TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል። በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል። በመንግስት…
#MoE #Placement

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል። ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።…
#MoE #Placement

🔴 " እስካሁን ድረስ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፎርም አልሞላንም ፤ ... ውጤት የመጣላቸውን ደግሞ ዝም ብለው መድበዋል " - ተማሪዎች

⚫️ " እውነት ነው ! ጉዳዩን ለክልል ብናሳውቅም መፍትሔ አልተገኘም " - አቶ ዘሪሁን ደርጫቦ

በ2016 ዓ/ም የ 12ኛ ክፍል መውጫ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያመጡ እና በሪሚድያል ፕሮግራም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያመሩ ተማሪዎች በተመደቡ መምህራን ፎርም እንዲሞሉ የት/ት ሚንስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።

በዚህም ሀሙስ ቀን ወደ ክፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ይሁንና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን አመካ ወረዳ ላይ በዲምቢቾ፣ ጌቻ እና ገነዶ ት/ት ቤቶችን እንዲሁም በጎምቦራ ወረዳ ሀቢቾ እና ቢሻና ትምህርት ቤቶች ፎርም አለመሙላታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት ጥቆማ ለማወቅ ተችሏል።

በወረዳው ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እስካሁን ፎርም እንዳልሞሉ እና ከመምህራኖቻቸው ' ሲስተም አስቸግሮናል ' የሚል ምላሽ እንዳገኙ የነገሩን ሲሆን ውጤት የመጣላቸው እንኳን ያልመረጡት እና ፍጹም ካላቸው ውጤት ጋር የማይገናኝ ዩኒቨርሲቲ እንደደረሳቸው ነግረውናል። 

በወረዳዎቹ ፎርሙን እንዲሞሉ የተወከሉት መምህራን ፎርሙን ለመሙላት ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት እንዳስቸገራቸውና መሙላት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

" እስከ ክልል ደውለን ለማሳወቅ ብንሞክርም ጥረታችን አልተሳካም " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዘሪሁን ደርጫቦ ነገሩ እውነት መሆኑን አረጋግጠዋል።

" እኚህ ብቻ ወረዳዎች አይደሉም ዛሬ ብቻ ከሻሸጎ፣ ሾኔ እና ሌሎችም ወረዳዎች እስከ 10 ከሚደርሱ ት/ትቤቶች ተደውሎልኛል" ብለውናል። 

ምክንያቱ ምን ይሆን ?

" የተማሪ ዳታ ሲሞላ በአምና user name ላይ ነበር እንዲሞላ የተደረገው የአምና ካልጠፋ / Delete ካልተደረገ በስተቀር አያስገባም እኔ ደግሞ በአምና ስገባ እኔን ያስገባኝ ቤንሻንጉል ላይ ነው የኔ አካውንት ካልጠፋ ሌላኛው ዞኑ ላይ መግባት አልችልም ማለት ነው የኔን አካውንት አጥፍታችሁ ዞኑ ላይ መልሱኝ ብዬ ለክልል ባሳውቅም ሳያደርጉ ቀርተዋል እዚህ ጋር ነው ክፍተቱ የተፈጠረው።

በዚህም ምንም ወረዳዎችን ላግዝ አልቻልኩም።

የትኛው ይሙላ አይሙላ የማውቀው ነገር የለም አድሚን ስትሆን አይደለ ሚያሳይህ እኔጋ የሚመጣው የቤንሻንጉል መረጃ ነው። ይህ እንዴት እንደሆነ አላውቅም ምናልባት ፌደራል ላይ መረጃ ሲገባ ሊሆን ይችላል ስህተቱ የተፈጠረው።

ምንም መረጃ ልንለዋወጥ አልቻልንም ሪሚድያል ሙሉ በሙሉ አልተሞላም ማለት ይችላል ክልል ላይ በተደጋጋሚ ለማናገር ሞክረን ነበር ነገር ግን አልተሳካም ከወረዳ ሲደወልልኝ ወደ ክልል እየላኳቸው ቆይቻለው " ብለዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia