TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

በትግራይ የክረምቱ ሃይለኛ ዝናብ ባስከተለው አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፋዋል።

በበርካታ የክልሉ አከባቢዎችም ከአሁን በፊት ታይቶ በማያውቅ መልኩ የመሬት መደርምስ አደጋ እየተከሰተ ነው።

ነሃሴ 17 እና 19/2016 ዓ.ም በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የሓውዜንና ብዘት ወረዳዎች የጣለ ሃይለኛ ዝናብና በጥልቅ ጉድጓድ በተጠራቀመ ውሃ የ7 እና 9 ዓመት እድሜ ህፃናት የሚገኙባቸው 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የሓውዜን ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ህፃናቱ በአከባቢያቸው በሚገኘው በጥልቅ ጉድጓድ በተጠራቀመ የዝናብ ውሃ ሊዋኙ ሲሉ ነው ለህልፈት የተዳረጉት። 

በዞኑ ብዘት ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት በሃይለኛ ዝናብ ምክንያት ቤታቸው በላያቸው ላይ ፈርሶ የ5 ልጆች አሳዳሪ የሆኑ ባልና ሚስት ወድያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

ልጆቻቸው እቤት ስላልነበሩ የሟቾች ቁጥር ሊቀንስ እንደቻለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከወረዳው ያጋኘው መረጃ ያሳያል።

ልጆቹ ወላጅ እናት አባታቸውን አጥተው በፈረሰ ቤት ሜዳ ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

ከአሁን በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።

በአላጀና ሰለዋ ወረዳዎች በሚገኙ አራት የቀበሌ ገበሬ ማህበራት ፣ በእንደርታና ሕንጣሎ ወረዳዋች ፣ በዓዴትና ፀለምቲ ወረዳዎች የመሬት መደርመስ አደጋ መከሰቱ ከአከባቢዎቹ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ🚨

“ በተለይ እንቅስቃሴያቸውንና ኑራቸውን አፋፍ ሥር ያደረጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ " - ኮሚሽኑ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በተለምዶ ሰላም ሰፈር አካባቢ 4 ሜትር ከሚገመት ከፍተኛ ቦታ በተከሰተ የአለት ናዳ 3 ሰዎች መሞታቸውን የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

አደጋው የደረሰው ዛሬ ነው።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ባደረጉት ጥረት የ8 ሰዎች ሕይወት ማትረፍ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
- የአደጋው ምንስኤ ምንድን ነው ?
- ይህ አደጋ በከተማዋ ሲከሰት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ?
- ማህበረሰቡ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት? የሚሉ ጥያቄዎችን ለኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ አቅርቧል፡፡

አቶ ንጋቱ ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ እንዲህ አይነት አደጋዎች በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እያጋጠሙ መሆኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሜትሮሎጅ ኢንስቲትዩትም የመሬት መንሸራተት፣ ጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም ስለሚችል ጥንቃቄ ይደረግ የሚል መረጃ ሲያስተላልፍ ነበር፡፡

ያልተጠበቀ ዝናብ ያጋጥማቸዋል የተባሉ ከተሞችን ሲጠቅስም አዲስ አበባም እዛ ውስጥ ተጠቅሳለች፡፡

በእርጥበት ምክንያት ናዳ፣ የአፈር መደርመስ ሊኖር ስለሚችል በተለይ እንቅስቃሴያቸውንና ኑራቸውን አፋፍ ሥር ያደረጉ ነዋሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ መፍትሄ ለመስጠት በሚደረገው ጥረትም የመፍትሄው አካል መሆን ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ሰዎችን ከቦታው ማንሳት ሊያስፈልግ ይችላል።

አዲስ አበባ ላይ የአለት ናዳ አደጋ አጋጥሞ አያውቅም፣ አላስታውስም፡፡ በእርግጥ ደረጃቸውን ያልጠበቁ፣ የአደጋ ደህንነት መስፈርት ሳይጠብቁ አፋፍ ላይ የተሰሩ ቤቶች ተንደው የሰው ሕይወት ጠፍቶ ያውቃል።

ጠሮ መስጂድ የሚባለው (አዲስ ከተማ ፍለ ከተማ ውስጥ) ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈበት ሁኔታ ነበር ከኮንስትራክሽን ጥራት ጋር በተያያዘ፡፡

ይሄኛው (የአሁኑ የአለት አደጋ) እዛው መሬቱ ጋር ተያይዞ የበቀለው አለት ከዝናብ ብዛት በመሬት መሸርሸር የሚያጋጥም ነው፡፡

የአለት አደጋውን መስንስኤ ማጣራት የሚጠይቅ ነው ግን ከክረምቱ ወቅት ጋር የሚያያዝ ሊሆን ይችላል ብለን እንገምታለን፡፡ አደጋ የደረሰባቸው መኖሪያ ቤቶቹ ከታች ነው ያሉት፤ አለቱ ደግሞ አፋፍ ላይ ነው ያለው፡፡ በግምት ወደ 4 ሜትር ከፍታ አለው፡፡

ብዙ ጊዜ አፋፍ ላይ ተንጠልጥለው ያሉ ቤቶች ላይ የመውደቅ እድልም አለው፡፡ የሰዎቹም የአኗኗር ሁኔታ፣ የቤቱ አቀማመጥና ደረጃ አስተዋጽኦ አድርጓል። ”


#TikvaEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Urgent🚨

በአማራ ክልል፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ፣ ጠለምት ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት አልፏል።

በርካቶችም ችግር ላይ ወድቀዋል፤ ተፈናቅለዋል።

ለተፈናቃዮቹ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል።

ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ወረዳው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርቧል።

የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ቃል ፦

“ አካባቢው ከዚህ ቀደም በድርቅ የተጠቃ ነው፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች ደግሞ ከ14, 400 በላይ እህል ያስፈልገናል።

የእርዳታ ምግብ ድጋፍ ፤ 480 ድንኳን / ሸራ ፣ እንደ ብረት ድስት፣ ሳፋ አይነት የቤት ቁሳቁሶች በአስቸኳይ የሚያስፈልጉ ናቸው። ”

#TikvahEthiopiaFamyAA

@tikvahethiopia
❤️

ከአሜሪካ ሃገር በመጡ ሐኪሞች የልብ ሕክምና ተልዕኮ (Mission) አገልግሎት እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የልብ ማዕከል-ኢትዮጵያ ውስጥ " ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ' በተሰኘ በአሜሪካን ሃገር በሚገኝ በዶ/ር ተስፋዬ ተሊላ እና ዶ/ር ኦብሲኔት መርዕድ የተመሰረተ የግብረ ሰናይ ድርጅት የነጻ የልብ ሕክምና ተልዕኮ አገልግሎት ከነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እየሰጠ ነው።

ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ የሕክምና ተልዕኮ መርሐግብር ነው።

የሕክምና አገልግሎቱ ከማዕከሉ በተጨማሪም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ100 በላይ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ታካሚዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ያቀደ ነው።

የሕክምና አገልግሎቱን ለመስጠት ከ17 በላይ የልብ ሕክምና ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የጤና ባለሞያዎች እየተሳተፉ ነው።

ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኦብሲኔት ፥ " በዚህ ዙር ደረት ሳይከፈት ከሚሰሩ ሕክምናዎች በተጨማሪ የልብ ቀዶ ሕክምና እና የልብ ምት ችግር ላለባቸው ሕሙማን የሚሰጡ ሕክምናዎች ተካተዋል " ብለዋል።

ድርጅቱ ለሕክምና ተልዕኮው ከ1.4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ለሕክምና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን አሰባስቦ ነው ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነው የጠቆሙት።

ወደፊት ተጨማሪ ተልዕኮዎችን እንደሚያካሂድ አመልክተዋል።

የልብ ማዕከል ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኅሩይ ዓሊ ፥ " በዚህ የሕክምና ተልዕኮ ላይ በርካታ ወረፋ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ሕሙማን ተጠቃሚ ናቸው። " ያሉ ሲሆን " ተልዕኮው ስኬታማ እንዲሆን ማዕከሉ ከዝግጅት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊ ሥራዎችን ሲሰራ ነበር ቆይቷል " ነው ያሉት።

#Ethiopia

@tikvahethiopia @thechfe
@heyonlinemarket

•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 37,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 25,000 Birr
•Meta Quest 2, 45,000 Birr
•Meta Quest 3, 73,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF #Tigray በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ። በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል። የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ…
#Tigray

" በቅርቡ ሁሉም ተቀባይነት ያላቸው ህጎችና አሰራሮች በመጣስ ጉባኤ አድርጊያሎህ የሚለው ህገ-ወጥ ቡድን በትግራይ ስርአት አልበኝነት እንዲስፋፋ እየሰራ ነው " ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሷል።

አስተዳደሩ ፥ ህዝብ ለማገልገል የሚያካሂዳቸው የመዋቅራዊ አደረጃጀት ማስተካከያዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የመንግስት ውሳኔና ተግባር የሚያደናቅፍ ማንኛውም አካል ሆነ ሃይል አልታገስም ብሏል።

" ህግና ስርዓት የሚጥስ አካል ሆነ ሃይል ህጋዊ አሰራር የተከተለ ተጠያቂነትና እርምጃ እንደሚወሰድበት ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቋል።

በአሁኑ ወቅት ማንኛውም የስልጣን ጥያቄ አለኝ የሚል ቡድን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ጠያቄውን ለሚመለከተው አደራዳሪ አካል   በሰላማዊ አግባብ የማቅረብ መብቱ ዝግ እንዳልሆነ ጠቁሟል።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንዲዳከም ሳያለሰልስ የሰራ ቡድን አሁን የሚደረጉት የስራ ምደባዎች ' ህጋዊ አይደሉም ' ብሎ በመቃወም ለዓመታት እስከ ታች በሰፋው ኔትወርክ እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል " ብሏል።

" ቡድኑ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተመደቡ አመራሮች ህጋዊ አይደሉም ተቀባይነት የላቸውም ' ከማለት አልፎ ባደራጀው ኔትወርክ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ በመውረድ ' እንዳትቀበሉዋቸው ' በማለት ህግ አልበኝነት እንዲነግስ በመንቀሳቀስ ላይ ነው " ሲል ከሷል።

" ህዝቡ ህገ-ወጥቶች ሃይ ሊላቸው ሊያስታግሳቸው ይገባል " ሲል አስገንዝቧክ።  

" ህዝቡ ተገቢውን  መንግስታዊ አገልግሎት እንዲያገኝ አልሞ የሚከናወነው የመዋቅር ማስተካከያ እርምጃ ተጠናክረው ይቀጥላሉ ፤ መንግስታዊ የመዋቅር ማስተካከያ እርምጃ በሚቃደናቅፍ አካል ሆነ ሃይል እርምጃ እንደሚወሰድ ህዝባችን ሊያውቀው ይገባል "  ሲል በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመራስ ጊዜዊ አስተዳደር አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
#Tigray

ዛሬ በአክሱም ከተማ የብዙዎች መነጋገሪየ የሆነ ፓለቲካዊ ክስተት ተከስቷል።

በመካከላቸው በተፈጠረው ፓለቲካዊ ልዩነት በርቀት በመግለጫዎች ሲጎነታተሉ የከረሙት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በዓመታዊው አክሱም ከተማ የዓይኒ ዋሪ በዓል አከባበር ላይ ተገናኝተዋል።

በመድረኩ በቅደም ተከተል ንግግር ያደረጉት ሁለቱ መሪዎች ከምር ይሁን ከአንገት በላይ በማይታወቅ የእጅ ሰላምታ ተጨባብጠዋል።

ከአክሱም ከተማ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከንግግራቸው በላይ አነጋገሪ የሆነው " በዓሉ ላይ እኔ ነኝ መገኘትና መሳተፍ ያለብኝ " የሚል ክርክርና ሰጣ ገባ መነሳቱ ነው።

ክርክርና ሰጣ ገባቸው የሃይማኖት አባቶች መሃል ገብተው አስማምተው ሁለቱም በመድረኩ እንዲገኙና ንግግር እንዲያደርጉ ለማሳመን የወሰደው ጊዜ ፕሮግራሙ ሳይጀመር ለሰዓታት እንዲራዘም ሆኗል።

ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት ሰጣ ገባ ደጋፊዎቻቸው ደረስ ዘልቆ እስከ አሁን ድረስ በማህበራዊ የትስስር ገፆ እያከራከረ ይገኛል።

ቀድመው ንግግር ያደረጉት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ድርጅታቸው በቅርቡ ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና አተገባበራቸው ያተኮረ ሲሆን ቀጥለው የተናገሩት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በንግግራቸው የጊዚያዊ  አስተዳደሩ የስራ አቅዶችና አንድነትን የሚመለከት ነበር። 

ፕሬዜዳንት ጌታቸው በስም ያልገለፁዋቸው " የውጭ  ጠላቶች " የሚያደርጉት ሙከራ ከትግራይ አቅም በላይ አይደለም ፤ ስለሆነም ከጨለማ ለመውጣት በአንድነት መጓዝ አለብን ብለዋል።

ለሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ትግራይ የነበሩት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ውጥረት መርገብ እንዳለበት ማሳሰባቸው መዘገባችን ይታወሳል። 

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia