TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሪልስቴት #አዲስአበባ

° “ ብራችንን እኔ አውጥተን ተሰቃየን ” - የኖህ ሪልስቴት ቤት ገዥዎች

° “ የመብራት፣ የውሃ፣ የውሃ ታንከር ጥያቄ አለ ትክክል ነው ” - ኖህ ሪልስቴት

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በኖህ ሪልስቴት ' የኖህ አያት ግሪን ፖርክ ቤት ' ገዢዎች ኖህ የገባውን ውል በመዘንጋት የቤት መሠረተ ልማቶችን እያሟላ እንዳልሆነ እና በጠበቃቸው በኩል ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ የገቡበት ቤት፦
- ውሃ፣
- መብራት፣
- ጀነሬተር
- የውሃ ታንከር የሚባሉ መሠረት ልማቶች እንደሌሉ ገልጸዋል።

ቤት ገዢዎቹ ከዚህ ቀደም፣ “ ቅሬታ ባቀረብንበት ወቅት የኖህ ጠበቃ በ1 ወር ከ 15 ቀን ጊዜ ውስጥ የጋራ መሠረተ ልማቶች አጠናቀው እንደሚያስረክቡ ቃል ተገብቶልን ነበር ” ሲሉ አስታውቀዋል።

“ እስካሁን እንኳን ሊጨርሱ ምንም እንቅስቃሴ የለም ” ብለው፣ “ ቤት ውስጥ የገቡ ቤት ገዢዎች ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል። መብራት የለም፣ ውሃ የለም፣ ውሃ ታንከር የለም ” በማለት አማረዋል።

“ እነዚህ መሰረተ ልማቶችን ውላችን ላይ አሟልተው እንደሚሰጡን ተስማምተን ነው ቤቱን የገዛነው። ኖህ ውሉን ጥሷል ” ነው ያሉት።

“ ይባስ ብሎ ቤት ገዢ #የቤት_ክራይ_ሽሽት ወደገዛው ቤቱ መሰረታዊ ነገር ባልተሟላበት ሁኔታ ለመግባት ተገዶ መብራት በሳይቱ ዙርያ ካሉ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ለመቀጠል ተገዷል ” ሲሉ አክለዋል።

“ ግቢው በተጠላለፈ የኤሌትሪክ ገመድ በገመድ ሆኗል ” ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ “ ይህ ለሚኖሩት ሰዎችም ሆነ ለልጆቻቸው ትልቅ አደጋ ይፈጥራል ” ሲሉ አስረድተዋል።

ሁነቱን የሚያሳይ ቪዲዮም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

በጠበቃቸው በኩል ኖህ ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልሰጣቸው አስረድተው " የመፍትሄ ያለህ " ብለዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ጠበቃቸው ለኖህ ሪልስቴት የጻፈው ደብዳቤ ፥ ኖህ የቤቶቹን መሠረተ ልማት እያሟላ እንዳልሆነ፣ ምላሽ እንዲሰጥ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳልሰጠ ያትታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ላነሷቸው እያንዳንዱ የቅሬታ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ ኖህ ሪልስቴትን ጠይቋል።

የድርጅቱ የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ አቶ ዮሴፍ ደስታ በሰጡት ቃል፣ “ የመብራት፣ የውሃ፣ የውሃ ታንከር ጥያቄ አለ ትክክል ነው ” ብለዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-10

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia