TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoSHE

በግል ተቋማት የህክምና መስኮችን ለመማር አነስተኛው የመቁረጫ ነጥብ (ከተፈጥሮ ሣይንስ መስክ ለሚመጡ ብቻ) ለሁለቱም ፆታ 450ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#MoSHE

በ2013 ዓ/ም 147,640 (88,153 ወንድ ፤ 59,487 ሴት) ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ። እነዚህ ተማሪዎች በ46ቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ ይደረግላቸዋል።

በተጨማሪም በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ መቀየር እንደሚቻል MoSHE አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦ - በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። - በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (#MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ…
#ማስተካከያ

ትላንት ይፋ በተደረገው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመቁረጫ ነጥብ ላይ የተደረገ ማስተካከያ (መስማት ለተሳናቸው እና ለአይነስውራን) እንደሚከተለው ቀርቧል።

ተፈጥሮ ሳይንስ ፦

- መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 275 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

ማህበራዊ ሳይንስ ፦

- መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 265 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- ለአይነስውራን ወንድ ተማሪዎች 240 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- ለአይነስውራን ሴት ተማሪዎች 235 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

መረጀውን ያገኘነው ከ #MoSHE ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MoSHE

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2013 ዓ/ም አዲስ የዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫቻውን በዩኒቨርስቲዎች ልየታ መሰረት እንዲያስተካክሉ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን ያንብቡ https://telegra.ph/MoSHE-04-16 ወይም ከላይ በቪድዮ የተያያዘው ይመልከቱ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የዩኒቨርሲቲ ምደባ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከዛሬ ሚያዝያ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይፋ ሆኗል።

በመሆኑም ተማሪዎች ከታች በተገለጸዉ የበየነ መረብ ጠቋሚ በመግባት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ ይችላሉ።

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተብሏል።

• ዉጤት ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፡- https://result.neaea.gov.et/Home/Placement

• ቅሬታ ለማቅረብ መግቢያ ዌብሳይት (በአካል መምጣት አያስፈልግም)፡- https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7

#MoSHE

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#MoSHE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት የምርምር፤ አፕላይድ ሳይንስ፣ ኮምፕሬሄንሲቭ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ቴክኒካል በሚል ከለያቸው ውስጥ የትኞቹ የቅድመ ምዘና ፈተና ይሰጣሉ ?

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በመባል ከተለዩት ፦
- ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ከኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ውጪ ምንም አይነት የቅድመ ምዘና ፈተና እንደማይሰጥ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለ @tikvahuniversity ገልጿል።

ሚኒስቴሩ አሁን ላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ እንደሚገቡ ነው የገለፀው፤ ሆኖም የመጀመሪያ ዓመት (freshman) ትምህርታቸውን አጠናቀው የትምህርት ክፍል ምርጫ ሲያደርጉ የምዘና ፈተና ሊወስዱ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በተጨማሪ መረጃ ፦ የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መኩሪያ ንጋቱ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጠዋል።

"የምንሰጠው ስልጠና 50 በመቶው የተግባር ስልጠና በመሆኑ ብዙ ተማሪዎችን መቀበል አንችልም" ያሉት ኃላፊው፤ ስልጠናው ብዙ ሰርቶ ማሳያ ማዕከላና ከፍተኛ ሃብት እንደሚጠይቅ ነው የገለፁት።

#CARD #TikvahUniversity

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#MoSHE

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተው የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ወደተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ እንደሚደረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።

የዘንድሮውን የመመዘኛ ፈተና ካለፉት ከ147 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 206 ተማሪዎች በሚፈልጉት የትምህርት መስክ እና የትምህርት ተቋም እንዲመደቡ መደረጉን ተገልጿል።

ከምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታ ካቀረቡ 23 ሺህ በላይ ተማሪዎች መካከልም ከ1 ሺህ 800 በላይ የሚሆኑት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ የምደባ ማስተካከያ ተደርጎላቸዋል።

የትምህርት መስክ ምርጫን አስመልክቶ በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረም 386 ተማሪዎች በመረጡት ዘርፍ እንዲመደቡ ተደርጓል ተብሏል።

ከፍተኛ የጤና እክል ያለባቸው፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች ፣ ነፍሰ ጡር እና ከሁለት አመት በታች ልጅ ያላቸው እናቶች ፣ አካል ጉዳተኞች እና ከአርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ቅሬታን በማየት በቂ ማስረጃ ላቀረቡት አዎንታዊ ምላሽ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል ፦ የትምህርት ተቋማትን ምርጫ በሚመለከት ርቀትን፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መሰረት አድርገው የቀረቡ ጥያቄዎችን ውድቅ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ማሳወቁን ኢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvagethiopiaBOT
#MoSHE

የኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወስደዉ ቅሬታ ያቀረቡ ተማሪዎች ዳግም ምደባ ከሰኞ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በበየነ መረብ መመልከት ይችላሉ ብሏል፡፡

የ2013 አዲስ ዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30 በየተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ይጠራሉ።

@tikvahethiopia
#MoSHE

የኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው ደብዳቤ #ሀሰተኛ ነው አለ።

ዛሬ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ለደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ እንደተጻፈ የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ ነው።

ደብዳቤው “የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት” የሚል አርዕስት ያለው ሲሆን ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እውቅና ውጭ ምደባ ማካሄዱን እንዲያቆም የሚያስጠነቅቅ ይዘት አለው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶን ለ "ኢትዮጵያ ቼክ" በሰጡት ቃል ደብዳቤው ሀሰተኛ መሆኑ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ፥ ደብዳቤው ተጻፈ በተባለበት የታሕሳስ ወር የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ገና መሰጠት አልተጀመረም ነበር ብለዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የ2012 ዓ.ም ፈተና ከካቲት 19 ጀምሮ እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን ውጤቱ ይፋ የተደረገው በመጋቢት ወር አጋማሽ እንደነበር አስታውሰዋል።

ሚኒስትሩ ፥ የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምደባ በሚያዚያ ወር የተከነወነ መሆኑ በመግለፅ ደብዳቤው ተጻፈ በተባለበት ታሕሳስ ወር ምንም አይነት የተማሪዎች ምደባ እንዳልነበር አስረድተዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ደብዳቤውን እርሳቸው እንዳልጻፉት ገልጸዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል በታህሳስ ወር የተማሪዎችን ምደባ የተመለከተ ደብዳቤ ሊጻፍ እንደማይችል አክለዋል።

ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ማምሻው በፌስቡክ ገጹ በለጠፈው አጠር ያለ መልዕክት “ዩኒቨርስቲያችንን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጩ ወሬዎች አሳሳችና የውሸት መሆናቸውን እንገልጻለን” ብሏል።

#ኢትዮጵያቼክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በትግራይ በሚገኙት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልጆቻቸውን ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች ሙሉ በሙሉ ኔትዎርክ በመቋጠረጡ ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ተማሪዎች ስላሉበት ሁኔታም በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ልጃቸውን ልከው የሚያስተምሩ የቲክቫህ አባል፥ ስላልጃቸው ደህንነት ማወቅ ባለመቻላቸው በከፍተኛ ሁኔታ…
#MoSHE

የኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻው በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ላሉ ተማሪዎች ቤተሰቦች አጭር መልዕክት አሰራጭቷል።

ሚኒስቴሩ በመልዕክቱ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት እና የተቋማት አመራሮች ጋር እየመከረ እንደሚገኝ ገልጿል።

የተማሪዎች ቤተሰቦችም በትዕግሥት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

@tikvahethiopia