TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመፈፀም ተጠርጥረው በቀረቡ ግለሰቦች ላይ በምስክርነት የቀረቡ ግለሰቦችን #ፎቶ_በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲያሰራጩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ሁለቱ ግለሰቦች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ፍርድ ቤቱ በድብቅ በመግባት ምስክሮችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ድረገጽ ላይ ሲያሰራጩ ነበር ተብለው #የተጠረጠሩ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው በአሁን ወቅት ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን፥ በነገው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ፍጽመዋል ተብለው በምርመራ ላይ በሚገኙ ግለሰቦች ምስክርነት በመስጠት በፍርድ ቤት ቅድመ መርመራ ላይ እያሉ ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ #በማሰራጨት ስጋት ለመፍጠርና እንዲሸሹ ለማደረረግ መሞከራቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ፖሊስም በአሁኑ ወቅት የምስክሮችን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር በቂ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የተመለከተው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፎቶ:የመቐለ 70 እንድርታ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች☝️ #ጋንታመቐለ70እንድርታ #Congratulations🏆🥇

🗞ቀን ሰኔ 30/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የመጨረሻ ተጨማሪ 3 ቀን ሰጥተናል " - ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 222 ግለሰቦች እስካሁን የወሰዱትን ገንዘብ መመልስ እንዳለጀመሩና እነዚህ ግለሰቦች ጋር ያለው ገንዘብ 4,034,979 ብር ከ75 ሳንቲም መሆኑን ገልጿል። ባንኩ አሁንም ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ የመጨረሻ የ3 ቀናት ስለመስጡትን አሳውቋል። ባንኩ ከዚህ ቀደም ሙሉ በሙሉና በከፊል ገንዘብ ያለመለሱ እንዲመልሱ 2 ጊዜ የመጨረሻ…
#ፎቶ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108 ሺህ እስከ 305 ሺህ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ " እስካሁን አልመለሱልኝም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ ይፋ አደረገ።

ወደዚህ እርምጃ ከመግባቱ በፊት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁን አስታውሷል።

በዚሁ መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ ይፋ ማድረጉን ገልጿል።

አሁንም ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም የተራዘመውን የገንዘብ መመላሽ ዕድል ተጠቅመው ገንዘብ ያልመለሱ እንዲመልሱ አስጠንቅቋል።

በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ እንደሚያቀርብም ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፎቶ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ121 ሺህ እስከ 95 ሺህ ገንዘብ ያለአግባብ የወሰዱና እስካሁን ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ አሰራጨ።

በትላንትናው ዕለት 108 ሺህ እስከ 305 ሺህ ገንዘብ ወስደው ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ ማሰራጨቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፎቶ ⬆️ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ደረጃ እያካሄደው የሚገኘውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት 3ኛ ቀን መርሀ ግብር ዛሬ አከናውኗል።

ዛሬ በከተማ ደረጃ " #ታዋቂ#ተጽዕኖ_ፈጣሪ " ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ተገኝተው በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ስለ ሂደቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።

በተመሳሳይ በተለየ ቦታ ላይ ከ112 ወረዳዎች ከ11 የህብረተሰብ የተወጣጡ ተሳታፊዎች በየማኅበረሰብ ክፍላቸውን አጀንዳዎችን የለዩ  ሲሆን የሚወክሏቸውን 121 ተሳታፊዎች መርጠዋል።

ነገ ጠቅላይ የሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶችና ዛሬ የተመረጡ 121 ተሳታፊዎች ፤ መግለጫ የተሰጣቸው ተባባሪ አካላት በድምሩ ከ3 ሺ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ሀገራዊ የመክፈቻ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

@tikvahethiopia
#ፎቶ

አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲዮም ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ በኋላ እጅግ ከፍተኛ የተመልካች ቁጥር ተገኝቶበታል የተባለለትን የእግር ኳስ ፍልሚያ ዛሬ አስተናገደ።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ " #የኢትዮጵያ_ዋንጫ " የፍጻሜ ፍልሚያ ተደርጓል።

በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ፥ ወላይታ ዲቻን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።

የአዲስ አበባ ስታዲዮምም ከጫፍ እስከ ጫፍ በእግር ኳስ ተመልካች ተሞልቶ ነበር።

ስታዲዮሙ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ በዚህ ልክ እጅግ የበዛ ተመልካች አላስተናገደም ተብሏል።

ላለፉት ዓመታት እድሳት ሲደረግለትም ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ ከእድሳቱ በኃላ ለህዝብ ክፍት ተደረጎ በተካሄደው በዛሬው የፍጻሜ ጨዋታ በደጋፊዎች የተወሰኑ ወንበሮች የተነቃቀሉ ሲሆን የተጠባባቂ ተጫዋጮች ወንበሮችም ላይም ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

ከቀናት በፊት ጨዋታውን አስመልክቶ በተዘጋጀ የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ፥ " ስታዲየም ውስጥ ያሉ ንብረቶች የህዝብ ሀብትና የመንግስት ንብረት ናቸው ፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል ስሜታዊነት ባይጎላ " ሲሉ የአደራ መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

More : @tikvahethsport

@tikvahethiopia