TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በቤት እቃዎቻችን ላይ ከ10 እስከ 25% ቅናሽ ማድረጋችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው! 🌼🌼 ይምጡ እና ይጎብኙን በዕቃዎቻችን ጥራትና ጥንካሬ ይደመማሉ!

የውበት እና የጥራት ዳር ድንበር ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር!

አድራሻችን፦
1.ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251995272727
2.ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251957868686
3.ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251993828282

👉 Telegram:  https://t.iss.one/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር የነበሩት ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዶ/ር ደረጄ ባለፉት ዓመታት በፖለቲካው መስክ የሰሉ ትችቶችን በማቅረብ በብዙሃን ዘንድ ይታወቃል።

ዶ/ር ደረጄ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ህይወታቸው አልፏል።

የዶ/ር ደረጄ ዘለቀ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

@tikvahethiopia
#Oromia : በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች ባለፉት ሦስት ሳምንታት ልጆቻቸውን ቀንበር አሸክመው እና በማኅብረሰቡ ክብር ያላቸውን ዕቃዎች ይዞ ባልተለመደ ሁኔታ አደባባይ ወጥቷል።

ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ነዋሪዎች አደባባይ የወጡት ከአቅማቸው በላይ ለሆነ ችግሮች ፈጣሪ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመማጸን መሆኑን በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳታፊ የነበሩ እና ያስተባበሩ ሰዎች ተናግረዋል።

ይህ ለዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ቅርብ የሆነው እና በግብርና እንዲሁም በወተት ምርቱ ይታወቅ የነበረው አካባቢ ሰላም ርቆት ነዋሪዎች በሰላም ወጥተው መግባት፣ አርሶ መሰብሰብ፣ መገበያየት እና ልጆቻቸውን ትምህር ቤት መላክ ካቃታቸው ዓመታት ማለፋቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

በዚህ ምክንያት ላለፉት ሁለት ተከታታይ የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በአካባቢው ባሕል መሠረት ነዋሪዎች " ማለቂያ የሌለው ሰቆቃ " እንዲያበቃ ልጆቻቸው እና በሬዎቻቸው ላይ ሞፈር ጠምደው እንዲሁም የክብር የሆኑ መገልገያዎቻቸውን ይዘው በመውጣት ፈጣሪያቸውን ተማጽነዋል።

በዞኑ የሚገኙት ፦
- ኩዩ፣
- ደገም፣
- ሂዳቡ አቦቴ፣
- ወረ ጃርሶ፣
- ግራር ጃርሶ፣
- ደራ እና ያያ ጉለሌ ወረዳዎች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ከሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ተጠቃሽ መሆናቸው ይነገራል።

በታጣቂዎች እንቅስቃሴና መንግሥት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት የሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች ሰላም ከራቃቸው ዓመታት አልፈዋል።

በዞኑ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ፣ ዘረፋ ፣ መፈናቀል እና እገታ ነዋሪውን ዕለት ከዕለት እየረበሸው የሚገኝ ጉዳይ ሆኗል።

Credit - BBC AMAHARIC

@tikvahethiopia
🔈 #የወላጆችድምጽ

በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ከተሞች ለህጻናት ወሣኝ የሆኑ የወተት ምርቶች በተለይ ' ሁለት ቁጥር ' ማግኘት እንዳልቻሉ ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

" ይኸው የወተት ምርት ከሳምንታት በፊት በ950 ብር ሲሸጥ ነበር የምንዛሬ ዋጋ ከጨመረ ወዲህ ግን እስከ 1800 ብር ገብቷል " ብለዋል።

" ያውም ይሄ ዋጋ ወተቱን ማግኘት ስንችል ነው " ሲሉ አክለዋል።

አንድ ቁጥርም በገበያ ላይ እጥረት እንዳለ ከወላጆች ሰምተናል። ይበልጥ ግን ቁጥር ሁለቱን ማግኘት ፈተና እንደሆነና ዋጋም ለወላጅ የሚቀመስ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል።

ያነጋገርናቸው የፋርማሲ ባለሙያዎችና ወላጆች የወተት ምርቶቹ ሀገር ውስጥ ጠፍተዋል ብለው እንደማያምኑ የተያዘ ክምችት ሊኖር ይችላል ብለው እንደሚገምቱ ለዚህም የሚመለከታው አካል ኃላፊነቱን በመወጣት ችግሩን እንዲፈታ ጠይቀዋል።

የወተት ዋጋው እጅግ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ መጨመሩ ወላጆችን አስጨንቋል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የተመራው የህወሓት ጉባኤ አቶ ጌታቸው ረዳን ከምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶ/ር ደብረጽዮን በድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል። በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሌሎች የስራ አስፈጻሚና የማእከላይ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡ የድርጅቱ አባላት ከላይ ስማቸው ተያይዟል። ምርጫ ቦርድ ከጉባኤው ቀደም…
#TPLF #Tigray

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን " አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም ” ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " የህወሓት ሰዎች መመደብ አለባቸው " ብለው በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን " ካቋቋሙ ወገኖች ጋር ውይይት ያስፈልጋል " ብለዋል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከህወሓት በተጨማሪ የትግ ራይ ሠራዊት፣ ምሁራን እና ተቃዋሚው ባይቶና ድርሻ አላቸው።

በጉዳዩ ዙሪያ ከፌድራሉ መንግስት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ፥ " እኛ ትግራይ ውስጥ ብቻ የምንጨርሰው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን ህወሓት " የድርጅቱን አመራሮች የከፋፈለ ነው " የተባለለትን 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን በድጋሚ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳን በማንሳት አቶ አማኑኤል አሰፋን እንዲሁም ሌሎችንም አዳዲስ የማዕከላዊና የስራ አስፈጻሚዎችን መምረጡ ይታወቃል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግን ቀደም ብሎ ጉባኤው ሳይጀመር የቦርዱን አሰራር ላልተከተለ ጉባኤ እና በጉባኤው ለሚተላለፉ ማንኛውም ውሳኔዎችና ለውጦች እውቅና እንደማይሰጥ በይፋ አሳውቋል።

#TPLF #EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
#ኢራን

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ገድላለች።

በማዕከላዊ ኢራን " ዝድ ክልል "አስገድዶ መድፈር መፈጸሙ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት ግለሰብ ሞት ተቀጥቷል።

ግለሰቡ " በጥንቆላ ይተዳደራል " የተባለ ሲሆን ወደሱ የሚመጡ ሴቶችን በማታለል አስገድዶ ሲደፍር እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከ12 በላይ የክስ መዝገቦች የተከፈቱበት ይህ ሰው አሱን ጨምሮ ከነ ረዳቱ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው በሞት ፍርድ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ጥፋተኛ የተባሉት ሰዎች ታንቀው እንዲገደሉ ተደርጓል።

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉ ወንጀለኞች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚጥሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

መረጃው የአን አይን ኒውስ / አል አረቢያ ነው።

@tikvahethiopia
#Omo

የኦሞ ወንዝ ሙላት ከቁጥጥር ውጭ መሆኑን ተከትሎ የአካባቢው አርሶአደር በ4ቱም አቅጣጫ ንብረቱን ጥሎ መሸሽ ላይ ነው።

ችግሩ እንደሚከሰት ታውቆ በርካታ ስራ ሲሰራ ቢቆይም የኦሞ ወንዝ መጠን ከተለመደውና ከታሰበው ውጭ መሆኑን ተከትሎ ግን ለዞኑ መንግስትም ሆነ ለግብረሰናይ ድርጅቶች ሁኔታው ከባድ ሆኖባቸዋል።

የወንዙ ሙላት ከባድ መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ አርብቶ አደሩን በአራት ጊዜያዊ መጠለያ እንዳስቀመጡትና ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያሻዉ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማልኮ ገልጸው " በአሁኑ ወቅት የውሃው መጠን ከተለመደው ውጪ እየጨመረና ሰፊ ቦታ እየያዘ ከመምጣቱ የተነሳ ለኦሞራቴ ከተማ ማህበረሰብ እንደሚያሰጋ " ተናግረዋል ።

ችግሩ እየባሰ የመጣው የውሃውን አቅጣጫ የማስቀየርና የማፍሰስ ስራዎች በኢንቨስተሮች እርሻ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያስከተለ ነው በሚል በጅምር በመቆሙ መሆኑን የሚያነሱት የአካባቢዉ ነዋሪዎች በበኩላቸው ችግሩ በየአመቱ የሚፈጠር በመሆኑ ኑሯቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገዉ ይገልጻሉ።

በመሆኑም አሁን ላይ ማህበረሰቡ ቤቱ እየተዋጠበት ከብቱ እየሞተበትና የሚቀምሰውም በመጥፋቱ ተስፋ በመቁረጥ አካባቢውን ጥሎ መሸሽ መጀመሩ ተሰምቷል።

ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኦሞ ወንዝ ሙላት ጋር ተያይዞ በአከባቢው በተደጋጋሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሲከሰት እንደነበር የገለጹት የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀቴ በበኩላቸው አምና ከ79 ሺህ በላይ አርብቶ አደሮች በወንዙ ሙላት መጥለቅለቅ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀላቸውን ይናገራሉ።

እነዚህ አርብቶ አደሮች እስከ ዛሬ በጊዜያዊ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ የተደረገ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ታደለ ለእርሻ ስራ በሚል ወደ ቀድሞ ቀያቸው በተመለሱት ላይ አሁንም ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል ።

አሁን ላይ ወንዙ መደበኛ የፍሰት አቅጣጫውን በመልቀቅ የጉዳት መጠኑን አስፍቶና አርብቶ አደሩን አፈናቅሎ ለማህበራዊ ችግር እየዳረገ ሲሆን በኢፌዴሪ ውሃና ኢነሪጂ ሚኒስቴር አማካኝነት ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመረው የመከላከያ ፕሮጀክት መፍትሄ ያመጣል ቢባልም ሊጠናቀቅ አልቻለም።

በዚህ ምክኒያትም አሁን ላይ በ33 ቀበሌዎች የነበሩ መሠረተ ልማቶች ትምህርት ቤቶች ጤና ኬላዎችና መኖሪያ ቤቶች በውሃ ሊከበቡና ነዋሪው ለከፋ ችግር ይጋለጥ ዘንድ ምክኒያት ሆኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

ዛሬ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከለሊቱ 09፡00 ሰአት ጀምሮ በነበረው ከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት አብዛኞቹ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፉ ባለመቻላቸው በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ ኤርፖርቶች ተመልሰው እንዲያርፉ መገደዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

ይህ የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም-አቀፍ የጠዋት በረራዎች ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ አመልክቷል።

አየር መንገዱ ፥ " የመንገደኞቻችን ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብሎ " ከዚህ ጋር ተያይዞ በተሳፋሪዎቻችን የጉዞ ዕቅዶች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መስተጓጉሎችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግን እንገኛለን " ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞች ላጋጠማቸው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ይመለሳሉ💥

🔴 አርሰናል ሁለተኛውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በቪላ ስታዲዮም ከአስቶን ቪላ ጋር ቅዳሜ ነሐሴ 18 ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት በSS Premier League እና SS Liyu ቻናል በሜዳ ፓኬጅ በቀጥታ ይከታተሉ!

🤔አርሰናል የዓምናውን ሽንፈት መበቀል ይችላል? አርቴታ እምሪይን ማሸነፍ ይችላል?

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ያሳድጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#SafaricomEthiopia

🤩🎧 ማነው አሪፍ ድምጽ አለኝ የሚለው? እስቲ ቲክቶክ ላይ ፖስት ይደረግና ችሎታ ይታይ! ብዙ የሚታዩት ቪዲዮዎች የገንዘብ ሽልማት እና በታዋቂ አርቲስቶች የመሰልጠን እድል ያስገኛሉ! 

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
#Ethiopia : ነገ በመላ ሀገሪቱ በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ይካሄዳል ተብሏል።

ለዚህም ዘመቻ በፌዴራል፣ በክልል ፣ በዞን ፣ በወረዳ እንዲሁም በቀበሌ የተለያዩ መዋቅሮች ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

የችግኝ ተከላውን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) " አዋቂዎች ከ20 በላይ ፣ ታዳጊወች ከ10 በላይ ችግኝ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ " ሲሉ ጥሪ አቅርበው ነበር።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

“ አዋጅ ተጥሶ ነው ጋዜጠኞቹ እስር ቤት እንዲገቡ የተደረገው ” - ማኀበሩ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኀበር በአዲስ አበባ ከተማ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ስንት ጋዜጠኞች በእስር ላይ ይገኛሉ? ስለታሰሩ ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደቱ በአዋጁ መሠረት ምን መሆን ነበረበት/አለበት? ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ የታሰሩ ጋዜጠኞች አሉ? ጋዜጠኝነት ላይ የሚስተዋለውን ጫና ምን ይመስላል? ሲል ማኀበሩን ጠይቋል፡፡

የማኀበሩ ፕሬዚደንት እታገኘሁ መኮንን ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ በአዲስ አበባ በእስር ላይ ያገኘናቸው በቃሊቲ ሁለት ሴቶችን ፣ በቂሊንጦ ደግሞ አራት ወንዶችን ነው፡፡ ከታሰሩ ሁለት ዓመት አልፏቸዋል፡፡ ሁለት አመት ከ4 ወራት አካባቢ ሆኗቸዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ጋዜጠኞች ታስረው እንደሆን አጣርተናል፡፡ ግን ለጊዜው በቂ መረጃም አላገኘንም፡፡ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን አዋጁ፣ ጋዜጠኛ ሚዲያ ላይ በሰራው ሥራ ጥፋተኛ ተብሎ የሚጠየቅ ከሆነ ጉዳዩን ከማረሚያ ቤት ውጭ ሆኖ እንዲከታተል ይፈቅዳል፡፡

ነገር ግን ይሄ አዋጅ ተጥሶ ነው ጋዜጠኞቹ እስር ቤት እንዲገቡ የተደረገው፡፡ ከሁለት አመት በላይ በማረሚያ ቤት እንዲቀመጡ የተደረገው፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃም መያዛቸውና መታሰራቸው አግባብ አይደለም፡፡

ያም ከሆነ በኋላ ደግሞ ፍርድ ቤት (ለምሳሌ የጋዜጠኛ የዳዊት በጋሻውን ጉዳይ ብናነሳ በዋስትና እንዲወጣ ከተፈቀደለት በኋላ ነው በድጋሚ በሽብርተኝነት ክስ ስለሚከሰስ ተብሎ ዋስትናው ውድቅ ተደርጎ እዚያው እንዲቆይ የተደገው፡፡)

የሎሌቹም ተመሳሳይ ኬዝ ነው፡፡በሚዲያ ላይ በሰሩት ሥራ በጋዜጠኝነታቸው ተይዘው በኋላ ላይ ሌሎች ክሶች እየቀረቡ ነው፡፡ ለእሱም እካሁን ማስረጃ ሳይቀርብ ነው ፍርድ ቤት እየተመላለሱ ያሉት፡፡

እነርሱም ያነሱት ቅሬታ ይሄው ነው፡፡ ሚዲያ በሚሰራው ሥራ ሲጠየቅ ፅሑፉ ማስረጃው ነውና የሚደበቅ ማስረጃ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ጉዳያቸውን ከእስር ቤት ውጭ ሆነው መካታተል ይችሉ ነበር፡፡

ሌላኛው ቅሬታቸው፣ 'ፍርድ ቤት ያለ አግባብ እየተመላለስን ነው፤ በሽብርተኝነት ክስ ተከሰዋል ማስረጃ አቀርባለሁ ብሏል መንግስት ግን እየቀረበ አይደለም በዚህ ምክንያት እየተጉላላን ነው' የሚል ነው፡፡

የእኛም (የማኀበሩ) አቋምም ይሄው ነው፡፡ ይሄ መብት መከበር አለበት። ለጋዜጠኝነት የሚዲያ ነጻነት አለማግኘት፣ የጋዜጠኞች እስር፣ መሰደድ፣ አጠቃላይ የፖለቲካው አሉታዊ ተፅዕኖ ሚዲያው ላይ ትልቅ ጉዳት እያስከተለ ነው።

ነጻ ሚዲያ እንዲኖር፣ ሚዲያው ከፖለቲካ አተያይ ነጻ በሆነ መንገድ እንዲዳይ ነው የምንጠይቀው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" የሃሳብ ልዩነቱ ወደ ግጭት አያመራም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ዓመታዊው የ2016 ዓ/ም የአሸንዳ በዓል ዛሬ ነሃሴ 16/2016 ዓ/ም በመላ ትግራይ መከበር ጀምሯል።

በዓሉ እስከ ነሃሴ 24/2016 ዓ.ም አንደሚቀጥል የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።

በሌላ በኩል ፕሬዜዳንት ጌታቸው በ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የተገነባ የ10.2 ኪሎ ሜትር  የአስፋልት መንገድ ሲመርቁ ፤ የአሸንዳ አደባባይ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ዳግም የህወሓት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል የተባሉት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) በተምቤን በመገኘት የቀለም ፋብሪካ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አኑረዋል።

በመቐለ ትንሹ ስታድዮም በተከናወነው ይፋዊ የአሸንዳ ስነ-ሰርዓት ተገኝተው ፥ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉት አቶ ጌታቸው ረዳ " የተፈጠረው የሃሳብ ልዩነት ወደ ግጭት አይሸጋገርም "በማለት ታዳሚውን አረጋግተዋል።  

ዓመታዊ የአሸንዳ የሴት ልጃገረዶች በዓል በሽረ-እንዳስላሰ ፣ በአክሱም ፣ በዓድዋ ፣ በዓዲግራት ፣ በተምቤን ፣ በመቐለ ፣ በማይጨውና በሌሎች ከተሞች በድምቀት መከበር ጀምሯል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia