TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.6K photos
1.6K videos
216 files
4.35K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CHINA

ቻይና በኢትዮጵያ 🇪🇹 እየተሻሻለ መጥቷል ያለችውን የሀገር ውስጥ ሁኔታና መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀነ ገደብ ከመድረሱ በፊት እንዲያበቃ ያሳለፈው ውሳኔ ደስ እንዳሰኛት ገልፃለች።

የኢትዮጵያ ህዝብ የውስጥ ጉዳዩን በአግባቡ የመቆጣጠር ጥበብና ብቃት እንዳለውም አምናለሁ ስትል አስታውቃለች።

@tikvahethiopia
👍766👎6340😁37🔥8😢1
#CHINA

ሹዌ ቢንግ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ።

#ቻይና በአሁኑ ወቅት በግጭት እየታመሰ ላለው የአፍሪካ ቀንድ ሹዌ ቢንግን ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ መሾሟ ታውቋል።

ሹዌ ቢንግ ቀደም ሲል በፓፑዋ ኒው ጊኒ የቻይና አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። በአፍሪካ፣ በአሜሪካ እና በኦሺንያ የመሥራት ልምድ እንዳላቸው የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ዛሬ ማክሰኞ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
👍295👎2014🥰8😱6👏2
#US #CHINA

ቻይና በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ዜጎቿ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበች።

በአሜሪካ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በሀገሪቱ ያለው የደህንነት ሁኔታ ለቻይናውያን ዜጎች አሳሳቢ ነው ብሏል።

በመሆኑም አሜሪካ የሚገኙ ቻይናውያን ዜጎች ለግል ደህንነታቸው ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኤምባሲው አሳስቧል።

በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎች እና የእሲያ ፊት ያላቸው ሰዎች ላይ የሚንፀባረወቅ ጥላቻ እየጨመረ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።

በቻይና ዜጎች እና የእሲያ ፊት ያላቸው ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ የሚፈፀሙ " ተንኮል አዘል " ጥቃቶች የቻይና ዜጎች ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑንም ኤምባሲው አስታውቋል።

የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑ መካከልም በቻይና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን እንደሚገኙበትም ጠቅሷል።

በቻይናውያን ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ መሰል ጥቃቶች በአሜሪካ እየተበራከቱ መሆኑን ያስታወቀው ኤምባሲው፤ በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎች በሀገሪቱ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ለግል ደህንነታቸው ጥንቃቄ እንዲያድርጉ አሳስቧል።

መረጃውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ ነው ያስነብበው።

@tikvahethiopia
👍901😢43👎29👏29😱218🥰2
#CHINA #USA

ቻይና ለአሜሪካ ባለስልጣት የቪዛ አገልግሎት ላለመስጠት ወሰነች።

ይህ ውሳኔ አሜሪካ ለቻይና ባለሰልጣናት ቪዛ እንደማትሰጥ ከገለፀች በኃላ በቻይና የተሰጠ ተመሳሳይ የአፀፋ ምላሽ ነው።

አሜሪካ ሰኞ ዕለት በሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ላይ እጃቸው አለበት ባለቻቸው የቻይና ባለስልጣናት ላይ ነው የቪዛ እገዳ ጥላ ነበር።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
👍979👏68👎4542😱16🥰12😢8
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ታይዋንን ለቀው ወጥተዋል። የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና በሀገሪቱ የስልጣን እርከን ሶስተኛ ሰው የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን ጎብኝተዋል። ትላንት ታይዋን ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ብዙ ሲባልለት የነበረ እና በአሜሪካ እና ቻይና መካከል የፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት ዓለምን ያሰጋ ነበር። ቻይና ፔሎሲ ወደታይዋን እንደሚመጡ…
#US #CHINA

" ቻይና ማንንም መከልከል አትችልም " - ፔሎሲ

" ሀገሬን የሚዳፈሩ ሁሉ ይቀጣሉ " - ቻይና

በአሜሪካ በስልጣን እርከን 3ኛዋ ሰው ናንሲ ፔሎሲ ከታይዋን ጉብኝታቸው በኋላ " ቻይና የዓለም መሪዎችን ወይም ማንንም ወደ ታይዋን እንዳይጓዙ መከልከል አትችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

ቻይና ፤ ከፔሎሲ ጉብኝት በፊት ጉብኝቱ እንዳይደረግ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና ዛቻ ብታሰማም ፔሎሲ ወደ ታይዋን ገብተው ፤ ጉብኝት አድርገው ባለስልጣናትን አነጋግረው ሄደዋል።

ምንም እንኳን የፔሎሲ ጉብኝት ቢጠናቀቅም በቻይና እና አሜሪካ መካከል ያለው ውጥረት የቀጠለ ሲሆን ቻይና " ሀገሬን የሚዳፈሩ ሁሉ ይቀጣሉ " ስትል ዝታለች።

በሌላ በኩል ወደ ታይዋን ትልክ የነበረውን የተፈጥሮ አሸዋ መላክ ያቆመች ሲሆን ፍራፍሬና የዓሣ ምርቶችን ከታይዋን ማስገባት አቁማለች።

ታይዋን አካባቢ አሁንም የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ መቀጠሉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
👍1.02K👎109👏41🙏39😢3327🥰23
#China

ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ስለ ቻይና-ታይዋን ጉዳይ ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሞኑን የቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ለኢዜአ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኑን ተናግረዋል።

" የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት " አምባሳደር መለስ፤ " ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው " ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለ #አንድ_ቻይና ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉ ሲሆን ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት የሚያራምዱት አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

#ሱዳን

ሱዳን ለአንድ ቻይና መርህ ድጋፏን እንደምትሰጥ አሳውቃለች። ታይዋንም የቻይና ግዛት አካል መሆኗን ገልጻለች።

ሱዳን ፤ ቻይና ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነትዋን በመጠበቅ ረገድ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

#ኤርትራ

ኤርትራ የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነው ብላለች።

የአፈጉባኤዋ ድርጊት የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም " የአንድ-ቻይና " ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነው ስትል ገልፃለች።

ኤርትራ፤ አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች ነው ብላ ድርጊቱ አጸያፊ ነው ብላለች።

#CGTN #ENA #AlAIN #Shabait

@tikvahethiopia
👍1.54K👎16073🙏35👏30😢13🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ተመረጡ። የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሊዝ ትረስ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል። ትረስ እድሜያቸው 47 ሲሆን የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ሆነዋል። ሶስተኛዋ የሀገሪቱ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትርም እንደሆኑ ተገልጿል። ትረስ ተፎካካሪያቸው የነበሩት ሪሺ ሱናክን ሲሆኑ ያሸነፉት 57.4% ድምፅ በማግኘት እንደሆነ ዶቼ ቨለ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#UK #China

ሪሺ ሱናክ የዩናይትድ ኪንግደም ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው።

ሊዝ ትረስ በተሾሙ በሰባት ሳምንት ስልጣን በቃኝ ያሉ ሲሆን እሳቸውን ለመተካት በተደረገው ውድድር ሪሺ ሱናክ አሸናፊ ሆነዋል።

ሱናክ ፤ የዩናይትድ ኪንግደም #የመጀመሪያው " እስያዊ " ዝርያ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ።

ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ከሰባት ሳምንታት በፊት በተደረገ ፉክክር ሪሺ ሱናክ ተወዳድረው የነበረ ቢሆንም በሊዝ ትረስ ሊሸነፉ ችለዋል።

ሊዝ ትረስ ' ግብር እቀንሳለሁ፤ ንግድን አሳልጣለሁ " ያሉት አዲስ ፖሊሲ ፍጹም ያልተጠበቀ የገበያ ምስቅልቅልና ብሔራዊ ጦስ ይዞባቸው መጥቶ ነው ሥልጣን እንዲለቁ የሆኑት።
 
ለ45 ቀናት ያህል ስልጣን ላይ የቆዩት ሊዝ ትረስ በዩናይትድ ኪንግደም ታሪክ ለአጭር ጊዜ የቆዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመዝግበዋል። 

በሌላ መረጃ ፥  የቻይና ገዥ የሆነው ኮሚኒስት ፓርቲ ትላንት ባደረገው ጉባኤ ዢ ዢንፒንግን ዋና ጸሓፊ አድርጎ መምረጡን ተከትሎ ለ3ኛ ጊዜ ስልጣናቸው ተራዝሟል።

የፓርቲው #ዋና_ጸሃፊ በሃገሪቱ የመሪነት ቦታ የሚያስገኝ ሲሆን መጋቢት በሚደረገው የብሄራዊ ህዝቦች ጉባኤ በይፋ ስልጣናቸው ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
👍1.55K86👎78🙏65😱45😢18
#China

ቻይና ከ3 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ድንበሯን #ለጎብኚዎች ከፍት አድርጋለች።

ቻይና በመጋቢት 2020 ዓ/ም የኮቪድ  19 ወረርሽኝን ተከትሎ ነበር የጉዞ እግድ የጣለችው።

ከአሁን በኃላ ገቢ መንገደኞች ማቆያ ስፍራ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ መግባት ይችላሉ። ይሁንና ገቢ መንገደኞች #በ48_ሰዓታት ውስጥ የወሰዱትን የክትባት ማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ፅፏል።

@tikvahethiopia
👍271👎239🤔8🙏6🕊3😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) እንደሚመጡ ተሰምቷል። የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ በቅርቡ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እንደሆነ ተሰምቷል። ኪንግ ጋንግ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በአሜሪካ የቻይና አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።…
#ETHIOPIA #CHINA

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሆነ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ከምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሚኒስትሩ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ባሰራጩት አጭር ፅሁፍ ፤ " የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሁንም ጸንቶ ቀጥሏል " ብለዋል። " የዛሬው ውይይት ይህንን እና በልማት የምንጋራውን ስልታዊ የጋራ ዓላማ፤ እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል " ሲሉ ገልፀዋል።

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአቶ ደመቀ ጋር በተገናኙበት ወቅት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት እና ከፊል የዕደ ስረዛ ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱ የሁለቱን አገራት ጠንካራ ግንኙነትን ለማስቀጠል እና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋጋር እንደሚረዳ ተገልጿል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሁለትዮሽ ፣ቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አሳውቀዋል።

ቺን ጋንግ በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በ #ኢትዮጵያ እያደረጉ ናቸው።

መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
👍372👎4520😢5🕊4🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#China ቻይና ከ3 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ድንበሯን #ለጎብኚዎች ከፍት አድርጋለች። ቻይና በመጋቢት 2020 ዓ/ም የኮቪድ  19 ወረርሽኝን ተከትሎ ነበር የጉዞ እግድ የጣለችው። ከአሁን በኃላ ገቢ መንገደኞች ማቆያ ስፍራ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ መግባት ይችላሉ። ይሁንና ገቢ መንገደኞች #በ48_ሰዓታት ውስጥ የወሰዱትን የክትባት ማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ፅፏል። @tikvahethiopia
#Ethiopia 🛫 #China 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ #ቻይና ሳምንታዊ የበረራ ምልልሱን ከፍ ሊያደርግ ነው።

በቻይና መንግስት ተጥለው የነበሩ የኮቪድ-19 ክልከላዎች መነሳታቸውን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው የካቲት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ቻይና ወደሚገኙ መዳረሻዎቹ የሚያደርገውን ሳምንታዊ የበረራ ምልልስ ከፍ በማድረግ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን አየር መንገዱ ዛሬ አሳውቋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
👍509👎32🕊16🙏15🥰117
ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ?

ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር።

በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።

በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል።

" በእርግጥም ፤ የBRICS አባል መሆን እንፈልጋለን " ያሉት ፊዳን " ስለዚህ በዚህ አመት እንዴት እንደሚሄድ እናያለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ነገር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

አናዱሉ እንደዘገበው ደግሞ ቱርክ የBRICS  አባላት ሀገራትን ትብብር እየተመለከተች ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሁለት ቀን በፊትም ወደ ሩስያ አቅንተው ከBRICS አባሏ ሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በBRICS አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል።

ፑቲን ከሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ቱርክ ስብስቡን ለመቀላቀል (አብሮ ለመስራት) ያሳየችውን ፍላጎት በደስታ ተቀብለው ፤ ወደ ስብስቡ እንድትቀላቀል ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

የቱርክ መንግሥት BRICS'ን ለመቀላቀል ርምጃ ይወስድ እንደሆነ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በይፋ ስብሰቡን ለመቀላቀል ያለውን ፍላጎት በይፋ አሳውቆ አያውቅም።

ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።

#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።

#BRICS
#Turkey
#China
#Russia

@tikvahethiopia
🥰431212🙏77🤔55👏37😡29😱28😢26😭26🕊20
#Ethiopia 🇪🇹 #Africa #China

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ቻይና ውስጥ ተሰባስበዋል።

በቻይና የተሰባሰቡት ለቻይና አፍሪካ የመሪዎች መድረክ ነው።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ሉዑካቸው ቻይና ይገኛሉ።

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፥ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ደማቅ አቀባበል እንዳደሩጉላቸው ገልጸዋል።

ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውንም አመልክተዋል።

" ኢትዮጵያ የቻይናን ያልተቋረጠ ዘርፈብዙ ድጋፍ በእጅጉ ታደንቃለች። " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " እንደ ሀገር የተለያዩ ተግዳሮቶችን ብናስተናግድም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንደስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና ሌሎች ዘርፎች ትርጉም ያላቸው የለውጥ ርምጃዎች ተራምደናል " ብለዋል።

" በዚህ የእድገት ጎዳና የቻይና ኢንቨስትመንቶች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ፤ በቱሪዝም ብሎም በወረቀት እና እንደ ፐልፕ ያሉ ተያያዥ ግብዓቶች ኢንደስትሪንም ለማሳደግ እምቅ አቅም አለ። " ሲሉ ገልጸዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
👏434😡17295🙏28🤔27🕊14😭10😱6😢3
#China #Tibet

ለሊቱን እና ጥዋት ላይ በዓለም በተለያዩ ሀገራት የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል።

ከነዚህ ውስጥ እጅግ የከፋው እና የ53 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመሬት መንቀጥቀጥ በቻይና ፤ ቲቤት ግዛት ደርሷል።

የቻይና የመሬት መንቀጥቀጥ ኔትዎርክ ሴንተር በሬክተር ስኬል 6.8 የተመዘገበ ነው ብሏል።

የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ግን የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 7.1 የተመዘገበ ነው ሲል አመልክቷል።

በሬክተር ስኬል 6.8 ሆነ ከዛም በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እጅግ ጠንካራና አደገኛ ከፍተኛ የሆነ ውድመት ሊያደርስ የሚችል ነው።

በቲቤት 6 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ 7.1 ነው።

በመሬት መንቀጥቀጡ ህንጻዎች ፣ መኖሪያ ቤቶች ተደርምሰዋል።

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የቻይና ሚዲያዎችን ዋቢ በማድረግ በትንሹ 53 ሰዎች እንደሞቱ ነገር ግን ከፍርስራሽ ስር ያሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ በዚህም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የነፍስ አድን ስራ ላይ ተሰማርተዋል።

አደጋው ተራራማ በሆኑ የገጠራማ ክፍሎች የደረሰ ሲሆን ዋና ወደሚባሉ ከተሞች እንኳን አልተጠጋም።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በሰሜን ህንድ እና በኔፓል ዋና ከተማ ካታህማዱ ሌሎችም ቦታዎች በእጅጉ ተሰምቷል።

ባለስልጣናት ዜጎቻቸው እንዲረጋጉ እና ቀጣይ ለሚመጣው ሾክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።

ስፍራው በተደጋጋሚ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያስተናግድ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ቅፅበታዊ ፣ ለመገመት እና ለመተንበይ የሚያስቸግር የት ቦታ እንደሆነ እንጂ መቼ እንደሚፈጠር የማይታወቅ በመሆኑ ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ ንቁ ሆኖ መጠበቅ ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ያሰባሰበ ሲሆን ቪድዮዎቹና ፎቶዎቹን ከቲቤት እና ኔፓል የማህበራዊ ትስስር ገጾች ነው የወሰደው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ? የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ያንብቡ :
https://t.iss.one/tikvahethiopia/93267?single

@tikvahethiopia
😭1.18K271🙏145🕊96😢39😱32🥰18👏16🤔13😡11
TIKVAH-ETHIOPIA
የትራምፕ የታሪፍ ጦርነት ወዴት ያመራ ይሁን ? የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገራት ላይ የሚጣል አዲስ ታሪፍ ይፋ ካደረጉ በኋላ በተለይም ከቻይና ጋር ተፋጠዋል። ትራምፕ ከዚህ በፊት ሌሎች ሀገራት የአሜሪካ ምርቶች ላይ ከሚገባው በላይ ታሪፍ ጥለዋል ብለው እንደሚያምኑ እና ይህንን የሚስተካከል ታሪፍ እንደሚጥሉ ከተናገሩ በኋላ ነው አዲሱን ታሪፍ ያስተዋወቁት። በመጀመሪያው ዙር ፕረዚዳንት ትራምፕ…
#USA #China

ቻይና በአሜሪካ ላይ አፀፋዊ የሆነ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች።

ቻይና ከዚህ በፊት ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ84% ታሪፍ ጥላ የነበረ ሲሆን ዛሬ ሌላ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች።

የቻይና የፋይናንስ ሚኒስትር ከአሜሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ84% ወደ 125% ከፍ መደረጉን አስታውቀዋል።

የትራምፕ አስተዳደር  በቻይና ላይ የተጣለው አጠቃላይ ታሪፍ 145% መሆኑን የገለፀ ሲሆን የሃገራቱ የንግድ ጦርነት ውስጥ መግባት ትልቅ ስጋትን እየፈጠረ ይገኛል።

የቻይና የፋይናንስ ሚኒስትር አሜሪካ ተጨማሪ ታሪፍ መጣሏን ከቀጠለች በአለም የኢኮኖሚ ታሪክ አስቂኙ ነገር ይሆናል ያሉ ሲሆን ከዚህ በኋላ አሜሪካ ታሪፍ ከጣለች ቻይና ምላሽ አትሰጥም ብለዋል።

የፋይናንስ ሚኒስትሩ አሜሪካ ጤነኛ ያልሆነ እና አለም አቀፍ የንግድ ህጎችን የጣሰ ውሳኔ እየወሰነች ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም አሁን ባለው የታሪፍ ምጣኔ ከአሜሪካ ወደ ቻይና የሚገቡ ዕቃዎች ገበያ አይኖራቸውም ያሉ ሲሆን የቻይና የንግድ ሚኒስትር ቃለ አቀባይ ደግሞ ቻይና ከአሜሪካ ጋር በእኩል ተቀምጣ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ  የታሪፍ ጦርነት ማንንም አሸናፊ አያደርግም ያሉ ሲሆን ከአለም በተቃራኒ መጓዝ እራስን ከአለም ማግለል ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅትም የአውሮፓ ህብረት ከቻይና ጎን በመቆም አሜሪካ የምታደርገውን ትንኮሳ እንዲቃወም ጠይቀዋል።

ቻይና ለአሜሪካ የምትልካቸው ዕቃዎች የሃገሪቱን ጥቅል ምርት 3% እንደሚይዙ የተገለፀ ሲሆን በቻይና ከ10-20 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች ወደ አሜሪካ ከሚላኩ ዕቃዎች ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን እንደሚመሩ ተገልጿል።

ቻይና አዲሱን ታሪፍ የጣለችው አሜሪካ ከቻይና የሚገቡ ዕቃዎች አጠቃላይ 145% ታሪፍ እንደሚጠብቃቸው ካሳወቀች በኋላ ነው።

ቻይና በአሜሪካ ላይ የጣለችው አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባም ተዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ CNBC እና Reutersን እንደ መረጃ ምንጭነት ተጠቅሟል።

@tikvahethiopia
👏847219🤔93🕊69🙏27💔25😱18🥰16😢16😡14😭12
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #China ቻይና በአሜሪካ ላይ አፀፋዊ የሆነ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች። ቻይና ከዚህ በፊት ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ84% ታሪፍ ጥላ የነበረ ሲሆን ዛሬ ሌላ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች። የቻይና የፋይናንስ ሚኒስትር ከአሜሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ84% ወደ 125% ከፍ መደረጉን አስታውቀዋል። የትራምፕ አስተዳደር  በቻይና ላይ የተጣለው አጠቃላይ ታሪፍ 145% መሆኑን የገለፀ…
#USA #CHINA

የአሜሪካ እና የቻይና የታሪፍ ጦርነት !

ወደ አሜሪካ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከጣሏቸው የአፀፋ ታሪፎች ነፃ መሆናቸውን የአሜሪካ የጉምሩክ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

➡️ ስማርት ስልኮች፣
➡️ ኮምፒዩተሮች
➡️ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ክፍሎች ትራምፕ ከጣሉት ታሪፍ ነፃ መደረጋቸውም ተዘግቧል።

ውሳኔው የመጣው የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር በቻይና ላይ የ145% አጠቃላይ ታሪፍ መጣሉን ካስታወቀ በኋላ ሲሆን የታሪፉ መጣል እንደ አፕል ላሉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክ ምርት አምራቾች ስጋትን ፈጥሮም ነበር።

አፕል 90% የሚሆነውን የአይፎን ስልክ የሚያመርተው እና የሚገጣጥመው በቻይና ሲሆን ካውንተር ፖይንት የተሰኘው የጥናት ተቋም አፕል በአሜሪካ ያለው ክምችት ለ6 ሳምንታት ብቻ የሚሆን እንደሆነና እሱ ካለቀ የምርቱ ዋጋ መጨመር እንደሚጀምር ገልጾ ነበር።

አፕል ከአይፎን በተጨማሪ 80% የሚሆነውን አይፓድ እና ከ50% በላይ የሚሆነውን የማክ ኮምፒዩተር ምርቶቹን በቻይና እንደሚያመርት ተገልጿል።

አፕል ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነውን የአይፎን ምርት የሚሸጠው በአሜሪካ እንደሆነ ሲነገር በቻይና ላይ ታሪፍ መጣሉን ተከትሎ አብዛኛውን ምርቱን በህንድ ማምረት ለመጀመር ማሰቡም ተነግሮ ነበር።

አፕል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፀፋ ታሪፍ በሃገራት ላይ መጣል ከጀመሩ በኋላ የገበያ ዋጋው በ640 ቢሊየን ዶላር መቀነሱ የተዘገበ ሲሆን ከ600 ቶን በላይ ክብደት ያላቸው 1.5 ሚሊየን የአይፎን ስልኮችንም ከህንድ ወደ አሜሪካ በአውሮፕላን አጓጉዞ ማስገባቱ መዘገቡ ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንትና አንዳንድ ምርቶች በሚታወቁ ምክንያቶች እሳቸው ከጣሉት ታሪፍ ነፃ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረው ነበር።

ትራምፕ በጣሉት ታሪፍ የተነሳ የአይፎን ስልክ ዋጋ በሶስት እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ስጋቶች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶቹ ከአፀፋዊ ታሪፉ ነፃ መሆን ትልቅ ዕድል እንደሚሆን ተዘግቧል።

በውሳኔው መሰረትም #ሳምሰንግን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ አምራቾች ወደ አሜሪካ ምርታቸውን ሲልኩ ይጠብቃቸው ከነበረው የ10% መሰረታዊ ታሪፍም ነፃ መሆናቸው ተነግሯል።

ከታሪፉ ነፃ የሆኑ 20 የምርት ዘርፎች የተቀመጡ ሲሆን ለሴሚ ኮንዳክተር መሳሪያነት የሚያገለግሉ ማሽኖችም ከታሪፉ ነፃ መሆናቸው ታውቋል።

ኋይት ሃውስ፣ የአሜሪካ የአለም አቀፍ ንግዶች ኮሚሽን እና የአሜሪካ የንግድ ቢሮ በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።

#ዓለምአቀፍ #የታሪፍጦርነት #ቻይና #አሜሪካ

@tikvahethiopia
304🤔76🙏24👏21💔16🕊14😭13🥰10😡10😢4😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #CHINA የአሜሪካ እና የቻይና የታሪፍ ጦርነት ! ወደ አሜሪካ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከጣሏቸው የአፀፋ ታሪፎች ነፃ መሆናቸውን የአሜሪካ የጉምሩክ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል። ➡️ ስማርት ስልኮች፣ ➡️ ኮምፒዩተሮች ➡️ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ክፍሎች ትራምፕ ከጣሉት ታሪፍ ነፃ መደረጋቸውም ተዘግቧል። ውሳኔው የመጣው የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር…
#USA #CHINA

ቻይና እስከ 245% ሊደርስ የሚችል ታሪፍ እንደተጣለባት አሜሪካ አስታውቃለች።

ኋይት ሃውስ ባወጣው መግለጫ ቻይና አፀፋዊ እርምጃ በመውሰዷ እስከ 245% የሚደርስ ታሪፍ እንደተጣለባት ገልጿል።

በመግለጫው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት ከገቡ በኋላ የአሜሪካን ኢኮኖሚ ዳግም ለማሳደግ አሜሪካን ቀዳሚ ያደረገ የንግድ ፖሊሲ እየተከተሉ እንደሆነ የተመላከተ ሲሆን ከ75 በላይ ሃገራት ከአሜሪካ ጋር አዲስ የንግድ ስምምነት እንዲኖር ተወያይተዋል ብለዋል።

በውይይቶቹ የተነሳ በሃገራቱ ላይ የተጣለው ታሪፍ እንዳይተገበር የተወሰነ ስለመሆኑ ኋይት ሃውስ ገልፆ ቻይና ግን አፀፋዊ እርምጃ በመውሰዷ እንዲተገበርባት ሆኗል ብሏል።

ኋይት ሃውስ ጨምሮም ከወራት በፊት ቻይና እንደ ጋሊየም እና ጀርማኒየም ያሉ ወሳኝ የቴክኖሎጂ ቁሶች ወደ አሜሪካ እንዳይላኩ ከልክላለች ያለ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ ለመኪና ሰሪዎች፣ ለኤሮስፔስ እና ለወታደራዊ ግልጋልት የሚውሉ 6 የከበሩ ማዕድናትን ወደ ውጪ እንዳይላኩ ከልክላለች ብሏል።

ኋይት ሃውስ ቻይና በትክክል ምን ያህል መጠን ያለው ታሪፍ እንደተጣለባት ባይገልፅም አስከ 245% ሊደርስ እንደሚችል ገልጿል።

መረጃው የአናዶሉ ነው።

@tikvahethiopia
🤔45689🕊33🙏29😡27😢26👏14😭13😱12💔12🥰8
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#China #USA

ቻይና ዶናልድ ትራምፕ የጣሉትን ታሪፍ ተከትሎ አገራት ከአሜሪካ ጋር በሚያደርጉት የንግድ ድርድር ወቅት አሜሪካን የምትፈልገውን በማድረግ ለማስደሰት እንዳይሞክሩ አስጠነቀቀች።

የቻይና ንግድ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ዋሺንግተን መንግሥታት ወደ አሜሪካ የሚልኳቸው ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑላቸው ከቤይጂንግ ጋር በሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ ላይ ጫና ለመፍጠር ማቀዷ ከተሰማ በኋላ ነው።

የትራምፕ አስተዳደር ከንግድ አጋሮች ጋር ታሪፍን በተመለከት ንግግር መጀመሩ ተገልጿል።

ትራምፕ በጥር ወር ሥልጣናቸውን ከተረከቡ በኋላ ከቻይና የሚገቡ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ የጣሉ ሲሆን ሌሎች በርካታ የዓለም አገራትም ታሪፍ ተጥሎባቸዋል።

የቻይና የንግድ ሚኒስትር ቃል አቀባይ " ለማስደሰት የሚደረግ ጥረት ሠላምን አያመጣም፤ እንዲሁም ማመቻመች ክብርን አያቀዳጅም " ብለዋል።

" ቻይና ሁሉም አካላት ከፍትሃዊነት ጎን መቆም አንዳለባቸው ታምናለች. . . እንዲሁም ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሀብት እና የንግድ ሕጎች እንዲሁም የአገራት የንግድ ሥርዓትን መከላከል አለባቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት ዎል ስትሪት ጆርናል አሜሪካ ታሪፍን በተመለከተ ከአገራት ጋር በምታደርገው ድርድር ከቻይና ጋር በሚኖራቸው ንግድ ላይ አዲስ ገደብ በመጣል ጫና ለማድረግ እንደምትፈልግ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
344👏109🕊24🤔19🥰14😡10😭5😱2😢2🙏1💔1
TIKVAH-ETHIOPIA
#China #USA ቻይና ዶናልድ ትራምፕ የጣሉትን ታሪፍ ተከትሎ አገራት ከአሜሪካ ጋር በሚያደርጉት የንግድ ድርድር ወቅት አሜሪካን የምትፈልገውን በማድረግ ለማስደሰት እንዳይሞክሩ አስጠነቀቀች። የቻይና ንግድ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ዋሺንግተን መንግሥታት ወደ አሜሪካ የሚልኳቸው ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑላቸው ከቤይጂንግ ጋር በሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ ላይ ጫና ለመፍጠር ማቀዷ…
#USA #CHINA

ቻይና አንዳንድ የአሜሪካ ምርቶችን ከጣለችው የ125% ታክስ ነፃ አደረገች።

ቻይና ከአሜሪካ ወደ ሃገሯ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶች ከጣለችው የ125% ታሪፍ ነፃ ማድረጓ እና ድርጅቶች ከታክስ ነፃ መሆን አለባቸው ብለው የሚያስቧቸውን ወሳኝ ዕቃዎች ለይተው እንዲለዩ መጠየቋን ሮይተርስ ከምንጮች አረጋግጦ ዘግቧል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለታይም መፅሄት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ታሪፉን በተመለከተ ቻይናና አሜሪካ እየተወያዩ እንደሆነና የቻይናው ፕሬዚዳንት እንደደወሉላቸውም አንስተዋል።

ከቻይናው ፕሬዚዳንት ጋር መቼ እና ስለምን እንደተወያዩ ትራምፕ ያልተናገሩ ሲሆን የተለያዩ የመድኃኒት ድርጅቶች የሚያስገቧቸው ምርቶች ከታክሱ ነፃ ስለመሆን ያነሱ ሲሆን የፈረንሳዩ የአውሮፕላን ሞተር አምራች ሳፍራን ሞተሮች እና ጎማዎች ከታክሱ ነፃ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግሯል።

በተጨማሪ የቻይና የሴሚ ኮንዳክተር ኢንዱሰትሪ አሶሴሽን ለአንዳንድ የሚሞሪ ቺፕ አምራቾች 8 አይነት የማክሮቺፕስ አይነቶች ከታክሱ ነፃ ስለመሆናቸው እንዳሳወቀ ተዘግቧል።

የቻይና መንግስት በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም  131 የሚሆኑ የምርት አይነቶች ከታክሱ ነፃ እንዲሆኑ ስለመታቀዱ ነው የተነገረው።

ሁለቱ ኃያላን ሃገራት ወደ ንግድ ጦርነቱ ከገቡ በኋላ አሁን ላይ በራቸውን ለውይይት እና ንግግር ክፍት ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸው ወደ ቀውስ እየገባ ያለውን የአለምን ገበያ እንደሚያረጋጋ ታምኗል።

የመረጃው ምንጭ ሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia
🕊16777🙏24🤔17👏15😱8😭7😢3