TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሀርጌሳ " ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል። ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ…
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ

የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ #የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ (MOU) ይዘት ምን ይላል ?

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦

- #ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ስታደርግ እንደነበረው፤ ከሶማሌላንድም ጋር ከዚህ በፊት እንደነበረው አይነት ስምምነቶችን ያነሳና ይሄ ስምምነት ወደተሟላ ደረጃ መድረስ እንዳለበት ያስቀምጣል።

- ኢትዮጵያ አሁን ያለባትን ስጋት እንድትቀርፍ የህዝብ እድገቷን ፣ የኢኮኖሚ እድገቷን የሚመጥን አካባቢው ካለው የሁከት ተጋላጭነት የራሷን ደህንነት እንዲሁም የቀጠናውን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ሚና እንዲኖራት የሚያስችል እራሷ የምታለማውና የምትቆጣጠረው የተወሰነ የባህር በር ያስፈልጋታል የሚል ነው። ይህ ሚሊታሪ ቤዝ እና ማሪታይም / ኮሜርሻል አገልግሎት ነው።

- የሚሊታሪ እና የማሪታይም / ኮሜርሻል ቤዝ ቦታው አማካይ እንዲሆን ተሞክሯል።

- ቦታው በበርበራ እና በዛይላ መካከል የሚገኝ ስፍራ ነው። ለኢትዮጵያ ድንበር አጠር ያለና ለሚሰራውም መንገድ እና ባቡርም የቀለለ፣ ለጥበቃውም የተመቸ እንዲሆን ነው። " ሎጋያ " የተባለ ቦታ አለ ለድንበር ቅርብ እዛ ላይ እንሰጣችኃለን በሚል ተስማምተዋል።

- ርቀቱን በተመለከተ እነሱም እኛም ስንለው የነበረው ነበር አማካይ ላይ ተገናኝነትን በ20 ኪ/ሜ የሚሆን ቦታ ቤዝ ይኖረናል በዓለም አቀፍ ህጉ ውሃውንም ይጨምራል ፣ ከውሃው ወደ መሬት ያለውንም እንዲሁ።

- ከድንበር ወደሚመሰረተው ቤዝ የሚሄድ መንገድ ይሰራል።

- ጊዜው 50 ዓመት እንዲሆና ሲያልቅ የሚራዘምበትን አማራጭ ያስቀምጣል።

ምንድነው ኢትዮጵያ የምትሰጣቸው ?

የመንግሥት ፖሊሲ ግልፅ እንዳደረገው ከቴሌኮም ፣ ከኃይል ማመንጫ ፣ ከአየር መንገድ ... ብቻ አዋጭ ከሆኑ ተቋማት #እራሳችን በምንመራበት መንገድ ለሀገርም በሚጠቅም መልኩ #ድርሻ መስጠት ነው። ይሄ ለሶማሌላንድም የሚሰራ ነው። ምናልባት ከኤርትራ ፣ ከኬንያ ፣ ከጅቡቲ ስምምነት ቢደረግ ይሄ ይሰራል።

ፈጥኖ መግባባት ላይ የደረሰው #ከሶማሌላንድ ጋር ስለሆነ ነው እንጂ ንግግሩ ከሁሉም ሀገራት ጋር ይቀጥላል። የአሁኑ ብቻ በቂ ስላልሆነ ከሌላውም ጋር እንነጋገራለን።

በ50 ዓመቱ መግባቢያ ስምምነት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ይኖራቸዋል ብለናል። ድርሻው ስንትነው ? የሚለው ተዘርዝሮ አልተቀመጠም። እኛ ለእነሱ የምንከፍለው #ሊዝ / #ኪራይ ዋጋው ስንት ነው የሚለውን ገና አልጨረስንም። ስንጀምረው ስምምነት በሚሆን መንገድ ላይ ጀምረን እነዚህ ጉዳዮች ስላላለቁ ነው ወደ መግባቢያ ሰነድ (MOU) የተመለሰው።

ገና ዝርዝር ነገሮች ያስፈልጋሉ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትክክለኛ አቅሙ፣ በገበያ ዋጋ ሲተመን ስንት ነው የሚለው ዝርዝር ተሰርቶ ወደ ንግግር ይገባል። እኛ የምንሰጠው ስንትነው የሚለው በሊዝ ከሚገኘው ዋጋ አለመብለጡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

አሁን #በቀጠናው በሊዝ የተከራዩ በርካታ ሀገራት አሉ ፤ ጅቡቲ እንኳን በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት ቤዝ አላቸው በሊዝ የሚጠቀሙት ስለዚህ ትልቁን የሚከፍሉት ስንት ነው ? ለምን ? ትንሹን የሚከፍሉት ስንትነው ? ለምን ? አማካዩ ስንት ነው ? እኛ ካለን ቅርበትና ከምንሰጠው አገልግሎት ተያይዞ ስንት ነው የምንከፍለው የሚለው ይቀመጣል። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስንት ብንሰጥ ነው ተመጣጣኝ የሚሆነው የሚለው ዝርዝር ስራ ይፈልጋል። በዚህ ምክንያት ወደ MOU ተመልሷል።

በሌሎች ሴክተሮች ላይ የተሟላ ትብብር ማድረግ አለብን ፦
• በጤና ፣
• በትምህርት፣
• በውጭ ጉዳይ፣
• በከተማ ልማት
... በእነዚህ እራሳቸውን የቻሉ #ስምምነቶች መዘጋጀት አለባቸው ይሄም ገና አላለቀም።

በአጠቃላይ የመግባቢያ ሰነዱ ፦

* መሬት ከሶማሌላንድ በኪራን እንደምናገኝ
* መሬቱን እራሳችን እነምናለማው
* መሬቱን 50 ዓመታትን እንደምንገለገልበት ፤ እሱን የሚያስችል ክራዩንም የሚመጥን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ድርሻ #እንደምንሰጥ ይስቀምጣል።

ከዚህ ባለፈ ...

ለ30 ዓመታት #የተሟላ እውቅና ሳያገኙ ሀገር ሆነው ቆይተዋል። እውቅና ለማግኘት ይሞክራሉ ፤ ይሄን በተመለከተ የኢትዮጵያ አቋም ምን ይሆናል ? የሚለው ጉዳይ ይነሳል።

' ወደ ተሟላ ስምምነት ደርሶ፣ መሬቱን ተረክበን ሂደቱ ሲቋጭ እነሱ እውቅና ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት በተመለከተ ኢትዮጵያ #አቋም_ትወስዳለች የሚል አመላካች ነገሮች ነው ያሉት ሰነዱ።  '

አሁን ላይ ስምምነት ሆኖ አልተረከብንም ፣ ስምምነት ሆኖ አልሰጠንም። #መስማማት እንዳለብን ግን ተስማምተናል ፤ እሱንም በመግባቢያ ሰነድ ፈርመናል።

#AmbassadorRedwanHussein

@tikvahethiopia
#ሊዝ #አዲስአበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መሬትን በሊዝ ለማስተላለፍ 2ኛ ዙር ጨረታ አውጥቷል።

መሬትን በሊዝ የማስተላለፍ ተግባር ለአራት ዓመታት ከተቋረጠ በኋላ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል፡፡

2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታም ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም መውጣቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቢሮና ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ መረጃውን አግኝቷል።

በከተማዋ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መረጃ መሠረት፣ በ2ኛው ዙር ጨረታ 243 መሬት (ቦታ) የተዘጋጀ ሲሆን፣ እነዚህ ቦታዎችም በአስር ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው፡፡

በአራዳ ክ/ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ ፦
- በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
- በኮልፌ ቀራንዮ፣
- በአራዳ፣
- በአቃቂ ቃሊቲ፣
- በየካ፣
- በቦሌ፣
- በአዲስ ከተማ፣
- በቂርቆስ፣
- በጉለሌ እና በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎች በ2ኛው ዙር ጨረታ በሊዝ ሊተላለፉ እንደቀረቡ ታውቋል።

ከዚህ ቀደም አልሚዎች ተጫርተው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በሚተላለፉ የተለያዩ ቦታዎች ላይ “የይገባኛል” ጥያቄዎች ይነሱባቸው እንደነበር ነበር።

አሁን ለመተላለፍ የተዘጋጁ ቦታዎች ግን ከሶስተኛ ወገን ጥያቄ ነፃ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም.ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማዋ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ9 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ፣ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል ተብሏል፡፡

ተጫራቾች ቦታውን በአካል ቀርበው ለመመልከት ከፈለጉ በ16/8/16 ዓ.ም እና በ18/8/16 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 እና ከሰዓት በ8 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት ከፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኚዎች አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮና / ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዝርዝር የጨረታውን መረጃ ከታች (በቀጣይ ፖስት) እናያይዛለን።

@tikvahethiopia
#ሊዝ #አዲስአበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፤ በአራዳ ክፍለ ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ በ10 ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ የልማት ስራዎች የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ለ1 የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር መክፈል የግድ እንደሆነ ተነግሯል።

የጨረታው ሰነድ እስከ ሚያዚያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ እየተሸጠ እንደሚቆይም ታውቋል።

አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም ተብሏል። ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኘም ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል።

🔵 ከላይ ሙሉ የጨረታው ዝርዝር መረጃ የተያያዘ ሲሆን በአራዳ ክፍለ ከተማ ከተራ ቁጥር 5 - 13 ወረዳ 01 በሚል የተገለፁ ቦታዎች ትክክለኛ መገኛ " ወረዳ 05 " መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ  ጨረታ ተራዘመ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016…
#አዲስአበባ #ሊዝ

የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ይፋ ሆኗል።

• በአንድ ካሬ ሜትር አሸናፊ የሆነው ከፍተኛ ዋጋ 470 ሺህ ብር ሲሆን ዝቅተኛ 20 ሺህ 100 ብር ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የ2ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ተሰራጭቷል።

በጨረታው ዝቅተኛ ዋጋ የተመዘገበው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሲሆን ይህም በካሬ ሜትር 20 ሺህ 100 ብር ነው።

ከፍተኛው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካሬ ሜትር 470 ሺህ ብር እንደሆነ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በካሬ ሜትር 470 ሺህ ብር ያቀረበው " ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ት/ቤት " መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአሸናፊዎች ዝርዝር ላይ ተመልክቷል።

በአጠቃላይ 4 ሺህ 201 ተጫራቾች የጨረታ ሰንድ በኦንላን መግዛታቸው ተነግሯል። ከነዚህ ውስጥ 2 ሺ 972 ሰነዶች ተሟልተው ተመላሽ እንደተደረጉ ተገልጿል።

1ኛ የወጡ አሸናፊ ተጫራቾች በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም.ኤ ህንጻ  ላይ የአዲስ አበባ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የሊዝ ውል እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል።

1ኛ የወጡ ተጫራቾች ውል የማይፈጽሙ ከሆነ ዕድሉ 2ኛ ለወጡት ተጫራቾች ተላልፎ ይሰጣል።

@tikvahethiopia