TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#INSA

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ከሰኞ ጥቅምት 24 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2012 ዓ.ም “ትኩረት ለሳይበር ደህንነት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የዘንድሮው የ2019 የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ትኩረት ያደረገው ግለሰቦች ለሳይበር ደህንነት ሥጋቶች ትልቁን ድርሻ የሚይዝ መሆኑን በመረዳት በቤትም ሆነ በሥራ ቦታ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ለማስገንዘብ ነው፡፡

Via INSA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#INSA በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) የተዘጋጀው የመጀመሪያው ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ በይፋ ተጀመረ፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንቱ "ትኩረት ለሳይበር ደህንነት" በሚል መሪ ቃል ነው የሚከበረው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#INSA

የዛሬው የኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት...

በሀገሪቱ የፋይናስ ተቋሞች ላይ ሊደርስ የነበረ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል በዛሬው ዕለት INSA ኔትዎርክ ለማቋረጥ ተገድዶ እንደነበረ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃኒ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገለፁ። ዛሬ የተከሰተው የኢንተርኔት መቋረጥ በኢትዮ ቴሌኮም ቁጥጥር ስር የነበረ እንዳልሆነና፤ ታቅዶም እንዳልነበር አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጥ አልነበረም፤እኛም መቋረጡን ለደንበኞቻችን ለመንገር ግዜ አልነበረንም፣ ለጥቂት ደቂቃ በማቋረጥ ጥቃቱን ለመከላከል ይቻላል ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነበር ብለዋል።

ከINSA ጋር እየተነጋገርን ነው የምንሰራው ያሉት ወ/ሪት ፍሬህይወት በዛሬው ዕለት ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ችግር አጋጥሟቸው የነበር ይመስለኛል፤ አሁን በጉዳዩ ላይ እየተነጋገርን ነው ብለዋል። ለኢንተርኔት መቋረጡ ይቅርታ ጠይቀዋል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#INSA

በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፍ ተቻለ!

ዛሬ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የሳይበር ጥቃት ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የፋይናንስ ተቋሞችን የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኔትወርኩን ከ15 እስከ 20 ደቂቃዎች ለማቋረጥ ተገድዶ እንደነበር የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ተናግረዋል፡፡

ተመሳሳይ ችግሮችን ለማክሸፍ ኤጀንሲው ከኢትዮ ቴልኮም ጋር በመሆን እየሰራ መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በኤጀንሲ ውስጥ ኢትዮ ሰርት የሚባል የፋይናንስ ተቋማትን ለ24 ሰዓት የሚከታተል እና አዲስ ጥቃቶች ሲቃጡ የመከላከል ተግባር ያለው ክፍል መኖሩን ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ክፍል ጥቃቱ ሳይደርስ መከላከል መቻሉን ኢንጅነር ወርቁ ተናግረዋል፡፡

ስራው ብዙ ጊዜ የተለመደውና የኔትወርክ ለውጥ የሚደረገው ብዙ ሰው ኢንተርኔት በማይጠቀምበት ሰአት ምሽት እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ዛሬ ላይ የተፈጠረው አስቸኳይ ስለነበር ቀን ላይ እርምጃው መወሰዱን ተጠቁሟል፡፡ ጥቃቱ ከየት እንደተሰነዘረ ዝርዝር ጉዳዮችን እየተመለከቱ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#INSA

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለቀይ መስቀል የቢሮ መገልገያዎችን ድጋፍ አደረገ። ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2012 ዓ.ም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለቀይ መስቀል ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ 50 ኮምፒውተሮች፣ 28 የሀላፊ ወንብሮች ፣ ጠረጴዛ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጋል። ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን ወደ 400,000 /አራት መቶ ሺህ ብር/ የሚገመት ነው። ይህ ድጋፍ ቀይ መስቀል ለሚሰጠው አገልግሎት መጠናከር አይነተኛ አስተዋፅዖ ያለው በመሆኑ ለተቋሙ በአገልግሎታችን ተጠቃሚዎች ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን የሚል መልዕክት በቲክቫ ኢትዮጵያ በኩል እንዲደርሳቸው መልእክቱን ያስተላልፈዋል።

ህዝብ የቀይ መስቀል መስረት ነው!
የቀይ መስቀል አባል በመሆን ይመዝገቡ!
ለሰብአዊነት እንኖራለን!

(ማንደፍሮ ነጋሽ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#INSA

ኢንሳ ስያሜዉን “ከኤጀንሲ” ወደ “አስተዳደር” መለወጡን ገለጸ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA) ስያሜውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር” (Information Network Security Administration (INSA) በሚል መቀየሩን አስታወቀ።

ተቋሙ ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር " 808/2006 " መሰረት “የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ” ተብሎ ሲጠራ መቆየቱን ገልጿል።

በኢፌዴሪ የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ 1263/2014 አንቀጽ 78(3) በተመለከተዉ መሰረት ነው ስያሜውን “የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር” በሚል የቀየረው።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ( #INSA ) የ2016 ዓ/ም " National Cyber Talent Challenge Program " ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ወጣቶች በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።

የታለንት መስኮች፦

- Cyber Security
- Cyber Development
- Embedded Systems
- Aerospace ናቸው።

ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለአንድ ወር ይሰጣል።

አመልካቾች በዌብሳይት  https://talent.Insa.gov.et በመግባት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ ደግሞ +251904311833 ፣ +251943579970፣ +251904311837 ላይ ስልክ መደወል ይችላል።

@Tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ( #INSA ) የ2016 ዓ/ም " National Cyber Talent Challenge Program " ማዘጋጀቱን ገልጿል። በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ወጣቶች በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል። የታለንት መስኮች፦ - Cyber Security …
#INSA #ጥቆማ

የብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ምዝገባ መካሄድ ጀምሯል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2014 ዓ/ም እና በ2015 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ አመታት በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በክረምት ፕሮግራም (Summer Program) አሰልጥኖ ማስመረቁን ገልጿል።

ተመራቂዎችንም ፦

° #እንደየችሎታቸው እና #እንደስራዎቻቸው ከተለያዩ ባለሀብቶች ጋር የማስተሳሰር፤

° ኢመደአን (INSA) ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት #ተቀጥረው መስራት የሚችሉበት ሁኔታ እንዳመቻቸ አመልክቷል።

ባለፉት ሁለት አመታት የተከናወኑ የሳይበር ታለንት ልማት ፕሮግራሞችን መነሻ በማድረግ በ2016 በጀት አመት “ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ” ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገልጿል።

የዚህ ቻሌንጅ ዋና ዓላማ በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ መስኮች ልዩ ተሰጥዖ ያላቸዉን ሰዎች በመመልመል በዘርፉ ላይ ተጨባጭ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል ብሄራዊ የሳይበር ሰራዊት (National Cyber Army) መገንባት ነው ተብሏል።

በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው እና እድሜያቸው ከ11 አመት ጀምሮ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።

መመዝገቢያ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ነው።

መመዝገቢያ አድራሻው https://talent.insa.gov.et ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#INSA

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ያዘጋጀው የ2016 ዓ/ም “ ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ” ፕሮግራም ምዝገባ እስከ ሰኔ 10/2016 ዓ/ም ድረስ መራዘሙን አሳውቋል።

እስካሁን በርካታ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች መመዝገባቸው ተገልጿል።

ምዝገባው እስከ ሰኔ 10 ድረስ መራዘሙ ተጠቁሟል።

በሳይበር ደህንነት እና በተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

የታለንት መስኮች ፦

- Cyber Security
- Cyber Development
- Embedded Systems
- Aerospace ሲሆኑ ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ1 ወር ይሰጣል።

ተመራቂዎች ፦

° #እንደየችሎታቸው እና #እንደስራዎቻቸው ከተለያዩ ባለሀብቶች ጋር የማስተሳሰር፤

° ኢመደአን (INSA) ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተቀጥረው መስራት የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚማቻች ከተቋሙ ተሰምቷል።

የመመዝገቢያ ፖርታል ፦ https://talent.insa.gov.et

NB. እድሜ ፦ ከ11 አመት ጀምሮ ( #ኢትዮጵያውያን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#INSA የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ያዘጋጀው የ2016 ዓ/ም “ ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ” ፕሮግራም ምዝገባ እስከ ሰኔ 10/2016 ዓ/ም ድረስ መራዘሙን አሳውቋል። እስካሁን በርካታ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች መመዝገባቸው ተገልጿል። ምዝገባው እስከ ሰኔ 10 ድረስ መራዘሙ ተጠቁሟል። በሳይበር ደህንነት እና በተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች…
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ባዘጋጀው የ2016 ዓ/ም “ ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ” ፕሮግራም ላይ ተመዝግበው ለ3ኛ ዙር ፈተና ያለፉ ነዋሪነታቸውም በአዲስ አበባ ከተማ ለሆኑ ፈተናው የሚሰጠው ከማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም እስከ ዓርብ ሐምሌ 12/2016 ዓ/ም መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

ወደ 3ኛው ዙር ፈተና ያለፉ ስም ዝርዝር በ ' INSA የሳይበር ታለንት ማእክል ' የቴሌግራም አድራሻ ➡️ https://t.iss.one/cteinsa ላይ በመግባት ማየት እንደሚቻልም ተገልጿል። #INSA

@tikvahethiopia