TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሻሸመኔ ወደ መረጋጋት ተመልሳለች!

በዛሬዉ ዕለት በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል።

አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ነዉ።

በአደጋውም እስካሁን በደረሰን ሪፖርት የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱም ታዉቋል። በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ላለፈ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።

ከአደጋው ጋር ተያይዞም የተወሰኑ ህገወጥ ቡድኖች ከተማዋ ላይ ህገወጥነት፣ ብጥብጥ እና ግጭት ለማስነሳት ተንቀሳቅሰዋል። በዚህ ሂደትም ቦንብ ይዞ ተገኝቷል በሚል #ሀሰተኛ_ወሬ በአንድ ግለሰብ ላይ በቡድን ጥቃት በማድረስ የግለስቡ ህይወት ሊያልፍ ችሏል። ይህ ድርጊት አስነዋሪና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ሰላም ወዳዱን የሻሸመኔ ከተማ ህዝብም ሆነ የሻሸመኔን ቄሮ የማይወክል የክፋት ተግባር ነዉ።

ግለሰቡ ላይ የተፈፀመዉን ግድያም አጥብቀን #እናወግዛለን። በተጨማሪም አንድ የሻሸመኔ ከተማ የፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ተሽከርካሪ በእሳት ጋይቷል። ተሽከርካሪው ፀጥታ የማስከበበር ስራ ላይ በተሰማራበት ወቅት ቦምብ ጭኗል በሚል #የተሳሳተ መረጃ በመሰራጨቱ ነዉ። ሆኖም ግን በተሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት ቦምብ እንዳልነበረ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ማረጋገጥ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ሰላም ወዳዱ የሻሸመኔ ከተማ ህዝብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ጥረት ከተማዋ ወደ መረጋጋት ተመልሳለች።

በዛሬዉ ዕለት በተፈጠረዉ ችግር በመሳተፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦችንም ህዝቡ እና ፖሊስ በመቀናጀት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

©አቶ አዲሱ አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia