TIKVAH-ETHIOPIA
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግዳሮቶቹ ምንድናቸው ? ጠንካራ ጎኑን በሚመለከት በስፋት ከብሔራዊ ባንክ ሰነድ ላይ መረዳት ይቻላል። ስለ ተግዳሮቶቹ ደግሞ የባንክ ጉዳዮች ባለሙያው ሙሴ ሸሙ ተከታዩን ሙያዊ ትንተና አቅርበዋል። ከአስተያየታቸው መካከል ፦ - ገበያ መር (Free Floating) የውጭ ምንዛሪ ስርዓት በተረጋጋ፣ በቂ አቅርቦት እና ምርታማነት እውን በሆነበት ኢኮኖሚ ላይ ተመስርቶ ካልተተገበረ…
#የሐሳብ_መድረክ
(የባንክ ባለሙያ አቶ ሙሼ ሰሙ)
" ፓሊሲው (የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ) ተግባራዊ ከሆነ ሳምንት ተቆጥሯል።
ስጋቶች ከየአካባቢው እየተነሱ ነው።
አንዱ የስጋት ምንጭ የሆነው በገቢ እቃዎች ላይ የታየው የዋጋ ንረት ነው።
የችግሩ ምንጭና መፍትሔውን በጋራ እንመልከተው።
ነጋዴው ድሮም እቃ የሚያስመጣው በጥቁር ገበያ ተመን ነበር። እንዲያውም አሁን ላይ ከጥቁር ገበያ ባነሰ የዶላር ተመን የማስመጣት እድል እየተፈጠረለት ነው።
የምንዛሪ ዋጋ ለውጥ ከሌለ የእቃ ዋጋ ለምን ይጨምራል ? የሚል መከራከርያ በስፋት እየተሰማ ነው።
ይህ አቀራረብ ሁለገብ ምልከታ የጎደለው ስለሆነ ወደ ተረጋጋ መፍትሔ የሚወስድ አይመስለኝም።
በመጀመርያ ነጋዴው የሚያስመጣው ቁሳቁስም ሆነ ሸቀጥ 100% ከጥቁር ገበያ በሚገኝ የውጭ ምንዛሪ የሚገዛ አይደለም።
ሁለተኛ ነጋዴው ሚያስመጣው እቃ ዋጋ የሚወሰነው ጉምሩክ ባዘጋጀው የእቃዎች የዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ተመስርቶ ሲሆን ቀረጥ የሚከፍለው ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የእለቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት በማድረግ ነው።
ይህ ማለት ነጋዴው ከሳምንት በፊት በ100 ዶላር ለጫነው እቃ ቀረጥ የሚከፍለው በወቅቱ በነበረው የብሔራዊ ባንክ የአንድ ዶላር ተመን ብር 57.5 ተሰልቶ ሲሆን ዛሬ ላይ ቢጭን ደግሞ በባንኮች በሚያወጡት የውጭ ምንዛሪ አማካይ ተመን ላይ ተመስርቶ በሚሰላ ዋጋ 100 ብር ገደማ ነው።
ይህ ማለት የቀረጥ መጣያ ዋጋው በእጥፍ ጨምሯል ማለት ነው። ' ዋጋ ቀንስ ' ብቻ ሳይሆን ነጋዴው በተመን ለወጥ ምክንያት የተፈጠረበትን የቀረጥ ጭማሪ እንዴት ይሸፍን የሚለው ጥያቄ መመለስ ይስፈልጋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊታሰብበት የሚገባው ፦
° የአውሮፕላን ትኬት፣
° ኢንሹራንስ፣
° የጭነት ዋጋ፣
° የኮንቴይነር ኪራይ በእቃዎች ዋጋ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም።
ቀስ በቀስ በደሞዝና በድጎማ መልክ ወደ ኢኮኖሚው የሚፈሰው ገንዘብም አቅርቦትና ፍላጎትን በማዛባት ግሽበትና የዋጋ ንረት ማስከተሉ የሚጠበቅ ነው።
ሌላው የውጭ ምንዛሪ ግብይት በነጻ የገበያ ውድድር የሚመራ ከሆነ የእቃ ዋጋም ያለማንም ጣልቃ ገብነት ገበያው ውስጥ በሚኖረው አቅርቦት፣ ፍላጎትና የመተኪያ ዋጋን መሰረት አድርጎ መመራት አለበት። ይህ የተሻለው የዋጋ ማረጋጊያ መንገድ ነው።
በተቃራኒው በመመርያና በአስተዳደራዊ እርምጃ የሚተመን ዋጋ የግብይትና የአቅርቦት ስርዓትን በማፋለስ፣ የጥራት ጉድለትና የዋጋ ንረት በአጠቃላይ የገበያ ውጥቅጥን ማባባሱ የሚጠበቅ ነው።
በአስተዳደራዊ ውሳኔ አከፋፋዩም ሆነ ቸርቻሪው ዛሬ እጁ ላይ ያለውን ምርት በውሳኔው ዋጋ አጣርቶ ሊሸጥ ይችላል።
እጁ ላይ ያለው ምርት ካለቀ በኋላ ግን ነጋዴው እንደሚከስር እያወቀ እቃ ለማስመጣትም ሆነ ለማከፋፈል ፍላጎት እንደማይኖረው ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ የእቃ እጥረትና ተጨማሪ የዋጋ ንረት/ግሽበት ፣ እቃ መሰወር፣ ጥራት የጎደለው ምርት ማቅረብና ለኮንትሮባንድ ንግድ መጋለጥን ሊያስከትል ይችላል።
ጊዜያዊ በሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና በሙስና በተጨማለቁ ደንብ አስከባሪዎች ማዋከብ ነጋዴው ማህበረሰብ ስጋት እንዳያድርበት፣ እንዳይበረግግና ከገበያው እንዳይወጣ፣ በዚህ ምክንያትም ገበያው ይበልጥ እንዳይታወክ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
ከአቅራቢ፣ ከአከፋፋዩና ከቸርቻሪው ጋር በየደረጃው በመወያየት ነባራዊ ሁኔታውን በማስጨበጥ ስግብግብነት ካለም በእንጭጩ በመግታት የነጋዴውንም ችግር በዛው ልክ በመረዳት ነጋዴውን የችግሩ መንስኤ ሳይሆን የመፍትሔው አካል ማድረግ ዘላቂ ጥቅም አለው። "
#Ethiopia #Economy #MusheSemu
#YeHasabMedrk
@tikvahethiopia