TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የዓድዋ በዓል በአዲስ አበባ ? ዛሬ የዓድዋ ድል በዓል በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ነው። በመዲናዋ በሚገኘው የአፄ ሚኒሊክ ሀውልት ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ እንዳልነበር ወደ ስፍራው የሄዱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የቤተሰባችን አባል እንዲህ ሲል ዛሬ ጥዋት የተመለከተው አስረድቷል፦ " በመጀመሪያ ከጥቁር አንበሳ ጀምሮ ቀይ ለባሾች፣ አድማ በታኞች እና የፌዴራል…
#ዓድዋ

ዛሬ በምኒሊክ አደባባይ አካባቢ ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያያዘ ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ሰሜን ሆቴል አካባቢ ወደ ምኒሊክ አደባባይ እና ወደ ቅዱስጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ማለፍ ተከልክሎ እንደነበር ገልጿል።

" አስለቃሽ ጭስ እና ድንጋይ ውርወራ ነበር " ያለው ይኸው ቤተሰባችን አባል አንዳንድ ወጣቶች ላይም ድብደባ ተፈፅሟል " ሲል አስረድቷል።

በተመሳሳይ ፤ ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ዛሬ የፌደራል ፖሊሶችና አድማ በታኞች ወደ ጊዮርጊስ መስመር የሚሄደውን ሰዉ ከሰሜን ሆቴል እና ከዮሀንስ ቤ/ክ አካባቢ ማለፍ አይቻልም በሚል እየመለሱ እንደነበር ገልጿል።

እስካሁን #በመንግስት_አካላት በኩል በምኒልክ አደባባይ ስለነበረው እና ስለተፈፀመው ሁኔታ ማብራሪያ አልተሰጠም።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የድል በዓሉ በአደባባዩ መከበሩን በስፋት ዘግበዋል።

#ዓድዋ127

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መንግስት ምን አለ ? የኢፌዴሪ መንግስት በኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ 127ኛው የዓድዋ በዓል በብሔራዊ ደረጃ በአዲስ አበባ ፣ በመላው ሀገሪቱ እንደአመቺነቱና እንደ ሁኔታው #በድምቀት ፣በታቀደለት ልክ ተከብሯል ብሏል። አገልግሎቱ ዛሬ በምንሊክ አደባባይ ስለነበረው ሁኔታም በመግለጫው አብራርቷል። በምኒልክ አደባባይ የሚደረገውን በዓል ለመረበሽ የፈለጉ አካላት ሁከት ለመቀስቀስ…
#ዓድዋ127

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፦

" በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ዓመታዊውን የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 127ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል ለማክበር በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን ከየአቅጣጫው ተሰብስቦ ነበር።

ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው  ወጥተው የዑደት ሥነ ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ክብረ በዓሉ እየተከናወነ ባለበት ወቅት ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ የበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ሳይጠነቀቅ ታቦታተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።

ወደቅጽረ ቤተክርስቲያኑ በሚያስገቡ ሁለቱም መግቢያ በሮች በተወረወረው አስለቃሽ ጭስ በርካታ ምዕመናን በመጎዳታቸው ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። "

ከኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ ፦

" ... በምኒልክ አደባባይ የሚደረገውን በዓል ለመረበሽ የፈለጉ አካላት ሁከት ለመቀስቀስ ሞክረው ነበር።

እነዚህ አካላት የአደባባዩን በዓል መረበሽ ሲያቅታቸው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚደረገውን ሃይማኖታዊ በዓል ለመረበሽ ሞክረዋል፡፡

የጸጥታ አካላት ሑከት ፈጣሪዎችን ለማስታገሥ በሚያደርጉት ጥረት በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የነበረው ሃይማኖታዊ በዓል እንዲስተጓጉልና ለሃይማኖታዊ በዓል የመጡ ምእመናን ለጉዳት እንዲዳረጉ ጥረት አደርጓል።

በዚህም ጥቂት ምዕመናን ላይ ጉዳት ደርሷል።

ሆኖም የፀጥታ አካላት ባደረጉት ጥረት የከፋ ጉዳት ሳይደርስ የተሸረበዉ ሴራ ሊከሽፍ ችሏል።

መንግሥት ይሄንን መሰል ተግባር መፈጸም እንደሌለበት ያምናል። ሁኔታውን አጣርቶ በችግር ፈጣሪዎች ላይ ተገቢውን ርምጃ ይወስዳል። "

ቪድዮ ፦ Addis

@tikvahethiopia