TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

በሞያሌ ከተማ በጦር መሳሪያ በመታገዝ ከባድ የሰው #መግደል ሙከራና ግድያ የፈፀሙ ግለሰቦች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መሰረተ።

1ኛ ተከሳሽ ወታደር ማትያስ ሞጉሬ እና ሌሎች 5 ተከሳሾች በወንጅል ሕጉ አንቀጽ 27(1)፣32(1)(ለ) እና 539 (1) (ሀ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ሰውን ለመግደል በማሰብ መጋቢት 01 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት ሲሆን በሞያሌ ከተማ ልዩ ቦታው ሸዋ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በክስ መዝገቡ የተጠቀሰው 3ኛ ተከሳሽ ኮ/ል አብርሃ አረጋይ ማንኛውንም ጸጉረ ልውጥ ሰዎችን ተኩስ እና ግድሉ በማለት፣ ለ2ኛ ተከሳሽ አስር አለቃ ሀብታሙ ተገኝ፣ ለ4ኛ ተከሳሽ ወታደርር አብዱልፈታህ ዱቦ ለ5ኛ ተከሳሽ አስር አለቃ ስለሺ ሽናሞ እና ለ6ኛ ተከሳሽ አስር አለቃ አስደናቂ ወረና ትዕዛዝ በመስጠት ተከሳሾች በተለያዩ ሰዎች ላይ በክላሽ ጠመንጃ ጥይት በመተኮስ የአካል ጉዳት፣ የግድያ ሙከራና የግድያ ወንጅል በመፈፀማቸው በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የካቲት 28 ቀን 2011ዓ.ም በአንድ መዝገብ በ6ቱ ተከሳሾች ላይ 15 ክስችን መስርቷል፡፡

ተከሳሾች በመከላከያ እስር ቤት ለ 9ወራት በምርመራ ላይ ቆይተው ከወርሃ ጥቅምት2011 ዓ.ም ጀምሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቆይተዋል፡፡

አቃቤ ህግም በ1ኛ ተከሳሽ ላይ በሁለት የግድያ ሙከራና በአንድ ከባድ ግድያ፣ በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ በ3 ከባድ ግድያ በ1 ከባድ የግድያ ሙከራ፣ በሶስተኛ ተከሳሽ ላይ በ4 ከባድ የግድያ ሙከራ በ6 ከባድ ግድያዎች በ4 ተከሳሽ በአንድ ከባድ ግድያ በአንድ ከባድ ግድያ ሙከራ በ5 ተከሳሽ በ2 ከባድ የግድያ ሙከራና በ3 ከባድ ግድያ በ6 ተከሳሽ ላይ በአንድ ከባድ የግድያ ሙከራና በአንድ ከባድ ግድያ አቃቤ ሀግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

ተከሳሾች #ተከላካይ_ጠበቃ በግላቸው ማቆም እንደማይችሉና መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ለፍርድቤቱ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ፍርድቤቱም መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ፈቅዶ ለመጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም የክስ ሂደቱን ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia