TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Debark_university

የሰሜን ጎንደር ዞን ፣ የደባርቅ ወረዳ እና የደባርቅ ከተማ የአስተዳደርና የጸጥታ አካላት ከአካባቢው ማህበረሰብ ፣ የሃገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጋር በመሆን ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ወጥተው ደባርቅ ከተማ ላይ ካሉ ተማሪዎች ጋር የምክክር መድረክ ተፈጥሮ ውይይት ሲካሄድ ውሏል። በተጨማሪም ትናንት በነበረው አለመረጋጋት ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ተማሪ #ሞቷል እየተባለ የሚወራው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ALERT🚨 " ሰባ ሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም " ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከባድ ድርቅ መመታቱ ተገልጿል። በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉት። ወረዳው የ2015/2016 የምርት ዘመን #ድርቅ ክፉኛ መትቶታል። ወረዳው በከፊል አርብቶ አድር የሚታወቅ ሲሆን ከማሳው በሚያገኛት ጥቂት ኩንታል እህል በይበልጥ ለገለባው ዋጋ ሰጥቶ በእንሰሳቱ ኑሮውን…
#ALERT🚨

አንድ አንጀራ ለ10 ተሻምተው የሚበሉ ወገኖቻችን እንዳሉ እናውቅ ይሆን ?

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከፍተኛ ድርቅ ተመቷል።

ነዋሪው ችግር ላይ ወድቋል።

ሰው በረሃብ #ሞቷል ፣ እንስሳት ሞተዋል ፣ ተሰደዋል።

ወገኖቻችን በቂ ምግብ አጥተው 1 እንጀራ ለአስር እየተሻሙ እየበሉ ነው። ካዛ ውጭ ጨው በውሃ በጥብጠው ነው የሚጠጡት።

" በዚህ ሳምንት የሚበላ ካልቀረበ ልጆቻችንን አናገኛቸውም " ብለዋል።

የግብረሰናይ ድርጅቶች ቃል መግባት እንጂ ጠብ የሚል ነገር አላደረጉም። መንግሥትም ለገዛ ዜጎቹ እየደረሰ አይደለም።

ከፈጣሪ በታች ለህዝቡ ዋስትና ነው የሚባለው መንግሥት ፊቱን እንዳዞረባቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ሁኔታው ከሰባ ሰባቱም የከፋ ነው።

via @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

" ... የተኩስ ልውውጡ የነበረው ከሚሊኒየም አዳራች በሰንሻይን በኩል ወደ ቦሌ መድኃኒዓለም በሚያስወጣው መንገድ ነበር " - የአካባቢው ነዋሪዎች

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ቦሌ በፖሊስ እና ፋኖ አባላት መካከል የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚሊኒየም አዳራሽ ጎን በሰንሸይን ቪላ ቤቶች አድርጎ ወደ ቦሌ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ወደ ሚያስወጣው መንገድ ላይ እንደነበር በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ገልጸዋል።

በተኩስ ልውውጡ ሁለት የፋኖ አባላት እና አንድ መንገደኛ ህይወታቸው ጠፍቷል። ሁለት የፖሊስ አባላት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃል ፥ " ናሁሰናይ አንዳርጌ የሚባለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው እንቅስቃሴ ወቅት እጅ ላለመስጠት ከፍተኛ የሆነ ትግል ነው ያደረገው " ብለዋል።

" ከዚያም አልፎ በዚያ አካባቢ የሚሄድ አንድ ግለሰብ ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል። ሁለት የፖሊስ አባላት ላይ ተኩስ ከፍቶ ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል " ሲሉ ተናግረዋል።

ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃላቸው ፥ ቦሌ በነበረው የፋኖ አባላቱና እና የፖሊስ ተኩስ ልውውጥ ፦
- ናሁሰናይ አንዳርጌ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ #ሞቷል
- አቤኔዘር ጋሻው በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል፤
- ሀብታሙ አንዳርጌ የተባለ የፋኖ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከዚህ ባለፈ ፦
° አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ባለመኪና ‘#አልተባበርም’ ስላሉ መኪና ውስጥ በጥይት መትተውት ገድለውታል።
° የአንድ ግለሰብ ተሽከርካሪ መስታወት በጥይት መተውታል " ሲሉ ተናግረዋል።

በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከፖሊስ በኩል ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ቆስለው ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@tikvahethiopia