባቸው ባለሞያዎቹ አመልክተዋል።

ጥያቄያቸውን በሚጠይቁበት ጊዜ ጥያቄያቸዉ ወደፖለቲካ እየተጠመዘዘባቸው መሆኑን በመግለፅ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

" በደሞዝ መቆራረጥና ትርፍ ሰአት ስራ ክፍያ ተማሮ የሚለቀቀው ሰራተኛ ለአካባቢው ባለስልጣናት 40 እና 50 ሽህ ብር ተቀብሎ ለመቅጠር መንገድ ከፍቶላቸዋል " የሚሉት ሰራተኞቹ አሁን ላይ " የሰራንበትን ገንዘብ መጠየቅ እንደነውር ተቆጥሮ በደመወዝ በትርፍ ስራና በጉሸማ እየተሰቃየን ነው " ብለዋል።

ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የጤና ባለሙያ በሰጡት ቃል ፥ " በደመወዝ መዘግየትና በትርፍ ሰአት ክፍያ ችግር ምክኒያቶች እኔ በምሰራበት ሆስፒታል ብቻ ከላብራቶሪና ከኢመርጀንሲ አስተባባሪዎች እስከ ዶክተሮች ድረስ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከአምስት በላይ ሰዎች ለቀዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

ነገር ግን " እንዲህ ያለው ከፍተኛ ክፍተት አመራሩን አያሳስበውም " የሚሉት ሰራተኞቹ " እንዲህ ያለው አሰራር ህሊናህን እረፍት ከመንሳቱ በላይ ቅዳሜ እና እሁድ ሰው ሲያርፍ ወገብህ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ የሚጠበቅብህ በላይ ሰርተህ ክፍያዉ ሲቀር ምን ይሰማሀል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በርካታ የጤና ባለሙያዎች አሁን ላይ ኑሮ በእጅጉ መክበዱን ተከትሎ ከ5 እና 6 አመት ትግልና ሙከራ በኋላ ኑሮ ሲያሸንፋቸው ወደቤተሰብ መመለስን አማራጭ እያደረጉ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ ፤ " አሁን ላይ አኗኗራችን ሆነ የምናገኘዉ ገቢ ከቀን ሰራተኛ በታች ሆኗል " ብለዋል።

ባለሙያዎቹን ቅሬታ ይዘን ያነጋገርናቸው የአቶቴ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽህፍተ ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ኬሪ ፥ " ያልተከፈለ የትርፍ ሰአት ክፍያዉ የ6 ወር ሳይሆን የ4 ወር ነው " ብለዋል።

" የሰራተኛዉን ወርሀዊ ደሞዝ በጊዜዉ እየከፈልን ነው " የሚሉት ኃላፊው " የትርፍ ሰአት ክፍያውንም ለማጠናቀቅ ከሚመለከተዉ አካል ጋር እየተነጋገርን ነው" ሲሉ አክለዋል።

" ክፍያው ወደ 2017 ዓ/ም ከተሸጋገረ ሊቃጠል ይችላል " ለሚባለው ሀሳብ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በደመወዝ እና በትርፍ ሰአት ክፍያ ምክንያት ሰራተኛ ይለቃል የሚለውን ሀሳብ በተመለከተ " ሰው የተሻለ ሲያገኝ ነው የሚሄደው ፤ በዚህም ስራ ላይ የታየ ክፍተት የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ወደ 2017 ከተሸጋገረ ይቃጠላል " የተባለውን የ6 ወር ክፍያና የሰራተኛውን ስራ መልቀቅ እንዲሁም አጠቃላይ በክልሉ ያሉ የህክምና ሰራተኞችን ክፍያ በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ወንጋሮ ጥያቄ እንድናቀርብላቸው እድል ቢሰጡንም በስራ መደራረብ ምክኒያት ምላሽ መስጠት አልቻሉም።

በቀጣይ አነጋግረናቸው ምላሹን የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia