TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት  #አዲስአበባ

ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች ይኖራሉ።

ስለሆነም ነገ ለስራ፣ ለቤተሰብ ለጓደኛ ጥየቃ ለሌላም ጉዳዮች ፕሮግራም የያዛችሁ ፕሮግራማችሁን ከልሱ።

መንገድ የሚዘጋው " ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም " በሚል የጎዳና ላይ ሩጫ ስለሚካሄድ ነው።

ሩጫው መነሻውን መስቀል አደባባይ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ከዛም በባምቢስ፣ ዑራኤል አደባባይ ወደ ቀኝ፣ ፒኮክ መናፈሻ ፣ ሰላም መንገድ ፣ በወሎ ሰፈር ፣ ደንበል ፣ ፍላሚንጎ በማድረግ መስቀል አደባባይ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

በዚህም  ፦
- ከ22 ወደ ዘሪሁን ህንፃ
- ከዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ
- ከአትላስ መብራት ወደ ዑራኤል አደባባይ
- ከቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ወደ ወሎ ሠፈር
- ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ
- ከኤግዚብሽን ወደ ፊላሚንጎ
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቴሌ ማቋረጫ (ክቡ) ባንክ ወደ ስታድየም
- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከካዛንቺስ ሼል (ኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል) ወደ ባምቢስ
- ከዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:30 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ከዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በተጠቀሱ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

በኮሪደር ስራ ምክንያት ፦

➡️ ከፊጋ መስመር ወደ ቀኝ ታጥፎ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

➡️ ከጃክሮስ መስመር በኩል መብራቱን ተሻግሮ ወደ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

➡️ ከኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስቴር ጫፍ ታጥፎ ወደ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት አንስቶ ሙሉ ቀን እና ምሽት ለማንኛውም ተሽከርካሪ ዝግ እንደሆኑ ተገልጿል።

ሌላው ፤ ከአያት ወደ መገናኛ እና ከመገናኛ ወደ አያት ቀጥታ ማለፍ እንጂ አደባባዩን መዞርም ሆነ ማቋረጥ የተከለከለ ነው ተብሏል።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙም መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው ከአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሻሻሉ የቅጣት እርከኖች ፦

🗑 ለማንኛውም ግለሰብ/ድርጅት

- ደረቅ ቆሻሻ በግቢው ውስጥ በአግባቡ አለመያዝ፤ በዓይነት አለመለየት፤ ማዝረክረክ፤ ለጤናና የአካባቢ ገጽታ በሚጎዳ መልኩ ማከማቸት፤ ለግለሰብ 2 ሺ ብር ለድርጅት 50 ሺ ብር ቅጣት

- የሲጋራ ቁርጥራጭ፣ የሶፍት ወረቀት፣ ፌስታል የመሳሰሉት ጥቃቅን ደረቅ ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ ወይም በፓርኮች፣ በአረንጓዴ ቦታ፣ በኮሪደር ከጣለ 2 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከመኖሪያ ቤት ወይም ከድርጅት ግቢ ውጭ ያለውን የአካባቢ ንጹህና አረንጓዴ አድርጎ አለመጠበቅ ከመኖሪያ ቤት አጥር ግቢ ውጭ እስከ 5 ሜትር ርቀት አለማጽዳት፤ 20 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከድርጅት/ተቋም አጥር ግቢ ውጭ እስከ 10 ሜትር አለማጽዳት፤ 100 ሺ ብር ቅጣት

- ወቅታዊና ልዩ ዝግጅት አከናውኖ በዓሉ ሲጠናቀቅ በዕለቱና ወዲያው ዝግጅቱ የተከናወነበትን አካባቢ ከቆሻሻ ያላጸዳ የፕሮግራሙ አዘጋጅ፤ 50 ሺ ብር ቅጣት

- ዓመታዊ፤ ወርሃዊና ሳምንታዊ የእምነት በዓላት ሲከናወኑ ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ የዝግጅቱ ባለቤት በዕለቱና ወዲያው አካባቢውን ካላጸዳ፤ 20 ሺ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

🗑 ለጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት/ማኅበራት፦

- ማኅበሩ ደረቅ ቆሻሻ ሲሰበስብ ገጽታ ካበላሸ 25 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጭ የአገልግሎት ክፍያ ከደንበኛው ከተቀበለ  50 ሺ ብር ቅጣት፤

- ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦታዎችን እስከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱ ካላደረገ 50 ሺ ብር ቅጣት ይጣልበታል።

Credit ➡️ @tikvahethmagzine

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት

" ከዛሬ ጀምሮ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ የተቃራኒ ጉዞ ተከልክሏል " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

በአዲስ አበባ፣ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ ድረስ በስራ የመውጫ እና የመግቢያ ሰዓቶች ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ በሚል በጊዜያዊ መፍትሄነት ከአያት አደባባይ እስከ ሴንቸሪ ሞል በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ ተፈቅዶ ነበር።

ነገር ግን መጨናነቁን ይፈጥር የነበረው የሳዕሊተ ምህረት አደባባይ በመቀየሩ ከዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

አሽከርካሪዎች ይሄን ተገንዝበው የመደበኛ የጉዞ መስመሮችን ብቻ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#AddisAbaba #TMA

#TikvahEthiopia
@TikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት🚨

በአዲስ አበባ የጭነት ፣ ማሽነሪዎችን እና መሰል ተሸከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 149/2016 ምን ይላል ?

- መመሪያው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ክልል በሚገቡና በከተማ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ከተማዋን አቋርጠው በሚያልፉ የመጫን አቅማቸው ከ1 ቶን ወይም ከ1ዐ ኩንታል በላይ የሆኑ የተለያዩ የፈሳሽና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 3፡00 ሰዓት ከሰዓት በኃላ ከቀኑ 10፡30 እስከ ምሽቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ፣ ጭነት መጫንም ሆነ ማራገፍ እንዲሁም በዋና ዋና የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ መቆም የተከለከለ ነው፡፡

- በዚህ መመሪያ መሠረት ወደ ከተማ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የተከለከለ የጭነት ተሽከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ወደ ከተማ ለመግባት በእንቅስቃሴ ላይ እያለ የሰዓት ገደቡ ቢደርስበት በከተማዋ መግቢያ በሮች ላይ ከዋና መንገድ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ የአካባቢውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማያውክ መልኩ በመቆም የሰዓት ገደቡ እስኪያልፍ መጠበቅ አለበት።

- ማንኛውም የጭነት ተሽከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በከተማ ውስጥ በእንቅስቃሴ ላይ እያለ በዚህ መመሪያ የተደነገገው የጊዜ ገደብ ቢደርስበት የአካባቢውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማያውክ መልኩ ከመንገድ በመውጣት መቆም አለበት።

- በዚህ መመሪያ የተደነገገው የሰዓት ገደብ #እሁድ እና #የበዓል_ቀናት ላይ ተግባራዊ የማይደረግ በመሆኑ ማናቸውም የጭነት ተሸከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ፣ ጭነት መጫን ሆነ ማራገፍ ይችላል፡፡

የሰዓት ገደብ የማይመለከታቸው ተሽከርካሪዎች የትኞቹ ናቸው ?

1. ሰሌዳቸው በሀገር መከላከያ ወይም በፖሊስ የተመዘገቡ የሀገር መከላከያ እና ሌሎች የፀጥታ ስራዎችን የሚያከናወኑ ከባድና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች፤

2. በህግ መሠረት የድንገተኛ አደጋ ተሸከርካሪዎች ተብለው የተለዩ የድንገተኛ አደጋ የሚሰሩ ቀላልና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች፤

3. ነዳጅ የሚያመላልሱ ቦቴዎች

አስተዳደራዊ ቅጣቱ ምን ይመስላል ?

🔵 በተከለከለ ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ በመግባትና በዋና ዋና መንገዶች ላይ የቆመ ብር 10,000 (አስር ሺህ ) ይቀጣል፡፡

🔵 በዋና ዋና መንገድ ላይ የተንቀሳቀሰም ሆነ የጭነት መጫንና ማውረድ ተግባር የፈፀመ ወይም የኮንስትራክሽን ስራ የሰራ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) ይቀጣል፡፡

🔵 በመመሪያው ላይ የተደነገገወን የሰዓት ገደብ በመተላለፍ ከተቀጣ በኃላ ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋቱን በመድገም የተገኘ ማንኛውም ሰው ከላይ የተገለፀውን ቅጣት በእጥፍ ይከፍላል፡፡

NB. በተከለከለው ሰዓት በከተማው ውስጥ ሲንቀሳቃስ በመገኘቱ ቅጣት የተጣለበት አሸከርካሪ ሰዓቱ ሳይደርስ የቅጣት ወረቀት ይዞ በተከለከለው ሰዓት እንዲንቀሳቀስ አይፈቀድለትም። የትራፊክ ተቆጣጣሪው ፍሰት በማያሰናክል ቦታ ላይ ተሸከርካሪው እንዲቆም በማድረግ ቅጣቱን እንዲከፍል ማድረግ አለበት፡፡

🗓 ይህ መመሪያ ከመስከረም 2 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ውስጥ ከነገ ማለዳ 12 ሠዓት እስከ ዓርብ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ።

የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ፥ " ለመስቀል ደመራ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ሲባል ከመስከረም 16 እና 17 ቀን 2017 ዓ.ም ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ በመዲናዋ የሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት ተከልክሏል " ሲል አሳውቋል።

የትራንስፖርትና የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የትራፊክ ፖሊሶች አፈፃፀሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል።

መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የሚከተሉት ናቸው።

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ

- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

- ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ይዘጋል።

በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ይችላል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት🚨

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡

መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡

በዚህም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

መድኃኒቱ ' ሻይንፋርም ' በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ነው።

(የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት🚨 የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡ መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡ በዚህም ይህን መድኃኒት…
#እንድታውቁት🚨

የትኛው የወባ መድኃኒት ነው አትጠቀሙት የተባለው ?

አርቲሜተር የተባለ በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት /Arthemeter 80 mg/ml injection, Batch No. 231104SPF, manufacture Date; 11/2023 supplied by Shinepharm, China በተደረገ የገበያ ላይ ቅኝት የተገኘ እና በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ከገበያም ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሸ Arthemeter የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ይህን መድኃኒት ነው የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ማሳሰቢያ የተላለፈው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

ከኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ጋር በተያያዘ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 25/ 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል ፤ ይህን ተከትሎ የሚከተሉት መንገዶች ይዘጋሉ።

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ፤

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፤

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፤

- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)፤

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ፤

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፤

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ፤

- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ፤

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፤

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ፤

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ፤


ከመስከረም 24/ 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ይችላል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መገናኛ " የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል ፤ ለገንቢው እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው 45 ቀናት ነው " - አቶ ጥራቱ በየነ ከፍተኛ መጨናነቅ ባለበት " መገናኛ ' አካባቢ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል። በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ፣ መኪና የሚበዛበትና የሚገናኝበት ፣ እጅግ በርካታ እግረኞችም የሚንቀሳቀሱበት…
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለው የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ይታወቃል።

በመሆኑም በተለይ ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ ፤ ከቦሌ ወደ መገናኛ አደባባይ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን ተገልጿል።

እግረኞች በሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ በኩል ማለፍ ስለማይቻል በቦሌ ክ/ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ባለው የእግረኛ መንገድ እንዲጓዙ ተጠይቋል።

አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

#የአዲስአበባትራፊክማኔጅመንትባለስልጣን

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ የትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉ ተገልጿል።

1. መገናኛ ውስጥ ተርሚናል ሲሰጡ የነበሩ
ከመገናኛ - ቃሊቲ
ከመገናኛ - ሳሪስ
ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች
በጊዜያዊነት መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት እየተሰጠ ነው።

2. ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው
ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ)

3. ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች
ከመገናኛ - ገርጂ
ከመገናኛ-ጎሮ
ከመገናኛ - አያት እና
ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ ተዘዋውሮ በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት የሚሰጡ ማደያዎችና በመሰራጨት ላይ የሚገኝ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ከላይ ተያዟል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከነዳጅ ጋር በተያያዘ የተገልጋችን እንግልት ለመቀነስ ሲባል በየዕለቱ ነዳጅ ያለባቸውን ማደያዎች ይፋ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል።

ዛሬ በአንዳንድ ማደያዎች ረዘም ያለ ሰልፍ መኖሩን ተዘዋውረን ለማየት ችለናል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ለ24ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ነው።

ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ የሚዘጉት መንገዶች ፦

- ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ )
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )
- ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )
- ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )
- ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )
- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ )
- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ )
- ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ )
- ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
- ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ )
- ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )
- ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
- ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )
- ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )
- ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
- ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
- ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን (ጥቁር አንበሳ ሼል)
- ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ) ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ይዘጋሉ።

ፖሊስ " ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ ይኖራል " ብሏል።

" ከውድድሩ ዓላማ ውጪ ህገ-ወጥ ተግባራትንና መልእክቶችን ማስተላለፍ የውድድሩን መንፈስ የሚረብሽ ስለሆነ አዘጋጅ ተቋሙ እና ተሳታፊዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው " ሲልም አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች አገልግሎት ለማግኘት " ፋይዳ " ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ተደርጎ እየተሰራበት ነው።

@tikvahethiopia