TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አፈሳ

🔵 “ ወጣቶች እየታፈሱ ነው። የሚታፈሱትም ያለ ፍላጎታቸው ወደ ግዳጅ ሊላኩ ነው ” - የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች

🔴 “ ያገኘናቸው በጣም በርካታ ግኝቶች አሉ ” - ኢሰመኮ


በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቶች “ በመንግስት ፀጥታ አካላት ” እየታፈሱ መሆኑን፣ በዚህም እንዲህ አይነት ድርጊት በሚፈጸምባቸው ቦታዎች ወጣቶች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብታቸው እንደተገደበ ነዋሪዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለዋል።

ነዋሪዎቹ እየተፈጸመ ነው በሚል የተማረሩበት የአፈሳ ድርጊት በይበልጥ እየተካሄደ ያለው በባሌ ሮቤ፣ በሻሽመኔ፣ በአርሲ ነገሌ፣ ባቱ፣ ወንጂ፣ ጅማ፣ በአዳማ ከተሞችና በዙሪያ ገባው መሆኑም ተመላክቷል።

ነዋሪዎቹ፣ “ ወጣቶች እየታፈሱ ነው። የሚታፈሱትም ያለ ፍላጎታቸው ወደ ግዳጅ ሊላኩ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ወጣቶቹ ለመዝናናትም ሆነ ለሥራ ሰብሰብ ብለው መንገድ ላይ ሲገኙ ያለምንም ጥያቄ ታፍሰው በመኪና እየተጫኑ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየተወሰዱ ነው ” በማለት ሁነቱን አስረድተዋል።

“ ከዚች ቀደምም አፈሳ ወጣቶች በሚሰበሰቡበት ቦታ ለምሳሌ ዴኤስቲቪ ፣ ፑል ቤት ነበር አሁኑ ግን መንገድ ላይ የሚገኙት ጭምር በገፍ እየተወሰዱ ነው ” ብለዋል።

አንዳንድ ከ15 እስከ 18 ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎችም የተወሰዱበት ሁኔታ አለ ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ የክልሉ ነዋሪ “ ከሻሸመኔ አንድ የምናውቀው የቤተሰብ ልጅ ተወስዷል። ከሻሸመኔ ተጭነው ወደ ወላይታ ሶዶ አካባቢ መሄዳቸውን ለቤተሰቦቹ ተናግሯል ” ብለዋል።

አንድ የአዳማ ከተማ ነዋሪ ደግሞ ፥ “ ሰው በተለይ ወጣቱ ፈርቷል። ያለውን ወቅታዊ ነገር በመፍራት ስራውን ትቶ በጊዜ ቤት የሚመለስ አለ። ከወጣው እታፈሳለሁ በሚል ስጋት ከቤት የማወጡም አሉ። የጊዜ ገደብ የተቀመጠ ይመስል ውጭ ያለው ሰው 12:00 ስሆን ወደ ቤቱ ለመግባት ይጣደፋል ” ሲል ገልጿል።

“ ሰዎችን ያለምክንያት ይዘው ያስራሉ ሰው ካለው እና 20,000-30,000 መክፈል ከቻለ ይለቃሉ። ያልቻለ ደግሞ ተወስዶ ይሄዳል ” ሲልም አክሏል።

ሰሞኑን አንድ ጓደኛቸው ተይዞ የባንክ ሰራተኛ ነኝ ብሎ ማስረጃ አሳይቶ መለቀቁን ጠቁሟል።

ድርጊቱ በሚፈጸምባቸው አካባቢዎችም ሰዎች ከቤት ለመውጣት፣ ሥራ ለመስራት ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው አስረድተው፣ “ የሰው ልጅ መብት ግን ለይስሙላ ነው እንዴ የተጻፈው ? መቼ ነው ይህ መብታችን እንኳ የሚከበረው ? ከዚህ ቀደምም አፈሳ ነበር። ያሁኑ ግን ብሷል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በርካታ እናቶች ልጆቻቸው ከሚኖሩበት ሰፈር ሳይቀር ተወስደውባቸው በስንት ልመና ከተያዙበት ቦታ ያስወጧቸው አሉ።

በተለይ ወጣቶች ከተያዙ በኃላ የሚወሰዱት ወደ ማቆያ ቦታዎች ነው።

ከነዋሪዎች ዘንድ ለቀረበው ሰፊ ቅሬታ ምላሽ ለማግኘት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሙከራ ቢያደርግም፣ ስልክ ሆነ የፅሑፍ መልዕክት ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም።

ከቀናት በፊት የክልሉ መንግሥት “ በክልሉ የጅምላ አፈሳ አለ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ” ሲል በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በኩል ገልጾ ነበር።

እየተፈጸመ ነው የተባለውን የአፈሳ ድርጊት ሰምቶ እንደሆን በሚል የጠየቅነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግን አፈሳ እየተፈጸመ ነው የሚለው ቅሬታው ትክክል መሆኑን ነግሮናል።

ወጣቶችን ወደ ‘ግዳጅ ትሄዳላችሁ’ በሚል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸመ ነው የተባለውን አፈሰ ኮሚሽኑ ሰምቶ ነበር ? ስንል የጠየቅነው ኢሰመኮ በምላሹ፣ “ አፈሳውን በተመለከተ የሰራነው ብዙ ሥራ አለ።  ፐብሊክ ስቴትመንት ይሰጣል ” ብሏል።

“ ምንድን ነው የሚለውን በሂደት የምናያቸው ይሆናል። ግን ጉዳዩ ኦረዲ ብዙ ሥራ ተሰርቶበታል። መግለጫው ሲወጣ ይደርሳችኋል ” ነው ያለው።

አፈሳው ትክክል ነው ? እንዲህ አይነት ድርጊት እየተፈጸመ ነው? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ ኮሚሽኑ፣ “ በጣም ብዙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ ገብተን የሰዎች ማቆያዎችን አይተናል ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

“ ስለዚህ የማኀበራዊ ሚዲያው አሊጌሽን ምንድን ነው? የሚለው እንዳለ ሆኖ በእኛ በኩል ግን ያገኘናቸው በጣም በርካታ ግኝቶች አሉ ” ሲል አረጋግጧል።

“ ከክልሉ ጋር የተየጋገርንባቸው፣ እያደረግን ያለናቸው ጉዳዮችም አሉ ” ሲል ኮሚሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia