TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጋምቤላ

10 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ቅዳሜ ዕለት ከደቡብ ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የገቡ የ " ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች " 10 ሰዎችን ገድለው 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን ከጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ታጣቂዎቹ ቅዳሜ ምሽት 3 ሰዓት ተኩል ገደማ ድንበር ጥሰው በመግባት በማኩዌይ ወረዳ ቢልኬች ቀበሌ እንዲሁም በዋንቱዋ ወረዳ መተሀር ከተማ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በፈፀሙት ጥቃት በአጠቃላይ 10 ሰዎችን ገድለው ፤ 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል።

በጥቃቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ወደ ጋምቤላ ጠቅላላ ሆስፒታል ለህክምና የተላኩ ሲሆን ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ደግሞ በኝንኛንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተነግሯል።

ከጥቃቱ በኃላ በጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኑዌር ዞን በሙርሌ ጥቃት የደረሰባቸውን ዜጎች ምልከታ አድርጓል።

አቶ ቴንኩዌይ ጆክ  ፤ በተደጋጋሚ ወቅትና ጊዜ እየጠበቁ ጥቃት የሚሰነዝሩት የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ታጣቂዎች፣ ትቅዳሜ ምሽት ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ነው ጥቃቱን ያደረሱት ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለማደን ጥረት እያደረገ ነው ያሉ ሲሆን ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፀም የተጠናከረ ጥበቃ ይደረጋል ብለዋል።

የክልሉ መንግስት በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደምም እነዚሁ ድንበር ጥሰው የሚገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በኑዌር ዞንና አኙዋ ዞኖች ገብተው የተለያዩ ጥቃቶችን ማድረሳቸው ይታወሳል።

ድንበሩ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ህብረተሰቡ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል በተፈጠረ የእርስ በእርስ ግጭት 9 ሰዎች ሲገደሉ ፤ 17 ሰዎች ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ክልሉ አሳወቀ።

ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ የፀጥታ ችግር ተከስቶ እንደነበር የክልሉ ፕሬዜዳንት  ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በሰጡት መግለጫ ፤ " በክልሉ በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉን የፀጥታ ችግር በክልሉና በፌዴራል የፀጥታ አካላት ቅንጅታዊ ስራ በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል " ብለዋል።

በኢታንግ ልዩ ወረዳ በፒኝዋ እና ሌር ቀበሌዎች በሚኖሩ ግለሰቦች መካከል የተነሳዉ አለመግባባበት ወደ ግጭት ማምራቱን የገለፁት የክልሉ ፕሬዜዳንት በዚህም በወረዳውና በጋምቤላ ከተማ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል።

በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት የዘጠኝ (9) ሰው ህይወት ሲያልፍ 17 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ከፌዴራልና ከክልል የፀጥታ አካላት አስፈላጊው ኃይል ተጨምሮ የማረጋጋት ስራ መከናወኑን አመልክተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " ለዘመናት በአብሮነትና ወንድማማችነት ተከባብሮ የኖረውን ህዝብ ለማለያየት የሚሞክሩ አካላት አሉ " ያሉ ሲሆን " በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ጥረት ሴራቸው ሳይሳካ ቀርቷል " ብለዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ የሀሰት መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀው አሻፈረኝ ባሉት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል በተከሰተ የፀጥታ ችግር የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።

በክልሉ ሰሞኑን በተከሰተ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ ካቢኔ አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ችግሩን መነሻ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥቧል።

ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ተሽከርካሪም ሆነ ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

ከተመደቡ የፀጥታ አካላት ውጪ የትኛውንም ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻልም አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ሆነ አገልግሎት ሰጪ የንግድ ተቋማት ከነገ ጀምሮ መደበኛ ስራውቸዉን እንዲያከናዉኑ ካቢኔዉ ዉሳኔ አሳልፏል።

ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን በክልሉ ነዋሪ ከሆኑ ዜጎች ለመስማት ተችሏል።

የክልሉ መንግሥት ከሰሞኑን በተነሳው የፀጥታ ችግር ስለደረሰ ጉዳት ያለው ነገር የለም።

ዛሬ ደግሞ በተለይ በጋምቤላ ላይ የመንግስት ሰራተኞች ስራ ያልገቡ ሲሆን የንግድ እንቅስቃሴም ተስተጓጉሎ ውሏል።

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪው እንዲሁም አንድ መምህሩ ህይወታቸው ማለፉን አሳወቀ።

የዩኒቨርሲቲው የ2ኛ ዓመት የአካውንቲንግ ተማሪ የነበረው ኡጁሉ ቲሞቲ ቱትላም ሐምሌ 9/2015 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉን ተቋሙ ገልጿል።

ተቋሙ የተማሪውን ህልፈት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

በሌላ በኩል ፤  በተቋሙ የሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል መምህር የነበሩት ኳንግ ኒያል ፖች ሀምሌ 11/2015 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉን ጠቁሟል።

በመምህሩ ህልፈት ላይም ዩኒቨርሲቲው ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረገም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የፌዴራል ፖሊስ ለልጆቻችሁ #ሙሉ_ኃላፊነት ይወስዳል ፤ አስተማማኝ ጥበቃም ያደርግላቸዋል " - የጋምቤላ ትምህርት ቢሮ ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የፀጥታ ችግር መከሰቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰዓት እላፊ ገደብ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ…
#NewsAlert

በጋምቤላ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ቦታዎች እንዲሰጥ ተወሰነ።

በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ እና በጋምቤላ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሚሰጥ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ፤ " በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ያለውን ጫና ለመቀነስ ታስቦ ፈተናው በኮሌጅም ጭምር እንዲሰጥ ተወስኗል " ብሏል።

የክልሉ መንግስት ውሳኔውን ያሳወቀው ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት ጀምረዋል።

በተለይም በ #ኑዌር_ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት መጀመራቸው ተገልጿል።

#አኙዋ_ዞን፣ በከፊል ከ #ኢታንግ ልዩ ወረዳና ከ #ጋምቤላ_ከተማ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ በጋምቤላ ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በነገው ዕለት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ወደተመደቡበት የመፈተኛ ጣቢያ በመሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የክልሉ መንግስት አሳስቧል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርና ሀገር አቀፍ የፈተናዎች አገልግሎት ከክልሉ መንግስት ጋር በመነጋገር ነው በሁለት ቦታ ፈተናው እንዲሰጥ የተወሰነው።

መረጃው ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የጋምቤላ ክልል አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የትጥቅ ግጭቶችን፣ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶችንና አጠቃላይ የጸጥታ ችግሮችን እና በዚህ ሳቢያ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ተጎጂዎችን፤ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች እንዲሁም የክልሉን የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎችን በማነጋገር ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

በተለይ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ላለው የጸጥታ ችግር መነሻ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ በተወሰነ ነዋሪዎች መካከል የተነሳ አለመግባባት መሆነ ማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ይሄው አለመግባባት በፍጥነት ወደ ብሔርን መሠረት ያደረገ ውጥረት እንደተሸጋገረ ነዋሪዎች ያስረዳሉ።

ይህንኑም ተከትሎ የተለያየ ብሔር ታጠቂ ቡድኖች በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግ ወረዳ፤ በጋምቤላ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እና በከተማው በሚገኙ ሌሎች ሰፈሮች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በርካታ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል እና ንብረት ውድመት ደርሷል።

ኢሰኮ በጸጥታው ችግር ምክንያት ገና ወደ አካባቢዎቹ በአካል ደርሶ ምርመራ ለማድረግ ያልቻለ ቢሆንም፣ ነዋሪዎች በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ መንደሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደሙ መሆናቸውን አስረድተዌ።

ጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ ከጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን በሚመጡ ታጣቂ ቡድኖች በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እንዲሁም አልፎ አልፎ በክልሉ በሚኖሩ ብሔሮች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስ መሆኑ እንደሚታወቅ ኢሰመኮ በመግለጫው አመልክቷል።

ክልሉ ወደ 350 ሺህ የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በስምንት የተለያዩ ካምፖች ያስተናግዳል።

ከሁለት ወራት በላይ ለዘለቀው የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ችግር እና በክልሉ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በመድረስ ላይ ያሉ ግጭቶች ተሳታፊዎችን በተመለከተ ተጎጂዎችም ሆነ የክልሉ የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎች የተለያዩ ብሔር ታጣቂ ቡድኖችን ኃላፊነት ይጠቅሳሉ።

በአንዳንድ አካባቢዎች የክልሉ ኑዌር ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ በሌላ አካባቢ የአኝዋ ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ እንዲሁም ከጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች እና በአንዳንድ የስደተኛ ካምፖች ውስጥ አንደሚኖሩ የተገለጸ ሰዎች ጭምር በግጭቶቹ ተሳታፊ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡

እነዚህ ጥቃቶች እና ግጭቶች በአብዛኛው ብሔር ተኮር ሲሆኑ በሌላ በኩል ግጭት የሚደርስባቸውን አካባቢዎች ያለ የብሔር ልዩነት ሁሉንም ነዋሪዎች አካባቢውን ሸሽቶ ለመፈናቀል፣ ለንብረት ውድመት እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ያጋለጠ ነው ሲል ኢሰመኮ አመልክቷል።

የክልሉ ጸጥታ ሁኔታ በነዋሪዎች ላይ ያደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰትም የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ መሆኑን አስገንዝቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል ወንዞች ሞልተው ባስከተሉት የውሃ መጥለቅለቅ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቀሉ።

በክልሉ በጋምቤላ ከተማ ጨምሮ በ9 ወረዳች ወንዞች ሞልተው ባስከተሉት መጥለቅለቅ ዜጎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

እንደ ክልሉ መግላጫ ፦
- የባሮ፣
- የአልዌሮ፣
- የጊሎና
- የአኮቦ ወንዞች ሞልተው በመፍሰሳቸው ነው በነዋሪች ላይ ጉዳት የደረሰው።

በክልሉ ደጋማው አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በኑዌር ዞን የሚገኙ አምስቱም ወረዳዎች፣ ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግና ጆር ወረዳዎች ላይ የውሃ መጥለቅለቅ ተከስቷል።

የውሃ መጥለቅለቅ ከደረሰባቸው ወረዳዎች፤ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። ተፈናቃዮቹን ለጊዜው ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች እንዲጠለሉ ተደርጓል።

ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ለማድረግ የአደጋውን መጠን የመለየት ስራ እየተከናወነ ነው ተብሏል።

በቀጣይም የወንዞቹ ሙላት ሊጨምርና ከዚህ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጋምቤላ ክልል ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
በጋምቤላ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_ከግንቦት_ወር_2015_ለያዩ_ያ_የደረሱ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰቶችን.pdf
928.6 KB
#ጋምቤላ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፦

" ግንቦት 13/2015 ዓ.ም. በኢታንግ ልዩ ወረዳ ሥር በሚገኝ ፒኝዋ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አንድ ግለሰብ መጥፋታቸውን ተከትሎ፣ በፒኝዋ ቀበሌ እና አጎራባች በሆነው በሌር ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት በወቅቱ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የግለሰቦች እና የተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት እና ዘረፋ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚሁ ግጭት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በጎግ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ እና ጋምቤላ ከተማ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ጥር ወር 2016 ዓ.ም. በተለያዩ ወቅቶች በሰዎች ሕይወት እና በንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ደርሷል።

ኢሰመኮ ማረጋገጥ በቻለው መረጃዎች እና ማስረጃዎች መሠረት ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት አልፏል ፣ 113 ሰዎች ላይ አካል ጉዳት ደርሷል ፤ በግለሰቦች እና ተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። "

(ኢሰመኮ በጋምቤላ ክልል የተከሰቱ ግጭቶችና የፀጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ያስከተሉትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የላከልን ባለ 15 ገፅ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጋምቤላ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_ከግንቦት_ወር_2015_ለያዩ_ያ_የደረሱ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰቶችን.pdf
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ብቻ እንዲህ ሆኖ ነበር ....

ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦

ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ በጋምቤላ ከተማ፣ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው እና ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ትክክለኛ ቀኑ ባልታወቀበት ነገር ግን ሰዓቱ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ዶምቦስኮ ትምህርት ቤት አካባቢ አንድ ሰው ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች ተገድለዋል።

ግንቦት 14/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ 01 ቀበሌ ጀጀቤ ወንዝ አካባቢ 2 ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በጥይት ተመትተው ሞተዋል።

01 ቀበሌ ጀጀቤ ተራራ አካባቢ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ገደማ 7 ሰዎች በጥይት ተገድለዋል።

ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ አንድ በአካባቢው ማኅበረሰብ #የአእምሮ_ሕመም እንዳለበት የተገለጸ ሰው 04 ቀበሌ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አካባቢ #በቡድን በተሰባሰቡ ወጣቶች ጥቃት #በስለት_ተወግቶ ተገድሏል።

ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ገደማ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ፦
* የቀድሞውን የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል፤
* የጋምቤላ ክልል መደበኛ ፖሊስ
* የጋምቤላ ክልል ሚሊሻ መለዮ ልብሶችን የለበሱ እና ሌሎች የታጠቁ ሰዎች በ3 የተለያየ አቅጣጫ በመግባት በቦታው የነበሩ 9 ሰዎችን በጥይት ገድለዋል፤ ሌሎች 4 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት አካባቢ 04 ቀበሌ፣ ቄራ ሰፈር አጉኛ አካባቢ የታጠቁ ሰዎች ወደ አንድ መኖሪያ ቤት በመግባት ተኩስ ከፍተው፤ አንድ ሰው ሲገድሉ በሌላ አንድ ሰው ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፡፡

የኢሰመኮ ባለ15 ገፅ ሪፖርት ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/85541

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በየጊዜው እየተፈፀሙ ያሉት #ጎራን_የሚለዩ ግድያዎች ፣ ጥቃቶች አሁን ካለው የከፋ ነገር ይዘው እንደይመጡ ፦
➡️ ሳይረፍድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው
➡️ ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ
➡️ ለተበዳይ ወገኖችም ፍትህ መስጠት እንደሚገባ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች አሳስበዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ የክልሉ ነዋሪ ፥ " በየጊዜው እየተፈፀሙ ያሉት ግድያዎች የከፋ መዘዝ ይዘው ሊመጡ የሚችሉ ናቸው ስለዚህ ጠንካራ መፍትሄ ይፈልጋል " ብለዋል።

ከግድያ ባለፈም የሚፈፀሙ የወንጀል ተግባራት ደህንነትን የሚነሱ ናቸው ሲሉ አክለዋል።

ነገ እርስ በእርስ ሰዎች እንዳይጠፋፉ አሁን ያለው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይደረስ መድረግ አለበት ብለዋል።

ሌላኛው ቃላቸው የሰጡ ነዋሪ ፥ በዚህ ወር ብቻ ሰዎች በተለያዩ ስፍራዎች ተገድለዋል ብለዋል።

በጋምቤላ አንድ የትራፊክ አባል " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ሰዎች በጥይት ከተመታ በኃላ ችግሮች እየተባባሱ ሄደው በፍራቻ ምክንያት በከተማው እንቅስቃሴ እስከመስተጓጎል ደርሶ እንደነበር ገልጸዋል።

በአቦቦ ወረዳ ደግሞ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ቢያስን 3 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀድምም እዚሁ ወረዳ ግድያ ተፈፅሞ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከቀናት በፊት ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን ባለው መስመር ህዝብ ጭኖ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተፈፀመ ጥቃት 5 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

በኢታንግ ልዩ ወረዳም ግጭቶች እንደነበሩ ጠቁመዋል።

" እየተፈፀሙት ላሉ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች  ተጠያቂነት ሲረጋገጥ እያየን አይደለም " ብለው ችግሩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

ሌላው መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የክልሉ ነዋሪ ፥ " በቀን 18/7/2016 ከተርፋም ወደ ጋምቤላ መስመእ የህዝብ ማመላለሻ መኪናን ታጣቂዎች መትተውት እስካሁን የሰው ህይወት አልፏል ፣ የተጎዱም ሆስፒታል ገብተዋል " ብለዋል።

እኚሁ ነዋሪ ጥቃቱ የተፈፀመ ከተርፋም ወደ አቦል ሲቃረብ ቢያንስ 7 ኪ/ሜ እንደሆነ አስረድተዋል።

አቦል የምትባለው ወረዳ ላይ ዝርፊያና ግድያ በተደጋጋሚ እንደሚፈፀም ጠቁመዋል።

ነዋሪው ፥ ባለፈው ሳምንት አንድ  የትራፊክ ፖሊስ መሀል አደባባይ ላይ በባጃጅ በመጡ ሰዎች በጥይት ከተመታ በኃላ ነገሮች መባባሳቸውን ጠቁመዋል።

ሌላው በክልሉ ያለው ችግር የሚያጠፉ ሰዎች በህግ አለመጠየቃቸው ነው ያሉት ነዋሪው " የህግ የበላይነት የሚባለው ነገር ጠፍቶል " ሲሉ ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ አስረድተዋል።

ነዋሪዎቹ ጋምቤላ ክልል ያለው ሁኔታ ቸል የሚባል ስላልሆነ የፌዴራሉም መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥበት አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ፥ ጋምቤላ ክልል እየተከሰተ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር  ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት ነው የፌዴራል እና የክልል ፀጥታ አመራሮች ውይይት የተካሄደው።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሸነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ፥ አንዳንድ ግለሰቦች ጎራ እየለዩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ ማፈናቀልና የተለያዩ ጉዳቶችን እያደረሱ እንዳሉ መገምገሙን ተናግረዋል።

ችግር ፈጣሪዎችም በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።

የፌደራል ፖሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፀጥታ አካላት የፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍ ወደ #ኦፕሬሽን_ገብተው ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ ይገኛሉ ብለዋል።

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

አዲስ አመራር ከመጣ በኃላ በጋምቤላ መሻሻል ታይቷል ?

በጋምቤላ ክልል ካለፈው ነሐሴ 2016 ዓ/ም ወዲህ የአመራር ለውጥ ከተደረገ ወዲህ በክልሉ የነበረው የሠላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን አዲሱ አስተዳደር፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት በጋምቤላ ክልል በተለያዩ አካባቢዎችና ጊዜዎች ግጭቶች እየተከሰቱ በሰው ህይዎት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል።

ከሰብዓዊ ጉዳቱ ባሻገር በክልሉ ነዋሪዎች መካክል የነበሩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በአንዳንድ ቦታዎች እስከመገደብ ደርሰውም ነበር።

የክልሉ ልማትና ሰላምም በእጅጉ ተጎደቶ ነበር።

በተለይ ቀደም ባሉት ጊዜዎች የአኙዋክ ተውላጆች ወደ ኑዌር ሰፈር አይሄዱም፣ ኑዌሮችም በተመሳሳይ ወደ አኙዋክ ሰፈር ይሻገሩ አልነበረም።

አሁን ላይ ግን ሁኔታዎች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን የጋምቤላ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ጋትሏክ ሮን ምን አሉ ?

- ችግሮችን ለማስተካክልና በክልሉ ሠላም ለማስፈንና ህዝቡን ወደልማት ለማምጣት በክልሉ ከነሐሴ 2016 ዓ/ም መጀመሪያ ሳምንት ላይ የአመራር ለውጥ በመደረጉ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ሠላም ሰፍኗል።

- በክልሉ በነበረው የሠላም እጦት ምክንያት የጋምቤላ ከተማ የአኙዋክና የኑዌር በሚል ተከፍሎ አኙዋኮች ወደ ኑዌር ሰፈር፣ ኑዌሮችም ወደ አኙዋክ መንደር ለመሻገር ችግሮች ነበሩ። አሁን ያ ሁሉ ቀርቶ አዲሱ አመራር ወደ ሥራ ከገባና ህዝባዊ ውይይቶች ከተደረጉ በኋላ ሁሉም በሠላም በሁሉም ሥፍራ ይንቀሳቀሳል።

🔵 ማሉት ዴቪድ የተባሉ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩን ሀሳብ ይጋሩታል፣ አሁን አንዱ ወደ ሌላው ያለስጋት እንደሚንቀሳቀስ ነው ያረጋገጡት። ከተማውም ሠላም እንደሆን አመልክተዋል።

- አዳዲስ ሹመቶችና ምደባዎች ተሰጥተዋል። ይህም የትምህርት ዝግጅትንና የሥራ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው።

- ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ የታመነባቸው ቀደም ሲል ስልጣን ላይ የነበሩና ህዝባዊ አመለካከት ያላቸው በርከት ያሉ አመራሮችም በአዲሱ ሹመትና ምደባ እንደገና  ተካተዋል።

- " ሠላም ወርዶ ህዝቡ በልማት መካስ አለበት " በሚል እሳቤ እውቀት፣ ልምድና የተሻል አመለካክትና እይታ ያላችው ሠዎች ወደ አመራሩ ተካተዋል።

- በኮታ መታሰር ቀርቷል። ቀደም ሲል በነበረው አሰራር ወንጀል ያልሰሩ ሰዎች በኮታ ጭምር ይታሰሩ ነበር። አሁን ግን በወንጀል የተጠረጠሩትን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ አሰራር ተዘርግቷል።

- በፊት አንድ ኑዌር ቢያጠፋና ቢታሰር ሌላ አኙዋክ አብሮ እንዲታሰር ይደረግ ነበር፣ ሌላ አኙዋክ አጥፍቶ ቢታሰር  የኑዌር ተወላጅ ተደርቦ እንዲታሰር ይደረግ ነበር ፤ አሁን ግን ጠፋተኛው ከየትኛውም ወገን ይሁን ጠፋተኛ ከሆን ተጠርጣሪው ብቻ ተለይቶ ተጠያቂ ይሆናል። የኮታ እስር ቀርቷል።

" ከአዲሱ አመራር ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ " - ጋብዴን

የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጋብዴን) ሊቀመንበር አቶ ኡባንግ ኡሞድ ቀደም ሲል የነበረው አመራር ህዝቡን መምራት እንዳልቻለና ለውጥ እንዲመጣ ሲታግሉ እንደንበር ገልጠዋል።

ችግሩ የአመራሩ ሆኖ ሳለ ህዝቡን በከፍተኛ የሠላም እጦት ውስጥ ከትቶት ነበር ነው ያሉት።

በክልሉ የነበረውን ችግር እስከ የተፎካካሪ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት በማድረስ የነበረው የሠላም እጦት እንዲታወቅ መደረጉንና ለውጥ እንዲደረግ በግልም በጋራም ትግል ሲደረግ እንደነበር አስረድተዋል። 

አዲሶቹ አመራሮች በሕዝቡ ተቀባይነት ማግኘታቸውንና ፓርቲያቸውም በአዲሱ አመራር ደስተኛ መሆኑን አቶ ኡባንግ ተናግረዋል።

ከአዲሱ አመራር ጋርም በጋራ ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑም ነው የገለጡት። 

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ነሐሴ 9/2016 ዓ ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡመድን የመጀመሪያዋ የክልል ሴት ርዕሰ መስተዳድር፣ ዶ/ር ጋትሏክ ሮንን ደግሞ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia