TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የመምህራንድምጽ

" አይደለም ያለ ደመወዝ በደመወዝም እንኳን ኑሮን አልቻልነውም ፤ ደመወዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል " -  መምህራን
 
ከየካቲት ወር 2016 ጀምሮ #እየተቆራረጠ 50% ፣ 30% እየተከፈለ ቆይቶ እስከ የሰኔ ወር ሳይጨምር ውዝፍ ደመወዝ ከ70 እስከ 120% አልተከፈለንም ያሉ በጎፋ ዞን የአይዳ ፣ ገዜ ጎፋ እና ደምባ ጎፋ ወረዳ መምህራን ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ያለደሞዝ አይደለም በደሞዝም ኑሮን አልቻልነዉም " የሚሉት መምህራኑ " ስቃያችን መች ነዉ የሚያበቃው ? " ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር፥ " የመምህራኑን ድምጽ በተደጋጋሚ ለሚመለከተዉ አካል ሳሳዉቅ ቆይቻለሁ " ብሏል።

መምህራኑም አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል አቅርበው እንደነበርም አስረድቷል።

ነገር ግን የዞኑ አስተዳደር እና የትምህርት መምሪያው ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠቱ መምህራኑ የአመራሩን ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከሰምኑ እነዚህ መምህራን ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሠልፍ ለመጠየቅ ሲሞክሩ  የዞኑ መምህራን ማህበር ከአመራሩ ጋር ውይይት እያደረገ በመሆኑ ሠልፍ እንዳይወጡና በትዕግስት እንዲጠብቁ በማድረግ መመለሱን ማህበሩን አሳውቆናል።

ይሁና መምህራኑ ባልተደራጀ ሁኔታም ቢሆን ጥያቄ ለማቅረብ ወደተለያዩ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች መሄዳቸውና በዛም " በዚህ ደረጃ መቀጠል አንችልም ደሞዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል !! " በማለት ድምጻቸዉን ማሰማታቸዉ ተገልጿል።

እንዲህ አይነት ጥያቄዎች ካሁን በፊትም በሌሎች የክልሉ ዞኖች ውስጥም መስተዋላቸውን አንስተን ጥያቄ ያቀረብንላቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊዉ ዶክተር ታምራት ይገዙ ፤ "  ችግሩን እንደ ክልል ከየካቲት ወር ጀምሮ መቅረፍ ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሁን ላይ የመምህራንን ደሞዝ በተመለከተ አሰራሩ ዲሴንትራላይዝ ተደርጎ ለየዞኖቹ መሰጠቱን የገለጹት ኃላፊዉ " እኛ ቴክኒካል ድጋፍ እያደረግን ብቻ ነው ያለው " በማለት የደመወዝ ጉዳይ ለነሱ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

" ችግሩ በዚህ ደረጃ ከተስተዋለ ግን ገምግመን ድጋፍ የምንሰጥ ይሆናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM