TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቦትስዋና 👏 #ዴሞክራሲ

" ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " - ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ

በአህጉራችን አፍሪካ የተረጋጋ የዲሞክራሲ ስርዓት ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደሟ ቦትስዋና ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አድርጋለች።

በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች ለ58 ዓመታት ስልጣን ላይ የሚገኘውን ገዢ ፓርቲ ድምጻቸውን ነፍገውታል።

ፓርቲው አስደንጋጭ ነው የተባለ ሽንፈትን ተከናንቧል።

የፓርቲው መሪና የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫ መሸነፋቸውን አምነዋል።

ምንም እንኳን እስካሁን የምርጫው ውጤት በይፋ ባይታወጅም ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የከረመው ፓርቲያቸው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ ከፍተኛ ድምጽ አግኝቷል።

የፓርቲው እጩ ዱማ ቦኮ በዓለም ከፍተኛ አልማዝ አምራች ከሆኑት ሃገራት ውስጥ አንዷ የሆነችው ቦትስዋና ፕሬዝደንት ለመሆን ተቃርበዋል።

ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ለተቀናቃኛቸው ቦኮ ስልክ በመደወል በምርጫው መሸነፋቸውን ነግረዋቸዋል።

" በዲሞክራሲ ሂደቱ እጅግ ኩራት ተሰምቶኛል። ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " ብለዋል ፕሬዜዳንት ማሲሲ።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ማሲሲ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ሂደት ደስ እንደተሰኙ ገልጸው " የህዝቡን ፍላጎት እና ምርጫ አከብራለሁ " ብለዋል።

ደጋፊዎቻቸውን ረጋ እንዳሉ በእርጋታቸው እንዲቀጥሉና ከአዲሱ የሀገሪቱ መንግስት ጀርባ ተሰልፈው እንዲደግፉ በይፋ ጥሪ አቅርበዋል።

ቦትስዋና በአፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደም ነች በሚል ስትሞካሽ፣ በዓለም ከሩሲያ በመቀጠል ሁለተኛ የአልማዝ አምራች ሃገር ነች፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ ማግኘቱን ይገልጻል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦትስዋና

" የሀገራችንን የሰላም እሴቶች እናስቀጥል ፤ ... እንከን የለሽ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖር አረጋግጥላችኋለሁ " - ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ

ዱማ ቦኮ የቦትስዋና ፕሬዝደንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ይፋ ሆነ።

ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫው ተሸንፈዋል።

ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ከባድ ሽንፈት አስተናግዷል። ፓርቲውን ህዝቡ በድምጹ ቀጥቶት ሸንፈትን ተከናብቧል።

ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ በከፍተኛ ብልጫ አሸንፏል።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ፤ ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ቢፈልጉም በሰላማዊ ምርጫ መሸነፋቸውን አምነው ተቀብለዋል።

በሀገራቸው የዲሞክራሲ ሂደት ግን እጅግ ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ገለል ብለው በሽግግሩ ላይ እንደሚሳተፉም ጠቁመዋል።

ለተመራጩ ፕሬዜዳንትም ስልክ ደውለውላቸው በምርጫው መሸነፋቸውን አምነው " እንኳን ደስ አለህ " ብለውታል።

መላው ህዝብም በአንድነት አዲሱን የመንግሥት አስተዳደር እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም በጋራ የሀገሪቱን #የሰላም እሴቶች እንዲያስቀጥል ፤ እንዲያስከብር ጥሪ አቅበዋል።

እንከን የለሽ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖርም አረጋግጠዋል።

ሀገሪቱን ለማገልገል ለተሰጣቸው እድልም ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት አመስግነዋል።

ቦትስዋና አፍሪካ ውስጥ በተረጋጋ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቷ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦትስዋና

ከሰሞኑን በቦትስዋና በተካሄደው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸውን ያመኑት ሞከዌትሲ ማሲሲ ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዜዳንት ዱማ ቦኮ በይፋ በሰላም ፤ አቅፈዋቸውን ስልጣናቸውን አስረክበዋል።

ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ' የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ' ህዝቡ በድምጹ ቀጥቶት ከባድ ሽንፈት አስተናግዶ መሪነቱን ተነጥቋል።

ይህ ፓርቲ አፍሪካ ውስጥ ረጅም ዓመታትን በግዢነት የቆየ ነው።

ተቃዋሚ ፓርቲ የነበረው ' አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ' በከፍተኛ ብልጫ በማሸነፍ ፕሬዜዳንታዊ ስልጣኑን ተቆጣጥሯል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት በምርጫ መሸነፋቸውን ካመኑ በኃላ መላው ህዝብ በአንድነት አዲሱን የመንግሥት አስተዳደር እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ቦትስዋና አፍሪካ ውስጥ በተረጋጋ ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቷ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።

#ዴሞክራሲ #ምርጫ

@tikvahethiopia