TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲሱን አመት "አንድ ሆነን አንድ እንበል" በሚል መርህ #ኢትዮጵያዊነትን በሚገልፁ እሴቶች ለማክበር እየተዘጋጀ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ፦

#ኢትዮጵያዊነትን የሚፈታተኑ #ችግሮችን ለመከላከል ህዝቡ ለአንድነቱ ፀንቶ መታገል እንዳለበት አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አሳሰበ፡፡

ከዘረኝነትና ከማንነት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ #ግጭቶችን በአገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የዜጎች #መፈናቀልና ሞት መፈጠሩ አሳስቦኛል ያለው ፓርቲው መንግስት ከሰብዓዊ መብትና ከፀጥታ ጋር ተያይዘው ያሉ ህጎች ባአስቸኳይ ሊያስፈፅም ይገባል ብሏል።

በሃገሪቱ እዚህም እዚያም ያሉ #ግጭቶችን የሚፈጥሩ ግለሰቦችንም ሆነ ፖለቲከኞች የመለየት ስራ የህዝቦችም ሃላፊነት ነው ያለው ፓርቲው በየትኛውም አካል ጥፋት ህዝቡ መጎዳት እንደሌለበት ገልጿል።

መንግስት #ህጎችን በማስከበር ዜጎች በፈለጉት ክልል በነፃነት የመኖርና የመንቀሳቀስ መብታቸውን የማስከበር ህገ መንግስታዊ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተገልጿል።

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ...🔝

"ፀግሽ በአሁኑ ሰዓት በጎፋ ዛን ከመኖርያ ስፍራዎች ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ድጋፍ ለማድረግ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች እና አባቶች በጋራ በመሆን ወደጰስፍራው እያቀናን እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የአርባምንጭ ከተማን ነዋሪ አመስግንልን!!" #ፋሪስ ነኝ!

#ኢትዮጵያዊነትን ከመናገር በዘለለ #በተግባር ያገረጋገቹ የአርባምንጭ ከተማ እና አካባቢዋ ማህበረሰብ ላደረጋቹት መልካም ተግባር በፈጣሪ ስም እናመሰግናለን!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia