TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

" ከዚህ (ከሰላማዊ) ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

36ኛው ዓመት " የትግራይ የሰማእታት ቀን " ዛሬ ሰነ 15 ቀን 2016 ዓ/ም በመቐለ የሰማእታት ሀውልት ተከብሯል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " ልጆቻችን በአጋቾች ለሞት እየተጋለጡ ፣ ተፈናቃዮች በመቆያ መጠለያዎች በፀሀይና በብርድ እየተሰቃዩ ባሉበት ወቅት የሰማእታት ቃልና አደራ በተሟላ መልኩ እያከበርን ነው በማለት ማምለጥ አይቻለንም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የሰማእታት ቃል አክበረናል የምንለው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆን ይገባዋል " ብለዋል።

" የሰማእታት ቃል ማክበር ማለት በትግራይ የሃሳብ ብዙህነት እንዲከበር መስራት ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ጥቅም መዋደቅ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " አንዳንዶቻችን ይህንን በመዘንጋት ለስልጣንና ለሃብት ስንባላ መታየት አሳፋሪ ነውና ከዚሁ መውጣት ይህንን መቀየር አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው " ተፈናቃዮችን በጀመርነው ሰላማዊ መንገድ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በአንድነት መንፈስ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን መስራት አለብን " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ... የቤት አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ ነው " - ቤቶች ልማትና አስተዳደር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። ቢሮው ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ120 ወረዳዎች ምዝገባ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጿል። በቀሪ የ15 ቀናት ጊዜ ዜጎች…
" ' የቤት ኪራይ ጨምሩ ' ወይም ' ቤቱን ልቀቁ ' የሚል ግፊት ከደረሰባችሁ ደውላችሁ ጠቁሙኝ " - የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

በአዲስ አበባ ፤  ' ከአከራይ ተከራይ  የውል ስምምነት ' ጋር በተያያዘ ተከራዮች የሚገጥማቸውን ማንኛውም ችግር ጥቆማ ሊሰጡ እንደሚችሉ የከተማው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው ማንኛውም አከራይ ከመጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን አስገንዝቧል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ ተከራዮች የቤት ኪራይ ጭማሪ አልያም ' ቤቱን ይልቀቁልኝ ' የሚል ግፊት ከአከራዮች ከደረሰባቸው በስልክ ቁጥር +251118722917 / +251118553820 ላይ በመደወልና ጥቆማቸውን በመስጠት መብታቸውን ማስከበር እንደሚችሉ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ሰኔ 1 ላይ የጀመረው የአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ሊጠናቀቅ  14 ቀናት የቀሩት ሲሆን ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙት ወረዳዎች በማቅናት ምዝገባ እንዲያካሂዱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

አከራዮች የውል ስምምነቱን ሳይፈጽሙ እስከ ሶስት ወር ድረስ ከቆዩ የሁለት ወር የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ ተገልጿል።

መንግስት ጥናት በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ እንደሚሆን ተነግሯል።

#TikvahEthiopia
#HousingDevelopmentandAdministration

@tikvahethiopia
#አፖሎ_ሆስፒታል #ላንድማርክ_አጠቃላይ_ሆስፒታል

አፖሎ ሆስፒታል ከላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ልዩ የህክምና አገልግሎት ይዞላችሁ መጥቷል ።

የጉበት የጣፊያ ከአልኮል መጠጦች ጋር ተያይዞ የጉበት ህመሞች ፣ የጭንቅላት እጢ የነርቭ ችግር የአንገት የጀርባ አጥንት ህመም እና ሌሎች ተያያዥ ህክምናዎች ይሰጣል ።

ህክምናው የሚሰጠው ሰኞ እና ማክሰኞ ሰኔ 17 እና 18 2016 አስቀድሞ ቀጠሮ ለማስያዝ 0944038928 & 0947327953 ይደውሉ ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።

ቦርዱ ከዚህ ቀደም ምርጫ ባልተደረገባቸው ፦
- በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣
- በአፋር፣
- በሶማሌ
- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ነው ምርጫ እየተደረገ እንደሚገኝ ያመለከተው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

 በየዓመቱ ከ8 ቢሊዮን እስከ 5.6 ቢሊዮን ብር በጀት ሊመደብለት ይችላል።

የፌዴራል መንግሥት ፤ በየዓመቱ ከአገር ውስጥ ገቢ ምንጭ ከሚመድበው ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከ0.5 በመቶ እስከ አንድ በመቶ ያህል ለአረንጓዴ አሻራ እና ለተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ እንዲሰጥ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ረቂቅ አዋጁ ፤ " የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ለማቋቋም እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ " የሚል ስያሜ አለው።

ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ?

ለም/ ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ባለበት ሁኔታ ከፀደቀ በልዩ ፈንድ ከ2.8 ቢሊዮን ብር እስከ 5.6 ቢሊዮን ብር የሚደርስ በጀት ከመንግሥት ብቻ ሊቀርብለት ይችላል።

ልዩ ፈንዱ ዘጠኝ ዓላማዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል ፦
- የተጎሳቆለ መሬት በተፈጥሮና በመልሶ ማልማት መርህ በመታገዝ እንዲያገግም ማድረግ፣
- የደን ልማትና የደን መልሶ ማልማትን መደገፍ፣
- የአገሪቱን የካርቦን ልቀት ቅነሳ ግብ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ማድረግ፣
- የከተማ ማስዋብ እና አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን መደገፍ የሚሉ ይገኙበታል።

የልዩ ፈንዱ የፋይናንስ ምንጮች ፦
1ኛ. የፌዴራል መንግሥት የሚመድበው በጀት፣
2ኛ. የልማት አጋሮች፣
3ኛ. የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣
4ኛ. የግል ዘርፍ የሚሰጡት ድጋፍ ነው።

የፌዴራል መንግሥት ለፈንዱ ከሚመድበው በጀት የሚሰበሰበው ገንዘብ ለልዩ ፈንዱ በተከፈተው የባንክ ሒሳብ በየ3 ወራቱ በገንዘብ ሚኒስቴር ተቀማጭ ይሆናል። የሌሎች ምንጮች ድጋፍ የሚተዳደርበት አኳኋን የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያና የአሠራር ሥርዓት ይወሰናል።

መንግሥት የሚመድበው ዓመታዊ በጀት የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መሥፈርት መሠረት ለፌዴራል መንግሥትና ለክልሎች ይደለደላል።

ለክልሎች ከሚደለደለው በጀት ላይ የእያንዳንዱን ክልል ድርሻ ለመወሰን የሚያገለግለውን የገንዘብ ሚኒስቴር አዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይቀርባል። ሆኖም ለመሸጋገሪያነት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያፀደቀው ጠቅላላ የበጀት ድጋፍ ቀመር በጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

ከተደለደለው ዓመታዊ የሀብት ድርሻ ላይ በየ3 ወሩ ወደ ተጠቃሚ አካላት ገንዘብ ሊተላለፍ የሚችለው የሥራ አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ፣ ክልሎች ተጓዳኝ በጀት ሲመድቡና በክልሉ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ፈሰስ ሲያደርጉ ይሆናል።

ክልሎች የሚመድቡት ዝቅተኛ ተጓዳኝ በጀት ተፈጻሚ የሚሆነው በተጓዳኝ በጀቱ መጠን ላይ በረቂቅ አዋጁ የልዩ ፈንዱ አስፈጻሚ አካላት በሚል የተዘረዘሩት ፦
° የገንዘብ ሚኒስቴር፣
° የግብርና ሚኒስቴር፣
° የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣
° የኢትዮጵያ ደን ልማት በክልሎች የገንዘብ ቢሮዎች መካከል በሚደረግ ምክክር የጋራ ስምምነት ላይ ሲደረስና በየክልሉና በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤቶች ሲፀድቅ ነው።

እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ሳይተላለፍ የቀረ ገንዘብ በቀጣዩ ዓመት ለልዩ ፈንዱ ከሚመደበው በጀት ጋር ተደምሮ ይደለደላል።

የልዩ ፈንዱ ዓብይ ኮሚቴ አስፈጻሚ አካላት፦
° ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣
° ከኢትዮጵያ ደን ልማት
° ከክልሎች የገንዘብ ቢሮዎች የበላይ ኃላፊዎች ይዋቀራል። የገንዘብ ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ይሆናሉ።

ገንዘብ ሚኒስቴር ከተጠቃሚ አካላት ሚቀበለውን የሒሳብ ሪፖርት በማጠቃለል የልዩ ፈንዱን ሒሳብ ዘግቶ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ3 ወራት ውስጥ በፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይም የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሚወክለው ኦዲተር እንዲመረመር የማድረግ ኃላፊነት አለበት።

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በዚህም በ2017 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1332 የማስተማር ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል። 43 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው መሰረዙን አመልክቷል። 150 ትምህርት ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ወደፊት…
#AddisAbaba

" በ2017 ዓ/ም መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን መቀጠል ይችላል " - ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ

ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን  በ2017  የትምህርት ዘመን 41 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና ስታንዳርዱን ባለማሟላታቸው ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

ከነዚህ ትምህርት ቤቶች አንዱ ፍኖተ ሎዛ ቅድመ አንደኛ፤ የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ነው።

ይህ ትምህርት ቤትን በተመለከተ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባስስልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አንድ ደብዳቤ ጽፏል።

ጽ/ቤቱ በዚህ ደብዳቤው ት/ቤቱ ፦

" በማዕከል ደረጃ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ቅርንጫፍ እና እርክን ሳይጠቀስ በጅምላ የት/ቤቱ ስም ተጠቅሶ ' ከስታንዳርድ በታች በመሆኑ የተዘጋ ' በሚል የተቋሙን ስምና ዝና በማይመጥን መልኩ ተዘግቧል።

በዚህ ደረጃ የተዘጋ ተቋም ሳይኖር በትምህርት ቤቱ ባለቤቶች እና ማሕበረሰቡ ላይ ውዥንብር ተፈጥሮብኛል " በሚል እንዳመለከተ ገልጿል።

በዚህም ፍኖተ ሎዛ ሃና ማርያም ቅርንጫፍ ከቅደመ ስንደኛ እስከ ሁስተኛ ደረጃ ያለው ምንም ዓይነት የስታንዳርድ ችግርም ሆነ የስርዓተ ትምህርት ጥሰት የሌለበት መሆኑን አመልክቷል።

ፍኖተ ሎዛ ተብሎ የተጠቀሰው ትምህርት ቤት በቅርንጫፉ ወረዳ 15 የሚገኝ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤትም ውል ባለማቅረቡ ምክንያት ስሳልተገመገመ ስታንዳርድ ማሟላት አለሟሟላቱ አሁን መግለጽ እንደማይቻል አስረድቷል።

በሀና ማርያም የሚገኘው ተቋም ግን በ2017 ዓ/ም መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን መቀጠል እንደሚችል የን/ስ/ላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
በስርአተ_ትምህርት_ጥሰትና_ስታንዳርድ_ባለማሟላት_የተዘጉ_ተቋማት_ዝርዝር.pdf
901.1 KB
#AddisAbaba : በስርዓተ ትምህርት ጥሰት እና ስታንዳርድ ባለለመሟላት የተዘጉ ትምህርት ቤቶች ዝርዝር።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን አይቀጥሉም የተባሉ ናቸው።

ፍኖተ ሎዛን በተመለከተ ግን ይህን ያንብቡ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/88408?single

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
በራሳቸው የዘጉ ተቋማት ዝርዝር.pdf
1015.4 KB
#AddisAbaba

በራሳቸው የዘጉ ትምህርት ቤቶች ዝርዝርን ይመለከቱ።

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የቅድመ_አንደኛ_ተቋማት.pdf
10.8 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የአንደኛና_መካከለኛ_ደረጃ.pdf
6.1 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የአንደኛ እና መካከለኛ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የአጠቃላይ_2ኛ_ደረጃ.pdf
1.8 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#DStv

🔥 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች በድምቀት ቀጥለዋል!

ዛሬ ምሽት፡ ⚽️ Netherlands vs France ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM በSS Football 225 ጎጆ ፓኬጅ በSS Euro2024 222 በሜዳ ፓኬጅ

🤔 ዋንጫው የማን ነው? የእርሶን አስተያየት ያጋሩን

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር ከ350 ብር ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#Tigray

➡️ " እስከ ሰኔ 30 ወደ ቄያችን መልሱን !! - ተፈናቃዮች

➡️ " ከክረምት በፊት ወደ ቄያችሁ እንድትመለሱ ከፌደራልና ከአማራ ክልል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ 

በእንዳስላሰ ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ዓዲግራት ፣ ዓብዪ ዓድዋና መቐለ የሚገኙ ከምዕራብ ፣ ከሰሜናዊ ምዕራብና ምስራቅ የትግራይ ዞኖች የተፈናቀሉ ወገኖች ዛሬ እሁድ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም ወደ ቁያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተነግሯል።

ከምዕራባዊ ዞን ወረዳዎች ፣ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ባድመ ፣ ፀለምቲና አከባቢው  እንዲሁም ከምስራቃዊ ዞን ዛላንበሳና የኢሮብ ወረዳዎች ከቄያቸው መፈናቀላቸውን የገለጹት ተፈናቃዮቹ ፦
- እስከ ሰኔ 30 ወደ ቄያችን መልሱን !
- አርሰን እንድንበላ ወደ ቄያችን መልሱን !!
- የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ ይተግበር !
- የፌደራልና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃላፊነታቸው ይወጡ !
- የትግራይ ግዝታዊ አድነት ይከበር !
- የተፈናቃዮች ድምፅ ይሰማ ! የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን አሰምተዋል።

በተለይ በመቐለ ከተማ የሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች በሰልፋቸው ማጠቃለያ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት በመሄድ ድምፃቸው ያሰሙ ሲሆን ክረምት ከመግባቱ በአስቸኳይ ወደ ቄያችን መልሱን ብለዋል።

ሴቶችና ህፃናት የሚበዙባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቃይ ሰልፈኞቹ ምሬት የተሞላበት ድምፅና ሃሳብ ያደመጡትና ምላሽ የሰጡት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ " የዛሬው ሰልፍ የመጨረሻው እንዲሆንና ከክረምት በፊት እንድትመለሱ ከሚመለከተው አካል በቅንጅት እንሰራለን " ብለዋል።

" ወደ ቄያችሁ መመለስ በማስመልከት ከአማራ ክልል መንግስት እየተነጋገርን ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ህዝቡ ወደ ቄየው ሲመለስ ከቂምና በቀል በፀዳ መልኩ በቦታው ከቆዩ ወንድም እህቶቻቹ  የመተማመንና የመቻቻል መንፈስ በማጎልበት በአብሮነት መኖር ይገባዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
#ኢትዮጵያ

ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው በዚህ መመሪያ ዉስጥ የእህልና ጥሬጥሬ ፣ የግብርና ምርቶች እና የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች ይገኙበታል ።

በዚህ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ  እቃዎችን ለመወሰን በወጣው  መመሪያ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ማድረግ የወጪ ጫናውን በማርገብ ረገድ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ከተደረጉት መካከል ፦
➡️ ጤፍ፣
➡️ ስንዴ፣
➡️ ገብስ ፣
➡️ ማዳበሪያ ፣
➡️ የእንስሳት መድሃኒት እንዲሁም በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርብ የካፒታል ዕቃዎች ይገኙበታል።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
#EthiopianOrthodoxTewahedo

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመቱ ውስጥ ከሚጾሙ አጽዋማት መካከል  ' ጾመ ሐዋርያት ' (በተለምዶ የሰኔ ጾም) በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

ይህ ጾም የሚፈሰከው ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ነው።

ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነው ጾመ ሐዋርያት በየትኛውም አመት ላይ ቢውል ሰኞ ቀን ከሚጀምሩት አፅዋማት አንዱ ነው፡፡

ይህ ጾም የሚፈሰክበት ከሐምሌ 5 አይበልጥም ፤ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ነው።

እንደ ቤተክርስቲያኗ አስተምሮ ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሰማያዊ ተልእኮ ስለተሰማቸው ከ5ዐ ቀን በኋላ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማግስት የጀመሩት ጾም ነው።

ጾሙ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ነው።

ቤተክርስቲያኗም ትንሳኤ ከዋለ ከበዓለ 50 በኃላ የፆሙን አዋጅ ለልጆቿ አውጃለች።

ይህ ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ እንደሆነ ቤተክርስቲያን ታዛለች።

ከዚህ ጾም በኃላ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል የሆነው ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና ዓርብ) የሚጀምር ይሆናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia