TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#RUSSIA #AFRICA

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ወደ አፍሪካ ለሚገቡ የስንዴ ምርቶች ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ አሳውቀዋል።

ፑቲን የስንዴ ምርቶች ወደ አፍሪካ መላካቸውን ለማረጋገጥ ሃገራቸው እንደምትሰራም ገልጸዋል፡፡

ይህን የገለፁት ከወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና ከሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ጋር ከጦርነቱ ጋር በተያያዙ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሶቺ ከተማ በተወያዩበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ወቅት ማኪ ሳል አፍሪካ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖራትም በጦርነቱ ምክንያት ሰለባ መሆኗን ገልፀዋል።

በተለይ ከዩክሬንና ሩሲያ ይገቡ የነበሩ የግብርና ምርቶች እና ግብዓቶች ጉዳይ አፍሪካን ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር እንደዳረጋት አስረድተዋል።

ሩሲያን ጨምሮ የአፍሪካ አጋር የሆኑ ሁሉም ሃገራት የጣሏቸውንና በስንዴ እና በማዳበሪያ ላይ ያነጣጠሩ ማዕቀቦቻቸውን እንዲያነሱም ጠይቀዋል፡፡

የሩሲያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ሩድያ የምግዜም የአፍሪካ አጋር መሆኗን ገልፀው ከዩክሬን ወደ አፍሪካ ለሚገቡ የስንዴ ምርቶች በወደብ ላይ ለቀሩትም ጭምር ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዜዳንት ፑቲን ሰው ሰራሽ #የአፈር_ማዳበሪያ ምርቶች አፍሪካ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ዝግጁ ስለመሆናቸውም አሳውቀዋል።

ከ40 በመቶ የሚልቀው የአፍሪካ የስንዴ ፍጆታ በዩክሬን እና በሩሲያ የስንዴ ምርቶች የሚሸፈን ነው፡፡

መረጃው የአል አይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia