TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🕊ሰላም🕊

ሚዲያዎች ለሀገሪቱ #ሰላም የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ አለባቸው ሲሉ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒሰቴር ዴኤታዋ ወ/ሮ #አልማዝ_መኮንን ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "ምሁራን ትውልድን በእውቀት በማነፅ ሰላምን ይገነባሉ" በሚል መሪ ቃል በምሁራን በቀረበው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ተናግረዋል፡፡

ሰላም ከማህበረሰብ ጋር በመሆን የሚጠበቅ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስቴር ዴኤታዋ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ የህብረተሰቡ አንድ አካል መሆናቸውን ጠቅሰው የሰላም ሚኒስተር ደግሞ ይሄን በማሰብ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡

በጥናታዊ ፅሁፉ ላይ በዋናነት ሰላም በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ሁለንተናዊ ገፅታ በተለያዩ ምልከታዎች አብራርተውታል፡፡ በፅሁፉ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተወከሉ ምሁራንና ተማሪዎች ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱም ሰላምን ማስፈን የሁሉም ዜጋ ድርሻ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ🕊ትግራይ!

የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በሁለቱ ክልሎች #ሰላም ዙሪያ ተወያዩ።

በሁለቱ ክልሎች ሰላም ላይ ያተኮረው ውይይት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ መካሄዱን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ #አልማዝ_መኮንን፥ በየትኛው የታሪክ አጋጣሚ ህዝብ ከህዝብ #ተጣልቶ አያውቅም ብለዋል።

የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ህዝቦች ለዘመናት የኖረ #አብሮነት ያላቸው ተመሳሳይ ባህል የሚጋሩና የተዋለዱ ህዝቦች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰለም ለማሰፈን ችግሮችን ተሸክሞ የሚቆዝም ሰው ሳይሆን የይቅርታ ልብ ይዞ ህዝብን የሚያቀራርብ የሀገር ሽማግሌና የሀይማኖት አባቶች ያስፈልጉናልም ብለዋል።

ሚኒስቴር ዴኤታዋ የሀይማኖት አባቶች ከፖለቲካ ነፃ በመሆን መንግስት ሲሳሳት አደብ ግዛ ሊሉት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የሁለቱ ክልሎች የሀገር ሽማግሌዎች ሰፊ የሃሳብ ለውውጥ ካደረጉ በኋላ እርስ በእርሳቸው በመተቃቀፍ በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና ወንድማማችነታቸውን ለማጠናከር ቃል በመግባታ ተለያይተዋል።

በውይይቱ ላይ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፣ ፓስተር ዳንኤልና እና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
 
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ🔝

የሰላም ሚኒስቴር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር የግጭት አፈታትና የሰላም ባህል ግንባታን ላይ በጋራ ለመስራት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ #አልማዝ_መኮንን እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ሲሳይ_ሸዋአማረ አማካኝነት የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

የሰላም ባህልን ማሳደግና የሚፈጠሩና የተፈጠሩ #ግጭቶችን መፍታት አንዱ የማኅበረሰብ አገልግሎት ስራችን ነው ያሉት ዶ/ር ሲሳይ ግጭቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናትና የመፍትሔ ሀሳቦችን ለውሳኔ ሰጪ አካላት በማቅረብ ለዘላቂ መፍትሄ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንንም ዩኒቨርሲቲው በሰላም ባህል ግንባታ ላይ አለመግባባቶችን በሰላማዊና ዴሞክራሲያው መንገድ ለመፍታት የሚችል ማኅበረሰብ መፍጠር የሁሉም ምሁራን ድርሻ በመሆኑ ሊበረታታ ይገባዋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የሰላም ሚኒስቴር
©ዳንኤል መኮንን(ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia