“ ድርጊቱ ተፈጽሟል። ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ግን የኛ አባላት አይደሉም ” - የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል
የኃይማኖት አባቶች፣ ትልልቅ እናቶች፣ በእድሜ የበሰሉ አባቶች በጉልበታቸው ተንበርክከው እንዲሄዱ እንደተገደዱ የሚያሳይ ቪዲዮ በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል።
ተንበርክከው እንዲሄዱ የተገደዱትም ሰዎችም በቅርቡ የተቋቋመው “ የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል አባላት ” እንደሆኑ ተደርጎ ነው በማኀበራዊ ሚዲያው ወሬው የተራወጠው።
ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ፣ “ የ‘ፋኖ’ ታጣቂዎች ናቸው ” የተባለ ሲሆን፣ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ ደግሞ በጎጃም መሆኑ ተመላክቷል።
ይህንኑ ቪዲዮ የተመለከቱ ሰዎችም፣ በእናቶችና በኃይማኖት አባቶች ላይ በተፈጸመው ድርጊት ብስጭትና በሀዘን የተቀላቀለበት አስተያየት እየሰጡ ናቸው።
የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል ስለጉዳዩ ምን አለ ?
ድርጊቱ ሲፈጸምባቸው የተስተዋሉት እንደተባለው እውነትም አባሎቻችሁ ናቸው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል፣ “ ድርጊቱ ተፈጽሟል። ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ግን የኛ አባላት አይደሉም ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
“ የካውንስሉ ሰዎች አይደሉም ” ያሉት የካውንስሉ የህዝብ ግንኙነት አቶ እያቸው ተሻለ፣ “ ሲጀመር ደቡብ ሜጫ ላይ ነው ድርጊቱ የተፈጸመው " ብለዋል።
“ ደቡብ ሜጫ ደግሞ በ ‘ፋኖ’ እጅ ስላለ፣ ገና በቀጣይ ከፋኖ ጋር ተነጋግረን ነው ካውንስል ልናቋቁም እያስብን ነበር እንጂ የሰላም ካውንስል አልተቋቋመም እዛ ቦታ ” ነው ያሉት።
“ ስለዚህ ባለን መረጃ የሆነ የጤና ፓኬጅ NGO ውስጥ ያለ ተቋም ስብሰብ ጠርቷቸው እንደነበር ነው። እንጅ ገና ካውንስል እዛ ወረዳ አልተቋቋመም። እኛም አልጠራንም የኛ አባልም አይደሉም ” ነው ያሉት።
“ ቪዲዮውን ለሌላ ሽፋን ነው የተጠቀሙት፤ እንደተሳሳቱ ስላወቁት ነው ‘የሰላም ካውንስሉ’ ያሉት እንጂ አልተቋቋመም ሲጀመር ገና ከ ‘ፋኖ’ ጋር ተነጋግረን ነው በቀጣይ ልናቋቁም ያሰብነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
የተሰራጨው ቪዲዮ የሰዎችን ማንነት በግልጽ ያሳያል ቪዲዮውን አይታችሁት ነበር ? ሲል ቲክቫህ ላቀረበው ጥያቄ አቶ እያቸው፣ “ አይቸዋለሁ። ግን የኛ አባል አይደሉም ” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፤ ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑስ ካውንስሉ ያውቃል? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።
አቶ እያቸው በሰጡት ምላሽ፣ " አያውቅም። እነርሱ ራሳቸው ፋኖዎቹ ምላሽ ይስጡበት። እኛ አናውቅም እነማን እንደሆኑ " ነው ያሉት።
በሌላ በኩል ፥ አማራ ክልል በሰጠው መግለጫ በቪድዮ የሚታዩት የሰሜን ጎጃም ዞን፣ በደቡብ ሜጫ ወረዳ ልዩ ስሙ ገርጨጭ በሚባል አካባቢ ነዋሪ ናቸው ብሏል።
ለተለያዩ ስራዎች ባህር ዳር ከተማ ደርሰው ሲመለሱ ' የሰላም ኮሚቴ አባላት ለመሆን ነው ' በሚል ምክንያት መያዛቸውን ፣ በእንብርክክ እንዲሄዱ መደረጋቸውን፣ እከተያዙት ውስጥም የተገደሉ እንዳሉ አመልክቷል።
ከተገደሉት ውስጥ የወረዳ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጁ መርጌታ ግሩም፣ የሀገር ሽማግሌ አቶ አዘነ አድማሱ፣ የሀገር ሽማግሌ አቶ አስማማው አቤ፣ ወ/ሮ የኔአየሁ ዳኛው የተባሉ የከተማው ነዋሪ ይገኙባቸዋል ብሏል።
ሌሎች 13 አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Urgent🚨 የጎፋ ዞን ፖሊስ የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ የደረሰ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። " የሰው ኃይል በጣም ተዳክሟልም " ብሏል። በሌላ በኩል ፤ በጎ ፈቃደኞች በጉልበትም ፣ በምግብ እና በአልባሳት አቅርቦት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። በተለይ ወደቦታዉ ማቅናት የሚችሉ በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ቢኖሩ ብዙ ሊያግዙ ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን…
#ጎፋ🕯
በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ የሞቱ ዜጎቻችን ቁጥር ከ260 በላይ ደርሷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፍለጋው በተመለከተ ከጥቂት ደቂቃ በፊት የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉን አነጋግሯል።
አሁን ላይ የክልልና የፌደራል አመራሮች ቦታው ላይ እንደደረሱ ነግረውናል።
የእርዳታ አቅርቦቱ ጥሩ ነው ቢሆንም አሁንም ድጋፍ የሚሹ አካላት አሉ ብለዋል።
የቁፋሮ ማሽን መድረሱ ስራውን ቀላል እንዳደረገው ጠቁመዋል።
የሟች ወገኖቻችን ቁጥር 260 መድረሱን ከሰዓታት በፊት መረጃ እንደደረሰን ነግረናቸው ነበር።
እሳቸውም ፤ " ሪፖርት ከተደረገዉ ውጭ 10 አስከሬን አግኝተናል " ብለዋል።
ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ የዞኑን የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000511561276 መጠቀም ትችላለችሁ።
#TikvahEthiopiaFamilyHW

#teleTV
በድርጊት እና በአስፈሪ ዘውግ የተሞሉ የሃገራችን ድንቅ ፊልሞች "6 ሰአት ከለሊቱ" እና "ትዝታ" በቴሌቲቪ መተግበሪያ ብቻ!!
ዛሬዉኑ የቴሌቲቪን መተግበሪያ ከ Playstore ወይም ከ Appstore https://teletv.et/download በማውረድ አልያም በ ድህረ-ገጽ https://www.teletv.et ላይ በመግባት መመዝገብ ይችላል።
👉ቴሊቲቪ ላይ የሚገኙ ፊልሞችን መመልከት የሚቻለው መተግበሪያው ላይ ብቻ ነው!!
ቴሌቲቪ! ሲኒማ በስልክዎ !
#TeleTV #Tizita and #KeLelitu6Seat #Tiztamovie #6seatkelelit #Staytuned #Launch

#አግዙ
የጎፋ ዞን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በ8091 ድጋፍ እያሰባሰቡ እንደሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቆናል።
በደረሰዉ ድንገተኛ የሆነ የመሬት ናዳ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የሚውል ድጋፍ በ8091 ላይ ማድረግ ይቻላል።
አቅምዎ የፈቀደውን የገንዘብ መጠን በመላክ ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ TPLF ምን አሉ ?
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦
" የምርጫ ቦርድ ' ምርጫ አራዝማለሁ ' ሲል ብዙዎቻችን ስንስማማ TPLF አልስማማም ብሎ የገባንበት ቀውስ ይታወሳል። ምን ያክል ሰው እንደወደመ፣ ምን ያክል ሃብት እንደወደመ መገመት ይቻላል።
ያ የወደመ የሰው ህይወት እና የወደመ ሃብት በትክክል ሳይገመገም እንዴት ጠፋ ሳይባል ሌላ ጥፋት ማምጣት ጥሩ አይደለም። ህዝቡ ይጎዳል።
እኛ ባለፈው እናተም እንደምታውቁት TPLF እና መሰል ፓርቲዎች በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ሕጋዊ ፓርቲ እንዲሆኑ በአዋጅ አሻሽለናል። መንግሥት ፍላጎት አለው።
ከዚያ በኃላ ንግግሮች ነበሩ አቃቤ ህግ ለምርጫ ቦርድ መጻፍ ነበረበት ጽፈናል። ምርጫ ቦርድ ስራውን ሰርቶ የሚያጣራውን አጣርቶ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈቅድላቸው።
የአስፈጻሚውን ስራ 100% ሰርተናል።
ፓርቲ ለፓርቲ ውይይቶች ነበሩ የመንግሥት ለመንግሥት ውይይቶች ነበሩ ጥያቄዎች ተነስተው መልሰናል። ለምን ሰላም እና ሕጋዊ መንገድ ስለሚያዋጣ።
TPLF አሁን ማድረግ ያለበት ምርጫ ቦርድ ሄዶ በ2 እና 3 ሳምንት ውስጥ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ነው ጉባኤ ማድረግ ያለበት።
ባያደርግስ ? እኔ ብፈልግም ባልፈልግም ዋጋ የለውም። ምርጫ ቦርድ ካልተቀበለው TPLFን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፦
➡ በምርጫ ሊሳተፍ አይችልም
➡ መንግሥት ሊሆን አይችልም
ይህ ምን ማለት ነው ተመልሰን ጦርነት ውስጥ እንገባለን።
ተመልሰን ጦርነት ውስጥ ከምንገባ ተመልሰን ጭቅጭቅ ውስጥ ከምንገባ ቀላል ነው ዋና ዋናው አልቋል ሕግ ተበጅቷል ተስማምተናል የቀረች ጉዳይ አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ጉባኤ አካሂዶ ፓርቲውን መልሶ ወደ ፖለቲካ ስርዓት መመለስ ከሁሉ በላይ TPLFን ከTPLF የትግራይ ሕዝብን ፣ ከዚህ ቀጥሎ ሁላችንንም ይጠቅማል። "
[ ሰሞኑን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተወያዩበት ጊዜ የተናገሩት ]

Photo
#TPLF
የህወሓት / TPLF ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ይካሄዳል ከተባለው ድርጅታዊ ጉባኤ ራሱን አገለለ።
ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽኑሀምሌ 17/2016 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ጉባኤ ራሱን ስለማገለሉ የሚመለከት ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል።
ድርጅቱ በቀጣይ ትግል ይስተካከላል በሚል ከማእከላዊ ኮሚቴ ፣ ከቁጥጥር ኮሚሽን ፣ ከአባላት የተውጣጣ 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንደነበር አመልክቷል።
ይሁን እንጂ የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን ባካሄዱት ግልፅ መግባባት ስራቸው ቢጀምሩም ከተቀመጠው የጋራ አሰራር ውጪ ኢ-ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር መስፈቱን ችግሩ እርማት እንዲወሰድበት የቀረበውም ጥያቄ ተቀባይነትና ሰሚ እንዳላገኘ ጠቁሟል።
" የህወሓት 14ኛው ጉባኤ ዝግጅት ሂደት የበላይነት አለኝ በሚል ሃይል ተጠልፎ ወደ አደገኛ ሁኔታ እያመራ ነው " ያለው ኮሚሽኑ ግልፅነትና ዴሞክራሲያውነት የጎደለው አካሄድ የሚያስከትለው አደገኛ መዘዝ በመረዳት ኮሚሽኑ ከጉባኤው ራሱ ማግለሉም አሳውቋል።
በዚሁ መሰረት ፦
1ኛ. በጉባኤው ዝግጅት እንዲሳተፉ የተወከሉ የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ከዝግጅት አባልነታቸው እንዲነሱ መደረጉን አመልክቷል።
2ኛ. የቁጥጥር ኮሚሽኑ አካሄድ ወደ ጎን በመተው አደገኛ አካሄድ በመከተል ጉባኤ አካሂዳለሁ የሚለው ሃይል ወደ ሙሉ መተማመን እስኪደረስ ድረስ ማእከላዊ ኮሚቴ ሃላፍነት ወስዶ ከድርጊቱ እንዲያቆመው ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን በጥብቅ አስጠንቅቋል።
3ኛ. ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽኑ የሚያቀርበው ጥያቄና አቋም ወደ ጎን በመተው የጉባኤው ዝግጅት ከቀጠለ በዚሁ ሂደት ለሚከተለው ማንኛውም አደጋ ሃላፊነት የሚወስደው ራሱ ጉባኤ አካሂዳሎህ የሚለው አመራር መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ብሏል።
ትላንትና የህወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን " ህወሓት በሁለት ኔትወርክ ተከፍሎ እየታመሰ ነው " ማለቱ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamliyMK

ህወሓት ለማዘጋጀት ያቀደው ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ራሳቸው ከሃላፊነታቸው አገለሉ።
የኮሚቴው ም/ሰብሳቢ ተስፋይ ገ/እግዚአብሔር ለህወሓት ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ ከሃላፊነት ራሳቸው ስለማግለላቸው አሳውቀዋል።
" በኮሚቴው ስራ ውስጥ የሚታዩ ጣልቃ የመግባት ፣ ከፕሮግራም ውጪ ስብሰባ መጥራት፣ ውሳኔዎችን መጠምዘዝ የመሳሳሉ ተግባራት እንዲታረሙ ለመስራት ብሞክርም አልተሳካም " ብለዋል።
" የምታገልበት ድርጅት ዴሞክራሲያዊ ፣ ግልፅና አሳታፊ መሆኑ አምናለሁ " ያሉት ምክትል ሰብሳቢው " ሆኖም በኮሚቴው ስራ ውስጥ ልቋቋማቸው የማልችላቸው አካሄዶች እየታዘብኩ ነው " ሲሉ አብራርተዋል።
" ይህንን ስርዓት የለሽ አካሄድ ከእምነቴ ፣ ከትግል አቋሜና ከሞራሌ የማይሄድ በመሆኑ ከሀምሌ 13/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሃላፊነቴና ከኮሚቴ አባልነቴ አግልያሎህ " ብለዋል።
" የድርጅቱ አባልና አመራር ግልፅ እንዲሆንለት እስካሁን የገጠሙኝ እንቅፋቶችና ንቀት በመደበኛ ሚድያ ይፋ አደርጋለሁ " ብለዋል።
አቶ ተስፋይ የትግራይ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚም ናቸው።

ወጋገን ባንክ “እፎይታ” የተሰኘ የዲጂታል ብድር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።
ወጋገን ባንክ ከክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር “እፎይታ” የተሰኘ የዲጂታል ብድር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ወደ 3.2 ሚሊዮን የሚጠጉ አስተኛ እንዲሁም 7.8 ሚሊዮን ጥቃቅን የንግድ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ዜጎችን የስራ ማስኬጃ ካፒታል እጥረት ያጋጥማቸዋል።
ይህ የዲጂታል ብድር አገልግሎትም በዋናነት በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎች የንግድ ማስፋፊያ እና የስራ ማስኬጃ ካፒታል ለማሟላት ያለመ ነው ተብሏል።
በተለንም በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሥራ መጀመር ተስኗቸው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ በርካታ ሴቶች ፋይናንስ በማቅረብ እራሳቸውን እንዲችሉ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ታምኖበታል።
አገልግሎቱን ለመጠቀም ደንበኞች ማንነታቸውን የሚገልፅ መረጃ በማሟላት በባንኩ ሂሳብ መክፈት እንዲሁም የእፎይታ ብድር አገልግሎት የሞባይል መተግበሪያን ከፕሌይስቶር በማውረድ የብድር ጥያቄያቸውን በማቅረብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።
#ወጋገን_ባንክ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉንም ታላላቅ ሊጎች ለሁላችንም!
ሁሉንም ወሳኝ ጨዋታዎች ፣ ደማቅ ግጥሚያዎች ፣ የዋንጫ ፍልሚያዎች በዲኤስቲቪ!
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፣ ቻምፒዮንስ ሊግ ፣ ላሊጋ ፣ ሴሪአን ጨምሮ ከጨዋታ እስከ ትንታኔ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ ... ሁሉም በዲኤስቲቪ!
እንደየምርጫዎ በሁሉም ፓኬጅ ላይ ኳስ ያለው ዲኤስቲቪ!
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#DStvEthiopia
#ሁሉምያለውእኛጋርነው
#DStvSelfServiceET

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሐና አጥናፉ ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት ቃል ፦
" የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ በረራ እንዳያደርግ መታገዱን የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሶናል።
ይህ ከመደረጉ ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የምናደርገውን በረራ እንድናሳድ፣ የመጫን አቅማቸው ከፍተኛ የሆኑ አውሮፕላኖችንም እንዲጠቀም ተጠይቀን ነበር።
በረራ እንድናቆም የሚጠይቀው ደብባቤ ከመድረሱ ከሁለት ሳምንት በፊት ነው ፦
- የምናደርገውን በረራ ከ10 ወደ 15 እንድናሳድግ፣
- የምንጠቀመውን መለስተኛ አውሮፕላን ወደ ከፍተኛ አውሮፕላን እንድናሳድግ ፣
- በቀን ሁለት በረራ እንዲሁም በየሳምንቱ ዓርብ ሦስት በረራ እንድናደርግ ጠይቀውን የነበረው።
በረራ እንድናሳድግ የሚጠይቅ ደብዳቤና ፈቃድ በተሰጠን በሁለት ሳምንት ውስጥ አሁን በረራ እንድናቆም የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሶናል።
ይህም ባልተገባ መንገድ በማኅበራዊ ሚዲያ እንዲሰራጭ መደረጉ አስገራሚና አስደንጋጭ ነው።
ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንድናቆም በሚያሳውቀው ደብዳቤ ላይ በረራው እንድናቆም የተወሰነበት ምክንያት ደብዳቤው ላይ አንዳችም ቦታ አልተገለጸም።
በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተላከ ባለመሆኑ፣ በደብዳቤው ላይ ለተዘረዘሩት ጉዳዮች ምላሽና አስተያየት መስጠት አንፈልግም።
በጉዳዩ ዙሪያ ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ጋር ለመነጋገር እንሞክራለን። "
#EthiopiaAirlines🇪🇹

#አዲስአበባ #መታወቂያ “ በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” - CRRSA ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት በቅርብ ጊዜ መሰጠት ይጀመራል ተብሎ ነበር። ነገር ግን እስካሁን አገልግሎቱ አልጀመረም። ነዋሪዎችም መቼ እንደሚጀምር ጠይቀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቼ ነው አገልግሎቱ መስጠት የሚጀምረው ? ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት…
#አዲስአበባ #መታወቂያ
“ የትምህርት ቤት ምዝገባው ሲጠናቀቅ አገልሎቱን መስጠት እንጀምለራለን ” - CRRSA
ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት “በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን” መባሉን ከወራት በፊት ነግረናችሁ ነበር።
አሁንስ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትሰጡ ከዚህ ቀደም ገልጻችሁ ነበር፤ ለመሆኑ ጉዳዩ ከምን ደረሰ? ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን ዛሬ ጠይቋል።
የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ አለማየሁ በሰጡት ምላሽ፣ አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ገልጸዋል።
“ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀን ነበር ” ያሉት አቶ ዮናስ፣ “ ከተማ ውስጥ የትኛውም የየትምህርት ምዝገባ በልደት ካርድ መነሻ መሆን እንዳለበት አሰራር ዘርግተናል ” ብለዋል።
“ በዚህ መሠረት አሁን ባለው ሁኔታ ቢሮዎቻችን ይህንን አገልግሎት እየሰጡ ስለሆነ አብሮ ማስኬድ የማይቻል በመሆኑ ከትምህርት ቤት ምዝገባ በኋላ እንጀምራለን ” ሲሉ አክለዋል።
ከትምህርት ምዝገባ በኋላ መቼ እንደሚጀመር ቲክቫህ የጠየቃቸው አቶ ዮናስ፣ ከነሃሴ አጋማሽ 2016 ዓ/ም በኋላ እንደሆነ አስረድተዋል።
“ለዚህ የሚሆኑ ምቹ ሁኔታዎች አሉ” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ “ሁሉም ወረዳዎች (119ኙም) በአሁኑ ወቅት ዲጂታላይዝድ ሆነዋል። አዲስ አበባ የወረቀት መመታወቂያ ለአንዴና ለመጨረሻ ተሰናብታለች ሰኔ ወር ውስጥ” ነው ያሉት።
“ ምቹ ሁኔታዎች አሉ። የማጭበርበር አዝማሚያም ካለ እጅግ በጣም Rare ነው የሚሆነው። ከክልል ከተማ የሚመጡት ሰዎች አገግሎቱን ሲያገኙም ጥብቅ የሆን ቃለ መጠይቅ ይኖራል ” ሲሉ ተናግረዋል።
“ በቃለ መጠይቁ ውስጥ የምናገኛቸው ጉድለቶች፣ ግድፈቶች ካሉ አገልግሎቱን ልንከለክልበት የምንችል ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ” ብለዋል።
አቶ ዮናስ አክለው፣ “ ምክንያቱም ከክልል የሚቀርቡ መረጃዎችና መልቀቂያዎች ሀሰተኝነታቸው እየጨመረ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ እየሆነ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
“ ከፍተኛ ፍልሰት አዝማሚያው ምዝገባውን አግኝቶ ማስረጃውን ማግኘትም ጭምር ብቻ እንደሆነ አንዳንዱን ገምግመናል” ብለዋል።
“ በዚህ መልክ ተደራጅቶ እየተጠባበቀ ያለው ነዋሪ 47,000 ነው። ከዛ ውስጥ 40% ከአማራ ክልል፣ ኦሮሚያ ክልል 35%፣ ቀሪ የኢትዮጵያ ክልሎች 25% ሆኖ ተተንትኗል ” ነው ያሉት።
አክለው፣ “ ከእነዚህ ውስጥ ሃሰተኛ የሚያስመስሉ መሸኛዎች ያስገቡ መኖራቸውን አረጋግጠናል ” ብለዋል።
“ ጤነኛ የሆነ መሸኛ ይዞ የሚመጣ ደግሞ ይኖራል ” ያሉት አቶ ዮናስ፣ ህጋዊ የሆኑትን ለማስተናገድ ዝግጅታቸውን እንዳተጠናቀቁ፣ የት/ቤት ምዝገባ እንደተጠናቀቀ አገልግሎቱን መስጠት እንደሚጀምሩ አስረድተዋል።

ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture
አሁኑኑ ወደ መሸጫ መአከሎቻችን ይምጡ! በግብይትዎ ተደስተው ይመለሳሉ! የውበት እና የጥራት ዳር ድንበር!
አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282
👉 Telegram: https://t.iss.one/yonatanbt_furniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture

የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ ነገ ይከበራል።
የንግሥ በዓሉ በተለይም በቁልቢ እና ሀዋሳ እጅግ በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ይውሏል።
ምእመናን ለነገው የንግሥ በዓል ካለፉት ቀናት አንስቶ ወደ ከተሞቹ እየገቡ ሲሆን ዛሬ በዋዜማው በርካታ ምእመናን በመኪና እና በአየር ተጉዘው ገብተዋል።
ዋዜማውም በተለያዩ ስርዓቶች ተከብሯል።
በዚህ ባለፈ በአዲስ አበባ ከተማ የንግሥ በዓሉ በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (ቤተመንግሥት ቅዱስ ገብርኤል) በድምቀት እንደሚከበር የገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ገልጿል።
በዓሉ በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል።
በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ የፓርኪንግ አገልግሎት ችግር እንደማይኖር አስተዳደር ጽ/ቤቱ አሳውቆናል።