TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የተዋናይ ጌታቸው እጅጉ (ባቡጂ) ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

ተዋናዩ  ከ60 በላይ ፊልሞች ላይ ተውኗል።

ቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ በወቅታዊና በማህበራዊ ፣ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳቡን ሲያካፍል ፤ ጠንካራ የራሱን ትችቶችም በድፍረት በመናገር ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በ “ብሩህ ንግድ ፈጠራ ሀሳብ ” ውድድር ከተመዘገቡ 1,375 ተሳታፊዎች መካከል 150 አሸናፊዎች 2 ሺህ ዶላር ለሚያሸልመው ለመጨረሻው ዙር ውድድር መለየታቸው ተነግሯል።

እነዚህ 150 ተወዳዳሪዎች መካከል በአንድ ማዕከል ሆነው በቀጣዮቹ ቀናት ስልጠና ይወስዳሉ።

ከ150ዎቹ ተወዳዳሪዎች መከካል በፈጠራ ሃሳባቸው ለሚያሸንፉ 50 ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው 2 ሺሕ ዶላር እንደሚሸለሙ ተመላክቷል፡፡

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-26

@tikvahethiopia
🔈 #እናትፓርቲ

እናት ፓርቲ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር በተያያዘ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው " መንግሥት እየተገበረው ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፍቱን መድኃኒት ሳይሆን በጫናና አጣብቂኝ የመጠ የሥርዓቱን እድሜ ማራዘሚያ ኪኒን ነው " ሲል ገልጾታል።

በዚሁ መግለጫው ላይ ፤ የሚፈራ ማኅበራዊ ቀውስ እንዳለ በማመላከት ይህ ቀውስ ሊታከም ከማይችልበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን እንደገና እንዲያጤነው አሳስቧል።

መንግሥት በግል ዘርፉና ማኅበረሰቡ ላይ የጫነውን እንቅፋቶች ሁሉ እየመረመረ በአስቸኳይ እንዲያነሳም ጠይቋል።

የሠራተኛውና ደሞዝተኛው የዛሬ 6 ዓመቱ የኑሮ ደረጃን የሚመልሰውን (የሚያስተካክለውን) የደሞዝ ጭማሪ በአስቸኳይ እንዲያደርግም መንግስትን ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርሶ እንዳይበላና አቅርቦት እንዳይጨምር የምርት ግብዓቶች (factors of production) ሁሉ ከካድሬ እጅ ወጥቶ አምራቹ/ባለቤቱ እንዲይዘውና እንዲያዝበት እንዲደረግም ፓርቲው እናሳስቧል።

እናት ፓርቲ በላከው መግለጫ ፤ " በአጠቃላይ ሲንከባለል የመጣውና አሁን የባሰበት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በካድሬዎች ሳይሆን በባለሞያዎች እንዲመራ በማድረግ ግልጽ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ እንዲቀመጥ እንጠይቀለን " ብሏል።

በተጨማሪ ፥ መንግሥት ራሱ ፈቅዶና ፈርሞ ያመጣው ፖሊሲ የፈጠረውን ምስቅልቅል በነጋዴው ማኅበረሰብ ላይ እያመካኙ ሱቅ ማሸግና እጅ መንሻ መቀበል ሥራዬ ብለው የያዙትን ባለስልጣኖቹን አደብ እንዲያስገዛ አሳስቧል።

ፓርቲው ፤ " መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ " ሁሉንም ድስት እኔ ካልጣድኩ " ማለቱን አቁሞና ከሁለገብ ተጫዋችነቱ ወጥቶ ወደ የመንግሥት ዳኝነቱ ብቻ እንዲገባ፤ " ነጻ ገበያን ተቀብያለሁ " ካለ በነጻነት መሥራትንና ሀብት ማፍራትንም እንዲቀበልና ዜጎች እድሜ ልካቸውን ሠርተው ያፈሩትን ንብረት ያለ ካሳ እያፈረሱ ሕዝብን ማደህየቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም " ሲልም በጥብቅ አሳስቧል።

#እናትፓርቲ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Tigray : በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤቨን ማሲንጋ ዛሬ መቐለ ገብተዋል።

ማሲንጋ መቐለ ሲደርሱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትል ፕሬዜዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ተቀብለዋቸዋል።

በቆይታቸው በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ፣ በወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ፣ በተፈናቃዮች መመለስ ጉዳይ ላይ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

ፎቶ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አብና🕯 " የ4ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል ፤ የ6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም ! " በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 10 ሰዎች ሞተዋል። የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ምን አሉ ? " የ4 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ፤ የቀሪ 6…
#አማራ #ጎንደር🕯

በአማራ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን 3 ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ እና የተጎዱ ሰዎች ቁጥር በዛሬው ዕለት ጨምሯል።

ሟች ወገኖቻችን 23 ደርሰዋል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችን ደግሞ  8 መድረሳቸው ተነግሯል።

ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችን አጠቃላይ ከ2 ሺህ 700 በላይ ናቸው።

አደጋው የደረሰው በዞኑ በጠለምት፣ በጃናሞራ፣ በአዲአርቃይና በየዳ ወረዳዎች በሚገኙ 11 የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ነው፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሰሜን ጎንደር ኮሚኒኬሽን ነው።

#አማራ #ሰሜንጎንደር

@tikvahethiopia
#ትግራይ

ባለፈው ሳምንት በትግራይ 2 ወረዳዎች የነበረውን ሃይለኛ ዝናብን ተከትሎ በተፈጠረው ከባድ ጎርፍ የ3 ሰው ህይወት ጠፍቷል።

በክልሉ ምስራቃዊ  ዞን ጉሎመኸዳ ወረዳ አዲስ ተስፋ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ደንጎሎ መንደር ነሃሴ 16/2016 ዓ.ም ሌሊት የዘነበው ከባድ ዝናብ ቤት አፈርሶ የአንድ ሰው ህወይት አሳጥቷል።

እሁድ ነሃሴ 19/2016 ዓ.ም በደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሕንጣሎ ወጀራት ወረዳ ዓዲ ቐይሕ ከተማ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ሃይለኛ ጎርፍ የ2 ህፃናትን ህይወት ቀጥፏል።

በደቡባዊ ዞን የሰለዋ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር  ያጋጠመው የመሬት መደርመስ አደጋ በርካቶች አፈናቅሏል።

ተፈናቃዮቹ የመጠለያ ፣ የምግብና ሌሎች መሰረታዊ ነገሮች እገዛ ባለማገኝታቸው ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፥ የተከዘ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ሙላትን ለመቀነስ አልሞ የተለቀቀ ውሃ ከተፋሰሱ በታች በሚገኙ አከባቢዎች ጉዳት አድርሷል።

በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የታሕታይ አድያቦ ወረዳ እንዳስታወቀው ውሃው በሰፋፊ የአርሶ አደሮች መሬት የበቀለውን እህል በማጥለቅለቅ ከጥቅም ውጭ አድርጓል።

#ትግራይ #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማና ወምበራ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። በተለይም በወምበራ ወረዳ አገልግሎቱ ከተቋረጠ አራት ወራት እንዳስቆጠረ ገልጸው፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ) መፍትሄ እንዳልተገኙ ተናግረዋል። ሞባይል በጀነሬተር ቻርጅ ለማድረግ እንኳ በየቀኑ 20 ብር እንደሚያወጡ…
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

" አሶሳ ላይ ያለው የመብራት ጉዳይ አሁንም መፍትሄ ሊያገኝ አልቻለም። በየጊዜው እየተቆራረጠ ነው።

ማህበረሰቡ እጅጉን ተቸግሮ ነው ያለው።

በተለይም ዉሃ ፣ ወፍጮ እንዲሁም ከመብራት ጋር የተያያዘ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች በጣም ችግር ላይ ናቸው። ምንም ስራ ሳይሰሩ የቤት ኪራይ እየከፈሉ ነው።

የመብራት አለምኖር በአጠቃላይ የከተማውን የንግድ እንቅስቃሴን አቀዛቅዞዋል። በጄነሬተር ሞባይል ቻርጅ ለማድረግ 40 ብር  ነው። ኑሮን የበለጠ ከባድ እያደረገብን ነው።

በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ቦታ ብልሽት አጋጥሞታል ይባላል። ጠንካራን እና ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንፈልጋለን። "

#TikvahEthiopiaFamilyAssosa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" የ11 ወንዶች እና 2 ሴቶች አስክሬን ነው የተገኘው " - አይ ኦ ኤም

" ፍልሰተኞችን የጫነ ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ መስጠሙን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መሞተዋል ፤ አልያም ጠፍተዋል " ሲል የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት አሳውቋል።

አደጋው የበርካቶችን ህይወት ከቀጠፉና በተደጋጋሚ ከደረሱ የጀልባ መስጠም አደጋዎች የቅርብ ጊዜው ነው።

በታይዝ ግዛት ጀልባው ለአደጋ በተዳረገበት ወቅት 25 #ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን እና ሁለት የመናዊ መረከብ ዘዋሪዎችን ጭኖ እንደነበረ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም (አይ ኦ ኤም) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እስካሁን ድረስ የ11ወንዶች እና 2 ሴቶች አስክሬን የኤደን ባህረሰላጤ እና ቀይ ባህርን በሚያገናኘው በባበል ኤል መንደብ መተላለፊያ ባህር ዳርቻ መገኘቱን እና ሁለቱን የመናዊያን ጨምሮ 14 ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀ ተገልጿል።

ፍልሰተኞች ከጂቡቲ የተነሱ እንደነበሩ አይ ኦ ኤም አስታውቋል ።

እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በየመን የሚደርሱት ስደተኞች በሦስት እጥፍ አድጓል።

በ2021 27,000 ገደማ የነበረው የፍልሰተኞች ቁጥር ባለፈው አመት ከ97,200 በላይ ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 380,000 የሚጠጉ ስደተኞች ግጭት ባየለባት ሀገር ውስጥ ይገኛሉ።

የመን ለመድረስ ፣ፍልሰተኞቹ ቀይ ባህርን ወይም በኤደን ባህረ ሰላጤ ለማቋረጥ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካይነት አደገኛ በሆኑና በተጨናነቁ ጀልባዎች ይወሰዳሉ።

ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 2,082 ስደተኞች የገቡበት አልታወቀም ከእነዚህ መካከል 693 ያህሉ ሰጥመው ቀርተዋል።

በሰኔ ወር ቢያንስ 49 ስደተኞች በየመን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ጀልባቸው በመስጠሙ ሞተዋል።

140 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እንዳልታወቀ ድርጅቱ አስታውሷል።

ተጨማሪ 62 ስደተኞች ባለፈው ሚያዝያ ወር የመን ለመድረስ ሲሞክሩ በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ላይ በተከሰቱት ሁለት የጀልባ መገልበጥ አደጋዎች ህይወታቸው አልፏል። #IOM #VOA

@tikvahethiopia
#KABBA_TRANSPORT🚌

Safety is our priority !

ካባ በት/ቤቶች ውስጥ የተማሪ ሰርቪስ አገልግሎትን ለሚሰጡ አካላት በስልጠና እና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ደህንነቱ የጠበቀ እና ቁጥጥር ያለው የተማሪዎች ትራንስፖርት ሰርቪስ አቅርቦት ለመፍጠር ከት/ቤቶች፣ወላጅ ኮሚቴ እና ወላጆች ጋር መስራት ይፈልጋል፡፡
አብረውን ሁለት አመታት የሰሩ ት/ቤቶች ምስክር ናቸው፡፡
የትምህርት ዘመን ከመከፈቱ በፊት ቀጠሮ ያስይዙ 0960007700 አዲስ ተመዝጋቢ ወላጆች መተግበሪያውን በማውረድ ይመዝገቡ👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.vintechplc.kabba.parent
ስልክ ፡ 0960009900
ካባ ትራንስፖርት
#AmazonFashion

አማዞን ፋሽን : በቁጥር1 ሱቃችን ሱፍ ማከራየት ጀምረናል። በቁጥር 2 ሱቃችን አዳዲስ ሱፎች በብዛት አስገብተናል።

ኦርጂናል እና ኳሊቲ የቱርክ ሙሉ ልብሶችን በ11 ሺ ብቻ  የጨርቅ ሱሪ በ1300 ብር ሸሚዝ በ1200 ብር ኮት ብቻ በ3ሺ 500 ጫማ 2 ሺ 200  

አድራሻ ፥ ፒያሳ የገበያ ኣዳራሽ ወይም ፒያሳ የድሮው ዳውንታውን ህንፃ ምድር ላይ። 

ስልክ፦ 0920880443/ 0919339250

Telegram👉https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
#MinistryofEducation

ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ  የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ባሉ የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ትምህርት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡

በ2015 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ህፃናት ወይም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቻ እንዲማሩ የሚያዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

አሁን ግን በመጭው የትምህርት ዘመን ህፃናት ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መማር እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው 31ኛውን ጉባኤ ላይ ነው።

" ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቁ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከአፍ መፍቻ  ቋንቋቸው በተጨማሪ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲማሩ እናደርጋለን ያሉት " ሚኒስትሩ ብርሀኑ (ፕ/ር) " ተማሪዎቹ የትምህርት ደረጃቸው ከፍ ሲል የሚማሯቸው ትምህርቶች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ስለሚሆኑ ከልጅነታቸው ጀምሮ ቋንቋውን እንዲያውቁት ማድረግ አስፈላጊ ነው " ብለዋል፡፡

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ወደ ትግበራ ከገባት 2015 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲማሩ የቆዩት በአፍመፍቻ ቋንቋቸው ነው አሁን ደግሞ በመጭው የትምህርት ዘመን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራሉ ተብሏል። #ሸገርኤፍኤም

@tikvahethiopia
🔈#የመምህራንድምጽ

ድምጻቸውን ለማሰማት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተሰባስበው በመመካከር ላይ የነበሩ መምህራን በፖሊስ ተበተኑ።

በወላይታ ዞን ስር ያሉ መምህራን " ሀሳባችን እንዳንገልጽ ፖሊስ አደናቀፈን " ሲሉ ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

" ወደመንግስት አካላት በመሄድ ረሀባችን እወቁልንና ደሞዛችን በወቅቱ ክፈሉን በማለት  ልናሳዉቅ እንጅ ረብሻ ለመፍጠር አልነበረም ተሰባስበን ስንመካከር የነበረው " የሚሉት መምህራኑ " ከረሀባችን በላይ ተሰባስበን በመመካከር ድምጻችን እንዳናሰማ መደረጉ አሳዝኖናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ላለፉት 3 ወራት ያለደሞዝ ቆይተን የሰኔን ብቻ ሰጥተውናል ይሄ ለመምህራን ችግር ግድ የለሽ መሆናቸውን " አሳይቶናል ብለዋል።

አሁን ላይ በዱቤ ይሰጡን የነበሩ ነጋዴዎችም መከልከል በመጀመራቸዉ ተቸግረናል ሲሉ ለቲክቫህ አስረድተዋል።

" ስራቸውን ለመስራትና የባለስልጣናቱን ትእዛዝ ለመፈጸም የመጡ ፖሊሶች  እንኳን ረሀባችሁን እኛም እናውቀዋለን " በማለት እያዘኑ በተኑን በማለት ሀዘናቸውን የገለጹት መምህራኑ " ከዚህ በላይ ሞት እንጅ ሌላ ተስፋ እየታየን አይደለም "  ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።

" በመሆኑም አሁን ላይ በፖሊስ በመገፋታችንና ባለስልጣናቱም ስብሰባ ገቡ በመባላቸዉ  ወደመጣንባቸው አካባቢዎች ብንመለስም ረሀባችን የከፋ መሆኑን ለመግለጽ  ተጠናክረን መጮሀችን ይቀጥላል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በክልሉ ስላለዉ የመምህራን ደሞዝ መዘግየትና መቆራሪጥ ላነሳንለት ጥያቄ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ወረዳዎች ከገቢያቸዉ ክፍያ የሚፈጽሙበት አስራር መዘርጋቱንና ችግሮች ከተፈጠሩ ጣልቃ በመግባት እርማት እንደሚደረግ መግለጹ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Mpox #Ethiopia

ኢትዮጵያ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተገኝቷል ?

“ የእኛም ሰዎች እዛ ሂደው ስላዩ አረጋግጠዋል ሞንኪፖክስ አይደለም፡፡ ቺክንፖክስ ነው ” - ጤና ሚኒስቴር

ኦክስፋም ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በሶማሌ ክልል በዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የተጠረጠረ ኬዝ መገኘቱን የሚያሳይ አጭር ሪፖርት ትላንት ይፋ አድርጎ ነበር፡፡

ሌላ አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ድርጅትም እዛ ካሉ ሰዎቹ የበሽታው ኬዝ በሶማሌ ክልል መገኘቱን እንደሰማ ገልጿል።

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሶማሌ ክልል ባለስልጣን ግን " ምንም የተገኘ ነገር የለም ውሸት ነው ያወጡት ሪፖርት " ብለውናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ እውነት ተከስቷል ? የሚለውን ጉዳይ ለማጣራት ሞክሯል፡፡

ጤና ሚኒስቴርንም በሽታው ወደ ሀገራችን ገብቷል እንዴ ? ሲል ጠይቋል።

የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ደረጀ ጉዱማ (ዶ/ር) በሰጡን ምላሽ፣ “ አላጋጠመም፡፡ ያው ለነገሩ ትላንትም አረጋግጠን ነበር፤ ሰዎቹ (ኦክስፋም ኢትዮጵያን ማለታቸው ነው) የለጠፉትን እንዲያነሱ እያደረኩ ነበር፡፡ ቺክንፖክስ ነው ” ሲሉ ገልጸውልናል፡፡

“ የእኛም ሰዎች እዛ ሂደው ስላዩ አረጋግጠዋል ሞንኪፖክስ አይደለም፡፡ ቺክንፖክስ ነው፡፡ በእርግጥ ይመሳሰላል ሲምፕተማቸው፡፡ እንደ ቤተሰብ ሀፕን ያደረገ ነው፡፡ ኦረዲ ሌሎቹም ሪከቨር ስላደረጉ ሳምፕልም ወስደን ቼክ አድርገናል ሞንኪይፖክስ አይደለም ” ነው ያሉት፡፡

“ ቺክንፖክስ የሚባል አለ ፤ ሌላ በሽታ አለ ቀለል ያለ፡፡ ይህ ብዙ ቦታዎች አለ፤ ሰሞኑን ይሄኛው ስለተነገረ፣ ሰው ሲጠራጠር ቁስል፣ ቀላል የቆዳ ኢንፌክሽን እየመጣ ስለሆነ ከጥርጣሬ የተነሳ ነው ” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“ በእርግጥ ጥሩ ነው እንደዛ መሆኑ ግን ውዢምብርም ሊፈጠር ስለሚችል ጥንቃቄ አድርጉ፣ ፖስት እንዳታደርጉ ሚኒስቴሩ ነው ፖስት ማድረግ ያለበት ቼክ አድርጎ ከተፈጠረም፡፡ ሰስፔክትም አይባልም፡፡ ሰስፔክት በራሱ የራሱ ደፊኔሽን አለው ” ብለዋል፡፡

ቺክንፖክስ ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ ነው እንዴ ? ስንል የጠየቅናቸው ሚኒስትር ዴዔታው፣ “ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከ100 በላይ ተመሳሳይ ምልክቶች ያሏቸው የቆዳ ኢንፌክሽኖች፣ ሌሎችም ኢንፌክሽኖች አሉ ” ብለዋል፡፡

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በኢትዮጵያ ደረጃ ተከስቷል ? አልተከሰተም ? ለህዝቡስ ምን የጥንቃቄ መልዕክት ታስተላልፋለችሁ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

ሚኒስትር ዴዔታው፣ “ ምንም ነገር የለም በርካታ ሳምፕሎችን ወስደን ቴስት አድርገናል፡፡ የእኛ ልጆች በየክልልም እየወረዱ በሁሉ ቦታ ላይ ሩመር ሲነሳ ያያሉ፡፡ ኢንቨስቲጌት ያደርጋሉ፡፡ ሳምፕል ይወስዳሉ፡፡ ሳምፕሉ ወደ እኛ ወደ ላብራቶሪ ይላክል፡፡ በርካታ ቴስቶች አድረገናል፡፡ ግን ምንም የለም ኔጌቲቭ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

“ ኤርፖርት ላይ ሥራችንን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡ መግቢያና መውጫ በሮች ላይ የተያዩ ምልክቶችን እናያለን በተለይ ትኩሳት ያላቸውን ሰዎች እንለያለን፡፡ የትኛውም ቆዳቸው እብጠት ካለ እያረጋገጥን  እንገኛለን ” ብለዋል፡፡

“ ማህበረሰቡ ግን ይህን አይነት ምልክት ካለ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ግን በተለይ ለጤና ተቋማት ሪፖርት እንዲያደርግ ነው የሚጠበቀው፡፡ እንደዛ አይነት ሰው ካለ ደግሞ ንክኪ እንዳይኖር ጥንቃቄ  ማድረግ፡፡ ንክኪም ካለ ቶሎ በአግባቡ እጅን መታጠብ፣ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ከጤና ሚኒስቴር ጠይቆ ባዘጋጀበት ሰዓት ኦክስፋም ኢትዮጵያ " በሶማሌ ክልል በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠረ ኬዝ ተገኝቷል  " የሚለውን መረጃ ከገጹ ላይ አጥፍቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia