TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ፥ ስዊድንን እና ፊንላንድን አስጠነቀቀች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አስጠንቅቋል። አሁን በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ሩስያ ፊንላንድ እና ስዊድንን ማስፈራራቷ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል። የኃያላን ሀገራቱ ግብግብ በተለይ…
#Russia #Finland #Sewden

ሩስያ NATOን ለመቀላቀል ከሞከራችሁ እጅግ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ] ይኖራል ስትል ካስጠነቀቀቻቸው ስውዲን እና ፊንላንድ መካከል ስውዲን NATOን ለመቀላቀል ለማመልከት መወሰኗ ተሰምቷል።

የስዊዲን ጠ/ሚ ማግዳሌና አንደርሰን ሀገራቸው በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ለNATO ጥምረት አባልነት ለማመልከት መወሰኗን ገልፀዋል።

ፊንላንድ በበኩሏ ፤ አሁን ይኽ ነው የሚባል ውሳኔ ላይ ባትደርስም በሚቀጠሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ NATOን ለመቀላቀል የማመልከት ውሳኔ ላይ እደርሳለሁ ብላለች።

የፊንላንድ ጠ/ሚ ሳንና ማሪን እና የስዊድን ጠ/ሚ ማግዳሌና አንደርሰን በአካባቢው የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በስቶክሆልም ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በሩስያ እና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት አሁንም መፍትሄ የላገኘ ሲሆን ሩስያ ዩክሬን ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረችባቸው ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ NATOን ለመቀላቀል ሙከራ ማድረጓና ለደህንነቷ ስጋትን በመደቀኗ መሆኑ ይታወቃል።

የዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኃላ ሩስያ ፤ ስውዲን እና ፊንላድ እንዲህ ያለውን ነገር እንዳይሞክሩት ፤ የሚያደርጉት ከሆነ ግን ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጎጂ ውጤቶች እንደሚኖሩ አስጠንቅቃቸው ነበር።

አሁን ላይ ስውዲን NATOን ለመቀላቀል ጥያቄ እንደምታቀርብ መወሰኗ ፤ ፊንላንድም በቀጣይ ሳምንታት ውሳኔ ላይ ደርሳለሁ ማለቷ ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል።

@tikvahethiopia