TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz ° “ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ 3 ወር ሆነው። ጨለማ ውስጥ እየኖርን ነው” - የወምበራ ወረዳ ነዋሪዎች ° “ ከወረዳው መንግስት ጋር እየተየጋገርን ነው፤ በቅርቡ እንሰራዋለን ” - የደብረ ዘይት ማዕከል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ወምበራ ወረዳ ደብረ ዘይት ከተማ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ ጨለማ ውስጥ ለመኖር መገደዳቸውን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። “ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ…
#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፤ አሶሳ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋረጠ 2 ሳምንት አልፏል።

የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ አገልግሎት ሊቆም እንደሚችል አሳውቋል።

ሆስፒታሉ በየቀኑ ከ400 እስከ 500 ከዞን ፣ ከወረዳ፣ ከአጎራባቹ ኦሮሚያ ክልል ታካሚዎችን ያስተናግዳል።

ሆስፒታሉ ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር 24 ሰዓት ሙሉ የማይቋረጥ ኃይል ማግኘት ያለበር ቢሆንም ባለፉት ሳምንታት የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ በተቋሙ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል።

ኃይል ከተቋረጠበት ቀን አንስቶ ለጄኔሬተር በየቀኑ ከ180 እስከ 200 ሊትር ነዳጅ እየተጠቀመ ነው።

ሁለት ጄኔሬተሮች ያሉ ቢሆንም ሙሉ ሆስፒታሉን ኃይል እንዲያገኝ የሚያስችሉ አይደሉም።

ያለ ጊዜያቸው የሚወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን ለማቆየት የሚሆኑ ማሽኖችን ማስነሳትም ከባድ ሆኗል።

በዚህ ማሽን ውስጥ የሚቆዩ ሕጻናት ያልተቋረጠ ኦክስጅን ማግኘት ስላለባቸው ኃይል መቋረጥ ካጋጠመ በሕጻናቱ ላይ ሞት ሊያስከትል ይችላል።

ሆስፒታሉ የተወሰኑ የሥራ ክፍሎችን የኃይል አቅርቦት እያጠፋ ነው ጄኔሬተሩ ሲነሳ የኤሌክትሪክ ኃይሉን ወደ ጨቅላ ሕጻናት ማቆያ ማሽኑ የሚቀይረው። ሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ ኃይሉ ሲፈለግ ደግሞ ማሽኑን ለማቋረጥ ይገደዳል።

ቀድሞም የበጀት እጥረት የሚፈተነው ሆስፒታሉ ለጄኔሬተሩ የሚውለው ነዳጅ ወጪ ከአቅም በላይ እንደሆነ የነዳጅ ማከማቻም አለመኖር ፈተና እንደሆነ ገልጿል።

ሆስፒታሉ ነዳጅ ከተለያዩ መ/ቤቶች እና ባለሃብቶች በልመና ነው ማታ ማታ እየዞረ የሚያመጣው።

ሁኔታው በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ጭምር ሊቋረጥ የሚችልበት አዝማሚያ እንዳለ አሳውቋል።

የአሶሳ ዞን ፥ በአሶሳ ከተማ እና በአካባቢው የኃይል መቋረጥ የተከሰተው በአጎራባች የኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኝ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ላይ " በታጣቂዎች " በደረሰ ጉዳት እንደሆነ አሳውቋል።

#BBCAMHARIC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amhara

በነገው ዕለት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ይጀመራል።

በአማራ ክልል ውስጥ የተፈታኞች ቁጥር ከታቀደው በግማሽ እንደሚያንስ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።

ቢሮው በዚህ ዓመት ከ200 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀመጡ አቅዶ ነበር።

ነገር ግን አሁን ፈተና ላይ ይቀመጣሉ የተባሉት  96 ሺህ 408 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ቀሪ 106 ሺህ ያክል ተማሪዎች ፈተና አይወስዱም።

አሁን ላይ ፈተናውን የማይወስዱ ተማሪዎች  ተምረው በመስከረም 2017 ዓ/ም በሁለተኛ ዙር ለመፈተን እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።

በነገ ዕለት ፈተና የሚጀምሩት ተማሪዎች ለፈተናው መቀመጥ የሚያስችላቸውን ትምህርት የተከታተሉ እንደሆኑ ቢሮው አሳውቋል።

ባለፉት በርካታ ዓመታት የሀገሪቱ ከፍተኛው ውጤት የሚመዘገብበት እና እጅግ በጣም ጎበዝ ተማሪዎች የሚገኙበት አማራ ክልል ዘንድሮ የሚጠበቅበትን ያክል ተማሪ ባለማስተማሩ ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች በመጀመሪያ ዙር ፈተና ላይ መቀምጥ አልቻሉም።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ዘንድሮ ትምህርታቸውን መማር ከነበረባቸው 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎች መካከል መማር የቻሉት 3.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ናቸው።

ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት አልተማሩም።

ይኸው እስከ ዛሬ ትምህርት ያልጀመሩ ዞኖች እና ወረዳዎች አሉ።

በቅርቡ ቢሮው ዓመቱን ሙሉ በሙሉ ጭራሽ ምንም ያልተማሩ ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር።

ተማሪዎች ካልተማሩባቸው መካከል ሰሜን ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ዋነኞቹ ሲሆኑ ምንም አይነት ተማሪ / አንድም እንኳን ተማሪ የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና እንደማያስፈትኑ መግለጹ ይታወሳል።

#AmharaEducationBureau
#NationalExam
#DeutscheWelle

@tikvahethiopia
#Ethiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#NBE

@tikavhethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Bank_of_Abyssinia

ATM ካርድ በጠየቁበት ፍጥነት ወዲያው ማግኘት የሚችሉበት የቨርቹዋል ባንክ አገልግሎት ከአቢሲንያ ባንክ ያግኙ!

ይህንን አገልግሎት በጀሞ፣ ብሄራዊ ሙዝየም፣ ጎፋ እና መሀል ሰሚት በሚገኙት የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻንን ማግኘት እንደሚችሉ  እየገለጽን፣ አገልግሎቱ በቅርቡም ወደ ሌሎቹ የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች የሚስፋፋ ይሆናል፡፡

አጠቃቀሙን ለማየት ሊንኩን ይጫኑ:

https://www.tiktok.com/@abyssinia_bank/video/7387019078206098694

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia #Abyssiniabank
TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ዛሬ በድሬዳዋ በደረሰው ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ከንቲባ አቶ ከድር ፥ ከጥዋት 1 ሰዓት ጀምሮ በተለምዶ ' አሸዋ ' በሚባለው አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ፦ ሩዝ ተራ ማሽላ ተራ ሰልባጅ ተራ ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ አሳውቀዋል። ሌሎች በከፊል የተረፉ እንዳሉ ጠቁመዋል።…
#ድሬ

ከቀናት በፊት ድሬዳዋ ' አሸዋ ገበያ ' ስፍራ እጅግ በጣም የከፋ የእሳት አደጋ ደርሶ እንደነበር ይታወቃል።

በአደጋው በርካታ ነጋዴዎች አንድም ሳይቀር ነገር ሳይቀር ንብረታቸው ወድሟል።

አሁን ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጎጂዎች እንዲረዱ ለማድረግ " ድሬዳዋ ትጣራለች !! " በሚል ዘመቻ ጀምሯል።

ለተጎጂዎች ድጋፍ ማድረጊያ የሒሳብ ቁጥርም ይፋ ተደርጎ ድጋፍ እየተሰባደበ ነው። የሒሳብ ቁጥሮቹ  ፦
• ንግድ ባንክ ፦ 1000637750201
• ዳሽን ባንክ ፦ 5009786342011
• አዋሽ ባንክ ፦ 013211367855100
• የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፦ 1001300318808 ሲሆኑ ' BESAT ADEGA LETEGODU WOG DIGAF MAS ' ይላል።

በሌላ በኩል ፤ የስልጤ ልማት ማኅበር እና የስልጤ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት ለተጎጂዎች እያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር (በድምሩ 2 ሚሊዮን ብር) ድጋፍ ማድረጋቸው ተነግሯል።

#DireDawa

@tikvahethiopia
ጊምቦ ላይ ምን ሆነ ?

" በአካባቢው የሚታየው እንቅስቃሴ አሳሳቢ ነው " - እናት ፓርቲ

ከሰሞኑን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ፣ ሾምባ ቲጭብ ቀበሌ አለመረጋጋት ተቀስቅሶ ነበር።

ይህንን ሁኔታ በተመለከተ እናት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫ ልኳል።

እናት ፓርቲ ምን አለ ?

- በጊምቦ ወረዳ የተፈጸመ የግድያ ወንጀልን ተከትሎ በአማራ ማህበረሰብ እና በካፋ ማህበረሰብ መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚሰሩ ኃይሎች አሉ። እጃቸውን ሊሰበስቡ ይገባል።

- የአማራ እና ካፋ ማህበረሰብ ለዘመናት ተዋልዶና ተፋቅሮ የኖረ ማህበረሰብ ነው። " ከእስር ቤት አምልጦ ወጣ የተባለ ግለሰብ " ፈጸመው የተባለውን ግድያ ተከትሎ ድርጊቱን የብሔር ቅርጽ ለማስያዝ እየሰሩ የሚገኙ በዞንና ወረዳ ደረጃ የሚገኙ አንዳንድ አመራሮች እጃቸውን ሊሰበስቡ ይገባል።

- ከሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በአካባቢው የሚታየው እንቅስቃሴ አሳሳቢ ነው።

- ሾምባ ቲጭብ ቀበሌ ሁለት ቤቶች እንዲሁም ቢሪ አርሴማ በተባለ አካባቢ አምስት ቤቶች በጥቅሉ ሰባት የአማራ ማኅበረሰብ መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ሶስት ባጃጆች ተቃጥለዋል። ድርጊቱን የፈጸሙት የተደራጁ ወጣቶች ናቸው።

- በተለያዩ ቀበሌዎች የጸጥታ አካላት የአማራውን ማኅበረሰብ ነጥለው እያሰሩ ነው።

- የአማራና ከፋ ማህበረሰብ ለዘመናት ተዋልዶ፣ ተፋቅሮና ተጋምዶ የኖረ ማህበረሰብ ነው ፤ በማህበረሰቡ መካከል ምንም ችግር እንደሌለ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

- " አንዳንድ የማህበረሰብ አንቂ ነን" የሚሉ ግለሰቦች ብልሹ ሥነ ምግባር ካላቸው የዞንና ወረዳ አመራሮች ጋር በመቀናጀት ' አማራ መሬታችንን ለቆ ይውጣ ' የሚል ዘመቻ ጀምረዋል።

- የክልሉ መንግሥት፣ የዞንና ወረዳ አመራሮች ተናበው ለተፈጠረው ችግር አስቸኳይ እልባት እንዲሰጡ ተጠይቋል።

- ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ስለሚገኙ እየተፈጸመ የሚገኘው የጅምላ እስር፣ የቤት ቃጠሎና የንብረት ውድመት በአስቸኳይ እንዲቆም ተጠይቋል።

- አርሶ አደሩ እርሻ ላይ ተጠምዶ በሚገኝበት በዚህ ሰአት በፍቅር አብሮ እየኖረ በሚገኘው የአማራና ካፋ ማህበረሰብ መካከል ግጭት እንዲፈጠር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ  እንዲሁም በማህበራዊ ድረ ገጽ የጥላቻ ጽሑፍ በማሰራጨት የተጠመዱ አካላት እጃቸውን ሊሰበስቡ ይገባል።

" በርካታ ወጣቶች ታስረዋል ፤ የእርሻ ስራ ለመስራትም ፍርሀት ውስጥ ነን " - የአካባቢው ወጣቶች

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የእናት ፓርቲ መግለጫ ተንተርሶ የጊምቦ ወረዳ ወጣቶችን አነጋግሯል።

ወጣቶቹ አለመረጋጋት የተፈጠረው ከእስር ቤት ያመለጠ አንድ ግለሰብ በጊምቦ ወረዳ ውስጥ የአንድ ሰው ነብስ አጥፍቶ በመደበቁ እንደሆነ አመልክተዋል።

አሁን ላይ ምንም እንኳን አካባቢው በአንጻራዊነት ሰላም ቢሆንም ፖሊስ ወጣቶችን እያሰረ መሆኑን ተከትሎ በፍርሀት ውስጥ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በተለይ አለመረጋጋት በነበረባቸው ቀበሌያት ያሉ ወጣቶች ፖሊስ አሰሳ እያደረገ እና በርካታ ወጣቶችን ሲያስር በመመልከታቸው ምክንያት ወቅታዊውን የእርሻ ስራ ለመስራት ፍርሀት ውስጥ እንዳስገባቸው ገልጸዋል።

" አካባቢው ወደቀደመ ሰላሙ ተመልሷል " - የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወጣቶችን ፍርሀት እንዲሁም የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ የሽዋስ አለሙን አነጋግሯል።

እሳቸውም " አሁን ላይ የጸጥታ ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ  አካባቢዉ ወደቀደመ ሰላሙ ተመልሷል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም " ከእስር አምልጦ ሰው በመግደል አካባቢውን ሲበጠብጥ ነበር " ያሉት ግለሰብ ከአድማ ብተና እና ከክልሉ ፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደሉን ገልጸዋል።

የወጣቱን ፍርሀት በተመለከተ በወቅቱ ችግር ለመፍጠር የሞከሩትን ሰዎች ለመያዝ አንዳንድ እንቅስቃሴ መኖሩን ገልጸው ከዛ ውጭ ግን በጥርጣሬ የተያዙ ካሉ ተጣርተው እንደሚለቀቁና ፍርሀት ውስጥ መግባት እንደማይጠበቅባቸዉ አሳውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል) #NBE @tikavhethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ፦

" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የአንድ ቀን የብድር አገልግሎት (overnight lending facility) እና የአንድ ቀን የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት (overnight deposit facility) ይስጣል፡፡

እነዚህ የአንድ ቀን የብድር ወይም የተቀማጭ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ምክንያት ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ፍሰት አቋማቸውን ለማስተካከል እንዲረዳቸው ነው፡፡

እነዚህ ቋሚ አገልግሎቶች የሚሰጡት ከብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን 3 በመቶ በማስበለጥ ወይም በማሳነስ ይሆናል፡፡ "

#NBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
#Africa

የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ " ደመወዘኔን 40 በመቶ እቀንሳለሁ " ሲሉ አስታወቁ።

ጽ/ቤታቸው፤ " ፕሬዜዳንቱ ይህ እርምጃ የሚወስዱት ተጠያቂ አስተዳደር በመፍጠር አርዓያ ለመሆን እና ከዜጎች ጋር ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ነው " ብሏል።

ፕሬዚዳንት ቦአካይ ፥ ከጥቂት ወራት በፊት ዓመታዊ ደመወዛቸው 13 ሺህ 400 ዶላር (769 ሺህ ብር በላይ) እንደሆነ ገልጸው አሁን ባቀረቡት 40 በመቶ ቅነሳ ወደ 8 ሺህ ዶላር (459 ሺህ ብር በላይ) ያደርሰዋል።

የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የዚህ ዓመት በጀት ወደ 3 ሚሊዮን ዶላር ይጠጋል።

አንዳንዶች የፕሬዚዳንቱን የደመወዝ ቅነሳ እርምጃ ቢያደንቁም ሌሎች ግን እንደ ዕለታዊ አበል እና የህክምና ሽፋን ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያገኙ ጠቅሰው " ይህ በእውነት መስዋዕትነት ነው ወይ ?  ሲሉ ጠይቀዋል።

ከሳቸው በፊት የነበሩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ደመወዛቸውን 25 በመቶ ቀንሰው ነበር።

በሀገሪቱ ባለው ከፍተኛ ኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ ያሉት ላይቤሪያውያን አንደኛው ቅሬታ የሚያነሱት ጉዳይ የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ነው።

በላይቤሪያ ውስጥ በአማካኝ ከአምስቱ አንዱ ሰው ከ2 ዶላር (114 ብር) ባነሰ ዕለታዊ ገቢ ኑሯቸውን ለመግፋት ተገደዋል። #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ፦ " የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የአንድ ቀን የብድር አገልግሎት (overnight lending facility) እና የአንድ ቀን የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት (overnight deposit facility) ይስጣል፡፡ እነዚህ የአንድ ቀን የብድር ወይም የተቀማጭ አገልግሎቶች የሚሰጡበት…
#Ethiopia

" ባንኮች የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ባንኮች ማበደር ይችላሉ " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ፦

" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በርስ የሚበዳደሩበትን የተነቃቃ የገንዘብ ገበያ ለመመሥረት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት በቅርቡ ለመዘርጋት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

የገንዘብ ገበያው በኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ላይ ተመሥርቶ በሚገባ ሥራ ላይ ሲውል ትርፍ ገንዘብ ያላቸው ባንኮች የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ባንኮች ማበደር ይችላሉ፡፡

በመሆኑም፣ ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ወይም ትርፍ ገንዘብ ሲኖራቸው እርስ በርስ የመገበያየት ዕድል ይኖራቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ይህ አሠራር ሥራ ላይ ሲውል የባንክ ለባንክ የወለድ ተመን ከማዕከላዊ ባንኩ የፖሊሲ-ነከ የወለድ መጣኔ ጋር የሚጣጣም ሲሆን፣ ይህ ካልሆነ ግን ብሔራዊ ባንኩ ሁኔታውን ለማስተካከል ከባንኮች ጋር የግብይት ጨረታን ይጠቀማል፡፡ "


@tikvahethiopia
#NationalExam

አገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡

ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት ነው እየተሰጠ ያለው።

የመጀመሪያ ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ትላንት ሐምሌ 2 በቀድሞ ትምህርት ካሪኩሉም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የትግራይ ክልል ተማሪዎች አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጀመራቸው ይታወሳል።

Via @tikvahuniversity
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተገነቡት መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የጣሉ ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሄዱ እንዲሁም በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን ' በግዴለሽነት ' በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት መቀጣታቸውን አሳውቋል።

3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር ተቀጥተዋል።

5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ የተተከሉ ዘንባባ ዛፎችን ገጭተው በመጣላቸው እንደየጥፋት ደረጃቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር መቀጣታቸውን አሳውቋል።

11 ሰዎች ደግሞ ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር እንደተቀጡ ገልጿል።

ነዋሪዎች የተገነቡትን መሰረተ ልማቶች እንዲጠብቁ እና እንዲንከባከቡ ራሳቸውንም ከቅጣት እና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርቧል።

(የቅጣት ደረሰኞቹ ከላይ ተያይዘዋል)

#AddisAbaba #MayorOffice

@tikvahethiopia