TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... ድርጊቶቹ ከሞራል ወይም ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ናቸው " - አምነስቲ ኢንተርናሽናል

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የነፋስ መውጫ ከተማ ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ጊዜ የአስገድዶ መድፈር፣ ዘረፋ እና አካላዊ ጥቃቶች በነዋሪዎች ላይ መፈጸማቸውን ገለጸ።

አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት በከተማዋ ነዋሪ የሆኑና ያናገራቸው 16 ሴቶች በህወሓት አማጺያን የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

ሴቶቹ እንዳሉት በህወሓት ኃይሎች መሳሪያ ተደቅኖባቸው እንደተደፈሩ፣ ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም አካላዊ ጥቃት እና ስድብ እንደደረሰባቸው አመልክተዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጨምሮ ካነገራቸው አስገድዶ የመድፈር ጥቃት ከተፈጸመባቸው 16 ሴቶች መካከል 14ቱ ጥቃቱ #በቡድን እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል። አማጺያኑ በከተማ ባሉ የህክምና ተቋማት ላይ ዝርፊያና ውድመትን አድርሰዋል ብሏል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ የምትገኘውን የነፋስ መውጫ ከተማን የህወሓት ታጣቂዎሽ ተቆጣጥረው የቆዩት ከነሐሴ 06 አስከ 15/2013 ዓ.ም ድረስ ለአስር ቀናት ነበር።

የአምነስቲ ኢንትርናሽናል ዋና ፀሐፊ አግነስ ካላማርድ፥ "የአስገድዶ መድፈር ጥቃቱ ከደረሰባቸው የሰማናቸው ምስክርነቶች የህወሓት ተዋጊዎችን አጸያፊ ተግባራት፤ ከጦር ወንጀሎች እና በሰብአዓዊነት ላይ ከተፈጸሙ ወንጀሎች ጋር የሚስተካከሉ ናቸው። ድርጊቶቹ ከሞራል ወይም ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል።

የህወሓት ታጣቂዎች ወሲባዊ እና ፆታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶችን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች ጥሰቶችን በሙሉ በማቆም በፈጻሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Amnesty-International-11-10

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጋምቤላ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_ከግንቦት_ወር_2015_ለያዩ_ያ_የደረሱ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰቶችን.pdf
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ብቻ እንዲህ ሆኖ ነበር ....

ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦

ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ በጋምቤላ ከተማ፣ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው እና ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ትክክለኛ ቀኑ ባልታወቀበት ነገር ግን ሰዓቱ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ዶምቦስኮ ትምህርት ቤት አካባቢ አንድ ሰው ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች ተገድለዋል።

ግንቦት 14/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ 01 ቀበሌ ጀጀቤ ወንዝ አካባቢ 2 ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በጥይት ተመትተው ሞተዋል።

01 ቀበሌ ጀጀቤ ተራራ አካባቢ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ገደማ 7 ሰዎች በጥይት ተገድለዋል።

ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ አንድ በአካባቢው ማኅበረሰብ #የአእምሮ_ሕመም እንዳለበት የተገለጸ ሰው 04 ቀበሌ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አካባቢ #በቡድን በተሰባሰቡ ወጣቶች ጥቃት #በስለት_ተወግቶ ተገድሏል።

ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ገደማ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ፦
* የቀድሞውን የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል፤
* የጋምቤላ ክልል መደበኛ ፖሊስ
* የጋምቤላ ክልል ሚሊሻ መለዮ ልብሶችን የለበሱ እና ሌሎች የታጠቁ ሰዎች በ3 የተለያየ አቅጣጫ በመግባት በቦታው የነበሩ 9 ሰዎችን በጥይት ገድለዋል፤ ሌሎች 4 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት አካባቢ 04 ቀበሌ፣ ቄራ ሰፈር አጉኛ አካባቢ የታጠቁ ሰዎች ወደ አንድ መኖሪያ ቤት በመግባት ተኩስ ከፍተው፤ አንድ ሰው ሲገድሉ በሌላ አንድ ሰው ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፡፡

የኢሰመኮ ባለ15 ገፅ ሪፖርት ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/85541

@tikvahethiopia